tg-me.com/getem/15343
Last Update:
#ፀሃይና_ጨረቃዬ
.
.
.
በራሷ ልክ ለምታውቀኝ የኔን ናፍቆት ያቺን ድሃ፣
ላንዱ ልቤ የልቡ ራ'ብ ሆና ብትፈልቅ የፍቅር ውሃ።
ነይ ብሏታል ሰርክ ናፍቆ እዝነ ነፍሴ ተመልክቷት፣
ከሺ ልባም ከሴት መሃል ከቀይ እንቁ እሷን ሽቷት።
ትመጣለች እኔን ብላ፤
ትመጣለች ሀሳብ ጥላ፤
የምታውቀው ሩህሩህ መላዕክ በፍቅር ዘንግ እየመራት፣
መቼም እሱ ያውቅበታል፤
ከመጨከን ሳይቀላቅል ልቤ መሃል እሷን 'ሰራት ።
ከቆምኩበት ከዚያው ስፍራ፤
ባክሽ ፍጠኝ ድረሽ እያልኩ ከራሴ ጋር ሳጉረመርም፣
ከሀሳብ ባህር የወደቀን ብኩን እኔን ቆሜ ሳርም።
መጣችልኝ ያይኔ አበባ መጣችልኝ የልቤ ሰው፣
እንባና ሳግ ወንድ አንጀቴን ቁጡ ፊቴን ሳቅ ወረሰው።
( እኔ የምልሽ ? መቼ ነው ግን፤ )
( ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ከጥጋብ ደጅ የምደርሰው ? )
እንጃ'ባቴ !!!!!
ልብላ አላለች ወይ ልጠጣ፤
ልውረድ የለም ወይም ልወጣ፤
ናፍቆት ሆኖ የሷም ረሃብ ካለም ሁሉ የተለየ፤
ከወንዶቹ አስበልጦ ከህዝበ አዳም እኔን ያለ።
ፍቅር አይኗን ከደነችው፤
ጠፍር አልጋ መሃሉ ላይ ግራ እጄን ተንተርሳው፣
ሙቅ ትንፋሿ እፍፍ ሲለኝ ወንድ አካሌ ነፍሴን ረሳው።
አጀብ መቼም ያየሁትን፤
ስትነካካኝ በጣቶቿ ስትዳብሰኝ በመዳፏ፣
ንጉስ መሆን የዛን'ለት "የኔ አባት" ሲለኝ አፏ።
በነፍሷ ጫፍ ምኑ ዳሬን የቱ ጋር ነው የነካችኝ፣
የተጣላሁ ከራሴ ጋር በምን ብልሃት አስማማችኝ ?
በአርምሞ በፀጥታ፤
አይኗን አየሁ ሽፋሽፍቷን፤
ተመለከትኩ የነፍሷን ሀቅ ተኝታለች አለም ረስታ፣
አንገቴ ስር ካገኘችው ስስ ህይወቷን ተጠግታ።
የዛን'ለታ........
እያለ
እያለ
እያለ "ልሂድ" አለኝ፤
እኛን ሲያዩ የፈገጉ ሰማይ ምድር ተላቀቁ፤
በመሄድ ውስጥ ተከርችመው ነገን ሊሉ ሲታረቁ።
እቅፍ ብርሃን ፈነጠቀ ከአፅናፍ አፅናፍ ተዘረጋ፣
ፀሃይና ጨረቃዬን፤
በአክናዴ እንዳቀፍኳት ሆነ አዲስ ቀን ሌቱ ነጋ።
.
.
.
"አይኗን ገልጣ አይኔን አየች ከኔ ማዶ የራሷን ሀቅ፣
ፈገግ ብላ አዋሰችኝ የሰጧትን የ'ግዜሯን ሳቅ።"
ስትችልበት !!!!!!
✍ ዓቢይ ( @abiye12 )
@getem
@getem
@getem
BY ግጥም ብቻ 📘
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/getem/15343