የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የፕሪቶሪያው ስምምነት "እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር" ጠየቁ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር “በአካባቢው ማህበረሰቦች መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት በጥልቀት እየተከታተሉ” መሆኑን ገልጸው፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት “እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር” ጥሪ አቀረቡ።

የህብረቱ ሊቀመንበር በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ፤  ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት “በጣም አዋጭ አካሄድ”  የሆነው “የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ ያቀረቡ” ሲሆን በህወሃት እና ፌደራል መንግስቱ መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ  የተደረሰው የሰላም ስምምነት “እንዲከበር እና ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር ጠይቀዋል።
Ready to empower the next generation of learners? Join us on Edtech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia!
Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter.
#EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia
#DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia
#EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
በኮሪደር ልማት 1 ሺህ 135 ሰዎች አሁንም ምትክ ቤት ወይም ቦታ አለማግኘታቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናገሩ!

👉🏼ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸዉ አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው ተነስቶ ሌላ ቦታ የገባ ሰው የለም ብለዋል

በትናንትናው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ጥያቄ ካቀረቡ የምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ፤ ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች መካከል “1,135 ሰዎች አሁንም ምትክ ቤት ወይም ቦታ አለማግኘታቸውን” በማንሳት ጥያቄ አቅርበዋል።

“1,135 ሰው ማለት ቀላል አይደለም። በዚህ ወቅት፣ በዚህ የኑሮ ውድነት፣ በዚህ ጊዜ ተረጋግቶ የሚኖርበት አጋጣሚ ካልተፈጠረ፤ የሚሰራውን ስራ ሁሉ በዜሮ ድምር የሚያባዛ ነው የሚሆነውና እርሱ ለምን ግምት ውስጥ አልገባም?” ሲሉ መጠየቃቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በ90 ቀናት እንዲጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘለት በመጥቀስም፤ “የግድ በዚህ ሶስት ወር ውስጥ ስራ ማለቅ አለበት ወይ?” ሲሉ ተጨማሪ ጥያቄ አስከትለዋል። “በጊዜ ተለክቶ ስራ መሰራት አለበት፤ ልክ ነው። አምናም የ90 ቀን እቅድ ተብሎ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል። ሁልጊዜ ግን በዚህ መልክ በዘመቻ መሰራት አለበት ወይ? የሚል ጥያቄ ይስነሳል” ያሉት ዶ/ር ሲሳይ፤ “ነገሮች በተረጋጋ እና በታቀደ መልኩ እንዲሄዱ ለማድረግ መሰራት የለበትም ወይ?” ሲሉ አስተያየት አዘል ጥያቄ ማንሳታቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ የምክር ቤት አባሉ ከጠቀሷቸው የልማት ተነሺዎች ውስጥ “አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው ተነስቶ ሌላ ቦታ የገባ ሰው የለም።

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
       @ethio_mereja
🌺Foldable Push Up Board 
ተጣጣፊ ፑሽ አፕ መሳሪያ

         👉Training
   ✔️ Chest (ለደረት)
   ✔️ Triceps  (ለላይኛዉ ክንድ ጡንቻ)
   ✔️ Back (ለኃላ እጅ)
   ✔️ Shoulders (ለትከሻ)

 💦 ዋጋ፦ 1,400 ብር | ዴሊቨሪ ያስጨምራል

📍ውስን ፍሬ ነው ያለን/ Limited Stock

        ☎️ 0901882392
        ☎️ 0931448106
🪟ዋው የሚያስብሉ የግድግዳ ምስሎች😍

👉Shine laminated(የሚያብረቀርቅ)ናቸው።
👉በውሀ የሚፀዳ እና HD ማራኪ ናቸው!
👉በቀላሉ ባለው ማንጠልጠያ ሚሰቀል!!

     በትዛዝ በ3ቀን እናደርሳለን።

  ዋጋ :-  1.50*80 - 3500ብር
  ዋጋ :-  1.20*60 - 3000ብር

📍አድራሻ 4killo/ቀበና #ቤሊየር አልዘይን ህንፃ 207ቁ

     ☎️ 0901882392 /
     ☎️ 0931448106

ተጨማሪ T.me/Dinkwallarts
ON HAND - የጌታ እራት፣ Nature አለ።
ጊፍት ሪል ስቴት ከመንግስት ጋር በአጋርነት 2 ሺህ ቤቶችን በ3 ዓመታት ውስጥ ለመገንባት ስምምነት ተፈራረመ

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ጊፍት ሪል ስቴት ከመንግስት ጋር የሚሰራዉን የቤቶች ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ አስጀመረ።

በዚህ መርሃ ግብር ጊፍት ሪል ስቴት በዋና ከተማዋ ለገሃር አካባቢ በመጀመሪያ ዙር ግንባታ 4 ሺህ ቤቶችን መስራት መጀመሩ ተገልጿል። በሪል ስቴቱ የለገሃር መኖሪያ መንደር አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ አካላትን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ እንደሚያደርግ ጊፍት ሪል ስቴት አስታወቋል።

የዚህ የጊፍት ሪል ስቴት የለገሀር የመኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ግንባታ በ3 ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን 3 ሺህ 540 የመኖሪያ እንዲሁም 460 የንግድ ቤቶች እንደሚኖሩት ተገልጿል። የመኖሪያ መንደሩ ትምህርት ቤት እና ሌሎች ማህበራዊና ማህበረሰባዊ መገልገያዎችን ያካተተ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን የሕንጻዎቹ ከፍታ ከ14 እስከ 22 ወለል ይሆናል ተብሏል።

በሁለተኛ ዙር ለሚገነቡ 8 ሺህ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ግንባታ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል።

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
       @ethio_mereja
Ready to empower the next generation of learners? Join us on Edtech Mondays for an eye-opening discussion on Financing EdTech Startups in Ethiopia! Discover how investors are igniting innovation and driving change in the education landscape, overcoming unique challenges to support promising ventures. From bridging the digital divide to enhancing learning outcomes, explore the transformative potential of investing in EdTech startups. Tune in and be part of the movement to revolutionize education in Ethiopia!
Monday, April 29th at 8:10 pm on Fana FM 98.1 for insights that matter.
#EdTechEthiopia #EducationInnovation #JoinTheConversation #Ethiopia
#DigitalLiteracy #TechnologyInEducation #EdTechMondaysEthiopia
#EquityInEducation #Ethiopia #DigitalLiteracy #ShegaMedia #MastercardFoundation
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።(#MoE)

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
       @ethio_mereja
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አሳፋሪ ልማዶች አንዱ የሆነውን የመንገድ ላይ መፀዳዳትን እስከመጨረሻው ለማስቀረት በሺዎች የሚቆጠሩ የህዝብ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤት ቤቶችን ለመገንባት በጠ/ሚ አብይ አህመድ የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይፋ አድርገዋል ።

ጽዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚውለውን በጀት ለማሰባሰብ የጠ/ሚ ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት ዲጂታል ቴሌቶን አስጀምሯል። ይህን ተከትሎ ብዙዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የድርሻቸውን በማበርከት ላይ ይገኛሉ።
     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
       @ethio_mereja
🔖 ስራ እናስጀምርዎ - በነፃ

ከቤትዎ ሆነው በኦንላይን ከኛ ጋር ይስሩ!!!

ምንም ክፍያ አይጠይቅም፣ አሰራሩን በነፃ እናስተምራለን።

እቃዎችን በተለያዩ የኦንላይን አማራጮች
በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያግኙ፣ ገንዘብ ይስሩ!

👉100 ሪሴለሮችን እንፈልጋለን።

በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በማርኬትፕሌስ፣ በቲክቶክ፣
በኢንስታግራም፣ በራስዎ በማስተዋወቅ እቃዎችን ይሽጡ!

https://www.tg-me.com/AddisEkaResellers (ይቀላቀሉ)
https://www.tg-me.com/AddisEkaResellers (join-us)
https://www.tg-me.com/AddisEkaResellers (join-us)

Contact 👉 @Habeshastorechat

በተለይ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጎን ለጎን የምትሰሩት!

በስማርት ስልክዎ አሁኑኑ ካሉበት ስራ ይጀምሩ!
አሜሪካ ለዓለም ፍጻሜ መሸሸጊያ የሚውል አውሮፕላን እንዲሰራ አዘዘች፡፡

የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ እንደ ኑክሌር አይነት ጦርነት ቢነሳ ከአደጋ መጠበቅ የሚቻልበት አውሮፕላን እንዲሰራ ማዘዟ ተገልጿል፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ አሜሪካ በ1970ዎቹ የተሰራ የክፉ ቀን መጠለያ አውሮፕላን የሰራች ሲሆን ይህ አውሮፕላን አርጅቷል በሚል አዲስ ልዩ አውሮፕላን እንዲሰራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ለክፉ ቀን ማምለጫ ይሆናል የተባለው ይህ አውሮፕላንም 13 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይፈጃል የተባለ ሲሆን ሴራ ኔቫዳ ኮርፖሬሽን የተሰኘው ኩባንያ አዲሱን አውሮፕላን እንደሚሰራው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

ኢ-4ቢ የተሰኘ ስያሜ ያለው ይህ አዲስ አውሮፕላን አውሮፕላን በፈረንጆቹ 2036 እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል፡፡የአሜሪካ አየር ሀይል ንብረት የሆነው ይህ ልዩ የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እና ቴክኖሎጂዎችን ይዟል ተብሏል፡፡

እንዲሁም አውሮፕላኑ እንደ ኑክሌር ጦርነት፣ አውዳሚ አደጋዎች እና ሌሎች አስጊ ክስተቶች ቢከሰቱ መሪዎች በዚህ አውሮፕላን ላይ በመሆን ትዕዛዝ እና ውሳኔዎችን እንዲያካሂዱ ያገለግላልም ተብሏል፡፡ የመሰብሰቢያ ቢሮዎች፣ የነዳጅ መሙያዎች እና የተግባቦት መሳሪያዎችም ያሉት ሲሆን አሁን በስራ ላይ ያለው የክፉ ቀን መሸሸጊያ አውሮፕላን ከ2030 በኋላ ከአገልግሎት ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
       @ethio_mereja
2024/04/29 01:26:13
Back to Top
HTML Embed Code: