tg-me.com/Teyakaenamels/2913
Last Update:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫
መንፈሳዊ ጥያቄ ና መልስ
//ስለ ዘመነ ፅጌ// 💠
1️⃣ ዘመነ ፅጌ ማለት ምን ማለት ነው ?
መልስ => የአበባ ዘመን ማለት ነው ✅
2️⃣ ዘመነ ፅጌ እሚባለው ከምን ቀን እስከ ስንት ቀን ነው ?
መልስ => ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 6 ✅
3️⃣ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች የሚለውን ትንቢት ለመተርጎም በመጠራጠሩ ይህ ትንቢት እስኪፈፀም ሞትን ያላየው አባት ማን ይባላል ?
አረጋዊ ስምዖን ✅
4️⃣ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ፡ ይህ ቃል የት ይገኛል ?
ማቴዎስ 2-20 ✅
5️⃣ ጾመ ፅጌ ከሰባቱ አጹአማት መካከል ይመደባል እውነት ሀሰት?
ሀሰት ✅
6️⃣ አረጋዊ ስምዖን ና 71ሊቃውንት አባቶችን መፅሐፈ ብሉያትን እንዲተረጎሙ ያደረገው ንጉስ ማነው ?
ሀ/ ንጉስ ሄሮድስ
ለ/ ንጉስ በጥሊሞስ✅
ሐ/ ንጉስ ፈርዖን
መ/ ንጉስ ዳዊት
7️⃣ በዚህ በፆመ ፅጌ በተለየ ሁኔታ የሚዘወተረው ማህሌተ ፅጌ የተሰኘውን ድርሰት የደረሱት አባት ማን ይባላሉ ?
ሀ/ ቅዱስ ያሬድ
ለ/ ቅዱስ ኤፍሬም
ሐ/አባ ጊዮርጊስ
መ/ አባፅጌ ድንግል✅
8️⃣ ከመጽሀፈ ብሉያት መካከል ለአረጋዊ ስምዖን እንዲተረጎም የደረሰው የትኛው የትንቢተ መጽሀፍ ነው ?
ሀ/ ትንቢተ ኤርምያስ
ለ/ ትንቢተ ሕዝቅኤል
ሐ/ ትንቢተ ኢሳይያስ✅
መ/ ትንቢተ ሆሴዕ
9️⃣ የእመቤታችን ስደት ስቃይ እንግልት አስቀድሞ ታይቶት በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል፡ ብሎ ትንቢት የተናገረው አባት ማነው?
አረጋዊ ስምዖን ሉቃስ 2
34-35፤✅
🔟 በተአምር ማርያም እና በማህሌተ ፅጌ ተፅፎ እንደሚገኘው ጌታችን በምድረ ግብፅ በስደት ሳለ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጓል ከእነዚህም መካከል እናቱን እመቤታችንን የዘለፏትን ሁለት ሴቶች ከሰውነት ወደውሻነት ተቀይረዋል የሴቶች ስም ማን ና ማን ይባላል ?
መልስ => ትእማን እና ኮቲባ ✅
1️⃣1️⃣ የጌታችን እና የእመቤታችን ጥንተ ስደት የሆነው በምን ወር ነበር ?
መልስ => በግንቦት ወር ነው ✅
1️⃣2️⃣ ስልጣንን ሊቀማኝ ነው በማለት የአይሁድ ንጉስ ወዴት ነው ብሎ ጌታችን በመፈለግ ምክንያት 144ሺ የቤተልሔም ህፃናት ያስፈጀው እንዲሁም እመቤታችን ክፉኛ ያሳደዳት ንጉስ ማነው ?
ሀ/ ንጉስ አንጢያኮስ
ለ/ ንጉስ በጥሊሞስ
ሐ/ ንጉስ ናቡከደነጾር
መ/ ንጉስ ሄሮድስ✅
1️⃣3️⃣ ጌታችን በምድረ ግብፅ በስደት ከአደረጋቸው ተአምራትን አ
እንደ አንዱ የሚጠቀስ ሲሆን ይኽውም የሄሮድስ ጭፍሮች ደርሰው ልጅሽን ሊገድሉብሽ ነው ብሎ እመቤታችን በማስደንገጡ እስከ እለት ምፅአትት ድረስ ድንጋይ ሆኖ እንዲቆይ የተደረገው የዮሴፍ ልጅ ስሙ ማን ይባል ?
መልስ => ዮሳ ✅
1️⃣4️⃣ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የሚለውን ትንቢት የተናገረው ነብይ ማነው ቃሉስ የት ይገኛል ?
=> የተናገረው ነብዩ ሆሴዕ ነው ቃሉ ትንቢተ ሆሴዕ 11-1 ላይ ይገኛል ✅
1️⃣5️⃣ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፡— ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ፡ ይህ ቃል የት ይገኛል ??
መልስ => ማቴዎስ 2 ÷13 ✅
ወስበኃት ለእግዚአብሔር
https://www.tg-me.com/us/የድንግል ማርያም ልጆች& 33;ጥያቄና መልስ ቻናል& 33;/com.Teyakaenamels
BY የድንግል ማርያም ልጆች!♥ጥያቄና መልስ ቻናል!
Share with your friend now:
tg-me.com/Teyakaenamels/2913