Telegram Group Search
Ibn Yahya Ahmed
🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 5 ─────────── ▪️ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - 🔻«ዱንያ ውስጥ ካሉ ነገሮች አስደሳቹ አላህን ማወቅ ሲሆን አኺራ ውስጥ ካሉ ነገሮች አስደሳቹ ደግሞ አላህን መመልከት ነው ፤ ጥራት ይገባውና።» 📚 ۞ مجمـوع الفتـاوي【14/163】۞ ─────────── download app from: https://play.google.com/store/apps/…
🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 6
───────────
▪️ዓብዱሮህማን_ኢብኑ_ሐሰን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

🔻«የአንድ እውቀት ፈላጊ ተማሪ ኢኽላስ ምልክቶች መካከል አንዱ ከማያገባው ነገር ዝምታን መምረጡ፣ ለጌታው መዋረዱ እና ለአምልኮው መዋደቁ፣ ፈሪሀ አሏህ መሆኑ፣ ሀቅ በማንም አንደበት ቢሆንም ለመቀበል አለማመንታቱ፣ ለነፍሱ ሲል ትምክህተኛ አለመሆኑ፣ ቅናተኛና ኩራተኛ አለመሆኑ፣ ወደ ዝንባሌው አለማጋደሉ እንዲሁም ለዱንያ ጥቅም አለመቋመጡ ናቸው።»

📚 ۞ الرسائل النجدية【4/406】۞
───────────
download app from: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft
Ibn Yahya Ahmed
🔻ቤት የሚፈርስባችሁ ወንድሞቻችን አሏህ ትእግስቱን ይስጣችሁ! ታገሱ ከትእግስት ውጭ መጥፎ ቃላት ጌታችሁ ላይ አትናገሩ! ከቤታችሁም ከፈጣሪያችሁም እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ! አሏህ ይርዳችሁ @ibnyahya7
🔻ከባድ ጥንቃቄ!
አሏሁ - ተዓላ - ወይም ነብያችን - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - ከመሰከሩላቸው ሰዎች ውጭ እከሌ የጀነት ነው ማለት አይቻልም። ስለዚህ የጀነት ሙሽራ እያሉ ከመናገር እንጠንቀቅ!!

@ibnyahya777
«ግርግር ለሌባ ያመቻል!» እንዲሉ፤ ሰሞኑን አንድ ቪድዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር እያዬሁ ነበር፤ ብዙዎችም በውስጥ እየላኩልኝ ሲጠይቁኝ ነበር።

አውቃለሁ እየተፈጸመብን ያለው ግፍ ስሜታዊ ያደርጋል። ነገር ግን መፍትሄው ሸሪዓውን ያማከለና የሰከነ አካሄድ እንጂ ስሌት የሌለው የስሜት ጉዞ መሆን የለበትም።

ዳዒሾች (አይኤስ አይኤስ) የሚባሉት ቡድኖች ከሙስሊም ጠላቶች በላይ የጎዱት ሙስሉሙን ማኅበረሰብ ነው።
ገና ለገና «ጂ'ሃድ» ስላሉ ብቻ በቁጭት ተነሳስተን መንገዳቸውን መከተል የለብንም።

እነርሱ በመደበኛው ሁኔታ ተከታይ ስለማያገኙ እንደዚህ አይነት የቁጭት አጋጣሚዎችን ተጠቅመው እየሰበኩ ነውና እንዳትሸወዱ።

ነፍስያችንን ከመታገል ጀምሮ፣ ከወንጀል ከመራቅ ጀምሮ ገና ያልጀመርናቸው የነፍስያ ጂሃድ ጉዞዎች አሉና ቅደም ተከተሉን ጠብቀን ሸሪዓውን ባማከለ መልኩ እንጓዝ።
መንግስት እንኳን ይህን አይነት ሰበብ አግኝቶ፤ እንዲሁም የዶክመንተሪ ግብዓት ለማግኘት የሐሰት ዶክመንተሪ ሲሠራ በቀደምት ጊዚያት እናውቀዋለንና ለጠላቶቻችንም በር አንክፈት። መቼም ቢሆን ዓልይን የገደሉ ኸዋሪጆች መንገድ መንገዴ አይደለም።

ብዙዎቻችሁ እንደምትሳደቡ ባውቅም፤ ሐቁን ከመናገር ወደ ኋላ አልልም። ሽንት በሽንት አይጸዳምና! ሰላም ቀናውን መንገድ በተከተለ ሁሉ

||
www.tg-me.com/MuradTadesse
Ibn Yahya Ahmed
🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 6 ─────────── ▪️ዓብዱሮህማን_ኢብኑ_ሐሰን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - 🔻«የአንድ እውቀት ፈላጊ ተማሪ ኢኽላስ ምልክቶች መካከል አንዱ ከማያገባው ነገር ዝምታን መምረጡ፣ ለጌታው መዋረዱ እና ለአምልኮው መዋደቁ፣ ፈሪሀ አሏህ መሆኑ፣ ሀቅ በማንም አንደበት ቢሆንም ለመቀበል አለማመንታቱ፣ ለነፍሱ ሲል ትምክህተኛ አለመሆኑ፣ ቅናተኛና ኩራተኛ አለመሆኑ፣ ወደ ዝንባሌው…
🪀የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 7
───────────
▪️ሱፍያን_ኢብኑ_ዑየይናህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ :-

🔻«አስተዋይ ማለት መልካምና  እና መጥፎን ያወቀ ሰው አይደለም።እነሆ አስተዋይ ማለት መልካምን ባየ ግዜ የተከተለና መጥፎን ባየ ግዜ ደግሞ የራቀው ማለት ነው።»

📚 ۞ حليـة الأوليـاء لأبي نعيـم【8/339】 ۞
───────────
download app from: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.UlemaSpeech.Hudasoft
Forwarded from 🇸🇦 قناة الأنبار السلفية ٩٣٤١؁🇮🇶 (ٱلعيۧثٱويۧ آلآنَِٰہبّہآرٰيِٰ)
‏قال الإمام ابن باز رحمه الله :

لا يترك متابعة المؤذن إلا محروم
، ولمتابعة المؤذن أربع فضائل كبيرة :

١- مغفرة الذنوب .
٢- دخول الجنة .
٣- الفوز بشفاعته صلى الله عليه وسلم .
٤- إستجابة الدعاء بعده .

قال ابن جريج :

السلف كانوا ينصتون للمؤذن إنصاتهم القرآن .

[فتح الباري(2\92)]| .
🔖ዝሙተኛ ናት❗️

💥በትክክለኛ የነቢዩ صلى الله عليه وسلم
ሐዲሥ "ሽቶ ወይም መልካም ሽታ ያለውን ነገር ተቀብታ ወጥታ ሽታዋ ወንዶች ጋ የደረሰ ሴት ዝሙተኛ ናት" ከመባሉ ጋር ሽቶ ተለቅልቀው ከቤታቸው በመውጣት ያለፉበት መንገድና የቆዩበት ቦታ ሁሉ በሽታቸው እንዲታወድ ማድረግ የብዙ ሴቶችን የኢማን ወይም የእውቀት ድክመት በይፋ ከሚያሳዩ ነገሮች መካካል አንዱ ነው።

💥እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ! የሸሪዓን ህግ አክብሪ!

💥ከቤት ውጪ ሽቶም ይሁን የሚቆይና ከራስ አልፎ ሌሎች ጋ የሚደርስ ሽታ ያላቸው ቅባትና ክሬሞችን አትጠቀሚ።

@ ዛዱል-መዓድ
https://www.tg-me.com/ahmedadem
Forwarded from 🇮ዲን መመካከር ነው-الدين النصيحة🇮 (አቡሙዓዊያህ አሕመድ ኢብን ዐሊ)
◾️በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው

#አስሩ_የዙልሒጃ_ቀናት

🔻ዙልሒጃህ ብሎ ማለት የዐረበኛ 12ኛ ወር ሲሆን የዚህ ወር 10ቀናት ልዩ ትሩፋት እንዳላቸው ነቢያችን - ﷺ - ተናግረዋል። እንደዚሁ ቁርአን ላይም እነዚህ ቀናት ተጠቅሰዋል። አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ከፈጠራቸው ፍጡር ውስጥ አንዱን ከሌላኛው አበላልጧል። የረመዷን ወር ከወሮች ሁሉ በላጭ ነው። የረመዷን የመጨረሻዎቹ 10ቀን ለሊቶች ከለሊቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ምክንያቱም ለይለተል ቀድር በውስጧ ስላለ ነው።
°
🔻የዙልሒጃ አስሩ ቀናት ደግሞ ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ለዚህም ነው ሸይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያ - ረሒመሁሏህ - ከረመዷን የመጨረሻዎቹ 10 ቀናቶች የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናቶች እንደሚበልጡና ከዙልሒጃ10 ለሊቶች ደግሞ የረመዷን 10 የመጨረሻ ለሊቶች እንደሚበልጡ ተናግሯል። (መጅሙዓል ፈታዋ 25/287)
°
🔻አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - በተከበረው ቁርኣኑ ላይ እንዲህ ይላል ፦

{ لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ }

[| ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡ ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡ |] (ሐጅ ፥ 28).
°
🔻እነዚህ ቀናት ብሎ ማለት ዐብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንደገለፁት አስሩ የዙልሒጃ ቀናት እንደሆኑና በነሱም ላይ አላህን በጣም ማውሳት እንዳለብን ተናግረዋል።
°
🔻ከዚህም በተረፈ ዐብደሏህ ኢብን ዓባስ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ባስተላለፈው ነቢያችን - ﷺ - ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፦ [ ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም።] በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን! ተብለው ሲጠየቁ ፦ [ አዎ. በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን , ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ] (ቡኻሪ ፥ 969).
°
🔻ኢብኑረጀብ - ረሒመሁላህ - እነዚህ አስር ቀናት ከሌሎቹ ሊበልጡ የቻሉበት ምክንያት ሲናገሩ ፦ |' በጣም ዋና የሚባሉት የዒባዳ አይነት በአንድ ላይ ስለሚሰባሰቡበት ነው እነሱም ሰላት ፣ ፆም ፣ ሰደቃ እና ሐጅ ናቸው ብለዋል። '| (ፈትሑልባሪ ፥ 2/460)
°
🔻ዋና ዋና በዚህ ወር ልንሰራቸው ከሚገቡ ተግባራቶች ውስጥ ፦
1️⃣.ፈርድ ሰላትን ወቅት ጠብቆ መስገድ ይኖርብናል። ሱጁድ በማብዛት ወደ አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - መቃረብ ተገቢ ነው። ነቢዩም - ﷺ - [ ሱጁድ በማብዛት ላይ አደራ ; አንተ እኮ ምንም ሱጁድ አታደርግም በሰጁዱህ ልክ አላህ ዘንድ ማእረግህ ከፍ ቢል እና ወንጅልህም ቢራገፍልህ እንጂ ብለዋል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል). ሱና ሰላቶችንም ማብዛት ይጠበቅብናል። በተለይም 12ቱ "ራቲባ" የሚባሉትን እነሱም ፦ ከሱብሂ በፊት 2ረከዓ ፣ ከዙሁር በፊት 4ረከዓ , በኋላ 2ረከዓ ፣ ከመግሪብ በኋላ 2ረከዓ እና ከዒሻእ በኋላ 2 ረከዓ ናቸው።
°
2️⃣.ፆም መፆምም ተገቢ ነው። አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆንባቸው ቀናቶች የሉም ከነዚህ 10 ቀናቶች የበለጠ ሰለተባለ ፆም ደግሞ ከመልካም ስራ ስለሚገባ መፆም ተገቢ ነው። ኢማሙ ነወዊም አስሩ የዙልሂጃን ቀን መፃም የጠበቀ ሱና ነው ብለዋል።
3️⃣.ሰደቃ በመስጠት ላይም መጠናከር ይኖርብናል።
°
4️⃣.ተክቢር እና ተህሊልልን ማብዛትም ተገቢ ነው። ሰሓባዎችም በነዚህ ቀናት ውስጥ ተክቢርና ተህሊልን ያበዙ ነበር። በአሁን ሰአት ግን በጣም ከተረሳ ሱናዎች ውስጥ አንዱ ነው። ኢማም አል-ቡኻሪም እንዲህ ብለዋል ፦ ||" ኢብኑ ዑመርና አቡሁረይራ ወደገበያ ቦታ በመውጣት በነዚህ ቀናቶች ውስጥ ተክቢር ይሉ ነበር ሰዎችም በነሱ ተክቢራ ማለት ተነሳስተው ተክቢራ ይሉ ነበር። "||. አባባሉም ፦ አሏሁ አክበር , አሏሁ አክበር , ላኢላሀኢለላህ, አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ.
ሌሎችም በትክክለኛ ሐዲስ የተዘገቡ ተክቢራዎችን ማለት ይቻላል።
°
5️⃣.ከአስሩ ቀናት በተለየ መልኩ የ9ኛውን ቀንማለትም የዐረፋን ቀን መፆም ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ -  ስለዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል ፦ [ ያለፈውን አመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ] (ሙስሊም ዘግቦታል). በዚህም ቀን ዱዓን ማብዛት አስፈላጊ ነው።
°
6️⃣.ሌላኛው 10ኛው ቀን ላይ ሚተገበሩ ተግባሮች ናቸው። እነሱም ፦ ዒድ ሰላት መስገድ ፣ ኡድሂያን ማረድ ... ሐጅ ላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ጀመራት ይወረውራሉ ፣ ፀጉራቸውን ይላጫሉ ፣ ሀድይ የያዙ ሰዎች ሀድያቸውን ያርዳሉ ፣ ወደ መካ ተመልሰው ጠዋፈል ኢፋዷ ያደርጋሉ። በአጠቃላይ 10ኛው ቀን አላህ ዘንድ በጣም ትልቅ ነው።
°
🔻ስለዚህ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን በምናገኝበት ጊዜ ተውበት አድርገን ራሳችንን ለኸይር ስራ ዝግጁ አድርገን ከወንጀላችን ታቅበን ሌሎችንም ከዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ይሄን እድል እንዲጠቀሙ መገፋፋት ያስፈልጋል ። እንደዚህ አይነት እድል በሚመጣ ጊዜ ሳናውቀው ስለሚያልፈን መስነፍ አያስፈልግም መጠንከር እና ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል።
°
🔻በመጨረሻም ኡድሂያን ማረድ የፈለገ ሰው ከሰውነቱ ላይ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን እስኪያርድ ድረስ መቁረጥ የለበትም። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ - ኡሙሰለማ ባስተላለፈችው ሀዲስ እንዲህ ስላሉ ፦ [ የዙልሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና , ከእናንተ አንድኛችሁ ኡድሂያን ማረድ ከፈለገ ፀጉሩን እና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ። ] (ሙስሊም ፥ 1977 ላይ ዘግቦታል). አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገን።
___
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ አሕመድ አደም የድምፅ ፋይል የተወሰደ
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ  @ Ibn yahya Ahmed 
📆ዙልቂዕዳህ 28/1438ሂ. # ነሐሴ 15/2009 ላይ የተፃፈ

📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦https://www.tg-me.com/ibnyahya7

የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/Ibn Yahya Ahmed/com.ibnyahya777
📋የዐረፋ ቀንን መፆም
°
🔻ከአቢቀታዳ ተይዞ እንደተወራው ነብዩ - ﷺ - ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ እና እንዲህ አሉ ፦ [ ያለፈውን እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያብሳል ] (ሙስሊም ዘግቦታል)
~~~
@Ibnyahya777
በዘንድሮ ፡ ማክሰኞ ሰኔ 20/2015 ማለት ነው
#ኡድሒያን_የሚመለከቱ_ነጥቦች

♦️ኡድሒያ ማለት በዒድ ሰበብ የዒደል-አድሓ ቀናት ላይ ወደአላህን ለመቃረብ ሲባል ከታወቁ እንስሳዎች የሚከናወን የእርድ ስነ-ሥርአት ነው። ይህም በቁርአን ፣ በሐዲስ እና በሙሥሊሞች ስምምነት የፀደቀ ጉዳይ ነው። ኡድሒያን ማረድ አቅሙ ላለው ሰው ምንም እንኳን ከፊል ዑለማዎች ግዴታ ነው ቢሉም የተሻለው አቋም በጣም የጠነከረ ሱና ነው የሚለው ነው። (መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኑ ባዝ ፥ 18/36. ይመልከቱ).

♦️ኡድሒያ ላይ የሚታረዱ እንስሳዎች 3 አይነት ናቸው። እነርሱም ፦
◼️1.ግመል
◼️2.ከብት
◼️3.በግ እና ፍየል ናቸው።
ኡድሒያ የሚታረዱ እንስሳዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች አሉ። እነርሱም ፦
°
1️⃣.በሸሪዓው የተቀመጠላቸውን የእድሜ ገደብ መድረስ አለባቸው። እሱም ለግመል 5አመት ለከብት ሀለት አመት ለፍየል አንድ አመት እና ለበግ 6ወር ናቸው።
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ሙሲናህን እንጂ አትረዱ. በናንተ ላይ ከተቸገራችሁ በስተቀር ፤ በዚህን ጊዜ ከበግ ጀዝዓን ማረድ ትችላላሁ። ] (ሙስሊም ዘግቦታል)
ሙሲናህ ማለት በሸሪዓው የተጠቀሰላቸውን እድሜ የደረሱ እንስሳዎች ማለት ነው። ጀዝዓ ማለት ደግሞ ከበግ 6ወር የሞላው ማለት ነው።
°
2️⃣.ከጉድለት የፀዱ መሆን አለባቸው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ከኡድሒያ አያብቃቃም ፡ የአንድ አይኗ መጥፋት ግልፅ የወጣ የሆነች አንድ አይናማ , አንካሳነቷ ግልፅ የወጣ የሆነች አንካሳ , ህመምነቷ ግልፅ የወጣ የሆነች ህመምተኛ , (አጥንት ውስጥ የሚገኝ) መቅኔ የሌላት ከሲታ የሆነች። ]. (ነሳኢይ ዘግቦታል / አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)
°
♦️አንድ እንስሳ ለባለቤቱ እና ለቤተሰቦቹ ያብቃቀዋል። ከአቢአዩብ አልአንሷሪ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ፦ [ አንድ ሰው በነብዩ - ﷺ - ዘመን ለራሱ እና ለቤተሰቡ በአንዲት ፍየል ወይም በግ ኡድሒያ ያደርግ ነበር ፤  ራሳቸውም በልተው ሰዎችንም ይመግቡ ነበር። ] ( ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል / አልባኒም ሶሒሕ ብለውታል). ግመል ወይም ከብት ከሆነ ደግሞ ለ7ሰው ተጋርቶ ማረድ ይቻላል። ጃቢር - ረዲየሏሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላል ፦ [ የሑደይብያ ዓመት ላይ ከረሱል - ﷺ - ጋር አንድ ግመልን ለሰባት (ሰዎች) ፣ አንድ በሬን ለሰባት (ሰዎች) አረደን። ] (ሙስሊም ዘግቦታል)
°
♦️በሚታረድም ሰአት ደም መፍሰስ እና የአላህ ስም መወሳት ይኖርበታል። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ደም ያፈሰሰ እና የአላህ ሥም የተወሳበት ከሆነ ብላ ። ] (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል). ባለቤቱ ራሱ ቢያርድም ተመራጭ ነው። ካልቻለ በሚታረድ ሰአት መገኘት ይኖርበታል። በሚያርድም ሰአት "ቢስሚሏህ አሏሁ አክበር አሏሁመ ሀዛ ሚንከ ወለከ አሏሁመ ሀዛ ዓኒ ወዓን አህሊ በይቲ". ይላል። ( መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኒ ዑሰይሚን ፥ 25/55.ይመልከቱ). እርዱን ማሳመር ይኖርበታል። ቢላዋውን ፊትለፊቷ መሳል የበለትም እንደዚሁ ሌሎች እንስሳዎችን እያሳዩ ማረድም የለበትም።
°
♦️መታረድም ያለበት ከዒድ ሶላት በኋላ ነው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ከሶላት በፊት ያረደ ሰው ለራሱ እንዳረደ ነው (የሚቆጠረው) ፤ ከሶላት በኋላ ያረደ ሰው እርዱ ሙሉ ሆኗል የሙስሊሞችንም ሱንና አግኝቷል። ] ( ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል). ከዒድ በኋላ እስከ ሶስቱ የተሽሪቅ ቀናቶች ድረስ ማረድ ይቻላል።(መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኒ ዑሰይሚን ፥ 25/167.ይመልከቱ).
°
♦️ከታረደ በኋላ ስጋውን ለሚስኪኖች መስጠትም ተገቢ ነው። ለሚስኪኖች የሚሰጠውም ከበሰለው ስጋ ሳይሆን ከጥሬ ስጋ መሆን አለበት።(መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኑ ዑሰይሚን ፥ 25/132. ይመልከቱ). ለገፋፊው የሰራበትንም ዋጋ ከኡድሒያው መስጠቱ አይበቃም ፤ በስጦታ መልክ መስጠት ግን ይቻላል። (መጅሙዓል ፈታዋ ሊብኒ ዑሰይሚን ፥ 25/110. ይመልከቱ). የኡድሒያ ቆዳ መሸጥም እንደሚከለከል የሚያመላክት (ሶሒሑል ጃሚዕ ፥ 61118) ላይ የተዘገበ ሐዲስ አለ። አላህ ኡድሒያችንን ይቀበለን።
__________
አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ  @Ibn yahya ahmed
📆ዙልሒጃህ 9/1439ሂ. # ነሐሴ 14/2010.

📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦https://www.tg-me.com/ibnyahya7

የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/Ibn Yahya Ahmed/com.ibnyahya777
ከወንድሜ Abdu Musema.

🪀ከሰው ገለል ሲባል ስንት የሚፈፀም ጥፋት አለ?!
~
🔻 ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፦
لَأَعْلَمَنَّ أَقْوَامًا مِنْ أُمَّتِي، يَأْتُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِحَسَنَاتٍ أَمْثَالِ جِبَالِ تِهَامَةَ، بِيضًا، فَيَجْعَلُهَا اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ هَبَاءً مَنْثُورًا
"የቂያማ ቀን እንደ ቲሃማ ተራሮች የነጡ በጎ ስራዎችን ይዘው ነገር ግን አላህ የተበተነ ትቢያ የሚያደርግባቸው ሰዎችን በእርግጥም አውቃለሁ።"

🔻በዚህን ጊዜ ሠውባን ረዲየላሁ ዐንሁ፡
“የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ምን አይነት ሰዎች እንደሆኑ ይንገሩን። ሳናውቀው ከነሱ እንዳንሆን ሁኔታቸውን ይግለጡልን” በማለት ጠየቁ። ነብዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦
أَمَا إِنَّهُمْ إِخْوَانُكُمْ وَمِنْ جِلْدَتِكُمْ، وَيَأْخُذُونَ مِنَ اللَّيْلِ كَمَا تَأْخُذُونَ، وَلَكِنَّهُمْ أَقْوَامٌ إِذَا خَلَوْا بِمَحَارِمِ اللَّهِ انْتَهَكُوهَا
"እነሱማ የናንተው ወንድሞች የናንተው አይነቶች ናቸው። በሌሊት ዒባዳዎችን እንደምትፈፅሙት ይፈፅማሉ። ነገር ግን ከሰው ሲገለሉ ጊዜ የአላህን ክልከላዎች የሚዳፈሩ ናቸው።" [አሶሒሐህ: 505]

@ibnyahya777
Forwarded from Ibn Yahya Ahmed (Ahmedel Hadi)
▪️ተጠንቀቅ/ቂ

🔻ረሱል - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - እንዲህ ይላሉ ፦ [ አንድ ወንድ የሌላውን ወንድ ሀፍረተ-ገላ አይመልከት ፤ ሴትም የሌላዋን ሴት ሀፍረተ-ገላ አትመልከት። ] (ሙስሊም ዘግቦታል)

www.tg-me.com/Ibn Yahya Ahmed/com.ibnyahya777
Forwarded from Ibn Yahya Ahmed (Ahmedel Hadi)
▪️የልብ ድርቀት

🔻´´ከመከራዎች ሁሉ ትልቁና ከባዱ የልብ ድርቀት ነው።´´ (ሑዘይፋህ ኢብኒ ቀታዳህ / አስሲየር ፥ 9/284). አሏህ ከልብ ድርቀት ይጠብቀን

www.tg-me.com/Ibn Yahya Ahmed/com.ibnyahya777
"إذا رزق الزوج زوجة صالحة فليفرح بها وليعض عليها بالنواجذ"

#الشيخ رسلان حفظه الله🍂
Forwarded from Ibn Yahya Ahmed (Ahmedel Hadi)
" የተፈታች ሴት በፍፁም የውድቀት ምልክት አይደለችም። አሏህን ከፈራች ከፍቺውም ቡኃላ አሏህ ከችሮታው ያብቃቃታል። የተሻለ የህይወት መስመር ያበጅላታል። "
✍️ዐብዱረዛቅ አልሐበሺይ
Forwarded from Ibn Yahya Ahmed (Ahmedel Hadi)
ዘካተል ፊጥር.pdf
3.3 MB
▪️ዘካተል ፊጥር.Pdf

🔻ከሸይኽ ኢብኑዑሰይሚን "መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን" ኪታብ እና ከሸይኽ ኢልያስ አሕመድ "ዘካተልፊጥር" ከሚለው ሙሐደራ የተወሰደ.
Ibn Yahya Ahmed (ረመዷን 27/1441ሂ.)
___
https://www.tg-me.com/Ibn Yahya Ahmed/com.ibnyahya777
ሸዋል ተብሎ ዒድ የለውም። ሁሉም ብሄር ትክክለኛውን እስልምና ሊከተል ይገባዋል እንጂ ባህሌ ልምዴ እያለ ከአሏህና መልእክተኛው ﷺ ትእዛዝ ውጭ ሊወጣ አይገባውም።
@ibnyahya7
በረመዷንም ወደሰላት ኑ! ወደስኬት ኑ! ነው ጥሪው ከረመዷን በኋላም ጥሪው ያው ነው መላሹ ግን ተለያይቷል። ጥቂቱ ጥሪውን መልሶ ወደመስጂድ ሲሄድ ብዙሃኑ ግን አሻፈረኝ ብሏል። ለምን?
@ibnyahya777
2024/04/25 12:54:39
Back to Top
HTML Embed Code: