tg-me.com/Teyakaenamels/2914
Last Update:
#እንኳን #አደረሳችሁ #በዓለ_ደብረ_ቁስቋም_ማርያም
©አስምኪ ቦቱ
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር /፪/
ተፈጸመ /፭/ ማኅሌተ ጽጌ/፪/
ትርጉም:- የሰማይና የምድር ንግሥት ሆይ እነሆ ጽጌ ማኅሌት ተፈጸመ። ውድ ልጅሽ በእቅፍሽ አንደሚያርፍ አንቺም በዚህ ማኅሌት እረፊበት። ደስ ተሰኝበት።በመካከሉ ተገኝ አሳርፊው።
©ኀብረ ሐመልሚል
ኀብረ ሐመልሚል ቀይህ ወጸአድኢድ/፪/
ተፈጸመ/፭/ ማኀሌተ ጽጌ/፪/ እኽ
ትርጉም:- ቀይ እና ነጭ የሆነ የልምላሜ ምስጋናሽ ድንግል ሆይ ተፈጸመ።
©ዮም ጸለሉ መላእክት
ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም/፪/
እንዘ ይብሉ ስብሐት ስብሐት በአርያም ስብሐት በአርያም /፪/
ትርጉም፡- መላእክት በደብረ ቁስቋም ምስጋና በአርያም ይሁን እያሉ ማርያምንና ልጇን ከበቡ፡፡
የሚዘመርበት ወቅት፡- ኅዳር ፮
©ብርሃነ ሕይወት
ብርሃነ ሕይወት ዘኢይጸልም ኀደረ ደብረ ቁስቋም /፪/
ኃይል ወጽንዕ ዘእምአርያም /፬/ ኧኸ
ትርጉም፡- የማይጠፋው የሕይወት ብርሃን የአርያም
ኃይል በደብረ ቁስቋም አደረ ።
የሚዘመርበት ወቅት፡- ኅዳር ፮
©አብርሂ
አብርሂ /፪/ ኢየሩሳሌም /፪/
በጽሐ ብርሃንኪ ኢየሩሳሌም እግዚአብሔር /፪/
ትርጉም፡- ኢየሩሳሌም ሆይ ብርሃንሽ እግዚአብሔር ስለደረሰ አሁን አብሪ፡፡
የሚዘመርበት ወቅት፡- ኅዳር ፮
©ወተመይጠት
ወተመይጠት ማርያም ሀገረ እስራኤል አቡሃ /፪/
ነቢራ በግብጽ /፬/ አርብዓ ወክልኤተ አውራኀ /፪/
ትርጉም፡- ማርያም አርባ ኹለት ወራት በግብጽ ተቀምጣ ወደ አባቷ ሃገር ኢየሩሳሌም ተመለሰች፡፡
የሚዘመርበት ወቅት፡- ኅዳር ፮
©አልቦ እንበለ ሰሎሜ
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ /፪/
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይጸውር ስንቀኪ /፬/ ኧኸ
ትርጉም ፡- ከሰሎሜ ውጪ የሚያግዝሽ ከቅዱስ ዮሴፍም ውጪ ስንቅሽን የሚሸከምልሽ የለም።
©ውድስት አንቲ
ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት/፪/
አክሊለ በረከቱ ለዮሐንስ ወትምክሕተ ቤቱ ለእስራኤል/፪/
ትርጉም፡- የዮሐንስ አክሊለ በረከት የእሥራኤል ቤት መመኪያው የሆነሽ እመቤታችን በነቢያት
አንደበትና በሐዋርያት የተመሰገንሽ ነሽ፡፡https://www.tg-me.com/yaradawyimezmuroch
BY የድንግል ማርያም ልጆች!♥ጥያቄና መልስ ቻናል!
Share with your friend now:
tg-me.com/Teyakaenamels/2914