Telegram Group Search
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ።
በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው።

1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል

ኢኦቴቤ ሕዝብ ግንኙነት

http://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
Audio
ቅንነት|| ንጉሥ ሰሎሞንን ለማየት ውጡ

Size:-29.9MB
Length:-1:25:53

    በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

http://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
የብፅዕነታቸው በረከት ትድረሰን። ትጠብቀንም። አሜን!!!

http://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
††† >ግንቦት 24 ቀን እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት
በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

=>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ
አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች::

+በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ
የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ
እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ
ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን
አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት
ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም:
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

+የአምላክ እናቱ
*እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች:
እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን
እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት:
ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል::
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን
መርጠዋልና::

=>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ
ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል):
ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን
ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም::
ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

=>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት
ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

http://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
"ጉዳይ ከሌለኝ ከሀገረ ስብከቴ ወጥቼ አላድርም"

…እሑድና ሰኞ ዕለት ዲላ ከተማ ነበርን፡፡ ማግሰኞ ጠዋት ብፁዕ አባታችንን ተሰናብተን ለመውጣት ከቢሯቸው ኼድን፤ በብሩህ ገጽ ተቀበሉን፡፡ ጥቂት ተወያይተን ስንወጣ ከመኻላችን አንዱ"ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሲመጡ እናገኝዎታለን" አላቸው፡፡
"ያንጊዜ እንኳ ሰዓት የሚኖረኝ አይመስለኝም። የሲኖዶሱ ስብሰባ ሲጀምር እመጣለሁ፤ ሲያልቅ ወደሀገረ ስብከቴ ቶሎ እመለሳለኹ፤ ጉዳይ ከሌለኝ ከሀገረ ስብከቴ ወጥቼ አላድርም"፡፡ ብለው መለሱ፡፡

በእርግጥ በሀገረ ስብከታቸውም ብዙ ባለ ጉዳይ የለም፡፡ እርሳቸው ናቸው ወደባለጉዳዮች የሚኼዱ፡፡
የንግሥ በዐላትን ብዙ መምህራንና ካህናት ባሉበት ቦታ አይውሉም፡፡
ቀዳሽ በሌለበት፣መምህር በታጣበት፣ ለመኪና ጉዞ በማይመች ሥፍራ በእግር ተጉዘው ቀድሰው አስተምረው ይመለሳሉ፡፡ ሰኞ ዕለት ያደረጉት ይኽንን ነው፡፡ ብዙ አገልጋዮች ያሉበትን የንግሥ በዐል ጥለው፥ ካህናት ወደሌሉበት ገጠራማ ቤተክርስቲያን ነው ኼደው የዋሉ፡፡

አካኼዳቸውም ውዳሴ ከንቱ አይደለም፡፡ ትርፍ ያለው ጉዞ ነው፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ይሠራሉ፤
ሃይማኖታችንን አንተውም በማለታቸው ብዙ መከራ የሚደርስባቸውን ምእመናን በትምህርት ያበርታሉ፤በእያንዳንዱ ጉዟቸው አዳዲስ አማንያንን ወደቅድስት ቤተክርስቲያን ይጨምራሉ፡፡
በዚያ ሀገረ ስብከት ቄስ አይተን እንሙት ያሉ ምእመናን ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር በቋንቋቸው የሚያስተምርና የሚቀድስ ጳጳስ ላከላቸው፡፡
ወኢትሜህርዎሙ በውዕየተ ልብ ዳዕሙ በሥላቅ፤ [ስለሃይማኖታችሁ]በዋዛ ፈዛዛ እንጂ ልባችሁ እየነደደ አታስተምሩም"
የሚለው የሠለስቱ ምእት ተግሣጽ ያልነካቸው
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ቡርጂና አማሮ አህጉረ ስብከት ጳጳስ፡፡

መልካም ዕረኝነትን እነሆ በዚያ አየናት!

እንደ ተቋም፥ እርስ በእርስ ከመናቆር አባዜ ወጥተው፥ ለበጎቻቸው ራሳቸውን ሠጥተው የሚደክሙ ጥቂት ብፁዓን አባቶችን ስናይ ተስፋችን ሕያው ይኾናል፡፡

http://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
2024/06/02 00:22:29
Back to Top
HTML Embed Code: