tg-me.com/ewnet_lehulum/2900
Last Update:
አምላክ ጌታን ከሞት አስነሳው!
አብዛኛው ወልደ አዳም የፈጠረውን ፈጣሪ ትቶ ፍጡራንን አምላኪ ነው፤ ለእብለት ስር የለው! ለእባብ እግር የለው! እንደሚባለው ሁሉ፥ ያለ ማስረጃና ያለ እውነታ በጨለማ ውስጥ ይዳክራል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ላቅ ያለው ቅጥፈት ፈጣሪ ሞቷል ብሎ ማመን ነው። እንደው ጉድ'ኮ ነው! መቼም ለአፍ ለከት የለው! የፈጣሪን ክብርና ባህሪ ከመፅሐፋቸው ቢያነቡና ቢረዱ የተሻለ ነበር። ግና ችግሩ እንኳን ሊያነቡት ትራስ አድርገውታል!
ኢየሱስ እንደሞተ ባይብል ይናገራል ነገር ግን ያ የሞተው ሬሳ 'ጌታ' ተብሏል፦
ዮሐንስ 20 (John)
13፤ እነርሱም፡— አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? አሉአት። እርስዋም፡— ~ጌታዬን ወስደውታል~ ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም፡ አለቻቸው።
ዮሐንስ 20 (John)
2፤ እየሮጠችም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር መጥታ፡— -~ጌታን ከመቃብር ወስደውታል~ ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም፡ አለቻቸው።
ጌታን ከመቃብር ወስደውታል በማለት ሬሳውን ጌታ ብላ መጥራቷን ልብ ይበሉ! ለመጀመሪያ ጊዜ አምላክ ጌታን አስነሣው ብሎ ያስተማረው ጳውሎስ ሲሆን ይህ አስተምህሮ ነቢያት ያልነካኩትና የማያውቁት የጣዖታውያን(የሠይጣን) አስተምህሮ ነው።
“አምላክ ጌታን ከሙታን አንዳስነሣው፣ እኛንም ደግሞ በኀይሉ ከሙታን ያስነሣናል።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥14 (አዲሱ መ.ት)
ኢየሱስ እንደሞተ ባይብል ይናገራል፣ ኢየሱስ እንደታየም ባይብል ይናገራል። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አይኔን ግንባር ያርገው፣ በማለት ፍጡር የሆነውን ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የሚዳዳቸው አያሌ ናቸው። ይህን አስተሳሰባቸውን ከንቱ የሚያደርግና ፈጣሪ እንደማይሞት እንዲሁም እንዳልሞተ በመፅሐፋቸው ተቀምጧል፦
“እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16
“ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17
እውነተኛው አምላክ ብቸኛ ነው፣ አልሞተም፣ ማንም አላየውም ሊያየውም አይቻለውም። ይሄንን እውነታ የሚቀበልና የሚያስተነትን ሰው ኢየሱስ አምላክ ሳይሆን ጌትነቱም ሌሎች ነቢያቶች እንደተጠሩበት የፍጡር ጌትነት እንደሆነ በግልፅ ይረዳል። አንዱና ብቸኛው የአለማት ፈጣሪ ሙታንና ሬሳ ሲሆን አስባችሁታል?! አስታግፊረሏህ!!! ምን አይነት ጭንቅላት ያለው ሰው ነው እንዲ ሚያስበው?
ውድ ወገኖቻችን ሆይ! የተሠጠን አዕምሮ ልናስተነትንበት ነው አይደል? የፈጠረንን ፈጣሪ በእንደዚህ አይነት ተልካሻ ሃሳብ መሳሉ ራሱ እንዴት አዕምሮ ይቀበለዋል?
Al-Furqan 25:58
وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْحَىِّ ٱلَّذِى لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِۦۚ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا
በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡
ንቁ!!! ካላችሁበት ጨለማ ብርሃን ወደሆነው ኢስላም ኑ!
✍Abdulrauf
https://www.tg-me.com/us/እውነት ለሁሉ truth for all /com.ewnet_lehulum
BY እውነት ለሁሉ [truth for all]
Share with your friend now:
tg-me.com/ewnet_lehulum/2900