በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ አቆሙ‼️

በሳውዲ አረቢያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ እና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ ማቆማቸው ተጠቁሟል።

በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል ሪያድ፣ ዲሪያህ፣ ሁረይማላ ከዱርማ እና አል ቁዋይያህ ይገኙበታል ተብሏል።

የሀገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀው ለጥንቃቄ ሲባል በአሲር፣ ናጅራን እና በሌሎች የተጎዱ አከባቢዎች የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል።

ኪንግ ካሊድ ዩኒቨርሲቲ እና ናጃራን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም የቢሻ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲዎች በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ የተነሳ ስራቸውን ማቆማቸውም ነው የተገለጸው።

የሀገሪቱ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል በአየር ሁኔታ ዘገባው በምስራቅ እና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክልሎች በቀጣይ ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዮአል።

ከመካከለኛ እስከ ከባድ ነጎድጓዳማ ንፋስና በረዶ የታጀበ የአየር ሁኔታ በሪያድ ክልል እስከ ሰኞ ድረስ እንደሚቀጥልም ማዕከሉ ገልጿል።

በተጨማሪም ማዕከሉ በቀይ ባህር እና በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ያለው የባህር ላይ የንፋስ ፍጥነት በሰአት እስከ 50 ኪ.ሜ እንደሆነና እና በነጎድጓድ ጊዜ ከፍታው ከሁለት ሜትር ሊበልጥ እንደሚችል ማስታወቁን ገልፍ ኒዊስ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የለኝም‼️

🗣የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንደሌለው አስታውቋል፡፡

አጭበርባሪዎች የባንኩን ስምና አርማ እንዲሁም ቀለማት በመጠቀም ሀሰተኛ ገጾችን በመክፈት የማጭበርበር ወንጀል እየፈፀሙ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ለህበረተሰቡ በማሳወቅ ላይ እንደሚገኝም ባንኩ ገልጿል።

በምስሉ የተመለከተው በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ የቴሌግራም ገፅ ሀሰተኛ መሆኑን የገለፀው ባንኩ፤ ይህ ሀሰተኛ ገፅ አባላትን ስታስገቡ (Add member) ሽልማት ታገኛላችሁ በሚል የማጭበርበሪያ መልእክት የተከታዮቹን ቁጥር በማሳደግ ላይ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ባንኩ በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንደሌለው ግልፆ፤ ደንበኞች የባንኩን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ እና ከአጭበርባሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼️

በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስታውቋል።

ከኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር፣ ከሶማሊያና ኬኒያ የሚያዋስኑ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲል የጉዞ መረጃዎችን በሚሰጥበት ድረገፅ አስፍሯል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል ገለጸ ‼️

የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሀድ ተከታታይ ውይይትና ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ከህወሓት አጭር መረጃ እንደተመለከተችው "ህወሓት እና ብልጽግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው" በማለት በይፋዊ ገጹ ሰፍሯል።

ይኹን እንጁ ልዩነቶቹ እንዳሉ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች በመኖራቸው ተከታታይ ውይይት ተጀምሯል ተብሏል።

"ከዚህ ባለፈ ግን ህወሓት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው" ሲል ድርጅቱ ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ሕወሓት ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ ነው በሚሉት ዘገባዎች የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር መጀመራቸው እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀ መንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው ድርድሩን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

እነዚሁ ዘገባዎች በህወሓት ውስጥ ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው" በሚሉ እና "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው" በሚሉት ሃሳቦች መከፋፈል መኖሩን የጠቆሙ ቢሆንም ህወሓት ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ሐሰተኛ መረጃ‼️

በአማራ ክልል የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት ይመለከታል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ነው።

ሰሞኑን በአማራ ክልል ‘የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታትን ይመለከታል’ በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተጠቆመ።

ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደሮች በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ደብዳቤ የተጻፈ በማስመሰል የወጣው መረጃ ፍጹም ሐሰት መሆኑን ክልሉ አረጋግጧል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በክልሉ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።

በዚህም በክልሉ ያሉ የጸጥታ ኃይሎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅተው እያመጡት ያለው ውጤት ኪሳራ ያደረሰባቸው ኃይሎች በሚልሻውና ህብረተሰቡ ውስጥ መደናገርን ለመፍጠር አልመው የፈጸሙት እኩይ ድርጊት መሆኑ ተገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ስራ እስካሁን ከ9ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተነገረ‼️

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
[CREATINE MONOHYADRATE ]

ጡንቻን ለመገንባት እና ጉልበት ለማግኘት፤ ለሰውነትዎ የሚያስፈልገውን ይስጡት!

ጥንካሬ፣ብርታት እና ፈጣን የሰዉነት ጥገና ያስፈልገኛል ብለዉ ካሰቡ ክሬቲን ይገባዎታል
👨🏾‍⚕️የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት እንደሚያሳየዉ ክሬቲን የሚጠቀሙ አትሌቶች እና ስፓርተኞች 23 % የተሻለ አፈጻጸም እና ጥገና ያሳያሉ!🏃‍♂️

ለነፃ የምክር አገልግሎት እና የተሟላ መረጃ ወደ ጥሪ ማእከላችን ይደውሉልን።

አድራሻችን;- ሆሳዕና ጮራሞ ሕንፃ 1 ፎቅ የቤት ቁጥር 07 ጎራ በማለት የሚፈልጉትን ያገኛሉ።

☎️ +251966114766 ☎️

☎️ 9369 ላይ ይደውሉ   ☎️
ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት‼️

🗣አቶ ጌታቸው ረዳ

በማህበራዊ ሚዲያ " ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ድርድር እየተካሄደ ነው " የሚሉት መረጃዎች ፍጹም ሐሰተኛ ናቸው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለ ' ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ' ተናግረዋል።

ብልፅግና እና ህወሓት ንግግር ማድረግ መጀመራቸውን የገለጹት አቶ ጌታቸው "  እነዚህ ንግግሮች ከውህደት ጋር የተያያዙ አይደሉም " ብለዋል።

" የቅርብ ጊዜው ንግግራችን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ስለማድረግ ነው። ውህደት አጀንዳም ሆኖ አያውቅም " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ስላላቸው የስራ ግኝኑት በተመለከተ ፥ " ጥሩ የሥራ ግንኙነት ነው ያለን። የራሳችን የሆነ ልዩነት አለን። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አመለካከቶች አሉን " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያው ስምምነት አብረን እንድንሠራ ዕድል ስለሰጠን፤ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችን ምንም ይሁኑ ምን አብረን እንድንሠራ አስችሎናል። ይህም ወደፊት ይቀጥላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ አቶ ጌታቸው በጦርነቱ ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ በሙሉ ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል።

" ማንም ሰው ቢሆን፤ እኔን ጨምሮ መጠየቅ አለብን። ማንም ነጻ እንዲሆን መፈቀድ የለበትም። ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት " ሲሉ ገልጸዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው‼️

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡

አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል።

ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ምርመራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጾ መልስ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።ፍርድ ቤቱም በአያያዝ ላይ ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በሚመለከት በጽሑፍ በዝርዝር ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጾ፤ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም ክፍያ
ይህንን የቴሌግራም መተግበሪያ ይቀላቀላሉ።

https://www.tg-me.com/Poppycarmarket

☎️ 0911248768   👈 ይደውሉልን
በጾም ወቅት ምን ልጠቀም ብለዉ እያሰቡ ከሆነ በአንድ ማንኪያ ከ23 ግራም በላይ ፕሮቲን ሊያገኙበት የሚችሉትን 100% የቪጋን ፕሮቲን አመጣንልዎ።

🇺🇸🇪🇺 በከፍተኛ ጥራት የተመረተ

👉 አሁኑኑ ለማዘዝ ☎️ 9369 ☎️ላይ ይደውሉልን፣ የዘርፉ ባለሟያዎች ትክክለኛዎቹን ምርቶች ለመምረጥ እና ፈጣን አቅርቦትን ለማዘጋጀት ይረዳዎታል።

የሚያስፈልገው ጓደኛ ካለዎት share ማድረግዎን አይዘንጉ! 👇💪


📍 አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ☎️9369☎️


☎️ +251966113766 ☎️

Join  https://www.tg-me.com/+RCaZ_Ka6SOrlz0u5
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 21 ነጥብ 74 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤው 21 ነጥብ 74 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር ሬድዋን፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከቀጥተኛ ግብር፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ የግብር አገልግሎቶች እና ከሌሎች ዘርፎች 108 ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ አዳዲስ ፕሮጀክቶች በመጀመራቸው፤ የገቢ አፈጻጻሙ የተሻለ በመሆኑ እንዲሁም ካለፈው በጀት ዓመት ጥቅም ላይ ሳይውል የተላለፈ ሀብት በመኖሩ ተጨማሪ በጀቱ ጸድቋልም ነው የተባለው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
2024/04/27 05:25:52
Back to Top
HTML Embed Code: