Telegram Group & Telegram Channel
#ወንድ_እና_ምላስ

አሁን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው። ቴክኖሎጂ ማህበራዊ ሚዲያን በአስደንጋጭ ፍጥነት አሳድጎታል። ወንድ ልጅም ሰፈርሽ ተመላልሶ፣ ስትወጪ ስትገቢ ተከታትሎ፣ የሰፈር ልጆችን እስቲ አስተዋውቁኝ ብሎ፣ ወንድምሽን ተደብቆ፣ ከአባትሽ ሸሽቶ፣ አንቺን ባገኘው አጋጣሚ እየሸኘ፣ በእግሩ ተመላልሶ ከመጥበስ ነገርን ሁሉ በምላሱ ወደ መጨረስ ተሸጋግሯል።

አሁን ጅንጀናውም፣ ቃል መግባቱም፣ ልብ መጥባቱም በማህበራዊ ሚዲያ ሆኗል። ከልቡ የወደደሽ እና በምላሱ አጥቦ ሊበላሽ የመጣውን መለያ መስመሩ ደብዝዟል። ወንዶቹ ስሜትን ተቆጣጥሮ መዋሸትን ተክነውበታል። ሀይ ብሎሽ ጀምሮ ባይ ብሎ እስኪሰናበትሽ የሆነ ማደንዘዣ የወጋሽ ይመስል ነገሮችን ሁሉ ሳታገናዝቢ እንደ በግ እየነዳ ያስኬድሻል .... በምላሱ

እራሱን ሲያስተዋውቅሽ ለነገሮች ትኩረት የሚሰጥ፣ ስሜታዊ የሆነ፣ ትንንሽ ነገሮች የሚጎዱት፣ ሰዎችን መርዳት ስራው እንደሆነ፣ አይደለም ለሰው ልጅ ለእንስሳት እንደሚራራ፣ መንገድ ላይ የታመመ ውሻ ካየ ሁሉንም ነገር ትቶ እሱን እንደሚያስታምም፣ ገንዘብ ለጠየቀው ብድር ሳይሆን ስጦታ እንደሚሰጥ፣ ሰዎች አዝነው ሲያይ እንባው እንደሚቀድመው ....

እንዲህ እንዲህ እያወራ የምትይውን ሁሉ የሚያደምጥ እየመሰለ፣ ምነው ዝም አልክ ስትይው የነገርሽኝ ገርሞኝ እያሰብኩት የሚልሽ (እሱ እንደ ፌንጣ ከአንዳችሁ ወደ አንዳችሁ እየዘለለ በአንዴ አራታችሁንም እያወራ ነው)፣ የምትይውን ሁሉ እያደናነቀ (ቴሌግራም ላይ የእጅ ፅሁፍሽ እንዴት እንደሚያምር ሲነግርሽ ትገለፍጫለሽ)፣ አንቺን የመሰለች የተረጋጋች እና የሰከነች ሴት ፌስቡክ ላይ መገኘቷ ሲልሽ ልብሽ ጆሮሽ ስር መምታት ይጀምራል

ማታ በውድቅት ለሊት ልቡን ስለሰበረችው እና ከዛ በኋላ ሴት እንዳያምን ስላደረገችው ሴት ታሪክ ሲዘበዝብልሽ .... ከእንባ ጋር እየታገልሽ ሁሉም ሴት እኮ እንደሷ አይደለም እያልሽ እራስሽን ለእርድ ታመቻቻለሽ።

ይሄ ሁሉ መጓዝጎዝ በአካል አግኝቶሽ፣ አልጋ ላይ አስተኝቶ እንጧዬሽን እስኪበላት ነው። ከዛ በኋላ ሙቀቱ ይጠፋና በረዶ ይሆናል፤ ዝም አትበይኝ አውሪኝ የሚለው ይቀርና አትጨቅጭቂኝ ይከተላል፤ ንገሪኝ ይቀርና አትንገሪኝ መስማት አልፈልግም ይመጣል፤ መጀመሪያ በስሜት ቀጥሎ በአካል ይርቅሻል።

በየቀኑ የሚደውልልሽ እሱን ብቻ ማሰብ እስክትጀምሪ ነው፤ ጠዋት ደህና አደርሽ ማታ ደህና እደሪ የሚልሽ ልምድ እስኪሆንብሽ ነው፤ ጓደኞችሽን አስተዋውቂኝ የሚልሽ መረቡ ውስጥ እንድትገቢ ነው፤ ልደትሽን ንገሪኝ እና ሽቶ ልግዛልሽ የሚልሽ ጠረንሽን አንዴ እስኪምገው ነው

የወደደሽ መስሎሽ ስትወጅው .... ተገናኝተን ለምን አንጫወትም ይለሻል። ከግርግሩ አንድ ክፍል ይዘን ብናርፍ ጥሩ ነው ይልሻል። ከዛ በኋላ አንቺም፣ አይምሮሽም ህይወትሽም እረፍት ያጣል።

ያገኘሽው ከደመና ነበር አሁን እንደጉም ይበናል። ስትፈልጊው አይገኝም። ስትደውይለት አያነሳም። አርግዣለሁ ብለሽ ብትፅፊለት "ከማን" ይልሻል። አንቺን ጨርሶ ወደ ምትቀጥለው ሄዷል።

ተረኛዋን ልቧን እያጠበው ነው .... ወስዶ እስኪያሰጣት ሙሉ ትኩረቱ እሷ ብቻ ነች።

ይሄ ሰው ችግሩ ጎድቶሽ መሄዱ አይደለም። ምላሱ ከዚህ በኋላ ሌላ ወንድ እንዳታምኚ ማድረጉ ነው። ሊባሉ የሚችሉትን ነገሮች ሁሉ ጥግ ድረስ ብሎሻል። ነገ የትኛውም ወንድ ምንም ቢልሽ ዛሬ ይሄኛው ከነገረሽ የተሻለ አሳማኝ አይሆንልሽም። በራስ መተማመንሽን አጥፍቶታል። ሁለነገርሽን አስረሽ የምትቀመጪ ፈሪ ያደርግሻል።

እድሜ ለእሱ የእውነት ያፈቀሩሽን ሁሉ ትገፊያለሽ። የእውነት ከሚወዱሽ ትሸሻለሽ። ሁሉም ወንድ የሚፈልገኝ እንጧዬን በልቶ ሊሄድ ነው ትያለሽ።

ህመሙን የበለጠ የማይሽር የሚያደርገው ደግሞ ይህ ሰው በማህበረሰቡ አይን የተሻለ ቦታ ላይ ያለ ከሆነ ነው። ለምሳሌ በትምህርት ጥሩ ደረጃ ያለው፣ የተከበረ ስራ የሚሰራ፣ በሀይማኖት ተሳትፎ ከፊት የተሰለፈ፣ ባለትዳር፣ የልጆች አባት ....

እንደዚህ በእግር በፈረስ ብሎ፣ ምድር ከሰማይ ቧጦ አግኝቶሽ ከበላሽ በኋላ ዞር ይላል። ድንገት ነገሩን ሰው አውቆት ወይም በሆነ መልኩ አብሯችሁ ያያችሁ ሰው ፥ ምነው ከዚህች ልጅ ጋር ተጣላችሁ እንዴ ሲለው .... ምን ሴት ልጅ እኮ ሰው አታፈቅርም። እሷ የምታፈቅረው ብርህን እና ቁመናህን ነው ይላል። አስቢው አንድ የሆነ ጭልፋ እግር፣ መጋፊያ ፊት እንዲህ ሲመፃደቅብሽ? ክብርሽን በአደባባይ ጭቃ ላይ ጥሎት "ወንድ ነኝ በክብሬ ሲመጡብኝ አልወድም" ይልሻል። አንቺን ክብረቢስ አድርጎሽ ሲሄድ መሸፈኛው የሌለው፣ ኖሮት የማያውቀው እና ወደፊትም በምንም ሊኖረው የማይችለው "ክብሩ" ነው።

ልጃገረድ ሆንሽ ባለትዳር፣ የቤት እመቤት ሆንሽ ተማሪ፣ ሰራተኛ ሆንሽ አሰሪ ... እነዚህ ጭልፊቶች መረባቸውን መዘርጋት የሚጀምሩት ፖስት ያደረግሽው ፎቶሽ ስር "ደስ ትያለሽ" ሲሉሽ ገና አልያም ስቶሪ ያደረግሽው ፎቶ ላይ "በጣም ቆንጆ" ነሽ ሲሉሽ ነው። አመሰግናለሁ የሚለው መልስሽ ፥ "የቁንጅናሽ ሚስጥሩ ግን ምንድነው" ለሚለው ማማለያቸው በር ይከፍታል። ከዛ ..... ትበያለሽ።

{ መፍትሄው }

ሁሌም ቀልብሽን እመኝው። ቃሉን እና ተግባሩን ፈትሽው። ምላሱን እና ማንነቱን አስተያይው። ለነገሮች ሁሌም ድንበር አበጂ። የሆነ ጥግ ስር ተደብቆ የሚጠብቅሽ አጥማጅሽ እንጂ ወዳጅሽ አይደለም።

ከምንም በላይ አትፍሪ ምንም አላደርግሽም፤ ብቻችንን እንጫወት ብዬ ነው የሚልሽን ሰው ተጠንቀቂው። ጨዋታ ደንቡም ውበቱም ህዝብ በተሰበሰበበት ስታዲየም ሲሆን ነው።

እዚህ ሰፈር ወንድ በይው ሴት ፥ ከእርግቦቹ ጭልፊቶቹ በብዙ እጥፍ የበዙ ናቸው። በተለይ አብረው ከሚበሩት እራሳችሁን ጠብቁ ‼️

                    © Abby Junior

◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             www.tg-me.com/us/ISLAMIC SCHOOL/com.Islam_and_Science
💐<<<<<<>>>>>>⭐️<<<<<<>>>>>>💐
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group

tg-me.com/Islam_and_Science/6315
Create:
Last Update:

BY ISLAMIC SCHOOL

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/Islam_and_Science/6315

View MORE
Open in Telegram

ISLAMIC SCHOOL Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Start with a fresh view of investing strategy. The combination of risks and fads this quarter looks to be topping. That means the future is ready to move in.Likely, there will not be a wholesale shift. Company actions will aim to benefit from economic growth, inflationary pressures and a return of market-determined interest rates. In turn, all of that should drive the stock market and investment returns higher.

Telegram has exploded as a hub for cybercriminals looking to buy, sell and share stolen data and hacking tools, new research shows, as the messaging app emerges as an alternative to the dark web.An investigation by cyber intelligence group Cyberint, together with the Financial Times, found a ballooning network of hackers sharing data leaks on the popular messaging platform, sometimes in channels with tens of thousands of subscribers, lured by its ease of use and light-touch moderation.ISLAMIC SCHOOL from us

Telegram ISLAMIC SCHOOL
FROM USA