tg-me.com/Ethio_Jobs_In_Ethiopia/2068
Last Update:
በአንድ ወቅት አንድ በእድሜ የገፉ አሮጊት ጠርቀም ያለ ገንዘብ በመያዝ ወደ ባንክ በመሄድ በባንክ አካዉንታቸዉ ላይ እንዲያስገባዉ ለባንኩ ማናጀር የያዙትን ገንዘብ ይሰጡታል።
ሰውየውም የያዙትን ገንዘብ በዚህ እድሜያቸዉ ከየት እንዳመጡት ለማወቅ በመፈለግ ሁኔታ ''ይህን ሁሉ ገንዘብ ከየት ልታመጡ ቻላችሁ?'' ብሎ ይጠይቃቸዋል።
አሮጊቷም ''ልጄ ጎበዝ ቁማርተኛ ነኝ ቁማር እጫወታለሁ እና ሁሌም ነዉ የማሸንፈዉ።'' ይሉታል
ማናጀሩም እንዲያብራሩለት ፈለገና ''እንዴት ሁሌ ያሸንፋሉ? ቁማር ላይ ሁሌ መብላት እኮ ይከብዳል።'' ይላቸዋል።
እሳቸዉም ''አይ ልጄ........ እኔ አሸንፋለሁ!
ለምሳሌ አንተ ነገ ቂጥህን ትነቀሳለህ (tato) ብዬ ካንተ ልወራረድ እችላለሁ።'' ይሉታል።
''እናም ማናጀሩ እኔ እኮ ነገ አልነቀስም ስለዚህ እኔ እበላዎታለሁ።'' ሲላቸዉ ''አይ አትበላኝም ነገ ትነቀሳለህ እኔ እበላለሁ ከፈለክ እንውረድ።'' ይሉትና በ30 ሺ ብር ይወራረዳሉ።
እሳቸዉ ቂጥህን ነገ ትነቀሳለህ ሲሉ እሱ ነገ ቂጤን አልነቀስም ሲል ይወራረዱና ለማግስቱ ይቀጣጠራሉ።
በማግስቱ አሮጊቷ ከሁለት ታዛቢዎች ጋር በመሆን ማናጀሩ ወዳለበት ባንክ ቤት ይመጡና ''የተነቀስከውን ለማየት ሱሪህን አዉልቅ!'' ይሉታል።
ሰውየውም አለመነቀሱን እርግጠኛ ስለሆነ ሱሪውን ዝቅ በማረግ ቂጡን ያሳያቸዋል። ሴትየዋም እሺ በቃ ሱሪህን ልበስ አሸንፈኸኛል ይሉታል። እና የተወራረዱትን 30 ሺ ብር ማናጀሩ በአሸናፊነት ይረከባል።
ማናጀሩም ''ትላንት እኮ ሁሌም አሸንፋለሁ ብለውኝ ነበር።'' ታዲያ እኔ እንዴት አሸነፍኩዎት? ሲላቸዉ
አይ ልጄ አላሸነፍከኝም።
እኔ አሁን ከመጡት ሰዎች ጋር ዛሬ የማናጀሩን ዙሪ አስወልቀዋለሁ ብዬ በመቶ ሺህ ብር ተወራርደን ነዉ የመጣሁት ስና ሱሪህን ስላስወለቅኩህ 100,000 ብር ከእነሱ በልቻለሁ ይሉታል።
ወዳጄ ልትሸነፍበት በምትችልበት ሜዳ በጭራሽ አትጫወት። ሁሌም ማሸነፍያ መንገድህን ቀይስ።
ይቀላቀሉን!
@Gamel_Tube
@Gamel_Tube
@Gamel_Tube
BY Ethiojobs.com
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/Ethio_Jobs_In_Ethiopia/2068