tg-me.com/Tzta_lay/3586
Last Update:
" የተለየሽኝ እ- ለት " 🚶♀
የከፋኝ ቀን ፃፍኩሽ፣
እንዳላቅፍሽ 👬 የለሽ፤
የልቤን እንዳልነግርሽ፤
ፍቅሬን አንዳልገልጽልሽ፣
ባካል ባይሆንልኝ ከወረቀት ፃፍኩሽ።
አንቺ የሔድሽ ቀን........
የተለየሽኝ ለት፦
በምዕራብ ፀሀይ ወጣች፣
በጠዋት ጨረቃ፣
ከሀዘን ተዛመድኩ፣
አይን አይንሽን እያየሁ
እየሳኩ አለቀስኩ።
የተለየሽኝ ለት........
ከቆምንበት ቦታ፣
ካለፍናቸው መንደር፣
እጄን ኪሤ አርጌ፣
ድንጋይ እየለጋሁ፣
ብዙ ተመላለስኩ፤
እንቺን ብሎ እያለ ልቤ ሢያስጨንቀኝ፣
ግራ ግብት ቢለኝ ትንሽ ላረጋጋው፣
ካለሽበት መንደር ከሰፈርሽ መጣሁ፤
እሡቅ ብትላኪ ድንገቱን አግኝቼሽ
ፍቅርህ ያችው ልለው።
የተለየሽኝ ለት........
ብቸኝነት አውቆኝ፣
ብዙ እንደናፈኩሽ፣
ሳቅሽ እንዳማረኝ፣
ትንሽ ሳይቀልልኝ፣
ልሔድ ነው ሣትይኝ፤
አይኔ በሀዘንሽ እንባ እንዳቀረረ፣
ተሰፋዬም ካንቺው ጋር የዛኔው በረረ።
የተለየሽኝ ቀን........
አንቺን ያጣሁኝ ለት፦
ልቤ አንቺኑ ብሎ እንደወጣ ቀረ፣
አይኔ አይንሽን ማየት፣
በእጆቼ ፊትሽን መዳሰሱ ቀረ፤
የኖርኩለት ፍቅር
ገሎኝ እንደጠላት ከእኔ እጅጉን ራቀ፤
ናፍቆትሽን ብቻ ልቤን እያስታጠቀ።
አንቺን ያጣሁኝ ለት.........
ፍቅር እንደራበኝ፣
ትዝታሽን ብቻ ሁሌ እየኖርኩኝ፣
ካዋልሽኝ ደጃፎች፣
ካለፉት ግዜያቶች፣
ሲከፋኝ በእነሡ አይኖቼን እያበስኩ፤
ዛሬም ድረስ አለሁ አንችኑ እንዳሰብኩ።
የኔ ላትሆኝ እንዲያው ላልመልስሽ፤
ይቀለኛል ላይኔ ከመንደርሽ ሔጄ
አንዴ እንኳንም ባይሽ።
አንቺን ያጣሁኝ ቀን.........
የተለየሽኝ ለት፦
ጨረቃ ጠዋቱን፣
ፀሀይ ሌሊት ወጣች፤
ተፈጥሮ እንኳ ሳትቀር
ሚዛኗን ነው የሳተች።
✍habeshiyu✍[BILAL]
ቻናላችንን join & share ያድርጉ
👇👇👇
@ibnu_mesud
BY ትዝታ
Share with your friend now:
tg-me.com/Tzta_lay/3586