tg-me.com/eotchntc/814
Last Update:
ትንቢተ ዮናስ Jonah 1
ምዕራፍ፡1።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደዐማቴ፡ልጅ፡ወደ፡ዮናስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤ተነሥተኽ፡ወደዚያች፡ወደ፡ታላቂቱ፡ከተማ፡ወደ፡ነነዌ፡ኺድ፥ክፋታቸውም፡ወደ፡ፊቴ፡
ወጥቷልና፥በርሷ፡ላይ፡ስበክ።
3፤ዮናስ፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ወደ፡ተርሴስ፡ይኰበልል፡ዘንድ፡ተነሣ፤ወደ፡ኢዮጴም፡ወረደ፥ወደ፡
ተርሴስም፡የምታልፍ፡መርከብ፡አገኘ፤ከእግዚአብሔርም፡ፊት፡ኰብሎ፟፡ከነርሱ፡ጋራ፡ወደ፡ተርሴስ፡ይኼድ፡
ዘንድ፡ዋጋ፡ሰጥቶ፡ወደ፡ርሷ፡ገባ።
4፤እግዚአብሔርም፡በባሕሩ፡ላይ፡ታላቅ፡ነፋስን፡አመጣ፥በባሕርም፡ላይ፡ታላቅ፡ማዕበል፡ኾነ፥መርከቢቱም፡
ልትሰበር፡ቀረበች።
5፤መርከበኛዎቹም፡ፈሩ፥እያንዳንዱም፡ወደ፡አምላኩ፡ጮኸ፤መርከቢቱም፡እንድትቀል፟ላቸው፡በውስጧ፡
የነበረውን፡ዕቃ፡ወደ፡ባሕር፡ጣሉት፤ዮናስ፡ግን፡ወደ፡መርከቡ፡ውስጠኛው፡ክፍል፡ወርዶ፡ነበር፥በከባድ፡
እንቅልፍም፡ተኝቶ፡ነበር።
6፤የመርከቡም፡አለቃ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርቦ፦ምነው፡ተኝተኻል፧እንዳንጠፋ፡እግዚአብሔር፡ያስበን፡እንደ፡ኾነ፡
ተነሥተኽ፡አምላክኽን፡ጥራ፡አለው።
7፤ርስ፡በርሳቸውም፦ይህ፡ክፉ፡ነገር፡በማን፡ምክንያት፡እንዳገኘን፡እናውቅ፡ዘንድ፡ኑ፥ዕጣ፡እንጣጣል፡
ተባባሉ።ዕጣም፡ተጣጣሉ፥ዕጣውም፡በዮናስ፡ላይ፡ወደቀ።
8፤የዚያን፡ጊዜም፦ይህ፡ክፉ፡ነገር፡በማን፡ምክንያት፡እንዳገኘን፡እባክኽ፡ንገረን፤ሥራኽ፡ምንድር፡
ነው፧ከወዴትስ፡መጣኽ፧አገርኽስ፡ወዴት፡ነው፧ወይስ፡ከማን፡ወገን፡ነኽ፧አሉት።
9፤ርሱም፦እኔ፡ዕብራዊ፡ነኝ፤ባሕሩንና፡የብሱን፡የፈጠረውን፡የሰማይን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡
አመልካለኹ፡አላቸው።
10፤እነዚያም፡ሰዎች፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡እንደ፡ኰበለለ፡ርሱ፡ስለ፡ነገራቸው፡ዐውቀዋልና፥እጅግ፡
ፈርተው፦ይህ፡ያደረግኸው፡ምንድር፡ነው፧አሉት።
11፤ባሕሩንም፡ሞገዱ፡አጥብቆ፡ያናውጠው፡ነበርና፦ባሕሩ፡ከእኛ፡ዘንድ፡ጸጥ፡እንዲል፡ምን፡
እናድርግብኽ፧አሉት።
12፤ርሱም፦ይህ፡ታላቅ፡ማዕበል፡በእኔ፡ምክንያት፡እንዳገኛችኹ፡ዐውቃለኹና፡አንሥታችኹ፡ወደ፡ባሕር፡
ጣሉኝ፥ባሕሩም፡ጸጥ፡ይልላችዃል፡አላቸው።
13፤ሰዎቹ፡ግን፡ወደ፡ምድሩ፡ሊመለሱ፡አጥብቀው፡ቀዘፉ፤ዳሩ፡ግን፡ባሕሩ፡እጅግ፡አብዝቶ፡ይናወጥባቸው፡
ነበርና፥አልቻሉም።
14፤ስለዚህ፥ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸው፦አቤቱ፥እንደ፡ወደድኽ፡
አድርገኻልና፥እንለምንኻለን፤አቤቱ፥ስለዚህ፡ሰው፡ነፍስ፡እንዳንጠፋ፡ንጹሕም፡ደም፡በእኛ፡ላይ፡
እንዳታደርግ፡እንለምንኻለን፡አሉ።
15፤ዮናስንም፡ወስደው፡ወደ፡ባሕሩ፡ጣሉት፤ባሕሩም፡ከመናወጡ፡ጸጥ፡አለ።
16፤ሰዎችም፡እግዚአብሔርን፡እጅግ፡ፈሩ፥ለእግዚአብሔርም፡መሥዋዕትን፡አቀረቡ፥ስእለትንም፡ተሳሉ።
BY ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ)
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/eotchntc/814