በቅርቡ መክፈል ይጀምራል ተብሎ በብዙዎች ዘንድ እየተጠበቀ ያለውና Bitcoin የተባለውን መገበያያ ይገዳደራል የተባለው notcoin የቴሌግራም bot ይህ ነው።

ስንት Coin ሰራችሁ? እውን ይከፍላል ብላችሁ ታስባላችሁ?

ቦቱ አሁን ላይ ታብ በማድረግ ብቻ ለተጠቃሚዎች coin እያጠራቀመ ይገኛል።

ለመጠቀም 👇

https://www.tg-me.com/notcoin_bot?start=r_573809_33060966

ከዚያም Start ማለትና የወርቅ ሳንቲሟን ታፕ ታፕ በማድረግ coin ማጠራቀም ይቻላል።
ምንም እንኳ ብዙዎች በቅርቡ እንደ ቢትኮይን መገበያያ ይሆናል ቢሉም በዚያው ልክ ደግሞ ተቃራኒውን የሚያነሱ አልጠፉም። በተመሳሳይ ደግሞ ለማንኛውም በሚል ቦቱን አስጀምረው ከ1,000,000 በላይ coin ያጠራቀሙም ብቅ እያሉ ነው። ሩሲያውያን የቦቱ ባለቤቶችም በቅርቡ ጠብቁን ብለዋል።

በቅርቡ እናያለን
በኢትዮጵያ ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ ምክንያቱ ‹‹ከፍተኛ የሙቀት መጠን ነዉ›› ሲል  የዓለም ባንክ ገለጸ🤔

የዓለም ባንክ አደረግኩት ባለዉ ጥናት በኢትዮጵያ ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ ምክንያቱ ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር ነዉ ብሏል፡፡

ከፈረንጆቹ 2003-2019 በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የወሰዱ ወደ 2.5 ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎችን ዳታ ሰብስቦ ያገኘዉ ዉጤት መሆኑን ነዉ ይፋ ያደረገዉ፡፡

በትምህርት ዓመቱ ለከፍተኛ ሙቀት የተዳረጉ በተለይ ደግሞ በፈተና ወቅት ከባድ ሙቀት የሚያገኛቸዉ ተማሪዎች ፤ቀዝቃዛ አየር ባለባቸዉ ስፍራዎች ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር ሲወዳደር ዉጤታቸዉ በእጅጉ ቀንሶ ተገኝቷል ነዉ ያለዉ፡፡

እንደዚህ ዓይነት ተጽዕኖ በተለይ በሰብ-ሰሃራ አፍሪካ አገራት ላይ የበረታ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለዉጡን ለመቋቋም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች በስፋት አለመኖራቸዉ ሁኔታዉን እንደሚያባብሰዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የጥናቱ መሰረታዊ ግኝት የሆነዉ በትምህርት ዘመኑ ከፍተኛ ሙቀት የሚስተናገድባቸዉ ቀናት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸዉ እንዲቀሩ የሚያደርግ መሆኑን ነዉ፡፡

ይህም በኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎች ላይ ወደ 2.28 በመቶ ዝቅ ያለ ዉጤት እንዲመዘገብ እንደሚያደርግ ነዉ፡፡

በጥናቱ ይፋ እንደሆነዉ ግልጽ የሆነ ምክንያት ባይቀመጥለትም ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በሙቀት መጨመሩ ምክንያት የፈተና ዉጤታቸዉ ዝቅ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከወንዶች ጋር ሲነጻጸሩም ሴቶች በተሻለ መልኩ በትምህርት ገበታቸዉ ላይ የሚገኙ እና ለትምህርታቸዉም ከፍተኛ ቦታ ያላቸዉ ሆነዉ ተገኝተዋል፡፡

አሁን ላይ በተለያዩ የአለማችን አገራት ለተማሪዎች ዉጤት መቀነስ የሙቀት መጨመር ምክንያት መሆኑን ማስረጃ አለን ሲሉ በዓለም ባንክ የሪሰርቸሮች ግሩፕ ዋና ተመራማሪ ፓትሪክ ቤህረር ተናግረዋል፡፡

ፓትሪክ ጨምረዉም ከፍተኛ ሙቀት ከተማሪዎቹ በተጨማሪ በመምህራን የስራ እንቅስቃሴ ላይም የራሱ ተጽዕኖ ይኖረዋል ነዉ ያሉት፡፡

ፖሊሲ አዉጪዎች ይህንን ጉዳይ በደንብ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ያሉት ተመራማሪዉ ፤በመማሪያ ክፍሎች ዉስጥ ያለዉን የሙቀት መጠን በማስተካከል ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ስፍራን መፍጠር አለባቸዉ ብለዋል፡፡

የተሻለዉ አማራጭ እንደየአከባቢዉ የሚለያይ ቢሆንም ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሲሉ የሚጨምሩት ተመራማሪዉ ፤ይህም ተማሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ያልተጋለጡ አከባቢዎች ላይ እጅግ በተሻለ ሁኔታ መማር እንደሚችሉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በ2022 ዘ ጋርዲያን ይዞት በወጣዉ አንድ ጽሁፍ ከፍተኛ የሙቀት መጨመር በጥራት እንዳናስብ በማድረግ ፣ የማሰላሰል እና የማመዛዘን ችሎታችን ላይ ተጽዕኖ ስለሚኖረዉ ስህተት የመስራት ዕድላችንን ከፍ ያደርገዋል ሲል አስታዉቆ ነበር፡፡

@NATIONALEXAMSRESULT
አዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ዛሬ ማለትም ቅዳሜ ከምሽቱ2:30 ጀምሮ በtiktok አካውንቷ ብቅ ብላ ስለ ኦቲዝም ምንነት  ትተነትናለች። በፕሮግራሙ ዶ/ር ስመኝ ተስፋዬ ስለ ኦቲዝም ምንነት ያዘጋጀችውን ካጋራችን በኋላ የውይይት ጊዜ ይኖረናል።

ዶ/ር ስመኝ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ መምህርት ስትሆን፣ በማህበራዊ ገጿም ጤና ነክ ጉዳዮችን ለማህበረሰቡ በመልቀቅ ከሚመጡ ችግሮች ቀድመው ይጠነቀቁ ዘንድ ማህበራዊ ግዴታዋንም እየተወጣች ያለች እህታችን ናት። በዚህም በኦቲዝም ዙሪያ ትኩረት አድርጋ ለመስራት የምትሻ በመሆኗ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከኦቲዝም ጋር በተያያዘ ተሳትፎ ታደርጋለች።

ዛሬ ምሽት የአዲስ ዓለም የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት ታድማ ስለ ኦቲዝም  ከቃረመችው ብሎም ለእናንተ የእውቀት ምንጭ የሚሆን መረጃ ይዛ ስለምትቀርብ በፕሮግራሙ በመታደም ብዙ ታተርፋላችሁ።

ወንድምና እህቶቼ ምናልባት እርስዎ በማጋራትዎት አንድ ሰው ሊጠቅሙ ይችላሉና ሳይሰስቱ የሚመለከታቸው ሰዎች ላይ ይደርስ ዘንድ ያጋሩ

ፕሮግራም ዛሬ ቅዳሜ ምሽት 2:30

ፕሮግራሙ የሚተላለፍባት ገጽ
👉http://tiktok.com/@belayzgetnet
👉http://tiktok.com/@simegn.tenachin
የ8ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን...

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ሰኔ 4 - 5/2016 እንዲሰጥ ተወስኗል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
ዒድ ሙባረክ !

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445 ዓ/ሂ የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።
በዓሉ የሰላም፣የመተሳሰብ እና የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

ዒድ ሙባረክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የፃፈው ደብዳቤ ፡


ጉዳዩ፦ ያለአግባብ ገንዘብ ከባንክ ወጭ ያደረጉ ተማሪዎችን ይመለከታል፤

እንደሚታወቀው ባንካችን መጋቢት 06/2016ዓ.ም የሲስተም ማዘመን ስራ እየተሰራ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ምክንያት ደንበኞች ያለአግባብ ገንዘብ ሳይኖራቸው ከሂሳባቸው ወጭ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ባንካችን ከአ/ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር በተሰራው የማስመለስ ስራ አብዛኛው ደንበኞች ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ መመለስ ችለዋል፡፡ ነገር ግን ጥቂት የሚባሉ ደንበኞች ዕዳቸውን ከፍለው በሚፈለገው ፍጥነት ሊመልሱ አልቻሉም፡፤

በመሆኑም ዩኒቨርስቲው ይህንን የሀገር ሃብት ለማስመለስ እስካሁን ድረስ ለሠራው ሥራ ምስጋናችንን እያቀረብን፣ የቀረውን ገንዘብ ማስመለስ ይቻል ዘንድ ከዚህ ደብዳቤ ጋር ባያያዝነው ሠንጠረዥ ላይ በተመለከተው ዝርዝር መሠረት ልክ እንደዚህ ቀደሙ በተቋሙ ለሚገኙ ተማሪዎች ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ #በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተመላሽ እንዲደረግ ልዩ የሆነ መመሪያ እንዲሰጣቸው በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

[የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ]

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ በማሰባሰብ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በኩል አረጋግጠው ባሳለፍነው ሳምንት ለትምህርት ሚኒስቴር መላካቸውን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
በመጪው ሰኔ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የአገልግሎት 500 ብር የመክፈል እና ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
ተማሪ መመገብ ያልቻሉ ዩኒቨርስቲዎች እየበዙ ነው🤔

ዲላ ዩኒቨርስቲም የምግብ በጀት እጥረት እንደገጠመው ገልቷል፡፡

ቀደም ሲል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተመሳሳይ እጣፈንታ እንደገጠመው መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አብዛሃኛዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለመመገብ ችግር እንደገጠማቸው በዚህ ዘገባችን ስር ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡

ለማሳያነትም ድላ፣ ሀዋሳ እና አምቦ ዩኒቨርስቲ በበጀት እጥረትና በምግብ ግብኣት ችግር ተማሪዎቻቸውን መመገብ እንዳልቻሉ ከተሰጡት አስተያየቶች መረዳት ችለናል፡፡

ዲላ ዩኒቨርስቲው በለጠፈው ማስታወቂያ እንደ ሀገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረትና የምግብ ዋጋ መጨመር ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት አስቆጥሯል ብሏል፡፡

ተማሪዎቼ ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ አትክልት እንዲመገቡ እያደረኩ ነው ብሏል፡፡

በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦ እንዲሟላልን ጠይቂያለሁ ያለው የድላ ዩኒቨርስቲ የአቅርቦት ሁኔታው እስከሚስተካከል በትዕግስት ጠብቁ ሲል አስታውቋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው  ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

© ትምህርት ሚኒስቴር

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
ለጥናትና ምርምርዎ እገዛ ይፈልጋሉ?
    አዎ ከሆነ መልስዎ!
በመንግስትም ሆነ በግል ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ በዲፕሎማ፣ዲግሪ እና በማስተርስ ፕሮግራም ለምትማሩ እና ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ የምርቃት ጊዜያችሁን በጉጉት ለምትጠብቁ ሁሉ ስለ ጥናትና ምርምር በቂ እዉቀትን በመያዝ የመመረቂያ ፅሁፋችሁን ተመራጭ እና ተወዳጅ አድርጋችሁ በመስራት በጥሩ ዉጤት ትመረቁ  ዘንድ እናግዝዎታለን፡

If you need support related to:    
1 Assignment / አሳይመንት
2 Research / ሪሰርች
3 Proposal / ፕሮፖዛል
4 Term Paper /  ተረም ፔፐር
5 Case study/ ኬዝ ስተዲ
6 Article Review
7  Mini research
8  Business plan
9  Environmental impact assessment [EIA]

Any other Questions
Contact us via
@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
በግዜ እጥረት እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ትምህርታችሁ ላይ አፋጣኝ እገዛ የምትፈልጉ ተማሪዎች እና ተመራቂዎች
Research ከtitle መረጣ እስከ ማጠቃለያ (Discussion, conclusion and recommendations) ድረስ እናግዛለን።
ማንኛውንም አይነት አሳይመንት እናግዛለን።
ለDefense - powerpoint ለሚፈልጉም ማዘጋጀት እና possible defense questions እናቀርባለን
ማንኛውንም እገዛ በጥራት እና በፍጥነት
ለእገዛ👉🏾@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 701 ሺሕ 489 ተማሪዎች ይወስዳሉ - የትምህርት ሚኒስቴር

የዘንድሮ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 701 ሺሕ 489 ተማሪዎች እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ዘንድሮ በሚሰጠው ድብልቅ የ12ኛ ክፍል መልቂያያ ፈተና ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን እንደሀገር የአቅም ችግር በመኖሩ ምክንያት ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት አለመቻሉን ተገልጿል።

በመሆኑም የዘንድሮ የፈተና አሰጣጥ በትምህርት ቤቶች አቅም የሚወሰን ይሆናል ነው የተባለው።

የኦንላይን ፈተና ውጤትን በቶሎ በማሳወቅ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፈተናን ለመስጠት፣ ስህተትን በመቀነስ እና በሌሎችም ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።

ከኢንተርኔት እና የመብራት መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ያሉ ስጋቶችን ለመቀነስ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር በመስራትና የመብራት መቆራረጥ እንዳይኖር ጀነሬተሮችን በፈተና መስጫ ተቋማት ማሟላት መቻሉ ተገልጿል።

ተማሪዎች ለኦንላይን ፈተና የመፈተኛ ኮምፒውተር እንዲያመጡ ተገደዋል የሚባለው ወሬ እውነትነት የሌለውና ከትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ውጪ እንደሆነም በመግለጫው ተነስቷል።


© ትምህርት ሚኒስቴር

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር 22 ሺህ የሚደርሱ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን አስታውቀዋል።በተለይም ለተማሪዎች የሚሰጠው የሪሚዲያል ፈተና መጀመሩን በማስታወቅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ፈተናውን የተሳለጠ ለማድረግ ለፈታኝ መምህራን በቂ ሥልጠና እየሰተጠ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ የሚረዳ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።ሚኒስቴሩ በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
2024/06/16 08:47:08
Back to Top
HTML Embed Code: