tg-me.com/bestletters/5981
Last Update:
"ትንሳኤከ ለእለአመነ
ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ..."
የሚል መዝሙር ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በስሱ ይሰማኛል...ክርስቲያኖች ዳግማዊ ትንሣኤ የሚያከብሩበት ሰንበት ነው...መዝሙሩን ስሰማ ባር ባር አለኝ ቤተስኪያን የማልቀርበት ልጅነቴ ታወሰኝ...አፌን የፈታውበት የአምላኬ ስም ናፈቀኝ...ወይ ከአለም ወይ ከፈጣሪ አለመኾኔ አሳሰበኝ...ሐዘንና የልብ ስብራት በፀፀት ገላ ተወጣጥሮ የተመለኽትኹት መሠለኝ...ጠቆር ያለውን ማኪያቶዬን ጎንጨት አልኹና ላነበው በእጄ የያዝኹትን መፅሐፍ ጠረቤዛው ላይ ጣል አደረግኹት።ጭንቅላቴን ግርግዳው ላይ ለአፍታ አስደገፍኹት...ወደ አዕምሮዬ የመጣውን የሐዘን ስሜት ላስተናግደው ሽቻለኹ...ፀፀቴን ኹሉ በእንባ አፍስሼ ከእኔ ባርቅ ምንኛ በወደድኹ...ዳሩ ልቤ ፀፀት ትቷል፤በደል ውስጥ በጨለማ ተውጦ እንኳን የተሳሳተ ነገር ላይ እንዳለ አይሰማውም።የትክክል እና የስህተት ሚዛኑ ተሠብሮበታል።መመዘን ትቷል።መፀፀት ትቷል።
...ማዘኑን ትቼ ማኪያቶውን እየተጎነጨው ስለ ቀኑ ማሰላሰል ዠመርኹ...ዳግም ትንሳኤ እንዴት ያለ ነገር ነው? ስል አሰብኹ...ልጅ እያለው ጌታ ዳግም የተነሳበት ቀን ይመስለኝ ነበር አድጌ ፂም ካበቀልኩ በኋላ ነው ኃዋርያቱ ከስቅለቱ በኋላ በዝግ ቤት ተደብቀውና በፍርሃት ተሸሽገው ሳሉ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሏቸው ሰላም ቢሰማቸው "ዳግም ትንሳኤ" ኾነ ማለታቸው እደሆነ የተረዳሁት።
ቀኑን አሳክኬ ጥያቄዬን አቀረብኩ በዚህ ማደግ በሚሉት በቆሸሸ እና በተጨማለቀ ስብዕና ውስጥ ተሸሽጎ ያለውን ልጅነቴን "ሰላም ለአንተ ይሁን" ብለህ ሰላሙን ሰጠው... እንደ አልዓዛር ከሞት ጥራኝ... ውብ በሚመስል በብልጭልጭ ጨርቅ የተገነዘውን ሙት ገላዬን ይዤ አለም ከሚሉት መቃብር አቤት ብዬ ልምጣ...ፈጣሪን ተማጠንኹ... ቤተክርስትያን ሄጄ ከፀለይኹ ቆየሁ...
.... ድንገት ልብ የገዛኹኝ እደው ባለሁበት ኹኔታና ቦታ እንዳለኹ ፀሎቴን አደርሳሁ ...ምንአልባት አንዳንዴ ፀሎት ማደርሰው በሀጥያት መሀል እያለኹም ሊኾን ይችላል።
ማኪያቶ ጎንጨት አልሁና መፅሀፌን አነሳው''የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ'' ይላል ገልጬ ካቆምኹበት ማንበብ ቀጠልኹ
"ምንም እንኳን ብንለያይ ''ቻው'' ብንባባልም፤መንገዳችን መልሶ ባይገጥም...ፈፅመሽ እንደማትረሺኝ አምናለኹ...ከስጋሽ አልፎ ከነብስሽ ጋር የተዋሀድን እስኪመስል ተቀራርበናል... ስንለያይ የሆነ አካሌ ካንቺ ጋር አብሮ እንደሚሄድ አምናለኹ...ቃል ሳንተነፍስ የተግባባንባቸውን ንግግሮቻችን እደማትዘነጊው አምናለኹ...ማንም ገብቶ በማያቀው ልብሽ ውስጥ የልቤ ዳና እንደማይጠፋ አምናለኹ...
ሄጃለኹ ባልሽኝ ስፍራ በልብሽ ይዘሺኝ እንደምትሄጂ አምናለኹ።"
የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
20/08/2015
#repost
©ሶፊ
BY 📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/bestletters/5981