Telegram Group Search
የምጥ ህመም ማስታገሽያ

ብዙ አይነት የምጥ ህመም ማስታገሽያዎች አሉ ሆኖም ግን በአይነቱ ለየት ያለና ዉጤታማ የሆነዉ የኢፒዱራል የምጥ ህመም ማስታገሽያ (epidural labour analgesia) ምንድን ነዉ?

የኢፒዱራል የምጥ ህመም ማስታገሽያ በጀርባ አጥንቶች መካከል በኢፒዱራል ክፍተት ዉስጥ በሚቀበር ረቂቅ በሆነ ትቦ አድርጎ የሚሰጥ የማስታገሽያ አይነት ነዉ።

በምጥ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ከአንገት በታች ለሆኑ ህመሞች እንደ ማስታገሽያነት ያገለግላል ። በተጨማሪም ታካሚው ሳይተኛ እንደ ከፊል አንስቴዢያነት ያገለግላል።

🔵 ጥቅሞች

- በምጥ ጊዜ ና ከምጥ በኋላ ያሉ ህመሞችን ያስታግሳል

- በእንግዴ-ልጅ ወደ ፅንሱ የሚደርሰዉን የደም ዝዉዉር ያሻሽላል።

- ከወሊድ በኋላ የሚመጡ ድብርተኝነት ይቀንሳል።

- በምጥ ህመም ምክንያት የሚመጡ የሱዉነት ጫናዎችን ይቀንሳል። ለምሳሌ በልብ፣ በጨጓራ፣በሳንባ ላይ የሚመጡትን ጫናዎች ይቀንሳል።

🟣በምን አይነት ታካሚዎች ላይ እንጠቀም?

- ለሁሉም ምጥ ላይ ላሉ እናቶች?
- በቀላሉ ደም የመፍሰስ ችግር የሌለባቸው
- የጀርባ ወይም የመቀመጫ ቁስል የሌላቸዉ
- የአዕምሮ እጢ ወይም ከፍተኛ የሆነ የአዕምሮ ዉስጥ ግፊት የሌላቸዉ መሆን አለባቸዉ።

- ሆኖም ግን በሀገሪቱዋ ዉስጥ ባለው እጥረት ምክንያት በመንግስት ሆስፒታሎች በተወሰኑ የልብ ወይም ሌላ ተጓዳኝ በሽታ ላላቸዉ እናቶች ይሰጣል።

⚫️የጎንዮሽ ጉዳቶች?

- ጥቂትና በቀላሉ የሚታከሙ የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት። እነሱም
- የደም ግፊት የማዉረድ
- የማሳከክ
- የራስ ምታት- ጋደም በማለትና ፈሳሽ በመዉሰድ ማስታገስ ይቻላል።
- የጀርባ ህመም- እረፍት በመዉሰድ ና ከባሰም በአፍ በሚወሰዱ ማስታገሻዎች ይጠፋል።

⚪️የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች

- የሀኪም ምርመራ
- አንዳንዴም የደም ምረመራ ሊያስፈልግ ይችላል።
- ከሀኪሙ ጋር ከተወያዩ በኋላ የስምምነት ፍርሚያ ያስፈልጋል።
- ምግብም ሆነ ፈሳሽ አይከለክልም።

🟤 ኢፒዱራል የማስገባቱ ሂደት እንዴት ይመስላል?

- መጀመሪያ ታካሚዉ/ነፍሰጡር በጎን ማስተኛት ወይም አጎንብሰው አንዲቀመጡ ማድረግ።

- የደም ግፊት መለኪያ ና የፅንሱን መቆጣጠርያ መሳሪያዎች ማድረግ።

- በመቀጠልም ጀርባቸውን በአልኮል ወይም ተመሳሳይ በሆነ አንቲሴፕቲክ ማጠብ።

- የሚቀባ ወይም አነስና አጠር ባለች መርፌ የሚሰጥ ማደንዘዣ በጀርባ መስጠት። በሂደቱ ላይ ያለን ህመም ይቀንሳሉ።

- ቀጥሎም ወደ አፒዱራል ክፍተት የሚገባዉን መርፌ ማሳለፍ።

- በመርፌ ዉስጥ የሚያልፈዉን ረቂቅ ትቦ ማስገባት ና መርፌውን ማዉጣት።

- በመጨረሻም በፕላስተር ቦታ አስይዞ ማጣበቅ።

- አንስቴዝዬሎጂስቱም ያዘጋጀዉን የአንስቴዝያ መድሀኒት በመመጠን በትቦዉ አድርጎ ይሰጣል። ከጎንም በመሆን የደም ግፊትና የፅንሱን ሁኔታ ይከታተላል።

- ባስፈለገ ልክ በየስዓቱ ወይም ከዚያ በታች በሆነ ጊዜ መድሀኒቱን ይሰጣል።

- ፅንሱ ከተወለደ ከተወሰነ ስዓት ወይም አንድ ቀን በኋላም ትቦዉን ማዉጣት ይቻላል።

ዶ/ር ይስሐቅ አብርሃም ፥ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንስቴዝዬሎጂ ስፔሻሊስት


@HakimEthio
Stay updated with the official Lancet General Hospital Telegram group: Access the latest updates on our specialists' schedules, new medical services, and offerings as well as advancements in the medical field.
Have your health related questions answered directly by our team of experienced professionals. https://www.tg-me.com/lancethealthplc

Lancet General hospital - Hub of Subspecialists

📍Megenagna, Afarensis Bldg
☎️9171/0977717171

Get in touch:
Telegram | Facebook | Instagram | TikTok | Website |
የመገጣጠሚያ እብጠት (Ganglion Cyst) ምንድነው?

Ganglion Cyst በመገጣጠሚያ ወይም በጅማት ሽፋን ላይ በፈሳሽ የተሞላ እብጠት ሲሆን ይህ ዕብጠት ጥቅጥቅ ካሉ ተያያዥ ቲሹዎች፤ ከጅማት ሽፋኖች፣ ከራሳቸው ከጅማቶች፣ እንዲሁም ከመገጣጠሚያ ሽፋኖች፣ መነሻቸውን አድርገው ይከሰታሉ ተብሎ ይታሰባል።

ይህ እብጠት እነማን ላይ ሊከሰት ይችላል?

Ganglion cysts በጣም ከተለመዱ የእጅ ላይ ቲሹ ዕጢዎች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀስ ሲሆን ይህ ዕብጠት በሁሉም ዕድሜዎች ሊከሰት የሚችል ቢሆንም በዋነኝነት ግን እድሜያቸው ከ 20-40 ዓመት የሆኑት 70% ያህል ተጋላጭ መሆናቸውን አንዲሁም በጾታዊ ክፍፍል ሲታይ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ይበልጥኑ ተጋላጭ መሆናችውን ጥናቶች ያመለክታሉ።

ይህ ችግር እድሜያቸው ከ 10 አመት በታች የሆኑ ህፃናት ላይ በብዛት ላይስተዋል ይችላል።

የመገጣጠሚያ እብጠት (Ganglion Cyst) በብዛት የት ይከሰታል?

ይህ ዕብጠት ብዙውን ጊዜ በእጃችን አንጓ መገጣጠሚያ ጀርባኛው ክፍል ላይ የሚከሰት ሲሆን አንዳንዴም በእጃችን አንጓ መዳፍ ላይም ሊታዩ ይችላሉ።

በእጃችን የጀርባ አንጓ ዕብጠቱን በደንብ ለማስተዋል, የእጃችን አንጓን ወደ ፊት በማጠፍ በይበልጥ በደንብ ለማየት ይረዳል።

ይህ እብጠት በተለምዶ የእጅ መገጣጠሚያ ላይ ይስተዋል እንጂ ባልተለመደ መልኩ የታችኛው የጣቶቻችን ክፍል ላይ ፤የጣቶቻችን ጫፍ ላይ ፤ጉልበት እና ቁርጭምጭሚት አካባቢ እንዲሁም የታችኛው የእግራችን አናት ላይ ሊታዩ ይችላሉ።

Ganglion Cyst መንሳኤው ምንድነው?

መንስኤው ብዙውን ጊዜ ባይታውቅም በተደረጉ ጥናቶች መሰረት መገጣጥሚያ ላይ በሚፈጠር ተደጋጋሚ ጫና ፈሳሽ አመንጭ ሕዋሳት (Mucin Cells) ምርታችውን አንዲጭምር በማድረግ ፈሳሽ ወደ ውጭኝው የሽፋን ክፍል በመሄድ አንዲከማች ሆኖ ለስላሳ፣ ክብ፣ የሚንቀሳቀስ እብጠት ሆኖ በመገጣጠሚያ (በተለይ የእጅ የጀርባ አንጓ) ይቀመጠል።

Ganglion Cyst ለመሆኑ ምልክቶቹ ምንድናችው?

፦ ለመዳሰስ በምንሞክርበት ወቅት ጠንካራ፣ ለስላሳ፣ ክብ፣ የሆነ እብጠት በመገጣጠሚያ (በተለይ የእጅ አንጓ) ልናስተውል እንችላለን።

፦ ብዙውን ጊዜ የህመም ስሜት ባይኖረውም አልፎ አልፎ፣ እብጠቱ የነርቭ መጨናን ካመጣ ህመምን ከማስከተል ባሻገር እዛ አካባቢ ሲነኩ ስሜት ከማጣት sensory loss እስከ ጣቶችን ማንቀሳቀስ አለመቻል ድረስ ሊደርስ ይችላል።

፦ የእብጠቱም መጠን በጊዜ ሂደት መለዋወጥ የመሳሰሉት በዋነኝነት ከምልክቶቹ ውስጥ ይካተታሉ።

Ganglion Cyst ህክምናው ምንድነው?

1) Conservative Management

ከእብጠቱ በቀር ምንም አይነት የህመም ምልክት ማይታይ ከሆነ ህክምና ሳያስፈልገው በራሱ የመጥፋት እድሉ 50% ሲሆን እስከ አንድ አመት ጊዜም ሊወስድ ይችላል።

2) Temporarily Brace (የመገጥጠሚያ ድጋፍ)

እብጠቱ ያለበት ቦታ ላይ የሚደረግ የመገጥጠሚያ ድጋፍ (Temporarily Brace) ለረጅም ጊዜ ይህንን መጠቀም የጡንችዎች መቀጭጭ የመገጠጥሚያ በቋሚነት አለመንቀሳቀስ ሊያመጥ ስለሚችል ብዙ ጊዜ አይመከርም

3) Ganglion Cyst Aspiration (የእብጠቱን ፈሳሽ ቀድቶ ማውጥት)

እብጠቱ ላይ ያለውን ፈሳሽ ቀድቶ ማውጥት (Ganglion Cyst Aspiration) ሌላው አማራጭ ሲሆን ከዚህ ህክምና በሑላ በእንድ አመት ውስጥ ተመልሶ የመምጥት እድሉ ከፍተኝ ነው

4) Ganglion cyst Excision (በቀዶ ጥገና እብጥቱን ቆርጥ ማውጥት)

በቀዶ ጥገና እብጥቱን ቆርጥ ማውጥት (Ganglion cyst Excision) ይህ የመጨረሽው እማራጭ ሲሆን ሙሉ ተቆርጥ መውጥቱን እርግጥኝ መሆን ይኖርብናል። ይህም ተመልሶ የመምጣት እድልን እንዲቀንስ ይረዳል።

References
© 2024 UpToDate, Inc.
Schwartz's Principles of Surgery

ሰናይ ምሽት ይሁንላችሁ
Dr. Ephream Adane


@HakimEthio
"አንድ ሃኪም ያለ ምንም እንቅልፍ ለሊቱን ሙሉ ሲሰራ አድሮ ስንት ብር የሚከፈለው ይመስላችኋል?🤔 እውነታውን ማህበረሰባችን ይወቅና ሀሳብ ይስጥበት።" - Dr. Musa Ibrahim

@HakimEthio
Congratulations

@HakimEthio
«ማዳን የእግዚአብሔር ነው ፤ ግን ህማሜን ስላስታገሰልኝ መድሐኒአለም ስቃይና እንግልት የሌለባትን ገነት ያውርሰው»።

ዛሬ ከአውቶቡስ ተራ ወደ አየር ጤና እየሄድኩ ሳለ የታክሲ ሒሳብ ለመክፈል እጄን ወደ ኪሴ ሳስገባ «ተከፍሏል» የሚል ድምፅ ከረዳቱ ተነገረኝ። ዞር ዞር ብል የማውቀው ሰው አጣሁኝና ጎንበስ ስል «እንደምን አለህ ዶክተር?» ብለው አንድ ትልቅ ሰውየ ኮፍያቸውን አውልቀው ሰላም አሉኝ ።

ሳያቸው ደነገጥኩኝ። ጅማ ሳለሁ አቃቸዋለሁኝ። በጣም በፅኑ የታመመ ወንድም ስለነበራቸውና ታካሚውን የምከታተለው ኢንተርን ሀኪም እኔ ስለነበርኩኝ በቶሎ አስታወስኳቸው።

ወንድማቸውን ለሳምንት ከተከታተልኩት በኋላ ዋርድ ቀየርኩኝ። ቢሆንም ግን አንዳንዴ እየሄድኩኝ አጠይቀው ነበር። ወንድማቸው ከ2 ሳምንት ቆይታ በኋላ ከዚህች አለም አለም ድካም አረፈ። ማረፉንም ካለሁበት ዋርድ ድረስ መጥተው ከነገሩኝ በኋላ አመስግነውኝና እጄን ስመውኝ በእንባ ተለያየን።

ይህ ከሆነ አመት አልፎታል። ዛሬ ግን ሰውየውን ሳያቸው ደነገጥኩኝ ያኔ የወንድማቸውን አስክሬን ታቅፈው እንኳ የለገሱኝ ፍቅርና ምስጋናና ምርቃት ታወሰኝ። ያ በእንባ የተለወሰ ስስ ፈገግታ ትዝ አለኝ።

«ዶክተር እዚህ ምን ትሰራለህ? »
ያለሁበትን ሁኔታ ስንጨዋወት እርሳቸው የታመመ ዘመድ ጥየቃ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መጥተው እየተመለሱ እንደሆነ ነገሩኝ።

«ልጄ ወንድሜ ያኔ ከተወጠረውና ካበጠው ሆዱ ፈሳሽ አውጥተህ ህመሙን ስታስታግስለት ምን እንዳለኝ ታቃለህ?»

«ምን አለዎት? » አልኳቸው እንባም ጉጉትም እየተጠናወቱኝ።

«ማዳን የእግዚአብሔር ነው ፤ ግን ህማሜን ስላስታገሰልኝ መድሐኒአለም ስቃይና እንግልት የሌለባትን ገነት ያውርሰው አለኝና ከታመመ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ አለ። ሁሌም ወደ አጠገባችን መጥተህ ሰላም ስትለንና ስታየው ፈገግ ይል ነበር።» እርሳቸውም ፈገግ አሉ።

እኔም ደስ አለኝ በእኔ በታናሹ ብላቴና አንድ ሰው እንደዚህ በ1 peritoneal tab ለደቂቃዎች እንኳ ትንሽ ህመመን ለደቂቃዎች ቢሆንም እንኳን የማስታገስ ስልጣን ፈጣሪየ ስለሰጠኝ እያመሰገንኩኝ እንዲሁም ከሀገሪቱ የኑሮ ሁኔታና የኑሮ ውድነት ጋር እርካታየን እያመዛዘንኩኝ እያለ ድንገት አውቶቡሱ መሀል ፌርማታ ላይ ቆመ። እዚሁ ነው የምወርደው ልጄ ፈጣሪየ ዘርህን ሁሉ ይባርክ አሉኝና የተሸበለለች 50 ብር ሠጥተውኝ እጄን ሳሙኝና እየሮጡ ወረዱ። ለማናገር እንኳን ጊዜ ሳይሰጡኝ ከአውቶቡሱ ወረዱ።

ማገዝ ሲገባኝ ብር መቀበሌ መጥፎ እንደሆነ ቢገባኝም ብሩን መመለስ አሊያ ደግሞ እርሳቸውን ጠርቶ ስለሁኔታው ማስረዳት ስሜታቸውን የሚጎዳ ስለመሰለኝ በመስኮት እጄን አስወጥቼ ተሰናበትኳቸው።

እውነታቸውን እኮ ነው ግን 😍😍 እኛ ከፈጣሪ የሰጠን መክሊት አለን፣ አንዴ የተቀባነው ካላረከስነው የማይረክስ ካልጣልነው የማይሰበር፣ ካሰርነው የማይበተን ሙያ አለን። በደሞዝ ማነስ የማይኮስስ፣ በማንቋሸሽ የማይቆሽሽ፣ መንግስት ቢዘነጋው ፣ ሰፊው ህዝብ የሚያስታውሰው ሙያ የተሸከምን፣ የጤና ባለሞያዎች ነን።

ዶ/ር አሰፋ ዓለሙ: ጠቅላላ ሀኪም

@HakimEthio
የሽንት ጠጠር (Urolithiasis) ምንድነው? | Cirrachi fincaanii maal?

👉ኩላሊት፣ የኩላሊት ቱቦ፣ ፊኛ፣ ወይም የሽንት ቱቦ ዉስጥ የሚፈጠር ጠጠር

✍️የሽንት ጠጠር ሽንት ውስጥ ካሉ ንጥረ ነገሮች የሚመጣ ጠጣር ነዉ። ሽንት ከሰዉነት የሚወጡ ብዙ አይነት ንጥረ ነገሮች አሉት። ሶድዬም(Sodium (Na))፣ ፖታሲዬም (Potassium(K))፣ ካልሲዬም (Calcium(Ca))፣ ኦግዛሌት (Oxalate)፣ ፎስፌት (Phosphate)፣ ማግኒዬዢም (Magnesium) ወ.ዘ.ተ ናቸዉ።

👉የሽንት ጠጠር ከነዝህ ብዙ አይነት ንጥረ ነገሮች እንደመፈጠሩ ብዙ አይነት የሽንት ጠጠሮች አሉ። በግርድፉ ካልሲዬም ያላቸዉና ካልሲዬም የለላቸዉ በማለት መክፈል ይቻላል።

1.ካልሲዬም ያላቸዉ እነ ካልሲዬም ኦግዛሌት(60%)፣ ሃይድሮክሲ አፓታይት(20%)ና ብሩሻይት(2%) ጠጠሮችን ያካትታል።

2.ካልሲዬም የለላቸዉ:- ዩሪክ አሰድ ጠጠር(7%)፣ እስትሩቫይት ጠጠር(7%)፣ ሲስቲን ጠጠር(1-3%) ወ.ዘ.ተ. ናቸዉ።
......ይቀጥላል
ዶ/ር ሚካኤል አብዲሳ
የኩላሊት፣ ሽንት ቱቦ፣ ፕሮስቴትና የወንድ ስነ-ተዋልዶ እስፔሻልስት

👉Cirracha kalee, Ujummoo kalee, Afuuffee fi Ujummoo fincaanii keessaatti ummaamudha

✍️Cirrachi Fincaanii elementoota fincaani keessa jiran irraa jajjaboo dhufudha. Fincaani elementoota qaama keessaa ba'an baayyee of keessaa qaba. Soodiyeemii, Potasiyeemii, kaalsiyeemii, ogzaaleetii, foosfeetii, magniziyeemii fi kan biroo hedduu qaba.

👉Kanumaaf cirrachi fincaaniis gosa adda addaa ta'e. Elementoota kana irratti hundaa'uun bakka gurguddaa lamatti qooduunis ni danda'ama.

1.Cirracha kaalsiyeemii qabu:- Kan akka kaalsiyeemi ogzaaleetii (60%), Haayidirooksii apatayiti (20%)fi Birushayitii (2%) dha.

2.Cirracha kalsiyeemii hin qabne:- Cirracha yuurik asiidii (7%), cirracha istiruvaayitii (7%), cirracha siistiinii (1-3%) fi k.k.f.dha.
Itti Fufa.......

Dr. Mikaa'eel Abdiisaa (Ispeeshalistii kalee, Ujummoo fincaanii, Pirosteetiifi sirna wal hormaata Dhiiraa)

@HakimEthio
2024/05/29 05:54:51
Back to Top
HTML Embed Code: