በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ ባሻገር ለልማት ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ እየተሰጠ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ

ግንቦት 30/2016 (አዲስ ዋልታ) በሶማሌ ክልል የአመራር አንድነትን በማምጣት ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ ባሻገር ለልማት ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የሶማሌ ክልል ለረጅም ጊዜ በነበረው የሰላም እጦት ሳቢያ ክልሉ ከልማት ስራዎች ወደ ኋላ መቅረቱን አንስተዋል።

የሶማሌ ክልል ህዝብ ሰላም ወዳድ ነው ያሉት ርዕሠ መስተዳድሩ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለሰላም ዘብ በመቆም በተግባር አረጋግጧል ብለዋል።

ላለፉት ስድስት ዓመታት በክልሉ በተረጋገጠው ሰላም በሁሉም መስክ ከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል። በክልሉ ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል እና ጠንካራ የአመራር አንድነት መገንባቱንም ተናግረዋል።

ይህም የህዝብን አንድነት በማጠናከር ዘላቂ ሠላም እንዲረጋገጥና የህዝቡን ጥያቄ በተጨባጭ መመለስ ያስቻሉ የልማት ስራዎች እንዲከናወኑ አስችሏል ብለዋል።
875 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ተመለሱ

ሰኔ 1/2016 (አዲስ ዋልታ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 875 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 18 ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሰኔ 2/2016 (አዲስ ዋልታ) “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነት ክብር” በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች እየተካሄዱ ነው፡፡

ውይይቱ ላይ የፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡

የውይይት መድረኮቹም በሸገር ከተማ፣ በጋምቤላ፣ በድሬዳዋ፣ ቢሾፍቱ፣ ደብረብርሃን እና ቦንጋ እንዲሁም ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው፡፡
ኢትዮጵያ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት 5ኛ ሆነች

ሰኔ 2/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት መካከል በአምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ገለጸ።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት መካከል አምስተኛ ደረጃን የያዘችው በሀገር ውስጥ ጠቅላላ ገቢዋ (GDP) 205 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በማስመዝገብ ነው፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አምስተኛ ከዓለም ደግሞ በ57ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

እንደ የዓለም የገንዘብ ድርጅት መረጃ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ እና አልጄሪያ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በቄለም ወለጋ ዞን 367 ሺሕ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዷል - የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት

ሰኔ 2/2016 (አዲስ ዋልታ) በቄለም ወለጋ ዞን በቀጣይ ክረምት ወራት ብቻ 367 ሺሕ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት መታቀዱን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሙልዓታ ዋቅጅራ እንደተናገሩት በዚህ ክረምት ከሚለማው 367 ሺሕ ሄክታር መሬት ውስጥ 288 ሺሕ ሄክታር መሬት በክላስተር ይለማል።

እስከ አሁን በተሰራ ስራም 353 ሺሕ ሄክታር መሬት የታረሰ መሆኑንና 11.8 ሚሊየን ኩንታል ምርት በዞኑ ከሚከወነው አጠቃላይ ልማት የሚጠበቅ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም በስፋት በዞኑ የሚለማው የበቆሎ ምርትም 50.6 ሺሕ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ መሆኑ ገልጸው ከዚህም 2.6 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ የተመራ ልዑክ በዞኑ ሰዲ ጫንቃ ወረዳ እየለማ የሚገኘውን የበቆሎ ምርትም ጎብኝቷል።

የወረዳው አስተዳዳሪ ዑመር አደም በወረዳው 31 ሺሕ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብል የሚለማ መሆኑን አንስተው 19 ሺሕ ሄክታር መሬት የሚሆነው በክላስተር የሚለማ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህም ውስጥ 4 ሺሕ 500 የሚሆነው ሄክታር መሬት በበቆሎ ምርት የሚለማ መሆኑንም ኃላፊው አንስተዋል።
በወረዳው ከበቆሎ ምርት ባሻገር የስንዴ፣ ሩዝ፣ ሰሊጥና ትኩረት የሚሰጣቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ገመቹ ጉርሜሳ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የቄለም ወለጋ ዞን በፀጥታ ችግር ሲፈተን መቆየቱን አንስተው በዚህም በርካታ የዞኑ ወረዳዎች ጉዳት አስተናግደው ቆይተዋል ነው ያሉት።

ይሁንና ባለፉት ሶስት ዓመታት ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተደራጅተው በመስራታቸው አሁን ላይ ሰላም መስፈኑን ተናግረዋል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ሲጎበኙ - በፎቶ
2024/06/11 00:32:53
Back to Top
HTML Embed Code: