tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology/386
Last Update:
ስለምንነቱ ትንሽ እናውራ!
ፓይተን ፕሮግራሚንግ (Python Programming) ከድረ-ገጽ ልማት እስከ ዳታ ሳይንስ፣ ከማሽን ለርኒንግ እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ከጨዋታ (ጌም) ስራ እስከ ሳይንሳዊ ምርምር... ፓይተን የሌለበት የቴክኖሎጂ ዘርፍ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ይህ ቋንቋ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሰረት ብቻ ሳይሆን፣ የወደፊትዎንም የሚቀርፅ ቁልፍ ነው።
ፓይተን ቀላል የሚመስል፣ ግን እጅግ ውስብስብ ስራዎችን መሥራት የሚችል!
ፓይተንን መማር ልክ አዲስ ቋንቋ መማር እንደመጀመር ነው። ቀላል ቃላትን እና አጫጭር ዓረፍተ ነገሮችን በመጠቀም ይጀምራሉ። ኮዱ ግልፅ፣ ለማንበብ ቀላል እና ለመረዳት የማያስቸግር ነው። ይህ ማለት በፍጥነት መማር እና ወደ ተግባር መግባት ይችላሉ ማለት ነው! በሌሎች ቋንቋዎች በደርዘን የሚቆጠሩ መስመሮች የሚፈጀውን ኮድ፣ በፓይተን በጥቂት መስመሮች መፃፍ ይቻላል!
ፓይተን ልክ አንድ ሁለገብ መሳሪያ የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰራ ሁሉ፣ ለተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ያገለግላል። አንድን ነገር በፓይተን መሥራት አይቻልም ብሎ ማሰብ ይከብዳል! ከድረ-ገጽ እስከ ሞባይል መተግበሪያ፣ ከዳታ ትንተና እስከ ሮቦት ቁጥጥር... ሁሉም በፓይተን ይቻላል!
ከፍተኛ ተወዳጅነት (Popularity) አለው: ፓይተን በአለም ላይ ካሉ በጣም ታዋቂ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ለምን? ምክንያቱም ይሰራል! ትላልቅ ኩባንያዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማት... ሁሉም ፓይተንን ይጠቀማሉ። ይህ ማለት የስራ እድልዎ ሰፊ ነው ማለት ነው! Stack Overflow, GitHub, TIOBE Index – እነዚህ ሁሉ የፓይተንን ተወዳጅነት ያረጋግጣሉ።
ፓይተን ድረ-ገጾችን ከመሰረቱ ጀምሮ ለመገንባት ያስችልዎታል። ልክ አንድን ቤት ሲሰሩ የተለያዩ ክፍሎች (ሳሎን፣ መኝታ ቤት፣ ወጥ ቤት...) እንደሚያስፈልጉት ሁሉ፣ ድረ-ገጽም የተለያዩ ክፍሎች አሉት። ፓይተን እነዚህን ክፍሎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመስራት ያግዝዎታል።
ከጀርባ (ከኋላ) ያለው (Back-End): ይህ ከፊት ለፊት የማይታየው፣ ነገር ግን ድረ-ገጹ እንዲሰራ የሚያደርገው ዋናው ክፍል ነው። ለብዙ አገልግሎት የሚውሉ ሎጂኮችን የሚይዝልን! ለምሳሌ ተጠቃሚዎች ፎርም ሲሞሉ፣ መረጃ ሲያስገቡ፣ ክፍያ ሲፈጽሙ... ይህ ሁሉ የሚከናወነው በBack-End ነው።
በዘመናችን መረጃ (data) እንደ ነዳጅ ነው። ግን ነዳጅ ብቻውን ምንም አይጠቅምም። መኪና ውስጥ ገብቶ መንቀሳቀሻ እስኪሆን ድረስ። ልክ እንደዚሁ፣ መረጃም ተተንትኖ፣ ተቀናጅቶ፣ ትርጉም እስኪያገኝ ድረስ ምንም አይጠቅምም። ፓይተን ይህን ሂደት በጣም ቀላል ያደርገዋል።
ማሽን ለርኒንግ ኮምፒውተሮች ከመረጃዎች (ከዳታ) እንዲማሩ ማድረግ ነው። ልክ አንድን ልጅ ሲያስተምሩ በተደጋጋሚ ምሳሌዎችን እያሳዩ እንደሚያስረዱት ሁሉ፣ ማሽን ለርኒንግም እንዲሁ ነው። ግን ማሽን ለርኒንግ ከልጅ ትምህርት የሚለየው፣ ኮምፒውተሮች በጣም ብዙ መረጃዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መማር መቻላቸው ነው!
AI ከማሽን ለርኒንግ ይበልጣል። AI ኮምፒውተሮች እንደ ሰው እንዲያስቡ፣ እንዲወስኑ እና እንዲሰሩ ማድረግ ነው።
ምሳሌ: ራሳቸውን የሚያሽከረክሩ ሹፌር አልባ መኪኖች (self-driving cars) በAI ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ፓይተን የእነዚህ መኪኖች "አንጎል" (ሞደል) ለመገንባት ያገለግላል።
በኮምፒውተርዎ ላይ ተደጋጋሚ ስራዎችን መስራት አሰልቺ ነው አይደል? ለምሳሌ መቶ ፎቶዎችን በአንድ ጊዜ ስም መቀየር፣ ብዙ ፋይሎችን ከአንድ ፎልደር ወደ ሌላ ፎልደር መገልበጥ... ፓይተን እነዚህን ስራዎች የሆነች ስክሪፕት በመፃፍ በቀላሉ በራሳቸው እንዲሰሩ ማድረግ ይችላል!
ምሳሌ: አንድ የሲስተም አስተዳዳሪ (system administrator) በየቀኑ የኮምፒውተሮችን ሁኔታ ለመፈተሽ እና ችግሮችን ለመፍታት ፓይተን ስክሪፕት ሊጠቀም ይችላል።
በMizan Institute of Technology (MiT) የፓይተን ኮርስ ስልጠና የምንሸፍናቸው ርዕሶች: