tg-me.com/ewnet_lehulum/2905
Last Update:
መደመምህን ቀጥል!
ተቆጥረው የማያልቁ የቁርዓን ተዓምሮችን ከቁርዓኑጋ አዋህደህ እያመሳከርክ ስትመለከተው እንደ ሙስሊምነትህ እያለቀስክ አላህን ከማመስገን ውጭ ምን ማድረግ ይቻላል? መንጋጋህን ወደታች ጥለህ፣ አፍህን ከፍተህ ወይም እጆችህን በአፍህ ላይ ጭነህ መገረም ብቻ! ሱብሐን አላህ! ይህን ቀላል ማስተንተን ወገኖቻችን ቢያስተውሉ ምንኛ በተመሩ ነበር?
እዚህጋ አንድ የምጨምርላችሁ ነገር ቢኖር በአረብኛ ቋንቋ "بطن" ወይም "በጥን" ማለት ሆድ ማለት ሲሆን ቁርዓን ግን ለንብ የተጠቀመው ቃል "بُطُونِهَا" ወይም "ቡጡኒሃ" የሚል ቃል ነው። ይህም ትርጉሙ "በሆዶችዋ" ማለት ሲሆን ንብ ከአንድ ሆድ በላይ እንዳላት ገላጭ ቃል ነው። አሁን ላይ ሳይቲስቶች ንብ ሁለት ሆዶች እንዳሏት አረጋግጠዋል።
ثُمَّ كُلِي مِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ فَاسْلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًا ۚ يَخْرُجُ مِن بُطُونِهَا شَرَابٌ مُّخْتَلِفٌ أَلْوَانُهُ فِيهِ شِفَاءٌ لِّلنَّاسِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
[ ሱረቱ አል-ነሕል፥ - 69 ]
«ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» "ከሆዶችዋ" መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት፡፡
ይሠመርበት "በዚህ ውስጥ "ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት፡፡"
وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
[ ሱረቱ አል-ነምል - 93 ]
ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቋትምአላችሁ» በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡
وَهُوَ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْحَمْدُ فِي الْأُولَىٰ وَالْآخِرَةِ ۖ وَلَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
[ አልቀሶስ - 70 ]
እርሱም አላህ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ምስጋና በመጀመሪያይቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
ሱብሐን አላህ!
https://www.tg-me.com/us/እውነት ለሁሉ truth for all /com.ewnet_lehulum
BY እውነት ለሁሉ [truth for all]
Share with your friend now:
tg-me.com/ewnet_lehulum/2905