tg-me.com/fikirnbewubekalat/190
Last Update:
🐏🐏😘በግ ተራ😁🐑🐑
ያኔ ፍሬሽ ሣለን : ግቢ ሥንገባ
ለብዙ ችግሮች : ሁነናል ሠለባ።
.
ሢኒየር ሢዝናናብን : ሥንገባ ሥንወጣ
በእንሥሣት ሠይመው : ይሉን ነበር ጦጣ።
.
ሤቷን "ፍሬህይወት" : ወንዱን ደሞ "ፍሬው"
ርዕሡ እኛ ነበርን ; የሢኒየሮች ወሬው።
፨
ሁሌም እማልረሣው
............
ድንገት ሣሥታውሠው : ዛሬም የሚያሥቀኝ
አንድ ሢኒየር ተሜ : በሶየን ሢነጥቀኝ።
.
ፍሬሽ እንደሆንኩኝ : አካሄዴን አይቶ
"ፍሬው" ብሎ ጠራኝ : ከኋላየ መጥቶ።
.
ሚሥጥሩ ሣይገባኝ..........
ፍሬው አደለሁም : እባላለሁ 'ሲሳይ'አልኩት
እባክህ አሣየኝ : የወንዶቹን ብሎክ።
.....ብየ ብናገረው : በመልሤ ተደንቆ
....በሣቅ ሊሞትብኝ : መንገዱ ላይ ወድቆ።
፨
እኔም ፍሬው ሞኙ : ሥሜን ረሥቸ
ሢሥቅ አየዋለሁ : ግራ ተጋብቸ።
.
ሣቁ ሢቆመለት......
" ምን ጣጣ አለው ታዳ : ደሞ ለዚህ ነወይ
እቃህን አምጣና : ከኔ ዶርም እንቆይ።
"
.
ይሉኝታ አለኝና : እኔም ተሣቅቄ
ልሠጠው ፈራሁኝ : ሻንጣየን አውልቄ።
.
ይህ ይሻላል ብየ : በሶየን ብሠጠው
ከጓደኞቹ ጋር : ወሥዶ በጠበጠው።
፨
ከ 10 ኪሎ በሶ : ለኔ አንድም ሣይሠጡ
ሢኒየሮች በሙሉ : ተካፍለውት ወጡ።
.
ሌላ ቀን ተዋወኩ : የዶርም ጓደኛ
ሥወጣ ሥገባ : እንዳልሆን ብቸኛ፣
.
ይሄም ጓደኛየ : ችግሬን ተረድቶ
ጧት ማታ ከዶርሜ : እንደማለቅ አይቶ
"ወክ እማትወጣው : ምን ብትሆን ነው ከቶ?
.
አቦ አትደብረኝ : አትሁንብኝ ፋራ
ይልቅ ለባብሥና : እንሂድ በግ ተራ። "
....አለና ገፋፋኝ : ውሣኔ አሥቀየረ
....ትልቁ ገጠመኝ : አሁን ተጀመረ።
፨
ለባብሠን ብንወጣ : ታውደን በሽቶ👓
በግ ተራን አየሁት : በወጣቶች ሞልቶ።
.
ሤቱም ወንዱም ወጣት : በበግ መሠየሙ
መቸም ሚሥጥር : አለው ምን ይሆን ትርጉሙ?
.
እኔማ የዚህን : ትርጉሙን ለማወቅ
ዛሬ ልየው እንጅ : መቸም ጊዜ አልጠብቅ።
፨
ምሽቱ ነገሠ : ሠአቱ ከነፈ
አይኔም ተወርውሮ : ካንዲት ቆንጆ አረፈ።
.
ፍርሀቴ እንዲለቀኝ : ከውሥጤ ተንፍሸ
ወደ እሷ ተጠጋሁ : ባይኖቸ ጠቅሸ።
.
እሷም ለምሽኮርመም : ትንሽ አመነታች
ልመለሥ ሢቃጣኝ : በገዛ እጇ መጣች።
፨
ይችማ የዋህ ናት እውነትም በግ ተራ
አንደበቷ ማር ነው : ደሞኮ ሥትፈራ።
.
በመጀመሪያው ቀን : ሥልኳን ሠታኝ መጣሁ
ሣልተኛ ነጋብኝ : ከዶርሜ እንደወጣሁ።
፨
........ጉድ መጣ
............
!
በሁለተኛው ቀን : እራሷ ደውላ
"ከተማ እንውጣ" : አለች ከሠአት በኋላ።
.
እኔም ያለችኝን : ገንዘቤን ሠብሥቤ
ያሻትን ልጋብዝ : ላኮራት አሥቤ፣
.
ብሩ አይበቃም ብየ : ለእሷ እንኳን ሥፈራ
4 ሁና መጣች : ልትከተኝ ኪሣራ።
.
እንደፈረደብኝ : አራቱን ጋብዠ
ገንዘቡ ቢያልቅብኝ : ሞባይል አሢይዠ📱📱📱
.
አሥተናጋጅቷን : አልኳትና አደራ
ይሄንን ችግሬን : ለእሷ እንዳታወራ፣
.
ለሽንት ቤት ብየ : ሣያዩኝ ወጥቸ
ተበድሬ መጣሁ : ከዶርም ጓዶቸ።
፨
.........ወይ ጣጣ ደሞ ምን ምኔ ቀራት ?.....
"ፍዝዝ አትበል እንጅ : አይዞህ የኔ ፍቅር
ሂሣቡን ዝጋና : ሥንጨፍር እንደር። "
.....ብላኝ እርፍ አለች : የፊቱ ሢቆጭኝ
.....ጭራሽ አሣብዳ : ፊቴን ልታሥነጨኝ።
.
ምን አማራጭ አለ : አልኩና በሆዴ
አንችን ደሥ ካለሺ : ችግር የለም ውዴ።
...ብየ ተናግሬ : ፀጉሬን እያሻሸሁ
...ገንዘቡ ቢያልቅብኝ : ሥጨነቅ አመሸሁ።
፨
ጨዋታው ሢጀመር : ጭፈራው ሢደራ
ወገቡን ሢፈትሽ : ሁሉም በየተራ።
.
ትንሽ እንደቆየች : ብትለኝ "ራበኝ
"
ባዶ ቦርሣ ይዠ :ገላየን አላበኝ።
፨
........ኡፍፍፍፍፍ........
በዚህ ውድቅት ሌሊት : ገንዘብ ከየት ላምጣ
ግቢ ትበያለሽ : ከዚህ ቤት እንውጣ፣
........ብየ ተናግሬ ያፌን : ሣልጨርሠው
.......አምባርቃብኝ ሄደች : የዋህ ናት ያልኳት ሠው።
፨
በግ ተራ ወጥቸ : ያገኘኋት ልጅ
የበግ ፀባይ የላት : የፍየል ነው እንጅ።
.
የዋህ በጎች መሥለው : ከግቢ ሢወጡ
ምግባቸው ጫት ብቻ : አልኮል የሚጠጡ
እንዴት ከበግ ተራ : ፍየሎቹ መጡ?
፨
በግ የሚለውን ሥም : ፍየሎች ተውሠው
ሠውን አሥቸገሩት : ጩኸታቸው ባሠው።
፨
ዩኒቨርሢቲወችም : ባንድ ላይ ይቀጡ
ከበግ ተራ መሀል : ፍየል እንዳይሸጡ።🐐🐐🐐
፨
አማን አውለኝ ብሎ : ከዶርሙ ተነሥቶ
ማን ፍየል ይገዛል : ለበግ ብሎ ወጥቶ።
.
ወይ ቦታው ቢለያይ : መግቢያውና መውጫው
ይገዛ ነበረ : ሁሉም እንደምርጫው።
፨
እነ ፍሬ ህይወት : በሉ ተጠንቀቁ
ፍየል ብቻ ቀርቷል : በጎች ተመረቁ።
፨
በግ የምትፈልጉ : ፍየል የማትሹ
ካሁን ጀምራችሁ : በበግ ተራ አታምሹ።
፨
ግቢወችም ይሥሙት : ይሄን አቤቱታ
ከእንግዲህ ይሥጡልን : ለፍየሎች ቦታ።።።።
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@fimanfikirnbewubkalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
አስተያየት👉@ABUNE05
❥❥________⚘_______❥❥
BY ኤፍ ማን ፍቅርን በውብ ቃላት ♥♠♥♠♥♣
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/fikirnbewubekalat/190