Telegram Group Search
Sponsored...
"የድሬዳዋ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ"
.
.
👇
Sponsored...
"የድሬዳዋ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ"
.
.
ከሐምሌ 2003 ዓ.ም በፊት በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ ይዞታዎችን ህጋዊ አድርጎ በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ ስራ እና በፕላን መሰረት መንገድ የማስከፈት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ፡፡
በቀበሌ 09 ከሐምሌ 2003 ዓ.ም በፊት የተያዙ ይዞታዎችን ህጋዊ የማድረግ ስራ እና በፕላን መሰረት መንገድ የማስከፈት ስራ አፈጻጸም እና በስራው ላይ የገጠሙ ችግሮች ተገምግመዋል፡
የመሬት ይዞታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሁሴን መሀመድሳኒ በቀበሌ 09 በስፋት የተጀመረውን ከ 2003 ዓ.ም በፊት የተያዙ ይዞታዎችን ህጋዊ የማድረግ እና የመንገድ ከፈታ ስራ ያለበት ደረጃ በቀበሌው በመገኘት ከቀበሌው አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ገምግመዋል፡፡
በዚህም የስራ አፈጻጸም ክትትል እና ግምገማ እነዚህን ይዞታዎች ህጋዊ የማድረግ ስራ በጽ/ቤቱ ብቻ የሚሰራ አለመሆኑ እና ቅንጅታዊ አሰራር የሚያስፈለግ በመሆኑ በቀበሌው የሚፈለጉ የባለቤትነት ሰነድ ማስረጃዎች ቶሎ ተጣርቶ ለ ጽ/ቤቱ መቅረብ እንደሚያስፈለግ ጠቁመዋል፡፡
ተያይዞም በዚሁ ቀበሌ መንገድ የመክፈት ስራ ከሚሰራባቸው አከባቢዎች መካከል ከገንደ ጨፌ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱም ተወካዮቹ በአከባቢው የመንገድ ችግር ያለ በመሆኑ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸው እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መቸገራቸውን አንስተዋል፡፡
የጽ/ቤቱ ኃላፊ  ዶ/ር ሁሴን መሀመድሳኒ  ጽ/ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት መንገድ የማስከፈት እና ህጋዊ የማድረግ ስራ በቀበሌው ልዩ ትኩረት ሰቶ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ በአከባቢው መንገድ የማስከፈት ስራው በአጭር ጊዜ እንደሚጀመር ለዚህም ስራ ህብረተሰቡ የበኩሉን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ከታች ያለውን የድሬዳዋ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮን የ Telegram ገጽ ተከታይ በመሆን ያላችሁን ቅሬታ እና ጥያቄዎችን መጠየቅ ትችላላቹ
Link👇
https://www.tg-me.com/Diredawalandanddevelopmentmanag
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እነዚህ ሰዎች በዚህ መልኩ እንዲዪቀረሹ ፈቃጁ ብልጽግና ነው‼️
🤔🤔🤔🤔
ወቅቱ የ1953 (በተለምዶ የታህሳሱ ግርግር) ተብሎ
የሚጠራው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከሽፎ ፤ ንጉሡም ንግስናቸውን አስቀጥለው ... የመፈንቅለ መንግስቱ አመራርና ተሳታፊዎች
የሞተው ሞቶ የተረፈው
ችሎት ፊት እየቀረቡ ክርክር እያደረጉ በነበረበት ከራሞት በአንዱ...

መፈንቅለ መንግስቱን ደግፈው ንግግር አድርገዋል በሚል ከድሬዳዋ ታስረው ወደ ፊንፍኔ የተወሰዱት ተከሳሽ ችሎት ፊት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እየሰጡ ነው ...

ዳኛው "ሠርተሃል ለተባለው ወንጀል ጥፋተኛ ነህ አይደለህም?" ሲል ጠየቀ። "የቱን ወንጀል?" አሉ ተከሳሽ ዳኛው ሰውየው ሠርተዋል የተባለውን የወንጀል ቃል በዚያ በተሰበሰበው ህዝብ ፊት ሊናገሩት አልወደዱምም አልደፈሩምምና "አንተ የሠራኸውን" ብለው ጠየቁ።
ተከሳሹም "እስቲ ወንጀል የተባለው ይነበብልኝ" ብለው አጥብቀው ይጠይቃሉ
..ይህን ጊዜ ዳኛው ሳይወዱ "ይሄን ጣሳ እግዚአብሔር ገላገለን፣ አወረደልን ማለትህን" ይሏቸውና "ለዚህ ጥፋተኛ ነህ አይደለህም?" ይሏቸዋል።
"የለም ተስተካክሎ ይጻፍልኝና እምነት ክህደቱን ልናገር" ይላሉ ዳኛው"የለም በዚሁ ላይ ጥፋተኛ ነኝ ወይ አይደለሁም በል" አሉ "ትክክለኛ ቃሌ ይጻፍና ነው እንጂ እንዲሁ ጥፋተኛ ነኝ አልልም" ብሎ ይመልሳሉ ሰውየው ...
"እሺ ምን ተብሎ ይስተካከል?" ሲሏቸው ... "ይህን የበሰበሰ የተጠረማመሰ አሮጌ ጣሳ እግዚአብሔር ገላገለን ነው ያልኩት..... " ሲሉ ዳኞች የተባለውን አልሰማንም ለማለት ጠረጴዛ ሥር ገብተው ተደበቁ። ... ጥቂት አቅማምተው ቆይተው በማመንታት "ይሄ ሰውዬ እብድ ነው። አማኑኤል ከአእምሮ በሽተኞች ጋር ይታከም" ብለው ላኳቸው ...

ምንጭ
"የታህሳሱ ግርግር እና መዘዙ"
ብርሀኑ አስረስ
ነገሮችን ሁሉ በኦሮሞ አጉል እየተረጎሙ ያሉ ሀይሎች ይሄን ሰካራም አስታወሱኝ

ሰውየው ስክር ቢልም አላቆመም፤ ስጋ ቤት በር ላይ ቁጭ ብሎ እየጠጣ ነዉ ።
ድንገት አንዲት ድመት ትመጣና "ሚ…ያውውው" ስትል ሰካራሙም "ግማሽ ኪሎ" ስጋ አለው ለስጋ ሻጩ ፡፡
ስጋ ሻጩም ግማሹን ኪሎ መዝኖ ሲሰጠው ለድመቷ ሰጣት ድመቷም በልታ ጨርሳ በድጋሚ "ሚ…ያ…ው.ውው" አለች ፡
አሁንም ሰካራሙ "ሩቡ ኪሎ" ስጋ አለ ስጋ ሻጩም መዝኖ ሲሰጠው አሁንም ለድመቷ ሰጣትና በልታ ሄደች ፡
ስጋ ሻጩ ሰካራሙን "ሂሳብ ስጠኝ?" ሲለው
ሰካራሙ ምን ብሎ ቢመልስለት መልካም ነው
.
"እንዴ ስጋዉ እኮ ለኔ አይደለም ድመቷ የምትለውን እያስተረጎምኩልህ ነበር እኮ" ብሎት አረፈው
Sponsored...
"የድሬዳዋ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ"
.
.
የሶስተኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ተገመገመ፡፡

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የሶስተኛ ሩብ አመት አፈጻጸም በቢሮው የማኔጅመንት አካላት ተገምግሟል፡፡

የአፈጻጸም ሪፖርቱ የቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዘላለም  ወጋየሁ የቀረበ ሲሆን የስራ ክፍሎች የእቅድ አፈጻጸም ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ እርምጃዎችን አካቷል።

በቀረበው ሪፓርት ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በዘጠና ቀናት ቀሪ በእቅድ የተያዙ የበጀት አመቱ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ትኩረት እንዲሰጥ ማኔጅመንቱ በጋራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም

ከታች ያለውን የድሬዳዋ የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮን የ ቴሌግራም ገጽ ተከታይ በመሆን ያላችሁን ቅሬታ እና ጥያቄዎችን መጠየቅ ትችላላቹ
Link👇
https://www.tg-me.com/Diredawalandanddevelopmentmanag
ከአሁን ቀደም ዝምባዋብዌ ድረስ በመሄድ መንግስቱ ሀይለማርያምን ቃለ መጠይቅ በማድረግ መጽሀፍ ያጋራችን ገነት አየለ ዛሬ የመንግስቱ ሀይለማርያም የ83ኛ አመት የልደት ቀኑ መሆኑን አስመልክቶ ምናልባትም ከሰላሳ አመት በላይ በምስል ያልታየችው የልጆቹን እናት (ባለቤቱ) ውባንቺ ቢሻውን ምስል አጋርታን ብመለከት "ነበር" በሚለው መጽሀፍ ገጽ 201 ላይ ስለ ውባንቺ ቢሻው የተጻፈውን ለማስታወስ ሞከርኩ ። እንዲህ ይላል...
"እሳቸው የፖለቲከኛ ሚስት መሆን የሚችሉ አልነበሩም። ምክንያቱም ፖለቲካ የዞረበትን አያውቁም ነበርና ነው።
የወታደር ሚስትም መሆን አልነበረባቸውም ምክንያቱም ድንጉጥ እና ስጉ ነበሩና ነው።
የነጋዴ ሚስት ሊሆኑም አይችሉም። ቸር እና ሩህሩህ በመሆናቸው።
የዳኛ ሚስትም አይሆኑም፤ ከአዛኝነታቸው የተነሳ አማላጅነታቸው ስለሚያስቸግር።
የቄስ ሚስት ግን መሆን ይችላሉ። ምክንያቱም ጥሩ የቤት እመቤት ሆነቅ ከትሁት ባል ጋር ሰላማዊ ኑሮ መኖር ያለባቸው ሴት ነበሩና። በአጭሩ ውብአንቺ ቢሻው ማለት እኚህ ነበሩ" ይለናል (የቄስ ያለው የዘንድሮውን ሳይሆኖ የድሮውን ቄስ እንደሆነ ይታወቅልኝ)
2024/05/28 00:11:10
Back to Top
HTML Embed Code: