Telegram Group & Telegram Channel
Forwarded from Bketa @¥

          ✥ ቅዱስ ያሬድ ✥

✥መላእክት ምስጋናቸው እረፍታቸው ፣ እረፍታቸው ምስጋናቸው ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ እግዚኣብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግናሉ፡፡ ቤተክስቲያንም አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ናትና ይህን አብነት በማድረግ ልዑል እግዚኣብሔር ሃያ አራት ሰዓት የሚመሰገንበትን የምስጋና ሥርዓት ዘርግታለች፡፡ሕያው እግዚኣብሔር የአዳም ልጆች በመላእክት ምስጋና እንዲያመሰግኑት በመውደዱ ሰማያዊውን ምስጋና ይማር ዘንድ ቅዱስ ያሬድን መረጠ፡፡

👉ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊው ሊቅ

ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ.ም ኣክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ ያሬድ ማለት መውረድ ማለት ነው ፡፡ ሰማያዊውን ጣእመ ዜማ ወደ እኛ የሚያወርድ ነውና፡፡‹‹ዋይ ዜማ!!! ዘሰማዕኩ እመላእክት ቅዱሳን ›› ‹‹ ከሰማይ ከቅዱሳን መላእክት የሚያስደንቅ ዜማ ሰማሁ›› በማለት እንደተናገረ በኣክሱም መጽሓፍትን እያስተማረ ሳለ ከሰማያውያን መላእክት ጣእመ ዜማን ተማረ፡፡
በተመስጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተነጠቀ፡፡ በዚያም መላእክት ልዩ ጣእም ባለው የዜማ ድምፅ ሲያመሰግኑ ሲዘምሩና ሲያሸበሽቡ አየ፡፡ ከጣዕመ ዜማውም የተነሣ ተደነቀ፡፡ የእግዚኣብሔርን ስም እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን በጠራ ጊዜ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ተገለጸለት፡፡ ተመልሶም ወደ ምሥራቅ ዞሮ እጁንም ዘርግቶ ‹‹ ሃሌ ሉያ ለአብ ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፣ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን . . . ›› ብሎ በኣክሱም ከተማ ሙራደ ቃል /የቃል መውረጃ/ በተባለችው ሥፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ ዜማን በዐውደ ምሕረት ያሰማ የዜማ ደራሲ ነው፡፡

👉የቅዱስ ያሬድ አስተዋጽኦ

📌ዓለም ከሚያውቃቸው የዜማ ደራስያን ከሞዛርትና ከሌሎችም አስቀድሞ ቅዱስ ያሬድ ግእዝ፣ እዝል ፣ አራራይ በተሰኙ የዜማ ስልቶች የማይሰለችና ዘመን ተሸጋሪ ዜማን፣ የዜማ ምልክቶችንና የተለያዩ ድርሰቶችን በመድረስ ሃገራችን የዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሃብት ባለቤት እድትሆን ኣድርጓል፡፡

📌📌 ቅዱስ ያሬድ በሰዓታት ፣በወራትና በዘመናት የተከፋፈሉ ድንቅ ምስጋናዎችን ከብሉያትና ከሐዲሳት ንባብና ምሥጢር ለቤተክርስቲያን እንደ ሰምና ወርቅ ኣስማምቶ የአገልግሎት ሥርዓትን የሠራ የቤተ ክርስቲያን ዓምድ ነው፡፡

📌📌 የቅዱስ ያሬድ ዜማ ድንቅና ጥልቅ የነገረ ሃይማኖት አስተምህሮት ፣ የቅዱሳት መጽሓፍትን ንባብ ትርጓሜ እንዲሁም የታሪክ ምስክርነትን የያዘ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ድርሰት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዛሬ በጉባኤ ቤት ለዜማ ትምህርት ቤተክርስቲያን የምትገለገልበትን ሥርዓተ ትምህርትና የመማሪያ መጽሓፍትን የደረሰ ሊቅ ነው፡፡ ድረሰቶቹም ምዕራፍ ፣ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ዝማሬና መዋሥዕት ይባላሉ፡፡

📌📌ቅዱስ ያሬድ በአክሱም በመምህሩ በጌዴዎን ወንበር ተተክቶ መጽሓፍተ ብሉያትና ሓዲሳትን ኣስተምሯል፡፡ ከኦቡነ አረጋዊና ከኣፄ ገብረ መስቀል ጋርም በመሆን በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎት በጣና ቂርቆስ ፣ በዙር ኣባ ኣቡነ ኣረጋዊ ገዳም እንዲሁም ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ እስከ ብርብር ማርያም በመሄድ ያስተማረ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡

  አጠቃላይ በሥነ ጽሑፍና በቋንቋ እድገት በነገረ መለኮትና በታሪክ ትምህርት እንዲሁም በሥርዓተ ጸሎት የቤተ ክርስቲያን ኣንድነት በማስጠበቅ ረገድ ጽኑ መሠረትን የጣለ ታላቅ ሊቅ ነው፡፡

👉 የቅዱስ ያሬድ ምናኔ

📌📌 ቅዱስ ያሬድ የሕይወት ዘመኑን በጸሎትና በብሕትውና ለማሳለፍ ወደ ሰሜን ተራራ ምድረ ጸለምት በመሄድ /በሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት በበየዳ ወረዳ በሚገኝ ሥፍራ/ ብርድ በጸናበት በረዶ በሚፈላበት በሐዊ ተራራ በጽሙና ተቀምጧል፡፡ በዚያም ጉባኤ ዘርግቶ ትምህርት አስፋፍቶ ለሃያ ሁለት ዓመታት ኣስተምሯል፡፡
📌📌ቅዱስ ያሬድ ዘመኑን ሁሉ በማኅሌት እግዚኣብሔርን በማገልገል በጣእመ ዜማው ዲያብስን ድል መትቶ በዚያው በሓዊ ተራራ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ ገብቶ ግንቦት 11 ቀን በሰባ ኣምስት ዓመቱ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ ተለይቷል(ተሰውሯል)፡፡ ቤተክርስቲያንም ቅድስናውንና ኣማላጅነቱን ኣምና በስሙ ጽሌ ቀርጻ፣ ቤተክርስቲያን አንጻ ፣ ድርስቶቹንም የቤተክርስቲያን መገልገያና የስርዓተ ኣምልኮ መፈጸሚያ አድርጋ እየተጠቀመችባቸው ተገኛለች፡፡

በምናኔ በኖረበት ሥፍራም በስሙ ገዳም ተገድሞ መናንያን አሰረ ፍኖቱን ተከትለው ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ በረዶውንና ውርጩን ታግሠው በስሙ እየተማጸኑ ይኖራሉ::

                  እንኳን አደረሳችሁ

tg-me.com/HISCULHEROFETHIOPIA/5740
Create:
Last Update:

BY ኢትዮጵያ

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/HISCULHEROFETHIOPIA/5740

View MORE
Open in Telegram

ኢትዮጵያ Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

The S&P 500 slumped 1.8% on Monday and Tuesday, thanks to China Evergrande, the Chinese property company that looks like it is ready to default on its more-than $300 billion in debt. Cries of the next Lehman Brothers—or maybe the next Silverado?—echoed through the canyons of Wall Street as investors prepared for the worst.

The Singapore stock market has alternated between positive and negative finishes through the last five trading days since the end of the two-day winning streak in which it had added more than a dozen points or 0.4 percent. The Straits Times Index now sits just above the 3,060-point plateau and it's likely to see a narrow trading range on Monday.

ኢትዮጵያ from us

Telegram ኢትዮጵያ
FROM USA