tg-me.com/ethio_enlightenment/137
Last Update:
መልዕክተ-Enlightenement
የተዘጋው በር
ሄሪ ሁዲኒ በአለማችን ላይ ዝነኛ ከሚባሉ ምትሃተኞች መካከል ግንባር ቀደም ነው። እጅግ አደገኛ የሆኑ ድርጊቶችን ያደርጋል ለምሳሌ ያህል በሰንሰለት ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መጣል፣ አየር በማያስገባ ሳጥን እንደ እቃ ታሽጎ ወደ ባህር መጣል ሌሎችም.....
° ° °
ታድያ ሁዲኒ በአለማችም ላይ ላሉ እስር ቤቶች የእንፋለም ጥያቄ ያቀርብላቸዋል የትኛውንም እስር ቤት በአንድ ሰአት ውስጥ ሰርስሬ(ሰብሬ) መውጣት እችላለው ከነሱ የሚጠበቀው ከነልብሴ እኔን ማስገባት ብቻ ነው።
° ° °
ታድያ በአሜሪካ ደቡባዊ ክፍል የሚገኝ በእድሜ የገፋ እስር ቤት የሁዲኒን ፍልሚያ ይቀበላል። ዙሪያው፥ጣሪያው በወፋፍራም ብረቶች የተሰራ ክፍል ውስጥ አስገብተው ዘጉበት!
° ° °
በቁጥር በርካታ የሆኑ ህዝቦችና ትዕይንቱን ለህዝብ ለማስተላለፍ የታደሙ ጋዜጤኞች በስር ቤት ዙሪያ ተመዋል።
በመጀመሪያ ሁዲኒ ያደረገው ነገር ኮቱን ማውለቅ ነበር። ቀጥሎም በድብቅ የተቀመጠች ጠንካራ፣ቀጭንና ተጣጣፊ ብረት ከቀበቶ ውስጥ አውጥቶ በሩን ለመክፈት ይሞክር ጀመር።
° ° °
ግማሽ ደቂቃ ያህል እንዳሳለፈ በመጀመሪያ የነበረው በራስ የመተማመን መንፈስ እንደ ጢስ መብነን ጀመረ።
ደቂቃዎች ሰአትን ወልደው የ 1 ሰአት ልፋቱና ድክመቱ በሩን ሊከፍቱለት አልቻሉም ከ ሁለት ሰአታት አድካሚና አሰልቺ ትግሎች በኋላ በሩ ተከፈተ!
° ° °
የተከፈተው ግን በመጀመሪያም በሩ ስላልተቆለፈ ነበር ።
ነገር ግን ለሁዲኒ ይህ እውነት አልነበረም ምክንያቱም በእርሱ አእምሮ ውስጥ ያበር እንዳይከፈት ተደርጎ በደንብ ተዘግቷልና።
° ° °
◾️አእምሮ እጅግ ሃይለኛ ሃይል ነው። በህይወትህ ውስጥ ምን ያህል በሮች የተዘጋብህ ይመስልሃል?
የአስተሳሰብ በርህ ተዘግቶብህ ለምን ያህል ግዜ እርምጃህን ገተሃል?
<<ውስጥህ ጠላት ከሌለህ የውጪ ጠላት አንተን አይጎዳህም>>
° ° °
አእምሮ እስከዛሬም ወደፊትም ከምትታገላቸው ሃይሎች ሁሉ እጅጉ ሃይለኛ ሃይል ነው። ውሸቶችን ይነግርሃል ፣ ማድረግ እንደማትችል፣ለምታስበውና ለምታደርገው ድርጊት በቂና መስፈርት እንደማታሟላም ጭመር። ነገር ግን ስለሰጠህ ሃሳብ አመስግነህ ፊት ንሳው!
° ° °
🔵ምክንያቱም ሁዲኒ እንዳሳየን የተዘጋ በር ያለው በራስህ አእምሮ ውስጥ ነው። በእውነታው አለም ግን በሩ ክፍት ነው ። አንተ ማድረግ ያለብህ በሩን ከፍተህመግባት ነው።
BY Ethio Enlightenment
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/ethio_enlightenment/137