tg-me.com/CoolmanEfu/2140
Last Update:
🌷@coolmanEfu🌷
🚺 ሚስት ስጦታ እንጂ ምርጫ አይደለችም 🚺
🔵 አንድ ምሽት በጎልማሶች የትምህርት ክፍለ ግዜ የሳይኮሎጂ መምህሩ ወደ ክፍል ገባና "ዛሬ አንድ Game እንጫወታለን" አለ፡፡
ተማሪዎቹም "ምን አይነት Game?" በማለት በህብረት ጠየቁ፡፡ መምህሩ ቀጥሎ "ፈቃደኛ የሆነ አንድ ሰው?" አለ፡፡ አንድ ፈቃደኛ ወንድ ተማሪ እጁን አወጣ፡፡
መምህሩም ተማሪውን በህይወቱ ትልቅ ቦታ ያላቸውን 30 ሰዎች ስም ጥቁር ሰሌዳው ላይ እንዲፅፍ ጠየቀው፡፡ ተማሪውም ከቤተሰቦቹ ጀመሮ የጎረቤቶቹን፣ የዘመዶቹንና የጓደኞቹን ስም ፃፈ፡፡
መምህሩ በመቀጠል በጣም ጠቃሚ ያልሆኑ 3 ስሞችን እንዲሰርዝ አዘዘው፡፡ እሱም የጎረቤቶቹን ስም ሰረዘ፡፡ አሁንም ሌላ 5 ስሞችን እንዲሰርዝ ነገረው፡፡ተማሪውም የሩቅ የምላቸውን ዘመዶቹን ስም ሰረዘ።
በዚህ መልኩ የአራት ሰዎች ስም ብቻ (የእናቱ፣ የአባቱ፣ የሚስቱና የብቸኛው ልጁ) እስኪቀር ብዙ ስሞችን ሰረ። ሙሉ የክፍሉ ተማሪዎች Gamu ለዚህ ተማሪ ብቻ እንዳልሆነ ተረድተው በተመስጦ ይከታተላሉ፡፡
አሁንም መምሩ ከቀሩት አራት ስሞች 2 እንዲሰርዝ አዘዘው፡፡ ተማሪውም በጣም ከባድ ምርጫ ነበር፡፡እያመነታና እንዳልተቀበለው በሚያስታውቅ መልኩ የወላጆቹን ስም ሰረዘ።
መምህሩ በስተመጨረሻ ከቀሩት ሁለት ስሞች 1 እንዲሰርዝ ነገረው፡፡ ተማሪውም ሙሉ በሙሉ አእምሮው ተረበሸ፡፡
በአይኖቹ እያነባ በሚንቀጠቀጡ ጣቶቹ የልጁን ስም ሰረዘ፡፡ መምህሩም ተማሪውን ወደ መቀመጫው እንዲመለስ ነገረው። ከደቂቆች በኀላ መምህሩ "ለምን ሚስትህን አስቀረህ?
►ቤተሰቦችህ ላንተ ብቸኞች ናቸው፤
►ልጅህን የወለድከው ( ወደ ህይወት ያመጣኸው) አንተ ነህ፤
►ሚስት ግን ሌላ ማግባት ትችላለህ፤
►ለምን ከእነሱ እሷን አስቀደምክ?" በማለት ተማሪውን ጠየቀው፡፡
►ሁሉም ተማሪውን ምላሽ ለመስማት ጓግቷል፡፡
ተማሪውም በተረጋጋ መንፈስ እንዲሁም በቀስታ እንዲህ ስል መለሰ፦
አንድ ቀን ቤተሰቦቼ ምናልባት ከእኔ ቀድመው ያልፋሉ፤ ልጄም ሲያድግ ለትምርት፣ ለስራ ወይም በማንኛውም ምክንያት ጥሎኝ ይሄዳል፡፡
ሙሉ ህይወቴን ሁሉን አብራ የምትጋራኝ ብቸኛ ሰው ቢኖር ባለቤቴ /ሚስቴ/ ናት፡፡" አለ።
ሁሉም ተማሪ ከመቀመጫቸው ተነስተው እውነተኛውን የህይወት ገፅታ ስላካፈላቸው አጨበጨቡለት 👏👏👏
✅️ #እውነት_ነው፡፡✅
✴ ሁላችንም ቤተሰቦቻችንን ምንም ያህል ብንወዳቸው ጥለናቸው እንሄዳለን፡፡
ለማን ስንል? ለባል ወይም ሚስት፡፡
✴ ልጆቻችንን ምንም ያህል ብንወዳቸው ጥለውን ይሄዳሉ፡፡ ለማን ሲሉ ለሚስታቸው ወይም ለባላቸው ሲሉ፡፡
✴ በስተመጨረሻ አብረው የሚዘልቁት ፈጣሪ ያጣመራቸው ሁለት ነፍሶች ብቻ ናቸው፡፡
ባልና ሚስት፤ ወይም ፍቅረኞች።
✴ ስለዚህ ወዳጄ የህይወት አጋሬ ናት የምትላትን ሴት ከምንም በላይ አክብራት፤ ቅድሚያም ስጣት፡፡ አንቺም እንደዛው እህቴ የእኔ እምነት አና አቋም ይህ ነው ፡፡
🌷🌷🌷
#አዎን_ወዳጄ ፦
🌷🌷
🚺 ሚስት ስጦታ እንጂ ምርጫ እንዳልሆነች ልብ በል
👇🌷👇🌷👇🌷👇🌷👇🌷👇🌷🌷🌷🌷👇🌷🌷
Join us
@CoolmanEfu
@CoolmanEfu
@CoolmanEfu
@CoolmanEfu
@CoolmanEfu
@CoolmanEfu
የተመቸው ሼር ያድርገው
BY ቃል ብቻ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/CoolmanEfu/2140