Telegram Group Search
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የ25% ቅናሽ የተደረገባቸውን የቤት ዕቃዎቻችንን ገዝተው ቤትዎን ያድምቁ!

የዘመናዊነት ተምሳሌት!


አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282

👉 Telegram:  https://www.tg-me.com/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
#NEVACOMPUTER

በጣም በተመጣጣኝ ዋጋ ዘመናዊ የሆኑ 2023 እና 2024 ቢዝነስ ላኘቶፓች፣ እጅግ ፈጣን የሆኑ የኤዲቲንግ ላፕቶፓች እንዲሁም ለተማሪዎች ቅናሽ የሆኑ ኢሮፕ ስታዳርድ እና ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች አሉን። ከበቂ መስተንግዶ መረጃ እና ከአንድ አመት ዋስትና ጋር እንጠብቆታለን።

ነቫ ኮምፒዉተር ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ👇
https://www.tg-me.com/nevacomputer

ስልክ፦ 0920153333
አድራሻ - መገናኛ ማራቶን ህንፃ ግራውንድ ፍሎር - NEVA COMPUTER
www.nevacomputer.com
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EU #Visa #ETHIOPIA

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ አስታውቃለች።

የአውሮፓ ህብረት ይህንን አቋሙን እንዲያጤነው ጠይቃለች።

ብራስልስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ምን አለ ?

- የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ያስተላለፈው የእግድ ውሳኔ በህብረቱ አባል አገራት ለመኖር ህጋዊ ፍቃድ የተነፈጋቸው ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በክብር፣ በስርዓት እና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ እንዲመለሱ ለማድረግ ሁለቱ ወገኖች በቅርበት እየሰሩ ባለበት ወቅት ነው።

- ውሳኔው ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስና ከማህበረሰቡ ጋር መልሶ ለማዋሃድ በኢትዮጵያ እና በህብረቱ መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር ያላገናዘበ ነው።

- ውሳኔው ማንነትን ለማረጋጋጥ የሚደረገውን አድካሚ ሂደት ከግምት ውስጥ ማስገባት አልቻለም።

- ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከህብረቱ አባላት አገራት ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን የቅበላ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራዊ እርምጃዎች ላይ እንቅፋት የሚፈጥር ነው።

የአውሮፓ ኅብረት ም/ ቤት ከሰሞኑ በኅብረቱ ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህ ዕገዳ መሠረት ፦

➡️ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም፤

➡️ ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉም፤

➡️ የዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ሀገራት ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ ተላልፏል።

የእገዳ ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግስት በአውሮፓ ያሉ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩትን ዜጎቹን ለመመለስ / ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ በመሆኑ የተላለፈ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

የመረጃ ምንጮች ቢቢሲ/ በቤልጂየም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የአውሮፓ ኮሚሽን ድረገጽ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ ላይት " ጥያቄ ቀረበበት። አዲሱ መተግበሪያው ' ቲክቶክ ላይት ' በፈረንሳይ እና ስፔይን አገልግሎት የጀመረው ቲክቶክ በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ያለውን ግምገማ በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲያቀርብ ዛሬ የአውሮፓ ኮሚሽን ጠየቀ። ከዋናው ቲክቶክ መተግበሪያ አነስ ብሎ የወጣው የቲክቶክ መተገበሪያ ተጠቃሚዎች #ተከፍሏቸው የቪዲዮ ምስሎችን እንዲመለከቱ…
#TikTok #EU

" የቲክቶክን አደጋ በትክክል እናውቃለን " - ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን

' ቲክቶክ ' አውሮፓ ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተሰማ።

ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ' ቶክቶክ ' በመላ ሀገሪቱ እንዲታገድ አልያም ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ ሕግ ማውጣቷ ይታወቃል። ለዚህም የሰጠችው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

አሁን ደግሞ መተግበሪያው የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተነግሯል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ለኮሚሽኑ የ2024 ምርጫ በተደረገ አንድ ክርክር ላይ ' ቲክቶክ ' በአውሮፓ ሀገራት የመታገድ ዕጣፋንታው ዝግ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ይህን ያሉት የአሜሪካ ' ቲክቶክ ' ን የማገድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሷን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ ነው።

ቮን ደር ሌየን ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም በተቋሙ ስልኮች ላይ መተግበሪያው እንዳይሰራ ያደረገ የመጀመሪያ ተቋም መሆኑን አስታውሰዋል።

" የቲክቶክን አደጋ በትክክል ምንእንደሆነ እናውቃለን " ሲሉ አክለዋል።

ምንም እንኳን የአውሮፓ ኮሚሽን አውሮፓ ሀገራት ውስጥ ' ቲክቶክ ' ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ቢሰጥም ልክ እንደ አሜሪካ በፍጥነት ተመሳሳይ መንገድ ይከተል እንደሆነ ለመደምደም ገና ነው ተብሏል።

የአውሮፓ ኮሚሽን በቅርቡ ከዋናው ቲክቶክ አነስ ብሎ የተዘጋጀው ' ቲክቶክ ላይት (ተጠቃሚዎች ተከፍሏቸው ቪድዮ የሚያዩበት) ' በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ጥያቄ ማንሳቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹

የትግራይ ክልል ክለቦች ወደ ዋናው ሊግ ሊመለሱ ነው።

የትግራይ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበሩበት ዋናው ሊግ ከቀጣይ 2017 ዓ/ም የውድድር ዘመን ጀምሮ ተመልሰው እንዲወዳደሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወስኗል።

ፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም አስተላልፎት የነበረውን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ በመሻር የትግራይ ክለቦች ከጦርነቱ በፊት ሲወዳደሩበት ወደነበረው ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ከመንግሥት የቀረበውን አቅጣጫ በመቀበል ውሳኔ አሳልፏል። 

በ2017 ዓ/ም የውድድር ዘመን 19 ቡድኖች ተሳታፊ እንደሚሆኑና 5 ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንደሚወርጉ ተገልጿል።

በ2018 ዓ/ም የውድድር ዘመን ሊጉ ከዚህ ቀደም ወደነበረበት 16 ክለቦች ተሳታፊ እንደሚሆኑበት የኢእፌ ገልጿል።

ከጦርነቱ በፊት ፦
➡️ መቐለ 70 እንደርታ ፣
➡️ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፣
➡️ ስሑል ሽረ ክለቦች በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ይታወሳል።

https://www.tg-me.com/+VvwzStMNcNHmhK0x

Via @tikvahethsport 
#AmharaRegion

በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን ፤ የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ በታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸውን ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ዘግቧል።

የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በተፈጸመ ጥቃት ነው የተገደሉት።

ባለስልጣናቱ ተኩስ የተከፈተባቸው ወልዲያ ከተማ የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቀው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ተነግሯል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ከላሊበላ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኘው " ኩልመስክ ከተማ " አቅራቢያ ነው።

ከሁለቱ ኃላፊዎች በተጨማሪም አንድ ሌላ ግለሰብ መገደላቸውን እና ሌሎችም መቁሰላቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል።

ጥቃቱ ሲፈጸም አብረው የነበሩ ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች ወደ ላሊበላ ከተማ የሚያደርጉትን ጉዞ አቋርጠው ወደ ኋላ በመመለስ ኩልመስክ ከተማ ማደራቸው ተነግሯል።

አንድ የላሊበላ ከተማ ነዋሪ በሰጡት ቃል " ማታ በዋና አስተዳዳሪው መኖሪያ ቤት ሲለቀስ ነው ያመሸው። አሁንም የአካባቢው ነዋሪ ወደ ለቅሶ እየሄደ ነው " ብለዋል።

የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪው አቶ ጌታቸው መልሴ የቀብር ስነ ስርዓት ጥቃቱ ከተፈጸመበት አካባቢ በምትገኘው የትውልድ ከተማቸው " ገነተ ማርያም " እንደሚፈጸም ተገልጿል።

የጤና ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ የቀብር ስነ ስርዓት በላሊበላ ከተማ እንደሚፈጸም የወረዳው አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ ኃላፊን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኑሮ ውድነቱ መፍትሄ ይሻል። መፍትሄ እንሻለን " - የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ  የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የስራ ግብር እንዲቀነስ ፤ የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ከኑሮ ውድነቱ አንፃር የዘገየው የሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እና የግብር ቅነሳ…
#ሜይዴይ

“ ኑሮ ውድነቱን ሠራተኛው ሊቋቋመው አልቻለም ” - አቶ ካሳሁን ፎሎ

ዛሬ የሜይዴይ በዓል እየተከበረ ነው።

በዓሉ አስመልክቶ ትላንት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ተገኝቶ ነበር።

ኮንፌዴሬሽኑ ፤ በባለፈው ዓመት በተከለከለው ሰልፍ ሳቢያ ከመንግሥት ጋር የገጠማችሁ አለመግባባት ተፈታ ? የሠራተኞች ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ አሁንስ ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል።

የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ “ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው ክልከላው ደርሶን የነበረው። በመነጋገር መፍታት አልቻልንም በወቅቱ ” ብለዋል።

“ ከዚያ በኋላ ግን ለምን እንደተከለከልን ከመንግሥት አካላት ጋር በየደረጃው ተወያይተናል። ክልከላው ሆን ተብሎ ሠራተኛው ያለውን ጥያቄ እንዳያቀርብ የተደረገ እንዳልነበር ተግባብተናል ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ከዚያም ጥያቄያችንን አደራጅተን ለጠ / ሚኒስትሩ አቅርበን ግብር እንዲቀነስ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ስኬል እንዲወሰን መጠየቃችን ይታወቃል። ጠ/ሚኒስትሩ በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ እንደሚሰጥ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ያኔ ” ሲሉ አስታውሰዋል።

“ አቅጣጫ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች እየተከታተልን ነው ” ያሉት አቶ ካሳሁን ፣ “ ነገር ግን አቅጣጫ የተሰጠባቸው የኑሮ ውድነቱን የተመለከቱ ጥያቄዎች ምላሽ አሁንም ዘግይቷል። ኑሮ ውድነቱን ሠራተኛውም ሊቋቋመው አልቻለም ” ብለዋል።

አሁን ምን አዲስ ነገር አለ ? ለሚለው ፦

➡️ ከሠራተኛው በነጻ መደራጀት ጋር በተያያዘ ለሁሉት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው መንግስትና ሠራተኛ ቁጭ ብለው የሚወያዩበት የአሰሪና ሠራተኛ አማካሪ ቦርድ ዘንድሮ ሥራ ጀምሯል፡

➡️ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሁሉም ክልሎች ሠራተኛ እና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች በሚገኙበት ስብሰባ ግምገማ ማካሄድ ተጀምሯል ጥያቄዎች በዚሁ አካሄድ ይፈታሉ ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

የሳምሰንግ ጋላክሲ S24 ስልኮችን በሳፋሪኮም ሱቆች መሸጥ ጀምረናል! በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ የሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት  ምርጥና እጅግ ዘመናዊ የሆኑትን ስልኮችን ዛሬውኑ ይግዙ ! 

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ  እንጋብዛለን።

👉Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
👉Telegram: https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC
👉Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
👉Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
👉 YouTube: https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm

#Furtheraheadtogether
TIKVAH-ETHIOPIA
" ' በኃይል ይዣለሁ ፣ ይዣለሁ ማለቱ ፍጹም ሰላም አያመጣም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ፥ " በወረራ " ተይዘዋል ያሏቸውን የትግራይ ክልል ግዛቶችን በሰላም ስምምነቱ መሰረት ነጻ እንዲወጡ እና የአካባቢዎቹ ሰላምና ደህንነት ተረጋግጦ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ኃላፊነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት…
#Update #Tigray

" የትግራይ ደቡባዊ ዞንና ፀለምት እስከ ግንቦት 30 ፤ የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ደግሞ እስከ ሰኔ 30 እንዲተገበርና እነዲፈፀም ስምምነት ተደርሶ ወደ ተግባር ተገብቷል " - ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕረዜዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ) ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ፥ " በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ላይ መሰረት ያደረገ ከአገር መከላከያ ሰራዊትና ከፌደራል መንግስት ጋር የሁለት ቀን ውይይት በማድረግ የአፈፃፀም ስምምነት ላይ ተደርሷል " ብለዋል። 

" በውይይቱ የማጠቃለያ ስምምነት መሰረት የትግራይ ደቡባዊ ዞንና ፀለምት እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ፤ የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም  እንዲተገበርና እንዲፈፀም ስምምነት ተደርሷል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ትጥቅ ማን ይፈታል ? ፣ እንዴት ይፈታል ? የትኞቹ አስተዳደሮችስ ይፈርሳሉ ? እንዴት ያሉ ተፈናቃዮች ይመለሳሉ ? በሚሉ ነጥቦች ውይይት ተካሂዶ ዝርዝር እቅድ ወጥቶሎታል " ሲሉ ገልጸዋል።

የእቅዱ አፈፃፀም በአፍሪካ ህብረት የክትትልና ቁጥጥር ቡድን እንዲመራና እንዲተገበር ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክተዋል።   

" በትግራይ አመራር መካከል በፕሪቶሪያ የውል ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያ ' ሰላም ፈላጊና ጦርነት ፈላጊ አለ ' በሚል እየተፈጠረ ያለው ትርክት ስህተት ነው " ያሉት ጄነራሉ " ትርክቱ ስህተት መሆኑን ለፌደራል መንግስት ገለፃ ሰጥተናል " ብለዋል።

በትግራይ በኩል የፕሪቶሪያ ውል ለመተግበር እስከ ታች የአስተዳደር መዋቅር ድረስ መግባባት ተደርሶ ወደ ትግበራ ለመግባት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ተመቻችቷል ሲሉ አሳውቀዋል።

" የፌደራል መንግስትም የስምምነቱ ትግበራ እስከ ታች ድረስ እንዲያወርደው እንጠብቃለን " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያው ውል ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ከማንኛውም አይነት ግጭት በፀዳ መልኩ ተፈፃሚ ይሆናል ተብሎ ባይጠበቅም ፤ አሁን መሬት ላይ ካለው ሁኔታ በመነሳት እንዳችም ለግጭት የሚጋብዝ ሁኔታ የለም  " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከምን ደረሰ ? " ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ መንገድ ይጠርጋል " የተባለው የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌለንድ ጋር ከተፈረመ ትላንት 1 ወር አልፎታል። የመግባቢያ ስምምነቱ እኤአ ጥር 1 ነበር የተፈረመው። ይህ ስምምነት በተፈረመበት ወቅት በመንግሥት ባለስልጣናት በኩል በተሰጡ ገለፃዎች ፦ * በ1 ወር ውስጥ የስምምነቱ ዝርዝር ይፋ እንደሚደረግ፤…
" ... ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን " - ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች / #UAE / ንብረት የሆነው ' ዲፒ ወርልድ ኩባንያ ' የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ማቀዳቸው ተሰምቷል።

ለዚህ የወደብ አጠቃቀምና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ስምምነት በኢትዮጵያና ሶማሌላንድ መካከል መፈረም አለበት።

ስምምነቱ ወደ መጨረሻውው ምዕራፍ መድረሱንና በሚቀጥሉት 60 ቀናት ተጠናቆ ሊፈረም እንደሚችል የሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር አሳውቋል።

የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ ፥ " ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን በአሁን ወቅት የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ወይም Transit Agreement እያዘጋጀን ነው። አንዴ ስምምነቱን ከተፈራረምን በመጀመሪያው ዓመት ከኢትዮጵያ ጭነት 30% እናስተናግዳለን " ብለዋል።

ይህን በተመለከተ " ስምምነቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸው በአንድ ወይም ሁለት ቀሪ ጉዳዮች ላይ እየተወያየን ነው ምናልባት በመጪዎቹ 60 ቀናት ሊጠናቀቅ ይችላል ከ60 ቀናት በኃላ እንፈራረማለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

ከወራት በፊት እ.አ.አ ጥር 1 ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በተመሳሳይ ወደ ተግባር የሚገባበት የመጨረሻው ስምምነት በ2 ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

መግባቢያ ምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን የቴክኒክ ኮሚቴዎችም መታጨታቸውን ተናግረዋል።

ይህ የመግባቢያ ስምምነት ወደ #መጨረሻው ደርሶ ወደ ተግባር ከገባ ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር በሊዝ ኪራይ የምታገኝ ሲሆን ሶማሌላንድ በበኩሏ ለረጅም አመታት ስትፈልገው የነበረውን እውቃና የማግኘት እድል እንደሚፈጥርላት ባለስልጣናቱ አመልክተዋል።

ለንግድ ስራ ሌላ ወደብ መገንባት ሳያስፈልግ የበርበራ ወደብን ኢትዮጵያ እንደምትጠቀምበት ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን " - ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች / #UAE / ንብረት የሆነው ' ዲፒ ወርልድ ኩባንያ ' የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ማቀዳቸው ተሰምቷል። ለዚህ የወደብ አጠቃቀምና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ስምምነት በኢትዮጵያና ሶማሌላንድ…
" ወደቡ ዝግጁ ነው፤ መንገዱም ከሞላ ጎደል ዝግጁ ነው " - ሰዓድ አሊ ሽሬ

ሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ #የኢትዮጵያን 30% ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለች።

ለዚህ ደግሞ አስፈላጊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸለች።

አሁን ላይ ስምምነት እንዲፈረም እየተሰራ ነው ተብሏል።

የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ሰዓድ አሊ ሽሬ ምን አሉ ?

" አካላዊ መሰረተ ልማትን በተመለከተ ወደቡን ገንበተናል።

አንድ ኪሎሜትር የሚሰፋ የመርከብ ማቆሚያ፤

ኮንቴነሮችን መጫንና ማውረድ የሚችሉ ክሬኖች ያሉት ዓለም አቀፍ ወደብ አለ፤

ከበርበራ ወደብ ድንበር ላይ እስከምትገኘው #ውጫሌ ያለውን መንገድ ገንብተናል፤

ስለዚህ ወደቡ ዝግጁ ነው። መንገዱም ከሞላ ጎደል ዝግጁ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በበርበራ ነጻ የኢኮኖሚ ዞኖች አሉን።

የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋኖች ከነዳጅ ጫኝ መርከቦች ማራገፊያ አዘጋጅተናል። አካላዊ ክፍል ከሞላ ጎደል አልቋል።

ለምሳሌ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል የወደብ አጠቃቀም ስምምነት (Transit Agreement) ሊኖረን ይገባል። የጉምሩክ ስርዓቶቻችን ማገናኘት ወይም ማስተሳሰር ይኖርብናል ይህ አሁንም በስራ ላይ ነው። የመጓጓዣ ስምምነትም ማባጀት አለብን ይሄም ሂደት ላይ ነው።

ከስርዓት አኳያ በሂደት ላይ የሚገኙ የተወሰኑ ጉዳዮች አሉ " ብለዋል።

እንደ ሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር ዳይሬክተር ሰኢድ ሀሰን አብዱላሂ ማብራሪያ ደግሞ ፥
ህጋዊው ጉዳይ በመንግስታት መካከል የሚፈርም እንደሆነ
ስምምነቱ እየተጠናቀቀ ስለመሆኑ
በአንድ እና ሁለት ቀሪ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን
በመጪው 60 ቀናት ስምምነቱ ሊጠናቀቅ እንደሚችልን ከ60 ቀናት በኃላ እንደሚፈረምና ኮሪደሩ ጥቅም መስጠት ይጀምራል።

በተጨማሪ ፦
° የUAE ዲፒ ወርልድ እና ሶማሌላንድ ከበርበራ ወደብ 15 ኪ/ሜ ርቀት ነጻ የኢኮኖሚ ቀጣራ ማበጀታቸውን
° ነጻው የኢኮኖሚ ቀጠና ከወደቡ ወደ ኢትዮጵያ በሚያመራው መንገድ ላይ እንደሚገኝ
° ነጻው የኢኮኖሚ ዞን 300 ሺህ ካሬ ጫማ የሚሰፋ ከማብሰያ ዘይት ማሸጊያ ፋብሪካ ጭምር አለው።

ከ6 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ከሶማሌላድ እና ዲፒ ወርልድ ጋር በተፈራረመችው ስምምነት በበርበራ ወደብ ልማት 19% ድርሻ ነበራት ግን አልዘለቀችበትም። ግን አሁን ኢትዮጵያ ወደቡ ላይ ድርሻ እንዲኖራት ትፈልጋለች።

የበርበራ ወደብ ያለበት ቀጠና ለዓለም አቀፍ የመርከብ እንቅስቃሴ ወሳኝ በመሆኑ ሶማሌላንድ እና ዲፒ ወርልድ አሁንም ማስፋታ ይፈልጋሉ።

ግዙፍ የኮንቴነር ተርሚናል ለመገንባት ሙከራ እየተደረገ መሆኑ፣ ተጨማሪ 600 ሜትር የሚሰፋ የመርከብ ማቆሚያ ፣ 7 ግዙፍ የእቃ መጫኛና ማውረጃ ለመጨመር እቅድ እንዳለ ታውቋል።

ይህን ተከትሎ የበርበራ ወደብ መርከብ መቆሚያ 1650 ሜርት እንደሚሆን 2 ሚሊዮን ኮንቴነርም ማስተናገድ እንደሚችል ለኢትዮጵያም ትልቅ አማራጭ መሆኑ በሶማሌላንድ ባለስልጣናት ተገልጿል።

Credit - DW (Eshete Bekele)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን ፤ የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ በታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸውን ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ዘግቧል። የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በተፈጸመ ጥቃት ነው የተገደሉት። ባለስልጣናቱ ተኩስ የተከፈተባቸው ወልዲያ ከተማ የነበራቸውን…
“ ማን እንደገደላቸው መረጃ የለኝም ፤  በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” - ስሜ አይገለጽ ያሉ ባለስልጣን

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው ጤና ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በጥይት  መገደላቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋገጧል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የሰሜን ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣን በሰጡት ቃል፤ “ ትላንት ከዞን ግምገማ ቆይተው ሲመለሱ ነው ግድያው የተፈጸመው። የሞቱት የወረዳው አስተዳዳሪ የወረዳው ጤና ኃላፊ ናቸው ” ብለዋል።

“ ኩል መስክ የሚባል ቦታ ነው ግድያው የተፈጸመው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላ የተጎዳ ሰው አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፣ “ ሌላ እዛው ኩል መስክ የቀበሌ ሊቀመንበር የተጎዳ አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ አርብና ቅዳሜ ግምገማ ነበረ፤ እዚያ ተመልሰው ኩል መስክ ቆይተዋል ለሁለት ቀናት ” ሲሉም አክለዋል።

ግድያውን የፈጸመው ማነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ እስካሁን መረጃው የለኝም፤ በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” ብለው፣ የገዳዮቹን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

“ ዞሮ ዞሮ በግድያ የሚመለስ አንድም ጥያቄ የለም። እነዚህ (ሟቾቹ) የሕዝብ አስተዳዳሪዎች ናቸው። ሕዝብም ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል እንጂ መሞት አለባቸው ብዬ አላስብም ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2024/05/01 20:49:48
Back to Top
HTML Embed Code: