በጎፋ ዞን ቡልቂ ከተማ የ16 አመት ታዳጊ የደፈሩ 2 ግለሰቦችና ታዳጊዋ እንድትደፈር ያደረገች ሴት በፅኑ እስራት ተቀጡ

በጎፋ ዞን በቡልቂ ከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱ 2 ግለሰቦችና ታዳጊዋ እንድትደፈር በማመቻቸት በአባሪነት የተከሰሰች አንዲት ሴት በጽኑ እሥራት መቀጣታቸውን የከተማው ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

1ኛ ተከሣሽ የሆነው አቶ በቃኃኝ ባቤና እና 2ኛ ተከሣሽ አቶ አበራ ሚኖታ የተባሉት ግለሰቦች የ16 ዓመቷን ታዳጊ በመድፈር ክስ ሲቀርብባቸው 3ኛ ተከሣሽ የሆነችው ወ/ሮ ብርቱኳን ከበደ ደግሞ በራሷ ምግብ ቤት በዕቃ አጣቢነት ቀጥራ የምታሠራትን ይህቺን ታዳጊ ሰራተኛ ያለፍቃዷ 1ኛ ተከሣሽ እንዲደፍራት በማመቻቸት መከሰሷ ተገልጿል።

የከተማው ፖሊስ የተፈፀመውን ወንጀል መነሻ በማድረግ ምርመራ አድርጎ ያጠናቀቀውን የምርመራ መዝገብ ለከተማው ዓቃቤ ሕግ አቅርቦ ዐቃቤ ሕግም የምርመራ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ፍርድ ቤቱ 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች ተበዳይን ያለፍላጎቷ አስገድደው ስለመድፈራቸው እና 3ኛ ተከሣሽም ተበዳይ በ1ኛ ተከሣሽ ያለፍላጎቷ እንድትደፈር ምቹ ሁኔታ መፍጠሯን በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህም የቡልቂ ከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከሣሾቹን ማቅለያ እና የዐቃቤ ሕግን ማክበጃ ሀሳቦችን ከመረመረ በኋላ

#1ኛ ተከሣሽ አቶ በቃኻኝ ባቤና በ9 ዓመት ጽኑ እሥራት፤
#2ኛ ተከሣሽ አቶ አበራ ምኖታ በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት፤
#3ኛ ተከሣሽ የሆነችው ወ/ሮ ብርቱኳን ከበደ በ6 ዓመት ጽኑ እሥራት እንዲቀጡ ወስኗል።

@TikvahethMagazine
እንኳን አደረሳችሁ!

ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ!

ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን!

ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764

ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 www.tg-me.com/bluebellgiftstore

😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://www.tg-me.com/bluebellgiftstore/627
ኢትዮጵያ የፓኪስታን ባንኮች በአዲስ አበባ ቅርንጫፎቻቸውን እንዲከፍቱ ጥሪ አቀረበች

የኢፌዲሪ አምባሳደር ጀማል በከር አብዱላ የፓኪስታን ባንኮች ከንግድ ጋር የተያያዙ ግብይቶችን ለማካሄድ ቅርንጫፎቻቸውን በአዲስ አበባ እንዲከፍቱ መጠየቃቸውን የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

አምባሳደሩ ጥሪውን ያቀረቡት በፋይሳላባድ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት (FCCI) ጋር በነበራቸው ንግግር ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማደላደል እና የሁለትዮሽ ንግድን ለማቀላጠፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የባንክ ቅርንጫፎችን መክፈት ትልቅ ፈተና እንዳለው የተናገሩት አምባሳደሩ ከተሳካ ግን የሁለትዮሽ ንግድን ለማጠናከር እና የፓኪስታን ላኪዎች ሰፊውን የአፍሪካ ገበያ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።

@TikvahethMagazine
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን አሳወቀ

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

በዚህም የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ

- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ ተጠቁሟል።

- አባል ሀገራት ከአሁን በኋላ ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉም ተገልጿል።

- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛውን የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱም ተነግሯል።

በተጨማሪም፣ መደበኛው ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ተቀይሯል።

ይህ ውሳኔ የተወሰነው የህብረቱ ምክር ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት የሚቆዩ ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።

@TikvahethMagazine
#ጥንቃቄ: በቦሌ ክ/ከተማ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

በዛሬው ዕለት ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የክረምት ወር መግባቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች 32 ሺሕ አባወራዎች ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸው ሲገለፅ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ልደታ፣ ቂርቆስና አራዳ ክፍለ ከተሞች በተደጋጋሚ ጎርፍ የሚያጠቃቸውና በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች መሆናቸው በጥናት ተለይተው ታውቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት የለየ ሲሆን ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ መልእክቱን አሰተላልፏል፡፡

@TikvahethMagazine
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቤሩት አል ሃሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ምን ገጠመው?

የሊባኖስ አቬዬሽን ባለስልጣን “ቴል አቪቭ” የተሰኘ መለያ ያለበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቤይሩት ሲደርስ ተቃውሞ ማሰማቱን የሀገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የሀገሪቱ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን ቤይሩት ያረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 787-9 አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ከመመለሱ በፊት ምልክቱን እንዲሸፍን አድርጓል።

በተጨማሪም፥ አውሮፕላኖች በቤይሩት ከመድረሳቸው በፊት ሊባኖስ "ጠላቴ ናት" ከምትላት እስራኤል ጋር የተያያዘ ምንም አርማ እንደሌለ ማረጋገጥ እንዳለበት አሳስቧል።

ሊባኖስ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ኖሯት የማያውቅ ሲሆን እንደ ጠላት ሀገር የሚተያዩ ናቸው።

ሁለቱ ሀገራት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመሀከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭትና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን የሆነው 'ሒዝቦላ' ጋር በሚያደርጉት ውጊያ ቀጠናው እና ሁለቱ ሀገራት የተካረረ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

አየር መንገዱ አዳዲስ አውሮፕላን ሲያስገባ አውሮፕላኖቹ የመጀመሪያ በረራ ያደረጉበት የመጀመሪያው ከተማ ስም በውጨኛው ክፍል ላይ ይጻፋል። ይህም የአየር መንገዱ ልምድ ነው።

በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ4 አመት በፊት ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኑን ወደ መስመር ሲያስገባ ቅድሚያ የበረረበትን የከተማ ስያሜ ' ቴል አቪቭ ' የሚል የሚል ስያሜ ሰጥቶት ነበር።

@TikvahethMagazine
እንኳን አደረሳችሁ!

ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ!

ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን!

ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764

ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 www.tg-me.com/bluebellgiftstore

😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://www.tg-me.com/bluebellgiftstore/627
በ2023 አምስት ምርጥ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

"ኢዱኬሽን ፈርስት" የተባለ ዓለማቀፍ የትምህርት ተቋም እድሜአቸው ከ 18 - 20 የሆኑ 2.1 ሚሊዮን ወጣቶችን ከ113 ሀገራት የእንጊሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን በመገምገም የሀገራትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብቃት ደረጃ አውጥቷል።

ተቋሙ የቋንቋውን ተናጋሪዎች ብቃት በጣም የላቀ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ በሚሉ አምስት የብቃት ደረጃዎች በመክፈል ነው ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው።

በሪፖርቱ መሰረትም ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተቀመጡ የአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል፦

🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇰🇪 ኬንያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇬🇭 ጋና
🇺🇬 ኡዳንዳ መሆን ችለዋል።

ከአፍሪካ በቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ  "#በጣም_የላቀ" በተባለው ከፍተኛ የእንግሊዘኛ ብቃት ያላችው ሀገራት ምድብ ውስጥ ተካትታለች።

2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኬንያ እንዲሁም 3ኛዋ ናይጄሪያ "#ከፍተኛ" በተባለው እንዲሁም  ዩጋንዳ እና ጋና "#መካከለኛ" በተባለው የቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ተመድበዋል።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ🇪🇹 #ዝቅተኛ የእንጊሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ውስጥ ከታንዛኒያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ግብፅ ጋር መመደቧ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ኔዘርላንድስ፣ ሲንጋፖር፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ከአለም ከ1 እስከ 5 ያለውን የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት ደረጃ መያዝ ችለዋል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት

ነገ ረቡዕ ሚያዚያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በአለም አቀፍ ደረጃ የሠራተኞች ቀን የሚከበርበት ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው መስሪያ ቤት እስከ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቹ ድረስ በሚገኙ ሁሉም ቢሮዎች ሁሉንም አገልግሎቶቹን እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

@TikvahethMagazine
#CholeraUpdate

በኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር እንደተመዘገበ ተነገረ

በአፍሪካ ባለፈው መጋቢት ወር በኮሌራ በሽታ ከተያዙ 14,441 አዲስ የኮሌራ ታማሚዎች መሃከል ከአህጉሪቱ ከፍተኛ ታማሚዎች የተመዘገቡባት ኢትዮጵያ መሆኗን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።

በተጠቀሰው ወር በኢትዮጵያ 4009 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው ተነግሯል። በኮሌራ ከተያዙት ሰዎች ውስጥም 24 ሰዎች መሞታቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ባለፉት 3 ወራት 9,429 ሰዎች በኮሌራ ተይዘው 111 ሰዎች መሞታቸውንም ሪፖርቱ አመልክቷል።

በአፍሪካ ከጃንዋሪ 1 ቀን 2023 እስከ ማርች 31 ቀን 2024 በጠቅላላው በ18 ሀገራት 271,119 ሰዎች በኮሌራ በሽታ ሲያዙ በተጠቀሰው ጊዜ በኢትዮጵያ 39,892 ሰዎች በበሽታው ተይዘው 524 ሰዎች መሞታቸውም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ ነው ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከዚህ ቀደም ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩና ሌሎች ወጣቶች በ2 ማኅበር ተደራጅተው በጀመሩት የዓሳ ማስገር ስራ ከህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ መሆኑ ተገለፀ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ግድቡ ውሀ መያዝ ከጀመረ ወዲህ በተለይም ለዓሳ ምርት ምቹ መሆኑ ሲገር በ8 ወራት ውስጥ 1729 ቶን ዓሳ ምርት ከህዳሴ ግድብ መገኘቱን ዶይቼ ቨለ በዘገባው አመልክቷል።

ወጣቶቹ የተደራጁበት ማህበርም 56 የሚደርሱ ወጣቶችን ያቀፈ ሲሆን በግደቡ ዳርቻ በሚሰሩት የዓሳ ማስገር ስራ በቀን ከ2 እስከ 3 ኩንታል ዓሳ እንደሚኝና በአካባቢው የዓሳ ማስገር ስራውን በማህበሰረብ አቀም ለማድረግና ለማሻሻል ዘመናዊ ጅልባዎች ያስፈልጋሉ ተብሏል።

@TikvahethMagazine
እንኳን አደረሳችሁ!

ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ!

ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን!

ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764

ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 www.tg-me.com/bluebellgiftstore

😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://www.tg-me.com/bluebellgiftstore/627
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"የዓለም ባንክ የአፍሪካ ሀገራትን መዋቅራዊ ችግሮች ከመደገፍ ለሴሚናር ገንዘብ ማውጣት ይቀለዋል" የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የዓለም ባንክ ድሃ የአፍሪካ ሀገራት ለዕድገታቸው እንቅፋት የሆኑ የእርሻ፣ ትራንስፖርትና መሰል መዋቅራዊ ችግሮችን እንዲፈቱ ብድር ከመስጠት ይልቅ ለሚዘጋጁት ‘ሴሚናሮች’ ብድር ቅድሚያ ይሰጣል ሲሉ ወቀሳ ሰነዘሩ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በኬኔያ በተካሄደው የአለም አቀፍ ልማት ማህበር የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ነው። " አለም ባንክ ሰዎች ተቀምጠው ለሚመገቡት ሴሚናሮች  ብድር ለመስጠት ፈጣን ናቸው። ነው ነገር ግን የመስኖ እና የመሠረተ ልማት ልማትን አይደግፉም " ሲሉ ወቅሰዋል።

ፕሬዝዳንቱ አፍሪካ ዘላቂ ልማት (Sustainable underdevelopment) አያስፈልጋትም አፍሪካ የምትፈልገው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ (Socio-Economic Transformation) ነው ያሉ ሲሆን ዘላቂ ልማትን የሚባለውን ፅንሰ ሀሳብ እድገት የሌለው ሲሉ ገልጸውታል።

"አንድ ሴት በዚህ ዓመት ካረገዘች በሚቀጥሉት ሦስት እና አራት ዓመታት እርጉዝ አትሆንም፥ ይህ ፈጽሞ አይፈጠርም ተፈጥሯዊው እድገት ለወራት ታረግዛለች ልጁ ያድጋል፤ ይወለዳል፤ ይጎለምሳል። የሆነ ምዕራፍ ላይ እርግዝናው (Quantitative) ወደ ልጅነት ይቀየራል (Qualitative) እነዚህን ቃላት በዶክመንታችሁ አስተካክሏቸው።" ሲሉ ገልጸዋል።

ፕሬዚደንት ሙሴቬኒ አክለውም፥ አፍሪቃ የጥሬ ዕቃዎቿን ወደ ውጭ መላክ እንድታቆም የጠየቁ ሲሆን ጥሬ እቃ ላይ እሴት ሳይጨመር መላክ በአፍሪካዊያን ሀብት ሌሎችን ማበልጸግ እንደሆነ የቡና እና የማዕድን ሀብትን በምሳሌ አንስተው አስረድተዋል።

"ኡጋንዳ ሀብታም ሀገር ብትሆንም አብዛኞቹ ዜጎቿ ለዕለት ጉርስ እንጂ ለኪስ የሚሆን ገንዘብ ከሚያገኙበትን ሥርዓት ( Money Economy) ውጪ ናቸው። ይህንን ለመቅረፍ ገንዘብ የሚሰጠኝ የለም ምክንያቱም ሁሉም ገንዘብ ለአቅም ማጎልበቻ (Capacity Building ) ነው። እኛ ግን በራሳችን ፈንድ እየሰራን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

በአፍሪካ የግሉ ዘርፍ እየተደገፈ ባለመሆኑ እድገት እየተመዘገበ እንዳልሆነ የገለፁት ሙሴቬኒ የግሉ ዘርፍ እንዲበረታታ በቅድሚያ በአነስተኛ ዋጋ ማምረት መቻል ለዚህም ደግሞ  የመንገድ የኤሌክትሪክ ሀይል ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅሰው የዓለም ባንክ ለእነዚህ ነገሮች ፈንድ ያደረገበትን ኦዲት ያድርግ ሲሉ ጠቅሰዋል።

(📹 28 MB)

@TikvahethMagazine
ልጆች 13 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ስማርት ስልኮችን ባይጠቀሙ ሲል በፈረንሳይ የተሰራ ጥናት አመለከተ።

በተለያየ የእድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ህፃናት እና ታዳጊዎች ስማርት ስልኮችን በመጠቀም የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ሲጠቀሙ አለፍ ሊልም በነዚህ የትስስር ገጾች ላይ ተሳትፎ ሲያደርጉ ይስተዋላል።

የስማርት ስልክ አጠቃቀም ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደሆነ ቢነገርም ሀገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ ስማርት ስልኮች ላይ የሚገኙት የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህፃናትና ታዳጊዎችን ለሱስ ከመዳረግ ባለፈ በልጆች ላይ ስነልቦናዊ ጉዳት እያስከተለ ስለመሆኑ ይነገራል።

ጉዳዩን አስመልክቶ በፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን ሀሳብ አመንጪነት ታዳጊ ልጆችን ከአደጋ ለመጠበቅ ኒውሮሎጂስት እና የዘርፉ ባለሙያዎች የስልክ ስክሪን አጠቃቀም መመሪያዎችን ለመንግስት እንዲጠቁሙ  በማሰብ 3 ወራትን የፈጀ ጥናት ተሰርቷል።

በጥናቱም ልጆች 13 አመት እስኪሞላቸው ድረስ ስማርት ስልኮችን እንዲጠቀሙ መፈቀድ እንደሌለበትና እንደ #ቲክቶክ#ኢንስታግራም እና #ስናፕቻት የመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችን እስከ 18 አመት ድረስ መጠቀም እንደሌለባቸው ጥናቱ አመልክቷል።

ጥናቱም ከ3 አመት በታች ያሉ ህጻናት የቴሌቪዥን ስክሪኖች ጨምሮ ለስልኮች ተጋላጭ መሆን እንደሌለባቸው የጠቆመ ሲሆን አንድ ህፃን 11 ዓመት ሳይሞላው ስልክ ሊኖረው እንደማይገባና ይህ ካልሆነ ህፃናት በልጅነታቸው ስሜታቸውን ከመግለፅ እና ነገሮችን ከመረዳት አኳያ ሊያዳብሯቸው የሚገባቸውን ችሎታዎች ሊጎዳ እንደሚችል ተገልጿል።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በጥር ወር ህፃናትን ላይ ጉዳት እየዳረገ ስለሚገኘው የስማርት ስልክ እንዲሁም የስክሪን አጠቃቀም " እገዳዎች ወይም ገደቦች " ሊኖሩ ይችላሉ ማለታቸውም ነው የተነገረው።

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ካለው የህፃናትና ታዳጊዎች ስማርት ስልክ አጠቀም አንፃር እንዴት ይታያል?

@TikvahethMagazine
እንኳን አደረሳችሁ!

ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ!

ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን!

ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764

ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 www.tg-me.com/bluebellgiftstore

😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://www.tg-me.com/bluebellgiftstore/627
#MOR

° ባለፉት ዘጠኛ ወራት 374.20 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል።

° 23ሺ ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ክፍያ መፈጸም ችለዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 9 ወራት 374.20 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ የ9 ወራት ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል።

መስሪያ ቤቱ 391.34 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ሲሆን፤ የዕቅዱን 95.62 በመቶ ማሳካት እንደቻለ ገልጿል።

ከነዚህ ውስጥ 23,071 ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ክፍያ መፈጸም መቻላቸውም ተገልጿል።

የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በቅንጅት በመስራት ባለፉት 9 ወራት የቴሌ ብር ሥርዓትን ለቀረጥና ታክስ አሰባሰቡ በሥራ ላይ ማዋል በመቻሉ 7,130 ግብር ከፋዮች በቴሌ ብር በኩል ክፍያቸውን እንደፈፀሙ ተነግሯል።

በተያየዘ የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴን ለማሳለጥ የታቀፉ የንግድ ባንኮች ቁጥር 21 እንዲደርስ የተደረገ መሆኑን ሲጠቆም የተቀሩት ባንኮችንም ወደ ሥርዓቱ ለማስገባት ሥራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነት ተቀበለ።

በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይ ላይት ሆቴል ተቋሙ በኩል እንዲወጣ ዛሬ የስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

ስምምነቱ በቅርቡ የተመረቁትን ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ እንዲሁም በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የጎርጎራ ፕሮጀክትንም ያካትታል።

"ቀጣይ የስራ ማስኬድ እና ማስተዳደር ተግባሩ ለብሔራዊ ሰንደቅ ተሸካሚው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃላፊነት መሰጠቱም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉም ባለፈ ለአለምአቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ይፈጥራል።" ሲል የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቋል።

@TikvahethMagazine
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን በሾኔ ከተማ አስተዳደር ማዞሪያ ቀበሌ ሌሊት 11:30 አከባቢ በደረሰው በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

አደጋው የተከሰተው ከወላይታ ሶዶ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ፒካፕ መኪና በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ ባለሶስት እግር ባጃጅ ጋር ተጋጭቶ ነው። በአደጋውም በውስጡ የነበሩ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት እና አንድ ጎረቤት በድምሩ የ 4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በ 2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከሟቾቹ መካከል ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እያመራች የነበረች እናት እንደምትገኝበት ተገልጿል። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine
ለጅማ ዩኒቨርስቲ እና በከተማዋ ለሚገኙ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 22 ሺ መፅሃፍት ተበረከተ

ተስፋ ለጅማ እና ሪቦ ፋውንዴሽን የተሰኙ ማህበራት ከ ስልሳ ሚሊዮን (60,000,000) ብር በላይ የሚገመቱ 22,000 መፅሃፍቶችን በስጦታት ማበርከታቸውን የጅማ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

ማህበራቱ ይህንን ያደረጉት ከተለያዩ አውሮፓ ከሚኖሩ የጅማ እና አካባቢዋ ተወላጆች እና የዲያስፖራ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ሲሆን የጅማ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ ማናጅመንት አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች በተገኙበት ርክክቡ ተደርጓል።

@TikvahethMagazine
2024/05/03 05:20:34
Back to Top
HTML Embed Code: