Telegram Group & Telegram Channel
ሰላም ጤና ይስጥልኝ!

ዛሬ ለካንሰር ህክምና አንዱ ምሶሶ ስለሆነው የኬሞቴራፒ ህክምና የተወሰኑ ነገሮችን እንማማራለን።

1) ኬሞቴራፒ ምንድነው?

ኬሞቴራፒ ማለት የኬሚካል ህክምና ሲሆን ህክምናውም በፍጥነት እያደጉ ያሉን ህዋሶችን በጠንካራ ኬሚካሎች የምንገልበት መንገድ ነው። ኬሞቴራፒን በብዛት የምንጠቀመው ካንሰርን ለመግደል ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት የካንሰር ህዋሶች በፍጥነት የመባዛትና የማደግ ባህሪ ስላላቸው ነው።

በካንሰር ህክምና ውስጥ ብዙ አይነት የኬሞቴራፒ መድኃኒቶች ሲኖሩን እነዚህን መድኃኒቶች ለየብቻ ወይም ተደባልቀው ሊሰጡ ይችላሉ።

ኬሞቴራፒ ወይም የኬሚካል ህክምና ብዙ የካንሰር አይነቶችን የመግደል ብቃት ሲኖረው እራሱን የቻሉም የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት።

እነዚህም የጎንዮሽ ጉዳቶች ቀላል እና ሊታከሙ የሚችሉ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ጉዳቶች ግን ከባድ እና ለህክምናም አዳጋች ናቸው።

2) የኬሚካል ህክምናው(ኬሞቴራፒ) ለምን ይሰጣል?

ኬሞቴራፒ በዋነኝነት የሚሰጠው ካንሰር ያጠቃቸውን የካንሰር ህዋሶች ለመግደል ነው። ይህም ህክምና የተለያዩ መልኮች ይኖሩታል።

እነሱም፦
I) ሙሉ በሙሉ ካንሰሩን ለማጥፋት የሚሰጥ የኬሚካል ህክምና(Curative or Radical Chemotherapy)

- ኬሞቴራፒን በብቸኝነት ያለ ሌላ ህክምና ዕገዛ ካንሰሩን ለማጥፋት የምንጠቀምበት አግባብ ነው።

II) ከሌላ ህክምና በኋላ የሚሰጥ አጋዥ የኬሚካል ህክምና(Adjuvant Chemotherapy) ፦

ይህም ማለት ታካሚው የቀዶ ጥገና ከተደረገለት ወይም ካንሰሩን የማዳከም ህክምና ከተደረገ በኋላ የሚሰጥ ህክምናን ያካትታል። ይህም ህክምና ካንሰሩን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ይረዳል።

III) ለዋንኛው ህክምና ለማዘጋጀት የሚሰጥ የኬሚካል ህክምና(Neoadjuvant Chemotherapy) :-
ኬሞቴራፒው የካንሰሩን መጠን ለመቀነስ እና በኋላ ላይም ዋንኞቹን የህክምና አይነቶች(ለምሳሌ፦ የጨረር ህክምና ወይም የቀዶ ጥገና) በቀላሉ እንዲደረጉ ማመቻቸትን ያጠቃልላል።

IV) የካንሰር በሽታ ህመምን እና ምልክቶቹን ለመቀነስ የሚደረግ ህክምና፦

ኬሞቴራፒ የበሽታውን ስቃይና ህመም እንዲቀንስ ተብሎ የሚሰጥበት አግባብ ነው። ይህም ህክምና ፓሊዬቲቭ ኬሞቴራፒ ወይም ስቃይን የመቀነስ ህክምና ተብሎ ይታወቃል።

3) የኬሚካል ህክምና ከካንሰር በሽታ ውጪ ሊሰጥ ይችላል?

የህክምናው ጠበብቶች የዚህን የኬሚካል ህክመና ከካንሰር በሽታ በተጨማሪ ለሌሎች በሽታዎች ህክምናም ይጠቀሙባቸዋል። ከእነኚህም በሽታዎች መካከል የመቅኔ እና በሽታን የመከላከል አቅምን ለሚጎዱ ይገኙበታል።( Bone Marrow Disease and Immune System Disorders)

4) የኬሞቴራፒ የጎንዮሽ ጉዳቶች ምን ይመስላሉ?

የኬሚካል ህክምናው የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደየ ህክምናው አይነት ቢለያዩም ብዙዎቹ ግን የመመሳሰል ባህሪ አላቸው። እያንዳንዱ ኬሚካል እራሱን የቻለ የጎንዮሽ ጉዳት ሲያመጣ፤ ውህድ ሆነው ተደባልቀው ሲሰጡ ደግሞ ጉዳታቸው በዛኑ ያክል ይጨምራል።

የጎንዮሽ ጉዳቶቹም ይህን ይመስላሉ፦

ሀ) ማቅለሽለሽ
ለ) ማስመለስ
ሐ) ተቅማጥ ወይም የሰገራ መለስለስ
መ) የፀጉር መመለጥ
ሠ) የምግብ ፍላጎት መቀነስ
ረ) ድካም
ሰ) ትኩሳት
ሸ) የአፍና የከንፈር ቁስለት
ቀ) ህመም
በ) የሆድ ድርቀት
ተ) የቆዳ ቁስለት
ቸ) የመድማት ችግር እና ወ.ዘ.ተ

እነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች ልንከላከላቸው የምንችላቸው እና ሊታከሙም የሚችሉ ናቸው። ብዙዎቹ የጎንዮሽ ጉዳቶችም ከህክምናው በኋላ የሚጠፉ ናቸው።

5) ከኬሚካል ህክምና በኋላ ላይጠፉ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችስ አሉ?!

የኬሞቴራፒን ህክምና ተከትሎ የሚመጡ የጎንዮሽ ጉዳቶች ከወራቶች እንዲሁም ከዓመታት በኋላ ሊታዩ ይችላሉ። እነዚህም ጉዳቶች የዘገዩ የህክምናው ጉዳቶች( Late Side Effects) በመባል ይታወቃሉ።

ከእነኚህም መካከል፦

i) የሳንባ ህዋሶች ጉዳት
ii) የልብ ችግር
iii) መካንነት
iv) የኩላሊት ችግር
v) የነርቭ ጉዳት እና
vi) ህክምናውን ተከትሎ ከረጅም ዓመታት በኋላ የሚከሰት የጎንዮሽ ካንሰር ሊሆኑ ይችላል።

ከላይ የተጠቀሱት የጎንዮሽ ጉዳቶች ለታካሚው በተሰጠው የኬሚካል አይነት፣ የኬሚካል መጠን እና ውህድ ላይ ይመረኮዛሉ። የእነዚህ ችግሮች ምልክት የታየበት ግለሰብ ሐኪሙን እንዲያማክር ይበረታታል!

6) ለኬሞቴራፒ ህክምና ምን አይነት ቅድመ ዝግጅት መደረግ አለበት?!

ቅድመ ዝግጅቱ እንደየ ኬሚካል ህክምና ባህሪ እና የልኬት መጠን ሲለያዩ ህክምናውም የሚሰጥበት መንገድ ላይ ይመረኮዛል።

መደረግ ያለበት ቅድመ ዝግጅት፦

ሀ) ጠቅላላ የሰውነት ምርመራ እና ተጨማሪ በሽታዎች አለመኖራቸው ሊታወቅ ይገባል።

ለ) የታካሚውን ሙሉ ጤነኝነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የላብራቶሪ ምርመራዎች መደረግ ይኖርባቸዋል።

ሐ) የጥርስ ህክምና ምርመራ ሊደረግ ይገባል።
ይህም የጥርስ ኢንፌክሽን ካለ በቀላሉ ለማከም ይጠቅማል።

መ) ህክምናው ሳይጀምር በፊት ስለጎንዮሽ ጉዳቶቹ በቂ ምክክር ከካንሰር ስፔሻሊስት ሐኪሞቹ ጋር ሊደረግ ይገባል።

ሠ) የኬሚካል ህክምናው ከመደረጉ በፊት ቤት ውስጥ እና መስሪያ ቤት ላለ ስራ አስፈላጊውን የትብብር ዕርዳታ መስጠት የሚችል አጋዥ(ተለዋጭ) ሰው ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

ረ) የመጀመሪያው የኬሚካል ህክምና ከመደረጉ በፊት ከጤና ባለሞያዎች ጋር ስለ አመጋገብ እና የኬሞቴራፒ ህክምና በሚደረግበት ወቅት ስለሚደረግ ቅድመ ጥንቃቄ መመካከር ያስፈልጋል።

7) በካንሰር ህክምና ላይ ከሚሰጡት ብዙ የኬሚካል አይነቶች ውስጥ የኬሞቴራፒ አይነቱን ሐኪሙ እንዴት ይመርጣል?

የካንሰር ሐኪሙ የኬሚካል ህክምናው ከመጀመሩ በፊት የኬሞቴራፒ አይነቶቹን መርጦ ይወስናል። ይህም ምርጫ፦ በካንሰሩ አይነት፣ በካንሰሩ ደረጃ ላይ፣ በታካሚው ሙሉ ጤንነት ላይ እና የድሮ ህክምና ላይ ተመርኩዞ የኬሚካል አይነቶቹን ይመርጣል።

8) ኬሞቴራፒ ወይም የኬሚካል ህክሜናው የሚሰጥባቸው መንገዶች ምን ይመስላሉ?

i) በደም ስር የሚሰጥ የኬሚካል ህክምና
ii) በአፍ የሚዋጥ የኬሚካል መድኃኒት
iii) በፍጥነት በደም ስር የሚሰጥ የኬሚካል ህክምና
iv) ቆዳ ላይ የሚቀባ የኬሞቴራፒ ክሬም
v) በሰውነት አካል ውስጥ በቀጥታ ገብቶ የሚሰጥ የኬሚካል ህክምና
vi) በቀጥታ ካንሰሩ ላይ የሚወጋ የኬሚካል መድኃኒት ሊሆኑ ይችላሉ።

9) የኬሚካል ህክምናው በጊዜ ሂደት አሰጣጡ ምን ይመስላል?

የካንሰር ህክምና ጠበብቱ ኬሞቴራፒው ለስንት ጊዜ ያክል መሰጠት እንደሚችል እና በየስንት ግዜውም መሰጠት እንዳለበት ይወስናል። ይህ ውሳኔ በካንሰር በሽታው ባህሪ እና አይነት ላይ ተመርኩዞ ይደረጋል። በብዛት በሀገራችን የሚሰጠው የኬሞቴራፒ ህክምና ዑደት በየ 21 ቀኑ ሲሆን ህክምናውም ቢያንስ ለስድስት ዙር ያክል ይደረጋል።

10) ኬሞቴራፒ የት ይሰጣል?

የኬሚካል ህክምና በማንኛውም የካንሰር ማዕከል ሊሰጥ ይችላል። ማዕከሉም የግዴታ በካንሰር ህክምና ላይ በሰለጠኑ ስፔሻሊስት ሐኪሞች እና የMSC Oncology ነርሶች ሊገለገል ይገባል። ኬሞቴራፒ ካለው የጎንዮሽ ጉዳት አንፃር ኬሞቴራፒውን ማዘጋጃ Chemo Hood or Biosafety Cabinet በማዕከሉ ሊገኝ ይገባል። በማዕከሉም የሚገኙት የጤና ባለሞያዎች ታካሚውን ከመርዳት ባሻገር እራሳቸውንም ከኬሞቴራፒ የጎንዮሽ ጉዳቶች መጠበቅ አለባቸው!

ቸር ይግጠመን!🙏

ዶ/ር ሚካኤል ሻውል ለማ: በካንሰር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር

@HakimEthio

tg-me.com/HakimEthio/26446
Create:
Last Update:

BY Hakim

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280

Share with your friend now:
tg-me.com/HakimEthio/26446

View MORE
Open in Telegram

Hakim Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

China’s stock markets are some of the largest in the world, with total market capitalization reaching RMB 79 trillion (US$12.2 trillion) in 2020. China’s stock markets are seen as a crucial tool for driving economic growth, in particular for financing the country’s rapidly growing high-tech sectors.Although traditionally closed off to overseas investors, China’s financial markets have gradually been loosening restrictions over the past couple of decades. At the same time, reforms have sought to make it easier for Chinese companies to list on onshore stock exchanges, and new programs have been launched in attempts to lure some of China’s most coveted overseas-listed companies back to the country.

To pay the bills, Mr. Durov is issuing investors $1 billion to $1.5 billion of company debt, with the promise of discounted equity if the company eventually goes public, the people briefed on the plans said. He has also announced plans to start selling ads in public Telegram channels as soon as later this year, as well as offering other premium services for businesses and users.

Hakim from us

Telegram Hakim
FROM USA