Telegram Group Search
Forwarded from Tere
ከላይ በመግቢያዬ እንደጠቀስኩት፤ መስቀል በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትልቅ ክብር፤ ልዩ ስፍራ አለው። ማንኛውም ሕንጻ ቤ/ክ ያለ ሞገሰ መስቀል አይሠራም። ስግደትና አስተብርኮም ይቀርብለታል። መስቀልን መሳለምና በመስቀል ማማትብ፤ መባረክም የቆየ የቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ሥርዓት ነው።

መስቀልን በአንገት ማሰር፣ በግንባርና በክንድ ላይ መነቀስ፣ በአልባሳት፣ በአክሊል፣ በዘውድ፣ በገንዘብና በበትረ መንግሥት ላይ የሚደረገው የመስቀል ሃይማኖታዊ ምልክት እንጂ ጌጥ አይደለም።

እንደ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ለቅዱስ መስቀል አብያተ ክርስቲያናት ታንጸዋል። ከመስከረም ፲፭ እስከ ፳፭ ያለው ጊዜም ዘመነ-መስቀል ይባላል። በዚህ ወቅት ነገረ መስቀል ይነገራል፤ መዝሙረ መስቀል ይዘመራል። በአጠቃላይ መስቀል በኢትዮጵያ ቤ/ክ የጸሎት ጥንትና ተፍጻሜት ነው።

በመጨረሻም፤ ንጉሠ ሣሕለሥላሴ ከ200 ዓመት በፊት በኢየሩሳሌም ስላለው የኢትዮጵያ ቤ/ክ ገዳም - ስለዴር ሱልጣን ጉዳይ ለእንግሊዛዊው ቆንሲል ሳሙኤል ጎባት የጻፉትን ደብዳቤ ስንመለከት የራስጌ ማሕተማቸው የመስቀል ምልክት እንደነበር ይታያል። ይህን ጥንታዊ ደብዳቤ ከዚህ ጽሑፍ ጋር አባሪ አድርጌያለሁ።

ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ፤

"እግዚአብሔርም በእርሱ፥ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ጥልንም/ጥላቻንም በመስቀሉ ገድሎ፤ በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና፤" እንዲል የአባቶቻችን አምላክ በኢትዮጵያ ምድር ጥልና ጥላቻ/ጠላትነት ተወግዶ የሰላምን ዘመን ምናይበትን ጊዜ ያቅርብልን!! አሜን!!

መልካም የመስቀል በዓል!!
Happening Now: Attending consultation meeting on CSOs and Academia on promoting and consolidating HR and Democracy
Forwarded from Tere
የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በኢትዮጵያ [በትግራይ] ተሰማ...!!

ባያድለን ነው እንጂ ይሄ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ሁሉ ኀዘን፤ የምድሪቱ ልቅሶ መሆን ነበረበት!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

"ኢትዮጵያ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው. . . ?!" 

እንደ መግቢያ፤

"የኢትዮጵያ ሀገሬ ታጠቂ በገመድ፤

የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ፤
ያም ልጅሽ ያም ልጅሽ፤
ያም ዘመድ ያም ዘመድ፤
ለማን ታድያለሽ ... ለማንስ ይፈረድ?!

(የባህል ሙዚቃ ንግሥቷ ማሪቱ ለገሠ/እንደው ዘራፌዋ)


የኢትዮጵያና የኢትዮጵያን የታሪክና የሥልጣኔ እምብርት፤ የክርስትና እና የኢስላም ሃይማኖቶች (የርዕሰ አድባራት አክሱም ጽዮን እና የአልነጃሺ) መሠረት/መነሻ ምድር ኢትዮጵያ/አክሱም/ትግራይ፤

ኢትዮጵያውያን ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ጫፍ ተጠራርተው ብሔርና ጎሳ፤ ሃይማኖትና ቋንቋ ሳይለያቸው በአጥንታቸው ብዕርነት በደማቸው ቀለምነት የነጻነትን ክቡር መንፈስ ከፍ ባደረጉበት፤ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ሰንደቅ በተውለበለበባት፤ የኢትዮጵያዊነት የቃልኪዳን ውሉ በተቋጠረባት በዐድዋ/በትግራይ ምድር፤

በወንድማማች ጦርነት በአንድ ጀምበር ለወሬ ነጋሪ አንዱ እንኳን ሳይተርፉላት አምስቱም ልጆቿ/ሁሉም ማለቃቸውን ሰምታ ራስዋን ስላጠፋች፤ ኀዘን አቅሏን ስላሳታት የትግራይ/የኢትዮጵያ ምስኪን እናት ምን ምላሽ፤ ምንስ የማጽናኛ ቃል አለን...?!

በአማራ፣ በአፋር፣ በቤሻንጉል ጉሙዝ፣ በወለጋ... በሁሉም ኢትዮጵያ ምድር በጦርነት ነዲድ እየተለበለቡ በገፍና በግፍ ስላለቁትና እያለቁ ስላሉት የኢትዮጵያ ልጆች ምን እያልን፤ ምን እያሰብን ይሆን...?!

በቤተ መቅደሱ ደጃፍ ስለታረዱት ካህናት፣ ደማቸውን ውሻ ስለላሰው፣ በድናቸውን ለአውሬና ለአሞራ ሲሳይ ስለዳረግናቸው ወገኖቻችን፤ ስለተደፈሩ መነኮሳት፤ የሴትነታቸው ክብር በአደባባይ ስለተዋረደባቸው፣ ስለተጎሳቆለባቸው ምስኪን እናቶቻችና እህቶቻችን ምን ቃል፤ ምንስ አንደበት ይኖረን ይሆን...?!

የጦርነት ነጋሪት ስንጎስም፣ በወንድማማች ሕዝብ፤ በኢትዮጵያውያን መካከል የጥላቻን፤ የመለያየትን ዘር ስንዘራ የነበርን ነፍሰ-ገዳዮች/ቃኤላውያን ሆይ አሁን ገና የደም ግብራችን አልረካ ይሆን...?!

የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በኢትዮጵያ [በትግራይ] ተሰማ...!!

እነዚህ ኃይለ-ቃላት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱ ጥቅሶች ሲሆኑ፤ በተለያዩ ጊዜያት የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ እስራኤል፣ ስለ ኢየሩሳሌም/ስለጽዮን ውርደት፣ መከራና ሰቆቃ የተናገሯቸው ናቸው። ጥቅሶቹ የእናት ምድራችንን የኢትዮጵያን ኀዘን፤ የኢትዮጵያውያን እናቶችን ሰቆቃ/ታላቅ ስብራት የሚገልጽ መስሎ ስለተሰማኝ ነው- ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በመተካት አካፍላችሁ ዘንድ የወደድኹት።

"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ [በትግራይ] ተሰማ፤ ራሔል [ኢትዮጵያ] ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን ፈጽሞ እንቢ አለች።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ፴፩፤፲፭)።

"ድምፅ በኢትዮጵያ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ የትግራይ እናት ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትንም አልወደደችም።"

ኢትዮጵያ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ በምድርም ላይ ጨለሙ፤ የእናቶች ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአልና፤

የኢትዮጵያ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፤ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፤ ደናግላን ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ።

ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች [የአክሱም መንገዶች] አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተጨነቁ፤ እርስዋም በታላቅ ምሬት ውስጥ አለች።

በኢትዮጵያ ሴቶችን፥ በከተሞቿም ደናግልን አጐሰቈሉ፤ አለቆች በእጃቸው ተሰቀሉ፤ በመቅደሱ የካህናት፣ በአደባባይም የሽማግሌዎች ፊት አልታፈረም። 

ጕልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ። ሽማግሌዎች ከአደባባይ፥ ጕልማሶች ከበገናቸው ተሻሩ።

አቤቱ፥ ተጨንቅናል፥ አንጀታችም ታውኮብናልና፤ ተመልከት፤ ልባችን በውስጣችን ተገላበጠብን፤ በሜዳ ሰይፍ ልጆቻችንን አጠፋ በቤታችንም ሞት አለ።

ድንጋጤና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን። ስለ ወገናችን ሴት ልጆች ቅጥቃጤ ዓይናችን የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች። እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይናችን ሳያቋርጥ ዝም ሳይሉ እንባን ያፈሳሉ። 

የልባችን ደስታ ቀርቶአል፤ ዘፈናችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል፤ ዓይናችን በእንባ ደከመች፥ አንጀታችንም ታወከ፤ ስለ ኢትዮጵያ ወገኖቼ ቅጥቃጤ ጉበታችን በምድር ላይ ተዘረገፈ። 

ኢትዮጵያ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው? 

ነቢያቶችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፤ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፤ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።

እንደ መውጫ፤

አንጋፋው ፖለቲከኛ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ፣ አዛውንቱ ዶክተር ኃይሉ አርዓያ- በዛን ጊዜው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ/የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበሩበት በ1950 ዎቹ ስለኢትዮጵያ የቋጠሩት ስንኝ ለአሁኗ ኢትዮጵያም የሚስማማት ይመስለኛል። እንሆ ከዶ/ር ኃይሉ አርዓያ እንጉርጉሮ/ስንኞች፤

"... ይኸው ትታያለች ለሕዝብ በይፋ፣
ጥቁር ተከናንባ ጥቁር ተጎናጽፋ፡፡
እኔስ መስሎኝ ነበር ዘመድ የሞተባት፣
የእናት ሞት የአባት ሞት፣
የልጅ ሞት ያጠቃት፣
ለካ እሷስ ኖራለች ዘመን የሞተባት...!!

(ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕ. ፭)
----------
፲፯፤ አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ። ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። 

፲፰፤ ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል። 

፲፱፤ አቤቱ፥ አንተ ለዘላለም ትኖራለህ፤ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው። 

፳፤ ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ? 

፳፩፤ አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ። 

፳፪፤ ነገር ግን ፈጽመህ ጥለኸናል፤ እጅግ ተቈጥተኸናል።

ሰላም ለኢትዮጵያ፤ ሰላም ለምድራችን🕊🕊
ስለ ኢትዮጵያዊነት፣
ኢትዮጵያዊነት የዜጎች ምብት ማስከበሪያ ድርጅት (ኢትዮጵያዊነት) እ.ኤ.አ በ 2012 ዓ/ም የተቋቋመ፣ በውጭና በሀገር ቤት የሚንቀሳቀስ፣ ፆታ፣ብሔር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ወዘተ የማይለይ፣  የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ የማህበረሰብ (ሲቪክ) ድርጅት ነው።  ድርጅታችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያየተደረጉትን ጥረቶች ፣ በከፊልም ቢሆን የሚገልፁ ፣ ሀገራዊ ይዘት ያሏቸውን ምስሎችና 
ቪዲዮዎችን በ ዩትዩብ : Voice of Ethiopiawinnet ላይ ያገኛሉ።
ዌብሳይት፡- https://www.ethiopiawin.net   
ፌስ ቡክ: https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA
ቴሌግራም፡ https://www.tg-me.com/Ethiopiawinnet CDCR ኢትዮጵያዊነት 🇪🇹/com.ethiopiawinnetaa
ሊንክደን፡ 
https://www.linkedin.com/company/79367322/
ዩትዩብ : Voice of Ethiopiawinnet

በቀጥታ ለማግኘት   [email protected]  / [email protected] ብለው ይፃፉልን።
ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ የአማራን ሕዝብ እንደ ጨቋኝ ያስፈረጀው ትርክቶች ያስከተሉት ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበረሠባዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶች” በሚል ርዕስ ሁለተኛው የዌቢናር ጉባዔ ቅዳሜ ኦክቶበር 21, 2023 10:00 AM EST ጀምሮ ይከናወናል።

ይህ ባለፈው ሳምንት በዌቢናር 1 ተደርጎ የነበረው "የፀረ አማራ ትርክቶች መንስኤዎች ምን ምን ናቸው? በሚል የተደረገው ታሪካዊ ውይይት ተከታይ ነው።

በመጭው ሳምንት ኦክቶበር 28፣ 2023 ዓ/ም ደግሞ፣ ከዚህ ምን እንማራለን ፣ ምንስ ማድረግ አለብን? በሚል በመፍትሔ ላይ ያተኮረ ውይይት፣ በምሁራንና ታዳሚዎች ይደረጋል። ይህ ይህ የመጨረሻው ክፍል ይሆናል።

እርስዎም የእነዚህ ዌቢናሮችታዳሚ እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን። ይመዝገቡ። ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ የአማራን ሕዝብ እንደ ጨቋኝ ያስፈረጀው ትርክቶች ያስከተሉት ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበረሠባዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶች” በሚል ርዕስ ሁለተኛው የዌቢናር ጉባዔ ቅዳሜ ኦክቶበር 21, 2023 10:00 AM EST ጀምሮ ይከናወናል።
For Registration: https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_262birqYQAKIOWyTQaw7TA
ዌቢናሩን ለመታደም በቀጣዩ ሊንክ በመክፈት እንዲመዘገቡ በአክብሮት እንብዛለን ይመዝገቡ፡: https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_TXdo1-akSJmMRGUEFykW5g Share to Others
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ዌብናሩን ለመታደግ የሚቀጥለዉን ሊንክ በመጠቀም መከታተል ይችላሉ። ቀኑ ሐምሌ 20 ቅዳሜ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ነዉ። ሊንኩን ለሌሎች ሰዎች በማጋራት እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን።https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_GuwFE_qYR9OurhWOuCIa3A
በታላቅ አክብሮት አብረውን እንዲሆኑ ተጋብዘዋል፤ ቀኑን ይመዝግቡ ለመሳተፍ ይመዝገቡ
የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ (ኢትዮጵያዊነት): “የኢትዮጵያን ሥርዓተ ትምህርት ማዘመን ለዕውቀት ልኅቀት፤ ለአንድነትና ለሃገር ግንባታ ዕድገት” በሚል ልዕለ ርዕስ የትምህርተ ሥርዓቱ የሄደበትን ረዢም ታሪክ የመረመረ፤ የትምህርት ሥርዓቱ አሁን ላይ ያለበትን ቁመና በመመርመር፤ የጎሣ ክፍፍል እንዲሰፍን ትኩረት ሰጥቶ የተጫወተውን ሚና በማሳየት፤ ጠንካራ ጎኑን እና ድክመቱን በመዳሰሰ ለማሻሻል ያለውን ዕድል (Addressing Weaknesses and Opportunities for Reform) የመረመረ አቅርቦት ይደረጋል።  በዚህ ዌቢናር፤ የብሄራዊ አንድነታችን መታወቂያና ባህላዊ ቅርስ የሆነው የግዕዝ ፊደል ለሕዝብ መቀራረብና ለትምህርት አቅርቦት እንዲሁም ሥሉጥነት ታሪክ በሰፊው የዳሰሰ ንዑስ አርዕስቶችን ያካተተ ጉባኤ (ዌቢናር) እአአ ቅዳሜ ታህሣስ 14 ቀን 2024 ዓም (Saturday December 14, 2024) ለማካሄድ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን በደስታ ስንገልፅ፤ በተዘጋጀው ዌቢናር ተካፋይ በመሆን እንዲሳተፉ በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናስቀድማለን።   
ቀደም ሲል ተካሂዶ በነበረው የግዕዝ ፊደልና አማርኛ እንደ ቋንቋ በስፋትና በጥልቀት የቀርበ መሆኑን እያስታወስን፤ በዚህኛው አቅርቦት የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት አሰጥጥ ከግዕዝ ፊደልና ከአማርኛ ቋንቋ እንዲርቅ እየተደረገ መምጣት የሕዝብ ለሕዝብ መግባባት ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ እንዲዳስስና በቅርቡም ይኸው አማርኛን የሚያገልለው የትምህርት ሥራዓት ፖሊሲ፤ ሕግ ሆኖ እንዲፀድቅና እንዲደነገግ ለፓርላማ ውይይት እንዲደረግበት መቅረቡ የጉዳዩን አሳሳቢነት አቅርቦ እንዲስተዋል ለማድረግና መፍትሄ እንዲሻ የሚያሳስብ ነው፡፡ 
This pivotal webinar brings together three distinguished experts on Saturday, December 14, 2024 to explore how Ethiopia’s education system can be transformed to achieve excellence while acting as a catalyst for unity and nation-building. Reflecting on Ethiopia’s historical legacy, current challenges, and proposal of future reforms, the presenters will explore how education can foster an inclusive national identity that transcends ethnic divisions. They will also highlight the crucial role of Amharic as a working language in preserving Ethiopia’s shared national heritage. 
This webinar will emphasize the role of education (both traditional and modern) in nation-building and fostering national unity. It will also highlight the importance of preserving Amharic as a foundational language in the education system, ensuring that it continues to serve as a bridge between Ethiopia's diverse ethnic groups.  Experiences from other African nations show that prioritizing foreign languages like English often leads to cultural fragmentation. Ethiopia must avoid this path by promoting Amharic alongside other languages, strengthening its role in nation-building. 
Please use the provided zoom link to register and join the discussion:
https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_UNDGeVnjRfai5XbSquJw0w 
2025/05/31 20:22:18
Back to Top
HTML Embed Code: