tg-me.com/bestletters/5972
Last Update:
ዳንሰኛው ወንድሜ ከተሰኘው ድርሰት የተወሰደ...
<<ትምህርት ብዙም ያልተጀመረበት ጊዜ ነበር...አስተማሪዎቹ ስላልመጡ ተጋድሜ ፊልም ሳይ ቆይቼ የእራት ሰዓት በመድረሱ ከጓደኛዬ ጋር ወደ መመገቢያ አዳራሽ በተለመደው መንገድ ሄድን...መንገድ ላይ ግን ያልተለመደ ውበት ተመለከትኩ...
...ብዙ ጊዜ ቆንጆ ሴቶችን ተመልክቼ፤አፍ አውጥቼ ባልናገረውም በልቤ አድንቄያለሁ...ያንቺ ውበት ግን ያፈዝ ነበር...እነኚያ የሚያስፈሩ አይኖችን ጣል ስታደርጊብኝ፤የልቤን ባዶነት የመረመሩ መስሎኝ ተሳቀቅኹ...ውበትሽ ልክ ፀሐይ ምድርን ልትሰናበት ስትቀርብ እንደምታሳየው ያለ ነው...ከፍ ብሎ ተቀምጦ መላ ተፈጥሮን እንደማድነቅ ያለ...ከሚወዱት ሰው ጎን ቆሞ የፏፏቴን ውብ ዝማሬ እንደመስማት ያለ የሚደንቅ ውበት...ፍቅር መስፈርት ባይኖረውም መስፈርት ብዬ ልደረድራቸው የምችለውን ሁሉ እንደምታሟይ እርግጠኛ ነኝ።
ያቺ የተያየንባት ሴኮንድ ምናልባትም ደቂቃ...አህምሮዬ እና ልቤ እየተቀባበሉ ደጋግመው ሲያሳዮኝ ትውውቃችን ዘለግ ያለ ጊዜን ያስቆጠረ ይመስል ነበር...ጥቂት ጊዜ ግን ጥልቅ ስሜት...አልተናገረውም እንጂ ሁኔታዬ ጓደኛዬን ሳያስገርመው አልቀረም...እንደተለመደው አላወራውም...ደስታው ብዙም ሊያስበላኝ አልቻለም...ተስፋው የተቀጠለለት ሰው ይመስል ፊቴ ፍክት ፍክክት አለ።
...ወደ ዶርም እንደተመለስን አልጋው ላይ በጀርባዬ ለጥ አልኩና ከሃሳብ ማጠራቀሚያ የአህምሮዬ ክፍል ውስጥ ምስልሽን ምዥርጥ አድርጌ፤ሁኔታሽን አጤን ጀመር...አጭሯን ቅፅበት ደግሜ ደጋግሜ አየሁ።
ድንገት ከመኝታዬ ፈንጠር ብዬ ተነሳሁና በለስ ሲቀናኝ የምደንሳትን ዳንስ ደነስኹ ያኔ ዶርም ውስጥ ያሉት ሁሉ ደስ እንዳለኝ ገባቸው...>>
BY 📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/bestletters/5972