tg-me.com/embtee/4083
Last Update:
+++"እንደ አባቶቻችን ከተመለስን ይምረናል"+++
ጥንት በአባቶቻችን ዘመን አስጨናቂ መከራ በተነሣ ጊዜ፣ ልመናን የሚያውቁ አባቶችና እናቶቻችን ራሳቸውን አዋርደው በፍጹም ንስሐ የፈጣሪያቸውን ምሕረት ደጅ ጠኑ። እርሱም ጩኸታቸውን ሰምቶ ዘንበል አለላቸው። መዓቱንም ከእነርሱ መልሶ በገጸ ምሕረቱ ጎበኛቸው። በቁጣው ቀን ተስፋ ያደረጉት ቸርነቱ አላሳፈራቸውም።
ዛሬስ? ዛሬም የእኛ ንስሐ እንደ አባቶቻችን እውነተኛ ከሆነ፣ በፈጣሪያችን ቸርነት ላይ ያለን መተማመን ከቀደሙት እናቶቻችን ካላነሰ፣ አምላካችን እኛን ይቅር ለማለት የታመነ ነው። መድኃኔዓለም መለወጥ እንደሚስማማው ደካማ የሰው ልጅ አይደለም። ልክ በፀሐይና በመሬት መካከል ባለ ዑደት (ዙረት) ምክንያት፣ አንዱ የመሬት ክፍል ከፀሐይ ብርሃን ተቀብሎ ሲያበራ በሌላኛው በኩል ያለው ደግሞ በግርዶሽ እንደሚጨልም እንዲሁ፣ የእግዚአብሔር ብርሃን (ቸርነት፣ ምሕረቱ) ለአንዱ አብርቶ ለሌላው የሚጋረድ አይደለም። ለብርሃኑ የተዘጋጀና በኃጢአት ጉድፍ ያልታወረ ዓይነ ልቡና እስካለን ድረስ የምሕረቱ ነጸብራቅ ለዘወትር በእኛ ላይ እንዳበራ ነው። ብቻ ንስሐችን እንደ ቀደሙት እናቶቻችን፣ መመለሳችንም በቃልና በተግባር እንደ ተመለሱት እውነተኞቹ አባቶቻችን ይሁን!
"በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ"
ያዕ 1፥17
#ኢትዮጵያ_እንደ_ነነዌ
"ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?" ዮና 3፥8
+++ "ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት" +++
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
BY ✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/embtee/4083