tg-me.com/fikirnbewubekalat/193
Last Update:
"ደስታየን ገለፅኩት "
በታህሳስ ወራት በቀንም ዘጠኝ
ቅዳሜን ከሰአት ዜና ሰማሁኝ
ሰሜን ወሎ ሀገር ራያን ጨምሮ ነፃ ወጣ አሉኝ
ታፍኖ የኖረው ደስታየም ፈንድቆ
እልል በል ይለኛ ከመሬት ላይ ወድቆ
ገና በክረምቱ በሀምሌውም ወራ ከቤቴ እንደወጣሁ
ከደስታየም የተነሳ መስሎም እጅግ ታየኝ ከቤቴ የገባሁ
በየ Tv ው ሁሉ በየ ድህረ ገፁ
የሀገሬን ዜና ዘጋቢወች በዙ
አቤት ያለ ደስታ.........
ገና አለ የደስ ደስ ሀገሬ ኢትዮጵያ ትቆማለች በክብር
በአማራ መሬት ላይ በክብር ለተሰውት አንድ ሆና ስትዘምር
የደስ ደሱን ብየ ግጥምንም ለመፃፍ ብእሬን አነሳሁ
ስሜቴን ለመግለፅ ከወረቀቴ ላይ ቃላት አንጠባጠብሁ
ስሜትና ደስታን በአንድነት ለመግለፅ እልፍኝ ቃላት አጣሁ
በደስታ የተነሳ ምግቡም አይበላኝ ውሀም አይጠጣኝ
ድንገት ክንፍ አውጥቸ ወደ ሀገር ቤቴ መብረር ነው ያማረኝ
ኡፍ ጨነቀኝ.........
በአንድ በኩል ደስታ በአንድ በኩል ሀዘን
ምክኒያት እጅጉን ደስ ያለኝ ሀገር ነፃ ስትሆን
የሀዘኔም ምክኒያት እጅግም የከፋኝ ቤተሰብ የት ይሆን
ይህን ያክል ወራት ድምፅ እንኳን ሳንሰማ ዝም ብለን ተቀመጥን
የደስታየዛሬ አድስ ቀን ነው የሀገሬን ሰላም መጥቶ እንድያበስረኝ ቁራውንም ላኩት
ቁራም መልዕከተኛ ሁሉንም እረስቶ መምጣትም ከብዶታል የሀገሬን ሰላም በሆዱ ለውጦት
የኖህን አብሳሪ ብስራቷን ፈልጌ ለእኔም እንድትሆነኝ እርግብን ስልካት
ሁሉን ነገር ቃኝታ ሁሉንም ተረድታ የሀገሬን ሰላም መጥታ አበሰረች ምንም ሳይበግራት
የሀገሬ ሰወች እንኳን ደስ አላችሁ
ጥምቀት እና ገናን ናችሁ ከቤታችሁ
ማንም ምንም ሳይሆን በሰላም በጤና ከቤተሰቦቻችሁ
ጥምቀትና ገናን በታላቅ ደስታ አውሉት ቤታችሁ
የሀገሬ እና መከነቱን አንሽ ወገብሽን አጥብቂ
ለበአሉም ድምቀት ድባቡ ነውና ድፎውንም ጋግሪ ጠላውን ጥመቂ
ሸወት ግባ ስትይ ታቦቱን ስትጠሪ ድምፅሽንም ልስማው
ከመንበሩ ሲደርስ ታቦቱም ሲገባ ሰብሕወ ሲባል ሲመታ ከበሮው
ወጣቱም"ተነሳ" ሁሉም በሚችለው በሽለላ ጭፈራው
ይህን ሁሉ ስርአት ዳግም እናያለን በየመስመሩ ላይ ሲበተን አበባው
አይርቅም ቅርብ ነው ሁሉም በአንድነት የመገናኛችን ቅርብ ነው ዋዜማው!!
የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ🙏🙏 https://www.tg-me.com/us/ኤፍ ማን ፍቅርን በውብ ቃላት /com.fikirnbewubekalat
https://www.tg-me.com/us/ኤፍ ማን ፍቅርን በውብ ቃላት /com.fikirnbewubekalat https://www.tg-me.com/us/ኤፍ ማን ፍቅርን በውብ ቃላት /com.fikirnbewubekalat
ታህሳስ09-04-2014
ተፃፈ
✍️ በኤፍሬም ጌታሁን
BY ኤፍ ማን ፍቅርን በውብ ቃላት ♥♠♥♠♥♣
Share with your friend now:
tg-me.com/fikirnbewubekalat/193