ኢትዮጵያ ወጣቶችን በማብቃት 2 ሚሊየን አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠር አቅዳለች- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ 2 ሚሊየን አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠር አልማለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሃብት መረጋጋትን እና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል ብለዋል።

በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚመራው ሥራ ምክክር እና እርቅ የሰላም ፍላጎታችን እና ተምኔታችን ማጠንጠኛ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ 2 ሚሊየን አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠር ማለሟንም ጠቅሰዋል፡፡https://www.fanabc.com/archives/244162
Live stream finished (43 minutes)
በመዲናዋ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል። የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸውን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ሕብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት መለየቱ ተገልጿል፡፡ ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈቱ…

https://www.fanabc.com/archives/244173
በኬንያ የኪጃቤ ግድብ መደርመስ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ከ45 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ኬንያ በጣለው ተከታታይ ከባድ ዝናብ አሮጌው የኪጃቤ የውኃ ግድብ መደርመስ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በካሙቹሪ መንደር የ45 ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት፤ አደጋው ያጋጠመው በአካባቢው የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ነው፡፡ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋው በመኖሪያ ቤቶች እና የመንገድ መሠረተ-ልማቶች ላይም ጉዳት ማድረሱን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ…

https://www.fanabc.com/archives/244182
ማስታወቂያ!

እንኳን አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 482/2013 የተቋቋመ ሲሆን፣ ዓላማውም ለገንዘብ አስቀማጮች የመድን ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት ለፋይናንስ ዘርፉ ጤናማነት አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡ በዚህም መሠረት አይበለውና አንድ ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኪሳራ አጋጥሞት ለገንዘብ አስቀማጮች ገንዘባቸውን መመለስ ቢያቅተው፣ ፈንዱ ኪሳራ ያጋጠመውን እና የወደቀውን ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ በመተካት ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ መቶ ሺህ ብር በፍጥነት የመመለስ ሃላፊነት አለው፡፡ ለገንዘብ አስቀማጮች የሚመለሰው ገንዘብም ከፋይናንስ ተቋማት የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል እስካሁን ባለው ሁኔታ ከብር 4.6 ቢሊዮን በላይ አረቦን (premium) ተሰብስቧል፡፡

ፈንዱ የራሱን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት፣ በየጊዜው የሚሰበስበውን አረቦን በሕግ አግባቡ መሠረት በመንግስት ግመጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115571597 እና +251115578534 መደወል ይቻላል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የ9 ወር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሦስት ቀናት የሚቆየው የብልጽግና ፓርቲ የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የዋና ጽሕፈት ቤቱ የዘርፍ ኃላፊዎች እና የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ቅቡልነት ያለው የሀገረ-መንግሥት ሥርዓት ለመገንባት፣ የሕዝቡን ተሳትፎ፣ ተጠቃሚነትና እርካታ ለማረጋገጥ…

https://www.fanabc.com/archives/244188
ኤልሳልቫዶር ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ልትከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤልሳልቫዶር በአፍሪካ ሁለተኛ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፈት መወሰኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በኤልሳልቫዶር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሌክሳንድራ ሂል ቲኖኮ የተመራ ልዑክ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ጋር ተወያይቷል፡፡ በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት እንዲሁም በደቡብ ደቡብ ማዕቀፍ በባለብዙ መድረኮች ትብብራቸውን በማጠናከር ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች…

https://www.fanabc.com/archives/244194
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። በዚህ መሰረትም ለማህበራዊ ሳይንስ ከሐምሌ 3 እስከ 5 ቀን፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ ከሐምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና…

https://www.fanabc.com/archives/244116
በምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሀገር ውስጥ በውጪ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር በቀል ምርቶች በመተካት 3 ነጥብ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከብክነት ማዳን መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ ከሚኒስቴሩ ሥራ አስፈፃሚዎች እና ሠራተኞች ጋር እየተወያየ ነው፡፡ በዚህ ወቅትም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት…

https://www.fanabc.com/archives/244201
በግብርና ሚኒስቴር የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም 2 የስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና ሚኒስቴር የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም 2 የስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ተካሂዷል፡፡ ፕሮግራሙ በግሎባል ክላይሜት ፈንድ (ጂሲኤፍ)የፋይናንስ ድጋፍ በ165 ሚሊየን ዶላር በጄት በአለም ባንክ አመቻችነት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የአምስት ዓመት በጀት 165 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ፥ ከዚህ…

https://www.fanabc.com/archives/244206
በሀሰት ሰነድ የመንግስት ይዞታ ላይ ካርታ የሰጡና ይዞታውን የሸጡ እስከ 13 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም በተጭበረበረ መንገድ 638 ካሬ ሜትር የመንግስት ይዞታ ላይ የማረጋገጫ ካርታ የሰጡና ይዞታውን ወስደው በመሸጥ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል ተብለው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ተወስኗል። የግራ ቀኝ የሰነድና የሰው ማስረጃዎችን መርምሮ የቅጣት ውሳኔ የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ…

https://www.fanabc.com/archives/244212
የውሃ ማጣሪያ ማሽን ለማምረት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢቲዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና አፒሞሶ ከተሰኘ የቼክ ሪፐብሊክ ኩባንያ ጋር የውሃ ማጣሪያ ማሽን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት፣ ለመገጣጠምና ለማምረት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)፣ የኢትዮ ኢንጂነሪግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ እና የአፒሞሶ…

https://www.fanabc.com/archives/244217
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ወደ ኬንያ ያመሩበትን የአይ ዲ ኤ ጉባዔ አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ኬንያ ያመሩበትን የአይ ዲ ኤ ጉባዔ አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው ዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባዔ ላይ ተሳትፏል፡፡

በጉባዔውም ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ 2 ሚሊየን አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠር ማለሟን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ጉባዔው የማኅበሩ ደጋፊዎችና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እያጋጠመ ያለውን አደጋ ለመቀነስ በትኩረት እየሰራች ነው – ጠ /ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እያጋጠመ ያለውን አደጋ ለመቀነስ በትኩረት እየሰራች እንደምትገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በናይሮቢ ኬንያ በተካሄደው የዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር ጉባዔ (አይ ዲ ኤ) ላይ ንግግር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው÷ የአፍሪካ ቀንድ በተለይ በአየር ንብረት…

https://www.fanabc.com/archives/244232
Live stream finished (1 hour)
2024/04/29 18:36:45
Back to Top
HTML Embed Code: