ኢድ ሙባረክ | Eid Mubarak for all Muslim Families

Are you looking for innovative, cost-effective healthcare solutions Specially on Ultrasound, GI Endoscope, Complete ENT, OR and ICU Products?
Check out Pelican Healthcare Solutions! Pelican Healthcare Solutions

Contact: 0923958483
                 0941134447

https://www.tg-me.com/pelicanmedicalimport
Happy Father’s Day!

የአባቶችን ቀን በውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ለሠራተኞች አባቶች ነፃ የሕክምና ምርመራ በማድረግ እንዲህ አክብረናል።

በፍቅርና በምሳሌነት ቤታቸው ለመሩ፣ ለቤታቸው ለደከሙ፣ ልጆቻቸውን ለቁም ነገር ለማድረስ ለታተሩ ትጉህ አባቶች ሁሉ ክብረት ይስጥልን!

አጠገባችን ላሉ አባቶች ሁሉ እድሜ እና ጤና ይስጥልን!

ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል

@HakimEthio
"ኮቴንም ቢሆን ሸጬ ትማራለህ"

ከቃላት በላይ ተሰቶ በመኖር ፣ ነገዬን ለማሳመር እራስህን ቆጥበህ እኔን ላንቀባረረከኝ: "ኮቴንም ቢሆን ሸጬ ትማራለህ ያሰብክበት ትደርሳለህ" – ከሀገር ሀገር እየቀየርክ - የተሻለ ትምህርት ቤት የቱ ነዉ - የትኛው መጽሐፍ ይሻላል

This words of your keeps me motivated and inspired to do what i do wright now.
Having a conversation on what i am doing , what i am planning is something i perish every single second of my life.

Even when i fail on things, your words are too soothing and makes feel like i have gained a lot.

I am proud to continue the legacy of being the third-generation health professional.
Bzw they call me Dr. Tadesse , I wish መተህ ሁለታችንም አብረን ስንዛር አቤት ስንል - it would have been more fun.

Happy to be born from you.
THANK YOU FOR BEING MY FATHER
ታዬ መልካም የአባቶች ቀን

ዶ/ር አንተነህ ታደሰ: ሰርጅን እና ዩሮሎጂ ሰብ ስፔሻሊስት

@HakimEthio
የማህበራዊ ሚዲያ መስኮት ሱስ

ለድባቴ ፣ ራስ ለማጥፋት እሳቤ ፣ ለመካንነት... ወዘተ በኪሳችን የምንይዘው ስልክ መንስኤ እየሆነ ነው ።

አለም ረቀቅ ብላለች። ሰው መረጃን በቀላሉ እንዲያገኝ ፤ እንዲለዋወጥ ፤ የቦታ ርቀት ሳይገድበው እርስ በራሱ እንዲገናኝ ያደረጉት የፈጠራ ውጤቶች ናቸው ። የመገናኛና የመረጃ መሳሪያዎች የሚሰጡት ጥቅም ቁጥር ስፍር ባይኖረውም የራሳቸው የሆነ አሉታዊ ጫና አላቸው ። መመጠን መልካም ነው ።

የማህበራዊ ሚዲያ መሳሪያ-መስኮት አጠቃቀም ርዝማኔ ገደብ ሳይኖረው ሲቀር ለከፍተኛ የጤና ቀውስ ሊያጋልጥ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ ። ጠቅለል ተደርጎ Screen addiction /የማህበራዊ ሚዲያ -መስኮት ሱስ / ተብሎ ተሰይሟል ።

ይኸ ሱስ ልክ እንደ ኮኬይንና አልኮል ሱስ አንጎልን ምጥጥ አድርጎ ለከፋ የአእምሮና አካላዊ ህመሞች የሚዳርግ የዚህ ዘመን አዲስ የሱስ አይነት ነው ። Digital Drug ብለው ይጠርሩታል ማህበራዊ ሚዲያ መስኮትን !

ለአእምሮ ጤና መታወክ፣ ለህፃናት አንጎል እድገት መገታት፣ ለመካንነትና ሌሎች አካላዊ ህመሞች እየዳረገ ስላለው የማህበራዊ ሚዲያ መገናኛ ቁስ- መስኮት ሱስ'ን በወፍ በረር ላካፍላችሁ ፦

ድባቴ በአለማችን ላይ ብዙዎችን እየፈተነ ያለ የአእምሮ ጤና መታወክ ህመም ነው ። ብዙዎች ህመማቸውን በጓዳ ደብቀው ለህመማቸው ሌላ ህመም እየሰጡ ያሉ አሉ ። ለዚህ ደ'ሞ ትልቁን ሚና የሚጫወተው ለአእምሮ ጤና የሚሰጠው ትኩረትና ጥንቃቄ ነው ። አእምሮ እንደሚታመም ፤ የታመም አእምሮ መታከም እንደሚችል የሚያቁ ቢኖሩም ያልተረዱት ያይላሉ ።

በቀን በስልካችን መስኮት ላይ የምናሳልፈው ግዜ ሲረዝም ለልዩ ልዩ የአእምሮ ህመሞች እንጋለጣለ ። በአንድም ሆነ በሌላ መስተጋብር ከስልካችን መስኮት ጋር ያለን የሁለት-እዮሽ ግንኙነት በቀን ከሁለት ሰዓት በላይ ሲሆን ለድባቴ ፣ ራስን ለማጥፋት እሳቤ ፣ ከልክ ላለፈ ፍራቻ፣ በራስ አለመተማመን ፣ አሉታዊ ለሆነ ቅናት፣... ወዘተ ችግሮች እንድንጋለጥ ያደርጋል ። ሲደብረን ዘና ለማለት የከፈትነው ማህበራዊ ሚዲያ ወደ ድባቴ ይዞን ይገባል ።

ወጣቶች በአእምሮ ህመም መጠቃታቸው ሳይታወቅ ሒወታቸውን የሚነጠቁበት አጋጣሚ እየሰማን ነው ። እያየን ነው ። መሳቅ የአንድን ሰው አእምሮ ጤና አለመታወክ አያረጋግጥም ። ብዙዎች እየሳቁ ይቺን አለም ሳይወዱ ተገደው ተሰናብተዋል ። የአእምሮ ጤና መታወክ ብዙ ምክነያቶችና ውስብስብ ጉዳዮች ቢኖሩትም ቴክኖሎጂ በራሱ ለከፉ የአእምሮ ህመሞች እየዳረገ ነው ። የስልክ ፣ የታብሌት፣ የቲቪ... አጠቃቀማችን አሁን አሁን አሳሳቢ ደረጃ ደርሶ ውጤቱ መታየት ጀምሯል ። ከነዚህ ቁሳቁሶች ጋር ረዘም ላለ ሰዓት ስንቆይ በቀጥታ ለድባቴ አሳልፈው ይሰጣሉ።

ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ የታዳጊ ህፃናት አንጎል ጤና ነው ። ህፃናት በስልክ፣ በታብሌት ፣ በቲቪ-መስኮት ላይ አዘውትረው ሲቆዩ አዳጊ በሆነው አንጎል ላይ ከፍተኛ የሆነ አካላዊና መዋቅራዊ ለውጥ እንዲካሔድ ምክነያት እየሆነ ነው ። አንጎል እድገቱ ይገታል ፥ እድገቱን ያልጨረሰ አንጎል አለያም መዋቅሩ የተዘበራረቀ አእምሮ ውጤቱ የከፋ ነው ። ልጆችን ለስነ ባህሪ ፣ ለትት አቀባበል ፣ ለትኩረት ማነስ ፣... ለብቸኝነት ወዘተ ችግሮች ሰለባ እየደረጋቸው ነው ። ሁሉም ወደ ልጆቹ ይመልከትና ትዝብቱን ይውሰድ ። ከዚህ ባለፈ ምናልባትም ቀስ በቀስ ሰው ሊያስብለን የሚችለውን አንጎል ሊያሳጣና ስነ ምግባር የሌለው አለያም አረመኔ ትውልድ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል ። ገና አዲስ ክስተት ስለሆነ ተጠንቶ አላለቀም ፤ ነገ አስደንጋጭ የጥናት ውጤት መስማታችን አይቀርምና ካሁኑ እንጠንቀቅ ።

አንድ አመት ከስድስት ወር በታች ለሆነ ህፃን ለምንም አይነት የመገናኛ ቁሳቁስ መስኮት ማጋለጥ እንደማይገባ ምሁራን ይመክራለሉ ። በቀን ከ1-2 ሰዓት በላይ የትኛውም ልጅም ሆነ አዋቂ መጋለጥ የለበትም ። የህፃናትን አንጎል መጠበቅ የወላጅ ብቻ ሐላፊነት ሳይሆን የሁሉም ሐላፊነት ነው ።

ወንዶችን ለመካንነት መዳረጉ ሌላው የስልክ መዘዝ ነው ። በተለይ በፊተኛው የሱሪ ኪስ መያዛቸው ከስልኩ የሚወጣው Electromagnetic radiation and thermal heat የወንድ ዘር ፍሬ አመራረትን በማስተጓጎል የወንድ ዘር ፍሬ እንዲቀንስና የተመረተውም የመቀሳቀስ አቅሙን እንዲያጣ በማድረግ መካን ያደርጋል ። በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ የወንድ ዘር ፍሬ ቁጥር በከፍተኛ መጠን መቀነሱ ይታወቃል ። ብዙ ምክነያቶች ቢኖሩም የስልክ አስተዋፅዖም የሚዘነጋ አይደለም ። በፊት ኪስ አይያዙ ወይም ቦርሳ ይዘው በውስጡ አኑረው በጀርባዎ ይሸከሙ !

ሰው ስልኩን ከፍቶ ያንንም ያንንም ሲያይ በሰውነት ውስጥ የሚመረቱ ቅመሞች(Hormones) ተፈጥሯዊ ዑደታቸውን ትተው በዘፈቀደ መመረት ይጀምራሉ ። መብዛት የሌለባቸው ቅመሞች ይበዛሉ ፤መኖር ያለባቸው ቅመሞች ይጠፋሉ በዚህም ሰውን ለዘርፈ ብዙ አካላዊና ስነ አእምሯዊ ህመም ይዳረጋል ። ሰው የሚደሰተው በነዚህ ቅመሞች ነው፤ የሚከፋውም እንደዛው ። በነዚህ የሰውነት ውስጥ ቅመሞች በሚፈጠር መዘበራረቅ ሳቢያ ብዙ ህመሞች ይከሰታሉ ። አንድ ሰው በቀን ከ362 ግዜ በላይ ከስልኩ ጋር ይፋጠጣል ። በተለይ ሌሊት ጉዳቱ የከፋ ነው ።

እንቅልፍን በማዛባት ቀዳሚ መሳሪያ ነው ስልክን መነካካት ። መልእክት ለብዙ ግዜ መላላክ አለያም የላኩት መልእክት መልስ እስኪያገኝ ደጋግመው የስልኮን መልእክት መቀበያ ሳጥን ሲያዩ በውስጦ ጭቀትና መረበሽ ይፈጥራል ። ቀስ እያለ በራስዎ የመተማመን አቅሞን እያሟጠጠ ወደ ከፋ ስነ ልቦናዊ ቀውስ ይወስዶታል ። በሌላ መልኩ ሰው ስልኩን እያሸራተተ ሲቆይ ለውፍረት ይጋለጣል ። ውፍረትን ተከትለው የሚመጡ እንደ ልብ ህመም ፣ እስትሮክ፣ ደም ግፊት መጨመር ... ቀስ እያሉ ይከተላሉ ።

ሁሉም ሰው የስልክ አጠቃቀሙ ላይ ለራሱም ለልጆቹም እቀባ መጣል አለበት ። በተለይ ቲክቶክ ከልጅ እስከ ደቂቅ እያደቀቀው ይመሰላል ። ዛሬ በስሜት እና በምን አለብኝነት የምናደርጋቸው ያልተገቡ ድርጊቶች ነገ አእምሯችንን እየጎነተሉ ወደ ቀውስ ሊወስዱ ስለሚችሉ በልክ መጠቀም የራስን ነገ ማሳመር ነው ።

ዛሬ እያጨበጨበ ማኖ ያስነካሽ ነገ <ፈጣሪ ይማርሽ> ሳይሆን የሚልሽ <አብዝታው ነበር > እንደሚል እያሰብሽ ነገሺን በዛሬ አታስታምሚ !!

ሚስት በቲክቶክ ሱስ ፣ ባል በመጠጥና ጫት ሱስ ሲለከፉ ትዳር የመፍረስ አደጋ ይገጥመዋል፤ የትውልድ ቅብብሎሽን ሊያመክን የሚችል መጥፎ ልምምድ ነው ይሆናል ። ሱስን እንከላከል!

ዶ/ር መስፍን በኃይሉ: ጥቁር አንበሳ

@HakimEthio
2024/06/16 16:36:23
Back to Top
HTML Embed Code: