Sheger Press️️
Photo
#ግመል በመርፌ ቀዳዳ ስትሾልክ አሳየው
በማቴ. 10÷3 እንደተጻፈው አባቱ እልፍዮስ ይባላል፡፡ በሉቃስ 6÷16 ደግሞ ሐዋርያው “ታዴዎስ ልብድዮስ”፣ “የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ” እየተባለም ተብሎ ሲጠራ እናያለን፡፡ ጌታችን ከሐዋርያት አስቀድሞ ይህን ቅዱስ ታዴዎስን እንደ መረጠው መጽሐፈ ስንክሳር ይናገራል፡፡ እርሱም በየአገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ከአይሁድና ከአረማውያን ወገን ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሶ አጥምቋል፡፡ አንድ ቀን ወደ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሦርያ ለስብከተ ወንጌል ሲሔድ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጐልማሳ አምሳል ተገልጦ “ወዳጄ ታዴዎስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ” ብሎ ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስም እንደ አባትነቱ ወደ ሦርያ አብሮት ሔዶ ነበረ፡፡ ከከተማዋ አጠገብ ሲደርሱም አንድ ሽማግሌ በሮችን ጠምደው ሲያርሱ አገኙ፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስም ሽማግሌውን ምግብ ለመናቸው፡፡ “በሮቼን ጠብቁ” ብላዋቸውም ሊያመጡላቸው ወደ ቤታቸው ሔዱ፡፡ ሽማግሌው እስኪመለሱ ቅዱስ ጴጥሮስ ሠላሳ ትልም ካረሰ በኋላ ቅዱስ ታዴዎስ በዚያ የነበረውን የሥንዴ ዘራበት፡፡ የተዘራውም ወዲያዉኑ በቅሎ፣ አድጎ፣ እሸት ኾነ፡፡ ሽማግሌው ምግብ ይዘው ከቤታቸው ሲመለሱም ሐዋርያት ያደረጉትን ተአምር አይተው ደነገጡ፡፡ ከእግራቸው ሥር ወድቀውም “እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን?” አሏቸው፡፡ እነርሱም “እኛ የእግዚአብሔር ባሮች እንጂ አማልክት አይደለንም” አሉ፡፡ ሽማግሌውም ስላደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱበት ቦታ ኹሉ ልከተላችሁን? አሏቸው፡፡ እነርሱም “በሬዎቹን ለጌታቸው መልስና በቤትህ የምንበላውን ታዘጋጅልን ዘንድ ለባለቤትህ ንገራት ወደ ከተማዋ ገብተን እግዚአብሔር እስከሚጠራን ጊዜ ድረስ እንቆያለንና” አሉት፡፡
ሽማግሌውም የሥንዴው እሸት ይዘው፣ በሬዎቻቸውን እየነዱ ወደ ከተማ ሲሔዱ ሰዎች ወቅቱ የእርሻ እንጂ የእሸት ጊዜ ስላልነበረ እየተገረሙ “እሸቱን ከወዴት አገኘኸው?” አሏቸው፡፡ ሽማግሌው ግን መልስ አልሰጧቸውም፡፡ ሐዋርያት እንደዘዟቸው በሬዎቹን ለጌታቸው መልሰው ሚስታቸው ራት እንድታዘጋጅላቸው ነገሯት፡፡ የከተማው መኳንንት ስለ እሸቱ ሲሰሙ “በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ከወዴት እንዳገኘኸው ንገረን” አሏቸው፡፡ ሽማግሌውም ሐዋርያት ያደረጉትን ሁሉና ወደ እርሳቸው ቤት ቢመጡ ሊያገኟቸው እንደሚችሉ ነገሯቸው፡፡ መኳንንቱም ሰይጣን ልቡናቸዉን አነሳስቶታልና ሐዋርያቱን ለመግደል ወሰኑ፡፡ ሌሎች ግን “አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ኹሉ ያደርግላቸዋልና ልንገድላቸው አንችልም፡፡ ይልቅ በከተማው በር አመንዝራ ሴት ርቃኗን ብናስቀምጥ ወደ ከተማችን አይገቡም” አሉ፡፡
እንደተባባሉትም አደረጉ፤ ሐዋርያቱ ግን በሰዎቹ ልብና በሴቲቱ ላይ ያደሩትን ርኩሳን መንፈስ አስወጥተው በማስተማር በሥላሴ ስም አጥምቀው አገልጋዮችን ሾመላቸው፡፡ ያቺንም ሴት ዲያቆናዪት አደርጎ ሾማት፡፡ ብዙ ድንቅና ተአምራትም አደረጉ፡፡ ሕዝቡም በእግዚአብሔር አመኑ፡፡ ከዚህ በኋላ አንድ ሰይጣን ያደረበትና ገንዘብ የሚወድ ጐልማሳ ባለጸጋም ታዴዎስን በበዙ ተፈታተነው እርሱም ጌታችን እንደተናገረ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ስትሾልክ አሳየው፡፡ ያ ባለጸጋም ከቅዱስ ታዴዎስ እግር ስር ወድቆ ይቅርታ ጠየቀ ገንዘቡንም ሁሉ ለድሆች አከፋፈለ፡፡ ተምሮና አምኖም ተጠመቀ፡፡ ቅዱስ ታዴዎስ በየአገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ ቆይቶ ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራ ከደረሰበት በኋላ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሐምሌ 2 ቀን ዐርፏል፡፡ በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ የሚያልፉ ቅዱሳን ገዳማውያንም የሐዋርያትን ፈለግ ተከትለው ዓለምን ንቀዋል፡፡ በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውንም እንደግፍ፡፡
ገዳማዊያኑን በመደገፍ ለነፍሳችን ስንቅን እንያዝ።
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ፈረንሳይ ዩራኒየምን ከኒጀር በኪሎ 0.80$ ብቻ እየገዛች በኪሎ ወደ 200 ዩሮ በመሸጥ ትልቅ ትርፍ ስታገኝ ቆይታለች።
ኒጀር እስካሁን በድህነት ያለች ሃገር ናት ይህ የኒጀር ዩራኒየም 70% የሚሆነውን የፈረንሳይ ኤሌክትሪክ በኒውክሌር ማብላያዋ ሲያመነጭ ቆይቷል ነገር ግን አብዛኛው ኒጄሪያውያን አስተማማኝ ኃይል ሳይኖራቸው በጨለማ ይኖራሉ።
ለብዙ አሥርተ ዓመታት የፈረንሳይ ኩባንያዎች የኒዠርን የዩራኒየም ማዕድን ማውጫዎች ኢፍትሐዊ በሆነ ስምምነቶች ተቆጣጠረው በርካሽ ዋጋ ወደ ሃገራቸው ያግዙት ነበር
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023፣ ጄኔራል ቺያኒ መፈንቅለ መንግስትን መራ ፕሬዝዳንት ባዙምን አስወገደ
እንደነዚህ አይነት ፍትኃዊነት የሌለው የሃብት ብዝበዛ እንዲቆሙ ጠየቀ የፈረንሳይ ወታደሮችን አባረረ ኒጀር የራሷን ሃብት እንድትቆጣጠር አደረገ ይህንን ማድረግ ሲጀምር የምዕራቡ ዓለም ጄኔራል ቺያኒን ጨቋኝ መሪ ነው ብለው ፈረጁት
ፈረንሳይ በበላይነት የኒጀርን ሃብት በርካሽ ስትበዘብ እና ስትጠቀም መሪዎች ዝም ሲሉ መሪዎቹ ችግር የለባቸውም ነገር ግን ይህ ኢፍትሀዊ የሆነ የሃብት ብዝበዛ መቆም አለበት ብለው ለሃገራቸው ሲሟገቱ እንደጨቋኝ ይታያሉ ::
ይህን ነው በአፍሪካውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው
@Sheger_Press

"ሌሊቱን ሙሉ ስንነጋገር አድረን ህንድና ፓኪስታን የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ አሜሪካ አስማምታቸዋለች። ሁለቱንም ሃገሮች አመሰግናለሁ" ዶናልድ ትራምፕ
የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳቅ ዳር በበኩላቸው "አገራችን በተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሳለች። ይህን የተኩስ አቁም ስምምነት በማደራደር ውስጥ “ሦስት ደርዘን አገሮች” ተሳትፈዋል። ከነዚህም መካከል ቱርክ ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ይገኙበታል።" ብለዋል።
በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ስልጣን ላይ እንደወጣው በሰዓታት ውስጥ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን አስቆማለው በሚል ቃል ገብቶ እስካሁን ያልተሳካለት፣ ዶናልድ ትራምፕ የህንድና ፓኪስታንን ክሬዲቱን ብቻውን ለምን መውሰድ ፈለገው? እንግሊዝም ለስምምነቱ ቁልፉን ሚና የተጫወትኩት እኔ ነኝ እያለች ነው።

በምስራቅ ቦረና ዞን ጉሚ ኤልዳሎ ወረዳ 13 የመንግስት ሰራተኞች መታገታቸው ተሰማ፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዳዮ ዳባ እንደተናገሩት ሀሙስ ጠዋት ላይ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የተባሉ ታጣቂዎች ወደወረዳው ገብተው 18 ሰዎችን አግተው ወስደዋል፡፡
ከእነዚህ መካከል 13ቱ የመንግስት ሰራተኞች መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኞቹ ለስራ ጉዳይ ከነገሌ ቦረና የመጡ መሆናቸውን የገለፁት አስተዳዳሪው እገታው የተፈፀመው በመኪና በሚጓዙበት ወቅት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከታገቱት ውስጥ አንድም ባለስልጣን እንደሌለበት ገልፀውም ‹‹የመንግስት ሰራተኞቹ ኑሯቸውን ለማሸነፍ የሚሰሩ እንጂ ከፖለቲካ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ናቸው›› ብለዋል፡፡
አስተዳዳሪው ከዚህ ቀደምም የኦነግ ሰራዊት ታጣቂዎች በወረዳው ውስጥ እገታ እንዲፈፅሙና ገንዘብ እየተቀበሉ እንደሚለቁ አስረድተዋል፡፡ ይህኛውንም እገታ የፈፀሙት እነዚሁ ታጣቂዎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በዚህ እገታ ዙሪያ የኦነግ ሰራዊት እስካሁን የሰጠው ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የሌለ ቢሆንም በተደጋጋሚ በሚፈፀሙ መሰል እገታዎች እጁ እንደሌለበት ሲናገር መቆየቱ ይታወሳል ሲል ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዘግቧል፡፡

ሜክሲኮ ጎግልን ከሰሰች
ሜክሲኮ ጎግልን የራሴ የሆነውን የሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ የአሜሪካ ባሕረ ሰላጤ እያለ በጎግል ካርታ ላይ እየተጠቀመ ነው በማለት ክስ መመስረቷን አስታውቃለች።
የሜክሲኮ ፕሬዚዳንት ክላውዲያ ሺንባውም መንግስታቸው ጎግልን ከዚህ ቀደም ይህን ስያሜ እንዳይጠቀም አስጠንቆ የነበረ ቢሆንም፤ ጎግል ግን ምንም ማስተካከያ ባለማድረጉ ወደ ክስ ሂደቱ ገብተናል ብለዋል።
ፕሬዚዳንቷ አክለውም፥ “እኛ ከአሜሪካ የባሕር ዳርቻዎች አካባቢ ላለው የባሕረ ሰላጤው ክፍል የአሜሪካ ባሕረ ሰላጤ ክፍል መባሉን አንቃወምም ነገር ግን ሙሉ የባሕረ ሰላጤው ክፍል በአሜሪካ መጠራቱን አንቀበለውም” ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጥር 20 በፈረሙት ትዕዛዝ የሜክሲኮ የባሕረ ሰላጤ ክፍል የአሜሪካ ባሕረ ሰላጤ ተብሎ እንዲቀየር የሚል ትዕዛዝ መፈረማቸው የሚታወስ ነው።
ጎግልም የካቲት 11 የባሕረ ሰላጤውን ስያሜ በመቀየር የአሜሪካ ባሕረ ሰላጤ በማለት በካርታው ላይ አስፍሮታል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው።

የኮሪደር ልማቱ ክስ ቀረበበት‼️
አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በከተሞች በሚያካሂደው የኮሪደር ልማት ሳቢያ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የግዳጅ መፈናቀልና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተመለከተ ሪፖርት በጋምቢያ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የሰብዓዊና ሰዎች መብቶች 83ኛ ጉባኤ ላይ ትናንት ማቅረቡን አስታውቋል።
የኮሪደር ልማቱ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ባሳደረው ተጽዕኖ ዙሪያ ጥልቅ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ የኢትዮጵያ መንግሥት ፕሮጀክቱን እንዲያቆም ኮሚሽኑ ጥሪ እንዲያደርግ አምነስቲ ጠይቋል።
አምነስቲ፣ መንግሥት ለኮሪደር ልማቱ ተፈናቃዮች ምትክ መኖሪያ ቤቶችን እንዲሠጥና በቂ ካሳ እንዲከፍል ጭምር ኮሚሽኑ በይፋ እንዲጠይቅም ጥሪ አድርጓል።

"በማንኪያ መመገብ የለብንም በራሳችን ችለን ለመኖር እና ለህዝባችን ምግብ ዋስትና ለመስጠት እንፈልጋለን "
የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
የኤርትራው ፕሬዘዳንት የምዕራቡ አለም የቅኝ ግዛት ሃይሎች በተለይም በቅርቡ በኢብራሂም ትራኦሬን በአሜሪካ ሴኔት ላይ ክስ የመሰረቱት የአሜሪካው ጄኔራል ሚካኤል ላንግሌይ የመንግስትን ማዕድን ሃብት ለመቆጣጠር እና ለመዝረፍ እየበዘበዙ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
ለተራበ ሆድህ ግድ የማይሰጡ የምዕራባውያን ሀያላን ሀገራት በአፍሪካ ነፃነትን ናፋቂ መሪ ሲነሳ አይወዱም ከቻሉ በሴራ ካልቻሉ በጉልበት ለማዉረድ ይነሳሉ ።
ለዛም ነዉ የቡርኪናፋሶውን ወጣት መሪ ልክ እንደ ሳንካራ ለማጥፋት የተነሱት ምክንያቱም አፍሪካ በእነሱ ላይ ጥገኛ ሁና የምግብ ተመፅዋች እንድትሆን ስለሚፈልጉ ።
"በማንኪያ መመገብ የለብንም በራሳችን ችለን ለመኖር እና ለህዝባችን ምግብ ዋስትና ለመስጠት መትጋት ያስፈልጋል ።ይህ የእኛ ኃላፊነት ነው እና እኛ ማድረግ ያለብን አንድ ሀገር ጠንክሮ በመሥራት እና የምግብ ፍጆታን ማሟላት ስላለበት ነው ።"
የምዕራቡ አለም የቅኝ ግዛት ሃይሎች በተለይም አሜሪካና አጋሮቿ ምዕራባዊያኑ በዕዳ ጫና የየራሳቸውን ፍላጎት የጫኑብንን ማንነት ተለቃልቀን በሁለት እግራችን ለመቆም ብቸኛዉ መፍትሄ ከስንዴ ፖለቲካ በመላቀቅ በምግብ ዋስትና እና የኢኮኖሚ ራስን መቻል ያስፈልጋል ።
ዘገባው የአፍሪካ ኢንሳይደር ነዉ ።

የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዜጎቹ ለወሳኝ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ወደኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ አወጣ፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ ባሰራጨው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ከዚህ ቀደም ባወጣው ላይ ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በአዲሱ ማስጠንቀቂያው መሰረት ካናዳዊያን ወደሰሜናዊ ኢትዮጵያ ክፍል ፈፅሞ መሄድ እንደሌለባቸው አሳስቧል፡፡ በአማራ፣ ትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ጦርነት፣ ህዝባዊ አመፅና የማይገመት የፀጥታ ሁኔታ እንዳለ ጠቅሶም ወደእነዚህ አካባቢዎች መሄድ አደገኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የካናዳ መንግስት ጨምሮም በመካከለኛው ኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች ብሎ በጠቀሳቸው በጋምቤላና ሲዳማ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ፣ ምእራብ ሸዋ፣ ምእራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ቀለጋ፣ ቄለም ወለጋና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ በተጨማሪም በሁሉም የኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች ፈፅሞ ዜጎቹ እንዳይሄዱ አሳስቧል፡፡
በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች ለወሳኝ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር መሄድ እንደሌለባቸውም አስጠንቅቋል፡፡

በዓለም ዙሪያ ለእናቶች የተላኩ ደብዳቤዎች
“እኔን ማህፀንሽ ውስጥ ብቻ አልነበረም የተሸከምሽኝ፤ በልብሽ እና በሐሳብሽም ተሸክመሽኛል። አሁንም ደግሞ በጸሎትሽ ተሸከምሽኝ”። - ማሪያ፣ ፊሊፒንስ
"ሁሌ በር ላይ ቆመሽ ትጠብቂኝ ነበር። ወደ ቤት ዘግይቼ ስመጣም እዛው ነሽ - በንዴት ሳይሆን በፍፁም ፈገግታ።” - ግሬስ፣ አየርላንድ
"አንድም ቃል ሳልናገርም የምፈልገውን ሁልጊዜ ታውቂያለሽ፤ ይህ ግን አስማት አይደለም፤ የእናት አዕምሮ ነው” - አሕመድ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ
“ሳቅሽ የልጅነቴ ማጀቢያ ነበር፤ ያንን ሳቅ በየቀኑ እናፍቀዋለሁ። - ኖህ፣ አውስትራሊያ
"ቤት ውስጥ የነበረውን ብቸኛ ምግብ ለኔ ሰጠሺኝና አንቺ እንዳልራበሽ ነገርሽኝ፤ ነገር ግን ያኔ ሆድሽ ባዶ መሆኑን ለመረዳት በጣም ትንሽ ነበርኩ። - ሳሙኤል፣ ኬንያ
“እናቴ፣ አንድ ጊዜ እንኳ ስታርፊ አይቼሽ አላውቅም፤ አሁን ሲገባኝ ያኔ ‘ደኅና ነኝ’ የምትይው ለኔ ስትይ መጠንከር ስለነበረብሽ እንደሆነ ገብቶኛል"። - ሊና፣ ጀርመን
"ሕልምሽን ለኔ ሰጥተሽ ጭንቀትሽን ሁሉ በዝምታ ተሸክመሻል፤ አሁን ላኮራሽ ብቻ ነው የምፈልገው"። - ፉአድ፣ ሳውዲ አረቢያ
“እናቴ መሆንሽን በጣም የምትወጂው ነገር እንደሆነ በአንድ ወቅት ነግረሽኝ ነበር፤ እኔም ልንገርሽ፣ ያንቺ ልጅ መሆን ትልቁ ስጦታዬ ነው።” - ላይላ፣ ሞሮኮ
“ምንም ጠይቀሽኝ አታውቂም፣ ግን ሁሉንም ነገር ሰጠሽኝ፦ ጊዜሽን፣ ወጣትነትሽን፣ ሕልምሽን”። - ናዲያ፣ ግብጽ
“ፍቅር ጫጫታ እና ጋጋታ ነው ብዬ አስቤ ነበር፤ ነገር ግን ፍቅርሽ የተረጋጋ እና በፀጥታ ውስጥ ያለ የእናት ፍቅር ነው” - ማቲዮ፣ ብራዚል
እነዚህ ደብዳቤዎች የእውነት የተኖሩ የእናትነትን የፍቅር ማሳያ ታሪኮች ናቸው።
Via Addis insider

የታዋቂው የአፍሪካ ቀንድ እና የኢትዮጵያ አጥኚ የሆኑት፣ የፕሮፌሰር ክርስቶፈር ክላፋም “የአፍሪካ ቀንድ” መጽሐፍ ተተርጉሞ በገበያ ላይ ዋለ።
መጽሐፉ፣ የአፍሪካ ቀንድ ከሌሎቹ የአህጉሩ አገራት በተለየ ኹኔታ ከዕርስ በዕርስ ጦርነት መላቀቅ ያልቻለበትን የፖለቲካ ታሪክ በአዲስ ኅልዮታዊ ዕይታ የሚያብራራ ሲሆን፣ በተለይም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ረዥም የግጭት እና የወዳጅነት አዙሪት ላይ አተኩሮ ሰፊ ታሪካዊ ማብራሪያዎችን ይዟል። ይኽ “የአፍሪካ ቀንድ-የመንግሥታት ምሥረታ እና ውርዘት” ተሰኝቶ ወደ አማርኛ የተመለሰው መጽሐፍ፣ አሁን የቀንዱ አባላት በተለይም በኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ዙሪያ ያላቸውን አቋም ለመረዳትም ኹነኛ ምሁራዊ ትንታኔዎችን ያቀርባል።
የመጽሐፉ ተርጓሚ፣ የቀድሞ የፍትሕ ጋዜጣ አዘጋጅ እና የዋዜማ ራዲዮ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ኃይለ መስቀል በሸዋምየለህ መሆኑ ተጠቅሷል። መጽሐፉ ስድስት ምዕራፎች ሲኖሩት፣ በ241 ገጽ ተቀንብቦ በ450 ብር ለሽያጭ ቀርቧል። በኹሉም የጃፋር መጸሓፍት ቤቶች ይገኛልም ተብሏል።

በድራማዊው ኤልክላሲኮ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን አሸነፈ‼️
በስፔን ላሊጋ 35ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ባርሴሎና ከሪያል ማድሪድ ያደረጉት ተጠባቂ ጨዋታ በባርሴሎና 4 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡
ኪልያን ምባፔ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች መምራት የጀመረው ማድሪድ ብዙም ሳይቆይ በባርሴሎና ተጨዋቾች የበላይነት ተወስዶበታል፡፡
በጨዋታው ጋርሲያ፣ ላሚን ያማል እንዲሁም ራፊንሃ ያስቆጠራቸው 2 ጎሎች ባርሴሎና 4 ለ 2 እየመራ እረፍት እንዲወጣ አስችሎታል፡፡
ከእረፍት መልስ ኪልያን ምባፔ ግብ አስቆጥሮ ልዩነቱን ቢያጠብም ጨዋታው በባርሴሎና 4 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡
በዚህም ባርሴሎና ላሊጋውን በ7 ነጥብ ልዩነት መምራት የጀመረ ሲሆን ቀጣዩን ጨዋታ ማሸነፍ ሻምፒዮን እንዲሆን ያስችለዋል።

ኤልክላሲኮው በባርሴሎና አሸናፊነት አጠናቋል
ለ260ኛ ጊዜ የተከናወነው እና የዘንድሮውን የላሊጋ አሸናፊን ይጠቁማል የተባለለት ተጠባቂው የኤልክላሲኮ ጨዋታ በካታሎኑ ቡድን ባርሴሎና አሸናፊነት ተጠናቋል።
በስቴዲዮ ሎስ ኮምፓኜስ በተደረገው ጨዋታ ባርሴሎና 4-3 በሆነ ውጤት ነው ጨዋታውን ማሸነፍ ችለዋል ፤ የጎል ፌሽታ በተንፀባረቀበት በዚ ጨዋታ ላይ የማድሪዱ ፈረንሳዊ አጥቂ ኪሊያን ማባፔ 3 ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል።
ውጤቱን ተከትሎ ባርሴሎና ነጥባቸውን 82 በማድረስ መሪነታቸውን ሲያጠናክሩ ሪያል ማድሪድ በ7 ነጥብ ዝቅ ብለው በ75 ነጥብ ባሉበት 2ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።
አስደናቂው የሀንሲ ዲተር ፍሉኩ ባርሴሎና በዚ አመት በተለያዩ ጊዜያቶች ላይ ያደረጉትን 4 የኤል ክላሲኮ ጨዋታ ሙሉ በሙሉ በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ሪያል ማድሪድ ላይ ያላቸውን የበላይነት አሳይተዋል።
ብሉግራናዎቹ ለ28ኛ ጊዜ ላሊጋውን ማሳካታቸውን ለማረጋገጥ 1 ጨዋታ ብቻ ማሸነፍ የሚበቃቸው ይሆናል።