Telegram Group Search
TIKVAH-ETHIOPIA
#Malawi ዛሬ የማላዊውን ምክትል ፕሬዝዳንት ሳውለስ ቺሊማን እና ሌሎች 9 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ተሰውሯል። እንደ አገሪቱ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ አውሮፕላኑ የማላዊ መከላከያ ኃይል ንብረት ነው። ጥዋት ከሀገሪቱ ዋናው ከተማ ሊሎንዌ ከተነሳ በኋላ " ከራዳር ዕይታ ውጪ " ሆኗል። ምን ውስጥ ይግባ አይታወቅም። የአገሪቱ የአቪዬሽን ባለሥልጣናት ከአውሮፕላኑ ጋር ግንኙነት ለማድረግ…
#Malawi

የማላዊ ምክትል ፕሬዜዳንት ሳውለስ ቺሊማን እና ሌሎች ባለስልጣናትን ይዞ ከራዳር እይታ ውጭ የሆነውን እና የገባበት ያልታወቀውን አውሮፕላን ፍለጋ እየተካሄደ ነው።

ፍለጋው እየተካሄደ ያለው በመከላከያ ወታደሮች ፣  በፖሊስ አባላት እንዲሁም በሌሎች ሲቪል ዜጎች እንደሆነ ተነግሯል።

የሀገሪቱ መንግስት #ያሰማራው_ኃይል እንዲህ አይነቱን ፍለጋ ለማድረግ አቅም ስለሌለው እና ምንም ማድረግ ስለማይችል ልክ እንደ ማንኛውም ሲቪል እየተንቀሳቀሰ ነው እየፈለገ ያለው።

ምናልባትም " አውሮፕላኑ ወድቆ ይሆናል " ተብሎ በታሰበበት ጫካ ውስጥ ፍለጋ በእግር እና በመኪና እየተካሄደ እንደሚገኝ ነው የተሰማው።

በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ም/ፕሬዜዳንቱ እና አብረዋቸው ያሉት ሰዎች " ጥሩ ነገር አልገጠማቸውም " የሚል ስጋታቸውን እያጋሩ ነው።

ም/ፕሬዜዳንቱ አብረዋቸው በርካታ የፓርቲያቸው ባለሥልጣናት ነበሩ።

የሀገሪቱ መንግሥት ለእንደዚህ አይነት አደጋ ወቅት የሚሆን ዝግጁነትና ለፍለጋ የሚሆኑ መሳሪያዎችን እንኳን አላሟልም በሚል እየተተቸ ነው።

አውሮፕላኑም ከተሰወረ ከረጅም ሰዓታት በኃላ ነው ለህዝቡ ያሳወቀው።

በቅርቡ ፥ የኢራን ፕሬዝዳንት የነበሩት ኢብራሂም ራኢሲ እና ሌሎች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በስራ ጉዳይ ሲጓዙበት የነበረ ሄሊኮፕተር ጫካ ውስጥ ተከስክሶ ሁሉም መሞታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Malawi የማላዊ ምክትል ፕሬዜዳንት ሳውለስ ቺሊማን እና ሌሎች ባለስልጣናትን ይዞ ከራዳር እይታ ውጭ የሆነውን እና የገባበት ያልታወቀውን አውሮፕላን ፍለጋ እየተካሄደ ነው። ፍለጋው እየተካሄደ ያለው በመከላከያ ወታደሮች ፣  በፖሊስ አባላት እንዲሁም በሌሎች ሲቪል ዜጎች እንደሆነ ተነግሯል። የሀገሪቱ መንግስት #ያሰማራው_ኃይል እንዲህ አይነቱን ፍለጋ ለማድረግ አቅም ስለሌለው እና ምንም ማድረግ ስለማይችል…
" ፓይለቱ ወደ ኃላ እንዲመለስ ተነግሮት ነበር ፤ ከዛ በኃላ ግን አውሮፕላኑ የት እንደገባ አልታወቀም " - የማላዊ ፕሬዜዳንት

የተሰወረው የማላዊ አውሮፕላን አልተገኘም።

በአውሮፕላኑ ውስጥ ከም/ፕሬዜዳንቱ ጋር የቀድሞው ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ ባለቤት / የቀድሞ ቀዳማዊ እመቤት ሻኒል ዲዚምቢሪ እንደሚገኙበት ተነግሯል።

አንዳንድ ሚዲያዎች እና የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ " በጣም ድቅድቅ ጨለማ ሆኗል " በሚል " በቃ ነገ ጥዋት ይቀጥላል ተብሎ " ፍለጋው እንደቆመ ተናግረዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ለሊቱን በሰጡት መግለጫ " ይሄ ውሸት ነው ምንም የቆመ ፍለጋ የለም ፤ የመከላከያ ወታደሮች በስፍራው ላይ ፍለጋ ላይ ናቸው " ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ ፕሬዝዳንቱ ለፍለጋው ጎረቤት ሀገራትን እና የአጋር ሀገራት አሜሪካ ፣ ኖርዌይ ፣ እስራኤል ፣ ዩናይትድ ኪንግደም መንግሥታትን " አፏልጉኝ " ሲሉ እገዛ እንደጠየቁ አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ አውሮፕላኑ ከዋና ከተማ ሊሎንግዌ ተነስቶ ወደ መዳረሻው መዙዙ ከተማ ሲጓዝ እንደነበር ገልጸዋል።

ነገር ግን ፓይለቱ በመጥፎ የአየር ሁኔታ የተነሳ ለእይታ ምቹ ሁኔታ ስላልነበር አውሮፕላኑን ማሳፈር እንዳልቻለ ፤ በኃላም የአቪዬሽን ሰዎች ወደ ኃላ (ሊሎንግዌ) እንዲመለስ እንደተነገሩት ከዛ በኃላ ግን የት እንደገባ እንዳልታወቀ አስረድተዋል።

አውሮፕላኑ ምክትል ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ሰዎችን ይዞ ነበር።

#Malawi #ChilimaMissingPlane

@tikvahethiopia
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ።

የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
#ሴጅ_ማሠልጠኛ

20% ቅናሽ ከሰኔ 01-21/2016 ዓ.ም ለሁሉም ተመዝጋቢዎች።
ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principles and Practices of Accounting) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin:
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#INSA

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ያዘጋጀው የ2016 ዓ/ም “ ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ” ፕሮግራም ምዝገባ እስከ ሰኔ 10/2016 ዓ/ም ድረስ መራዘሙን አሳውቋል።

እስካሁን በርካታ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች መመዝገባቸው ተገልጿል።

ምዝገባው እስከ ሰኔ 10 ድረስ መራዘሙ ተጠቁሟል።

በሳይበር ደህንነት እና በተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

የታለንት መስኮች ፦

- Cyber Security
- Cyber Development
- Embedded Systems
- Aerospace ሲሆኑ ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ1 ወር ይሰጣል።

ተመራቂዎች ፦

° #እንደየችሎታቸው እና #እንደስራዎቻቸው ከተለያዩ ባለሀብቶች ጋር የማስተሳሰር፤

° ኢመደአን (INSA) ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተቀጥረው መስራት የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚማቻች ከተቋሙ ተሰምቷል።

የመመዝገቢያ ፖርታል ፦ https://talent.insa.gov.et

NB. እድሜ ፦ ከ11 አመት ጀምሮ ( #ኢትዮጵያውያን)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአላማጣ ከተማ የተፈጠረው ምንድን ነው ?

በአማራ ክልል በኩል እንደሆኑና የራያ አላማጣ አካባቢ አመራር እንደሆኑ የገለጹ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ አመራር ፥ " የሕወሓት ታጣቂዎች አላማጣ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ  የግድያ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው " ሲሉ ከሰዋል።

እኚሁ ስሜ አይጠቀስ ያሉ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ከሰሞኑን አንድ ወጣት በሕወሓት ታጣቂዎች በግፍ ተገሏል " ብሏል።

በታጣቂዎች የተገደለው ወጣት ስሙ ያሬድ መልካሙ እንደሚባል ፤ የመብራት ሀይል ሰራተኛም እንደነበር ፤ መብራት ለመስራት ወጥቶ ታጣቂዎች በግፍ እንደገደሉት አስረድተዋል።

ከሳምንት በፊትም " የሕወሓት ታጣቂዎች በወረወሩት ቦንብ ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱ ደግሞ ቆስለዋል " የሚል ቃል ሰጥተዋል። 

የሰሞኑን የአንድ ሰው ግድያ ተከትሎ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ለሁለት ቀናት ሰላማዊ ሰልፍ እንደወጡ የቪድዮ ማስረጃ በመላክ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አሁን ላይ የአላማጣ ከተማ ከንቲባ እንደሆኑ የገለጹት ዝናቡ ደስታ (ከትግራይ በኩል) ከሁለት ሳምንት በፊት በከተማው ጤና ጣብያ ፊት ለፊት ላይ በሚገኝ መጠጥ ቤት የቦንብ ጥቃት ተፈጽሞ የአንድ እናት ህይወት መጠፉቱን እና ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአሁን ሰዓት አላማጣን #በከንቲባነት የሚመራትን አካል በተመለከተ ውዝግቦች የሚስተዋሉ ሲሆን ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አሁን ከተማዋን በከንቲባት የሚመራት ማነው ? ሲል የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮን ጠይቋል።

ቢሮው ምላሹ፣ " እኛ የምናውቀው ከተማው በክልላችን ስር እንዳለ ነው። ስለዚህ ከዚያ ውጪ ያለው ነገር #ምኞት_ብቻ_ነው " ብሏል።

በትግራይ በኩል ያለውን ምላሽ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

በአማራና ትግራይ ክልሎች መካከል የይባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው የራያ አላማጣ አካባቢዎች ከሰላም ስምምነቱ ወዲህም ከወራት በፊት በትግራይና አማራ ሚሊሻዎች በተደጋጋሚ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Yemen

በአብዛኞቹ #ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከየመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጣ 39 ሰዎች ሞቱ።

እንደ IOM እና ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች በተገኘ መረጃ ጀልባዋ 260 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍራ የነበር።

በካባድ ነፋስ ምክንያት መገልበጧ ተጠቁሟል።

መሞታቸው ከታወቀው 39 ሰዎች ውጪ ሌሎች 150 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። እነሱን ለማግኘት ፍለጋ እየተደረገ ነው።

71 ሰዎች ከአደጋው ተርፈዋል።

የሩደም አካባቢ ባለሥልጣናት ጀልባዋ ላይ ተሳፈረው ከነበሩት 260 ስደተኞች በአብዛኞቹ #ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንደነበሩ አመልክተዋል።

#Reuters #IOMYemen #IOMspokesperson

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ክልል እና ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

ፈተናው በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች (አዲስ አበባ እንዲሁም ድሬዳዋ) ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

ፎቶ ፦ ደሴ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሕዝብ_በዓላት_እና_የበዓላት_አከባበር_ረቂቅ_አዋጅ_.pdf
#Update

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ #አጽድቋል

ረቂቅ አዋጁ የተወሰኑ ማስተካከያዎች እንደተደረጉበት ተመላክቷል።

አዋጁ በ1 ድምፀ ተቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ " አዋጅ ቁጥር 1334/2016 " ሆኖ ነው የጸደቀው።

የጸደቀው አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት ሲሆን ፤ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ህግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩ አዋጆችን አከባበር መወሰን ይችላሉ ተብሏል።

ይህ የሚመለከተው እንደ ኢሬቻ፣ ጊፋታ፣ ጨምባላላ፣ አሸንዳ ፣ ሻደይ ፣ አሸንድዬ ፣ ...ሌሎችንም ሲሆን ክልሎች በራሳቸው አዋጆችን አውጥተው አከባበሩን መወሰን እንደሚችሉ ተመላክቷል።

https://www.tg-me.com/TIKVAH ETHIOPIA/com.tikvahethiopia/87926

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ #አጽድቋል። ረቂቅ አዋጁ የተወሰኑ ማስተካከያዎች እንደተደረጉበት ተመላክቷል። አዋጁ በ1 ድምፀ ተቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ " አዋጅ ቁጥር 1334/2016 " ሆኖ ነው የጸደቀው። የጸደቀው አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት…
#Ethiopia

የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በዛሬው እለት ጸድቋል።

ስለ አዋጁ ...

➡️ በልማድ ሲከበር የቆየውን " ግንቦት 20 " ብሔራዊ በዓልነቱ #አስቀርቷል፡፡ 

➡️ የሰማዕታትን ቀን ( #የካቲት_12 ) እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ( #ህዳር_29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ #ታስበው ይውላሉ።

➡️ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ፣ የሰንደቀ አላማ ቀን ፣ የሴቶች ቀን ፣ የአፍሪካ ቀን ሌሎችም ታስበው ይውላሉ።

➡️ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ይከበራል።

➡️ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ ያለባቸው ተቋማት ዝርዝር ተቀምጧል።

በዚህም  ፦
° የውሃ
° የመብራት
° የስልክ
° ሚዲያዎች (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ)
° የጤና ተቋማት እና መድሃኒት ቤቶች
° መከላከያ
° ፖሊስ
° ደህንነት
° የእሳት አደጋ መከላከል
° የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች
° ነዳጅ ማደያዎች
° ሙዝየሞች ፣
° ፓርኮች ክፍት ሆነው ከሚውሉት ውስጥ ናቸው።

ስለ አዋጁ ምን ጥያቄ ተነሳ ?

አንድ የምክር ቤት አባል ፦

" የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ተከብረው ከሚውሉት በዓላት ለምን አልተካተተም ? ለምን ታስቦ ከሚውል ውስጥ ተካተተ ? ምክንያቱም ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ሀገር ነች !! ታስቦ ይውላል እና ተከብሮ ይውላል የሚለው የተለያየ አጀንዳ አለው " የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር።

የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ከኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ አንድ በዓል እንዲከበር እና ታስቦ እንዲውል የሚያደርገው የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ተጠንቶ ነው ብለዋል፡፡

" ኢኮኖሚያችንስ ? " ሲሉ የጠየቁት ወ/ሮ ወርቀሰሙ " ሁል ጊዜ ስራ እየዘጋን ፤ በዓል እያከበርን መዋል በኢኮኖሚው ላይ የሚያመጣው ከፍተኛ ጫና አለ። ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል ታስቦ የሚውል በተለያዩ ነገሮች ደምቆ የሚውል ሊሆን ይችላል በሚል ነው በታሳቢነት እንዲቀጥል የተደረገው " ሲሉ አስረድተዋል።

#ShegerFM #TikvahEthiopia #HoPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፓይለቱ ወደ ኃላ እንዲመለስ ተነግሮት ነበር ፤ ከዛ በኃላ ግን አውሮፕላኑ የት እንደገባ አልታወቀም " - የማላዊ ፕሬዜዳንት የተሰወረው የማላዊ አውሮፕላን አልተገኘም። በአውሮፕላኑ ውስጥ ከም/ፕሬዜዳንቱ ጋር የቀድሞው ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ ባለቤት / የቀድሞ ቀዳማዊ እመቤት ሻኒል ዲዚምቢሪ እንደሚገኙበት ተነግሯል። አንዳንድ ሚዲያዎች እና የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ " በጣም ድቅድቅ…
#Update

የማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን ይዞ ሲጓዝ የነበረውን ከራዳር እይታ የተሰወረው አውሮፕላን #ስብርባሪ ተገኘ።

አውሮፕላኑ መከስከሱ ተረጋግጧል።

ምንም የተረፈ ሰው የለም።

በአውሮፕላኑ ውስጥ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ሳውለስ ቺሊማን እና የቀድሞው ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ ባለቤት / የቀድሞ ቀዳማዊ እመቤት ሻኒል ዲዚምቢሪን ጨምሮ 10 ሰዎች ነበሩ።

ሁሉም መሞታቸው ነው የተሰማው።

Photo Credit - Hopewell

@tikvahethiopia
#አፊኒ #ሲዳማ

በሲዳማ በህዝብ ዘንድ ቁጣ ፈጥሯል የተባለው መፅሀፍ ጉዳይ ምንድነው ?

ከሰሞኑ በዶ/ር አራርሶ ገረመዉ የተጻፈ " አፊኒ " የተሰኘ መጽሀፍ በአእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን ተመዝግቦ የባለቤትነት ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ በሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በኩል ጥያቄ ተነስቷል።

ቢሮው ለአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በላከው የቅሬታ ደብዳቤ " ለዶክተር አራርሶ ገረመዉ ' አፊኒ ' በሚል ስያሜ የተሰጠው የባለቤትነት እዉቅና በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል " በማለት ገልጿል።

የተሰጠዉ እውቅና " የባለቤት " የሚል ሀሳብ የያዘ ሲሆን ይህም የድርሰት ስራ በመሆኑ የቅጅና ተዛማጅ መሆን እንደሚገባዉና " የፈጠራው ባለቤት " የሚለው ቃልም አግባብ አይደለም በማለት ገልጿል።

በመሆኑም ' አፊኒ ' የመላዉ የሲዳማ ህዝብ እንጅ የደራሲዉ የዶ/ር አራርሶ ገረመዉ የፈጠራ ንብረት አለመሆኑ ታዉቆ ማስተካከያ እንዲደረግ በማለት ማብራሪያና ማስተካከያ ጠይቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዩን ሰምቶ የመጽሀፉን ደራሲ አነጋግሯል።

ዶ/ር አራርሶ ገረመው ፤ የተፈጠረዉ ሁኔታ ከርሳቸዉ ቀድሞ ሶሻል ሚዲያዉን ማጥለቅለቁን ገልጸዋል ፤ " በዚህም አዝኛለሁ " ብለዋል።

ሁኔታውን በንግግር እንደፈቱት ገልጸው ጥያቄውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለመመለስና ማህበረሰቡን ለማስቀደም በማሰብ ' አፊኒ ' የሚለዉ ርእስ እንዲስተካከል በመወሰን ስራ መጀመራቸውን አስረድተዋል።

' አፊኒ ' የሚለው ርዕስ ተቆርጦ የወጣ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አራርሶ ፥ አሁን ላይ መጽሀፉ ላይ ያለው ሙሉ አርእስት ' አፊኒ የሲዳማ ድንቅ ባህል ታላቅ ተቋም አስደማሚ የሰላም እሴት ' በሚል ለማስተካከል በደብዳቤ የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣንን መጠየቃቸውን ባለስልጣኑም እንደተቀበላቸውና ማስተካከያ እንደተደረገበት ገልጸዋል።

" ይህንን መጽሐፍ የጻፍኩት #የህዝቤን_ታሪክ ለማስተዋወቅ እና ለማጉላት መሆኑን በውስጡ ያሰፈርኩት አሳብ ይመሰክራል " ያሉት ደራሲው " በርዕሱ ምክኒያት የተፈጠረውን ቅራኔ በቀላሉ ከፈቃድ ሰጪው ጋር ተነጋግሮ መፍታት የሚቻል ቢሆንም በማህበራዊ ሚድያ የጥቂቶች ሀሳብ በዚህ ደረጃ መንጸባረቁ አስገርሞኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
2024/06/11 15:36:16
Back to Top
HTML Embed Code: