√ "#የሰሞኑ_አፈና"
•••
ቆይ ግን ምን አጠፋን ችግሩ ምንድን ነው ፣
ምንስ በደ'ልናችሁ ነገሩ ወዴት ነው ፣
ምን አስቀየ'ምን እና እንዲህ ምን'ቀ'ጣ'ው ፣
ከቶ'ስ ምን አደረግን በዛብን መከራው ፣
በጠራራ ፀሐይ #አፈናው ምን ቤት ነው ።
•••
👌 ይድረስ መንግሥት መስሎ መንጋ ለሆነው መንግሥታችን ፦ በሕግ አምላክ! በየቦታው የታፈኑ የዓምኻራ ልሒቃን ይለቀቁልን። የዓምኻራ ፋኖዎች፣ የመከላከያ ሠራዊቶች፣ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች በሙሉ ይለቀቁልን። ካልሆነ የከፋ ነገር ይመጣል። ይኸ ምስኪን ሕዝብ ዳቦ በሙዝ በተባለው የጅላጅል ብሒል እየተቀጣ ነው። ረሃቡ አድክሞታል። ኑሮው አጎሳቁሎታል። ተዉት። በኋላ የማይነካውን ነካክታችሁ ችግር ውስጥ እንዳትገቡ። እስካሁን ስለሆነብን ካሳ አልጠየቅንም። ከዚህ በኋላ ግን መታገስ መፍራት አለመሆኑን ለማሳየት የፈረጠመ ክንዳችንን ለማዘጋጀት እንገደዳለን። ዓምኻራ ግድግዳ ነው። ለኢትዮጵያ ዋልታ እንጂ ዋልካ ሆኖ አያውቅም። እንከባበር።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 9/9/2014 ዓ•ም
•••
ቆይ ግን ምን አጠፋን ችግሩ ምንድን ነው ፣
ምንስ በደ'ልናችሁ ነገሩ ወዴት ነው ፣
ምን አስቀየ'ምን እና እንዲህ ምን'ቀ'ጣ'ው ፣
ከቶ'ስ ምን አደረግን በዛብን መከራው ፣
በጠራራ ፀሐይ #አፈናው ምን ቤት ነው ።
•••
👌 ይድረስ መንግሥት መስሎ መንጋ ለሆነው መንግሥታችን ፦ በሕግ አምላክ! በየቦታው የታፈኑ የዓምኻራ ልሒቃን ይለቀቁልን። የዓምኻራ ፋኖዎች፣ የመከላከያ ሠራዊቶች፣ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች በሙሉ ይለቀቁልን። ካልሆነ የከፋ ነገር ይመጣል። ይኸ ምስኪን ሕዝብ ዳቦ በሙዝ በተባለው የጅላጅል ብሒል እየተቀጣ ነው። ረሃቡ አድክሞታል። ኑሮው አጎሳቁሎታል። ተዉት። በኋላ የማይነካውን ነካክታችሁ ችግር ውስጥ እንዳትገቡ። እስካሁን ስለሆነብን ካሳ አልጠየቅንም። ከዚህ በኋላ ግን መታገስ መፍራት አለመሆኑን ለማሳየት የፈረጠመ ክንዳችንን ለማዘጋጀት እንገደዳለን። ዓምኻራ ግድግዳ ነው። ለኢትዮጵያ ዋልታ እንጂ ዋልካ ሆኖ አያውቅም። እንከባበር።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 9/9/2014 ዓ•ም
√ "#አምፖል_አታምልኩ"
•••
ኧረ እኛስ ምን ጉድ ነን ያስቸገርን ለአምላክ ፣
በጠራራ ፀሐይ #አምፖል የምናመልክ ።
ፈጣሪ ለሰው ልጅ ፀሐይን ቢፈጥር ፣
አምላክ ለእኛ ብሎ ጨረቃን ቢፈጥር ፣
አምፖል እያመለክን ርቆናል ፍቅር ።
ብልጽግና ብሎ ብልግናን መስበኩ ፣
ፍቅር ሰላም ብሎ ዜጎችን ማወኩ ፣
ለውጡ ነውጥ ሆኖ ውሸት መፈብረኩ ፣
ይህ ነው ብልጽግና የሴራ መድረኩ ፣
ቢገባ ይግባችሁ የግጥሜ አቅሙ ልኩ ፣
በብርሃን ሂዱ አምፖል አታምልኩ ፣
በኋላ በጽልመት እንዳትታወኩ ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 9/9/2014 ዓ•ም
•••
ኧረ እኛስ ምን ጉድ ነን ያስቸገርን ለአምላክ ፣
በጠራራ ፀሐይ #አምፖል የምናመልክ ።
ፈጣሪ ለሰው ልጅ ፀሐይን ቢፈጥር ፣
አምላክ ለእኛ ብሎ ጨረቃን ቢፈጥር ፣
አምፖል እያመለክን ርቆናል ፍቅር ።
ብልጽግና ብሎ ብልግናን መስበኩ ፣
ፍቅር ሰላም ብሎ ዜጎችን ማወኩ ፣
ለውጡ ነውጥ ሆኖ ውሸት መፈብረኩ ፣
ይህ ነው ብልጽግና የሴራ መድረኩ ፣
ቢገባ ይግባችሁ የግጥሜ አቅሙ ልኩ ፣
በብርሃን ሂዱ አምፖል አታምልኩ ፣
በኋላ በጽልመት እንዳትታወኩ ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 9/9/2014 ዓ•ም
👌 ልብ በል ወዳጄ!
•••
ስልጤም ሁን ጉራጌ ፣
ጎጃም አምባላጌ ፣
ሃዋሳ መቀሌ ቦረና ደረስጌ ፣
ወላይታ ሲዳማ ናዝሬት ወይ አዲስጌ ፣
አፋር መተከል ሁን ሲያሻህም ከዘጌ ፣
ጂማ ከአባ ጂፋር ስትፈልግ ሐረርጌ ፣
ኦሮሞ ቤንሻንጉል ደቡብ ግርጌ ራስጌ ፣
አክሱም አላማጣ ራያ እና ሬጌ ፣
የትም ሁን!
#ኦርቶዶክስ ከሆንክ ፣
እመነኝ አንድ ቀን ፣
መባልህ አይቀርም ልክስክስ ባለጌ ።
(#በሃይማኖትህ የሚመጣብህ ይህ ነው። ተደራጅ። ተዘጋጅ።)
~ ... በሌላ በኩል ... ~
ጎጃሜም ሁን ጎንደር ስትፈልግ ከሸዋም ፣
ወሎ ደጋ ዳሞት ተጉለቴ ብትሆንም ፣
አበበ ከበደ አንድነት ቢመጣም ፣
አብርሃም ኢብራሂም ስም ቢሆንልህም ፣
ዲያቆን ወይ ደረሳ አገልጋይ ብትሆንም ፣
ወይ ቄስ አልያም ሼኽ ሥልጣን ቢኖርህም ፣
ሙስሊም ወይ ክርስቲያን አማኝ ነኝ ብትልም ፣
እኔ ልሙት ጓዴ!
ዓምኻራ ከተባልክ ገዳይ አያጣህም ።
~ ... በመጨረሻም ... ~
ጠቅለል ለማድረግ የግጥሜን ሃሳቦች ፣
ከላይ ያልኩህ ናቸው 👆
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁለቱ ክሥተቶች ።
•••
✊ ከየትኛውም ብሔር ተወለድ። ኦሮሞም ጉምዝም ደቡብም ዓምኻራም ትግራይም ምናምንም ሁን። #ኦርቶዶክስ ከሆንክ የመከራው ተካፋይ ነህ። በሌላ በኩል ሙስሊምም ሁን ክርስቲያን #ዓምኻራ ከሆንክ የመከራው ገፈት ቀማሽ ነህ። ስለዚህ #በሃይማኖትህ እና #በዓምኻራነትህ መከራ ስላለብህ ተደራጅ። ተዘጋጅ። ክተት። መክት። አንክት። ስበር። ድፈር። ቀልጥም። አገልድም። ሁሌም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋሉ። #ዓምኻራ እና #ኦርቶዶክስ ድሉ የእናንተ ነው። አትጠራጠሩ። እናሸንፋለን። ✊
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 10/9/2014 ዓ•ም
•••
ስልጤም ሁን ጉራጌ ፣
ጎጃም አምባላጌ ፣
ሃዋሳ መቀሌ ቦረና ደረስጌ ፣
ወላይታ ሲዳማ ናዝሬት ወይ አዲስጌ ፣
አፋር መተከል ሁን ሲያሻህም ከዘጌ ፣
ጂማ ከአባ ጂፋር ስትፈልግ ሐረርጌ ፣
ኦሮሞ ቤንሻንጉል ደቡብ ግርጌ ራስጌ ፣
አክሱም አላማጣ ራያ እና ሬጌ ፣
የትም ሁን!
#ኦርቶዶክስ ከሆንክ ፣
እመነኝ አንድ ቀን ፣
መባልህ አይቀርም ልክስክስ ባለጌ ።
(#በሃይማኖትህ የሚመጣብህ ይህ ነው። ተደራጅ። ተዘጋጅ።)
~ ... በሌላ በኩል ... ~
ጎጃሜም ሁን ጎንደር ስትፈልግ ከሸዋም ፣
ወሎ ደጋ ዳሞት ተጉለቴ ብትሆንም ፣
አበበ ከበደ አንድነት ቢመጣም ፣
አብርሃም ኢብራሂም ስም ቢሆንልህም ፣
ዲያቆን ወይ ደረሳ አገልጋይ ብትሆንም ፣
ወይ ቄስ አልያም ሼኽ ሥልጣን ቢኖርህም ፣
ሙስሊም ወይ ክርስቲያን አማኝ ነኝ ብትልም ፣
እኔ ልሙት ጓዴ!
ዓምኻራ ከተባልክ ገዳይ አያጣህም ።
~ ... በመጨረሻም ... ~
ጠቅለል ለማድረግ የግጥሜን ሃሳቦች ፣
ከላይ ያልኩህ ናቸው 👆
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁለቱ ክሥተቶች ።
•••
✊ ከየትኛውም ብሔር ተወለድ። ኦሮሞም ጉምዝም ደቡብም ዓምኻራም ትግራይም ምናምንም ሁን። #ኦርቶዶክስ ከሆንክ የመከራው ተካፋይ ነህ። በሌላ በኩል ሙስሊምም ሁን ክርስቲያን #ዓምኻራ ከሆንክ የመከራው ገፈት ቀማሽ ነህ። ስለዚህ #በሃይማኖትህ እና #በዓምኻራነትህ መከራ ስላለብህ ተደራጅ። ተዘጋጅ። ክተት። መክት። አንክት። ስበር። ድፈር። ቀልጥም። አገልድም። ሁሌም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋሉ። #ዓምኻራ እና #ኦርቶዶክስ ድሉ የእናንተ ነው። አትጠራጠሩ። እናሸንፋለን። ✊
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 10/9/2014 ዓ•ም
√ "#እናቴን_ፍቱልኝ"
•••
✍ ባል ነን እያላችሁ አትሟዘዙብኝ ፣
ጠባቂ ምናምን አትጃጃሉብኝ ፣
መከታ እንደ ራሴ አትበጥረቁብኝ ፣
ዓለቃ አስከባሪ አትላላጡብኝ ፣
እውነተኛ በሚል ተዉ አትግማሙብኝ ፣
ይልቅስ በጊዜ እናቴን ፍቱልኝ ።
(#ከኦርቶዶክስ ላይ እጃችሁን አንሱልኝ።)
•••
እርሷ ባል አይኑራት ትሁን ጋለሞታ ፣
ጠባቂም አይኑራት ጋሻ እና መከታ ፣
እረኛም አይኑራት የማያመነታ ፣
እጃችሁን አንሱ እወቁ ይሉኝታ ፣
ጋሻ መከታዋ ፤
ጥላ ከለላዋ ፤
አለኝታ ቤዛዋ ፤
በደሙ የዋጃት አላት አንድ ጌታ ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 10/9/2014 ዓ•ም
•••
✍ ባል ነን እያላችሁ አትሟዘዙብኝ ፣
ጠባቂ ምናምን አትጃጃሉብኝ ፣
መከታ እንደ ራሴ አትበጥረቁብኝ ፣
ዓለቃ አስከባሪ አትላላጡብኝ ፣
እውነተኛ በሚል ተዉ አትግማሙብኝ ፣
ይልቅስ በጊዜ እናቴን ፍቱልኝ ።
(#ከኦርቶዶክስ ላይ እጃችሁን አንሱልኝ።)
•••
እርሷ ባል አይኑራት ትሁን ጋለሞታ ፣
ጠባቂም አይኑራት ጋሻ እና መከታ ፣
እረኛም አይኑራት የማያመነታ ፣
እጃችሁን አንሱ እወቁ ይሉኝታ ፣
ጋሻ መከታዋ ፤
ጥላ ከለላዋ ፤
አለኝታ ቤዛዋ ፤
በደሙ የዋጃት አላት አንድ ጌታ ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 10/9/2014 ዓ•ም
√ #እስላም_vs_ዓምኻራ
•••
✍ ድሮ ልጅ እያለን የምንጫወተው ፣
ከሰፈር ልጆች ጋር የምንሯሯጠው ፣
እስላም እና ዓምኻራ ብለን የነበረው ፣
ግን ግን ምን ሆነን ነው ፣
አይ አይ አይ ምን ሆነን ነው ፣
ወይኔ ምን ሆነን ነው ፣
አይ አይ አይ ምን ሆነን ነው ፣
እስላም እና ዓምኻራ ብለን የዘመርነው ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 10/9/2014 ዓ•ም
•••
✍ ድሮ ልጅ እያለን የምንጫወተው ፣
ከሰፈር ልጆች ጋር የምንሯሯጠው ፣
እስላም እና ዓምኻራ ብለን የነበረው ፣
ግን ግን ምን ሆነን ነው ፣
አይ አይ አይ ምን ሆነን ነው ፣
ወይኔ ምን ሆነን ነው ፣
አይ አይ አይ ምን ሆነን ነው ፣
እስላም እና ዓምኻራ ብለን የዘመርነው ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 10/9/2014 ዓ•ም
√ "#ጳውሎስ_ወ_ማትያስ"
•••
✍ ኧረ ሰዎች ንቁ ኃጢአት ይቅርባችሁ ፣
ኧረ ወገን በቃ በደል ያስፈራችሁ ፣
ኧረ ሕዝቤ ንቁ ዝሙት አያጥቃችሁ ፣
ኧረ አዳሜ ንቁ ሙስና ይብቃችሁ ፣
ኧረ ሔዋን ንቁ ውበት አይግዛችሁ ፣
ይሁዳ እና ቀራጭ መሆን ይለፋችሁ ፣
ሳኦልም ሳውልም መሆን ይቆያችሁ ፣
ጳውሎስ ወይ ማትያስ መሆን አለባችሁ ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 10/2014 ዓ•ም
•••
✍ ኧረ ሰዎች ንቁ ኃጢአት ይቅርባችሁ ፣
ኧረ ወገን በቃ በደል ያስፈራችሁ ፣
ኧረ ሕዝቤ ንቁ ዝሙት አያጥቃችሁ ፣
ኧረ አዳሜ ንቁ ሙስና ይብቃችሁ ፣
ኧረ ሔዋን ንቁ ውበት አይግዛችሁ ፣
ይሁዳ እና ቀራጭ መሆን ይለፋችሁ ፣
ሳኦልም ሳውልም መሆን ይቆያችሁ ፣
ጳውሎስ ወይ ማትያስ መሆን አለባችሁ ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 10/2014 ዓ•ም
√ " 🦜ወ 🦜ፎ 🦜ቹ 🦜"
•••
አያርሱም አያጭዱም ፣
አይለፉም አይደክሙም ፣
አይወጡም አይወርዱም ፣
አይነዱም አይበርዱም ፣
አይሞቁም አይግሉም ፣
አይሮጡም አይድኹም ፣
አያጡም አይነጡም ፣
አይዘጉም አይከፍቱም ፣
አይሄዱም አይመጡም ፣
አይቆርጡም አይፈልጡም ፣
አይሾሙም አይሽሩም ፣
አይሰጡም አይነሱም ፣
አይሰርቁም አይቀሙም ፣
🤷 ... በቃ ምን አለፋህ ...
አይወድቁም አይደክሙም ፣
ተስፋቸው ከላይ ነው ከላ...ይ ከአርያም ፣
መጋቢያቸው አለ ቸሩ መድኃኔዓለም ፣
እናትም አላቸው ቤዛዊተ ዓለም ፣
ተስፋቸው ይገርማል የሚያስቡት የለም ፣
ለመብል ለመጠጥ መጨናነቅ የለም ፣
በምስጋና ብቻ በዝማሬው ቀለም ፣
በልተው ይጠግባሉ ወፎቹ ዘለዓለም ።
በፍቅር ተወልደው በፍቅር ይሞታሉ ፣
እንዳንተ ዘር ብሔር ክልል ሳይከልሉ ፣
ቀበሌ ወረዳ ጎጥ ሳይከፋፍሉ ፣
መንደሩን ከአውራጃ ሳይገነጣጥሉ ፣
በፍቅር በመዋል በሰላም ያድራሉ ፣
ዋ! ወፎች ልዩ ናቸው ከእኛ ይለያሉ ።
እኛ ግን ለስሙ #አስተዋይ ተብለናል ፣
በራሱ በአምሣሉ በእርሱ #ተፈጥረናል ፣
~ ... ግን ... ግን ... ~
እንደ ሰው ቀርቶብን
እንደ ወፍ ለመሆን ብዙ #ይቀረናል ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 11/2014 ዓ•ም
•••
አያርሱም አያጭዱም ፣
አይለፉም አይደክሙም ፣
አይወጡም አይወርዱም ፣
አይነዱም አይበርዱም ፣
አይሞቁም አይግሉም ፣
አይሮጡም አይድኹም ፣
አያጡም አይነጡም ፣
አይዘጉም አይከፍቱም ፣
አይሄዱም አይመጡም ፣
አይቆርጡም አይፈልጡም ፣
አይሾሙም አይሽሩም ፣
አይሰጡም አይነሱም ፣
አይሰርቁም አይቀሙም ፣
🤷 ... በቃ ምን አለፋህ ...
አይወድቁም አይደክሙም ፣
ተስፋቸው ከላይ ነው ከላ...ይ ከአርያም ፣
መጋቢያቸው አለ ቸሩ መድኃኔዓለም ፣
እናትም አላቸው ቤዛዊተ ዓለም ፣
ተስፋቸው ይገርማል የሚያስቡት የለም ፣
ለመብል ለመጠጥ መጨናነቅ የለም ፣
በምስጋና ብቻ በዝማሬው ቀለም ፣
በልተው ይጠግባሉ ወፎቹ ዘለዓለም ።
በፍቅር ተወልደው በፍቅር ይሞታሉ ፣
እንዳንተ ዘር ብሔር ክልል ሳይከልሉ ፣
ቀበሌ ወረዳ ጎጥ ሳይከፋፍሉ ፣
መንደሩን ከአውራጃ ሳይገነጣጥሉ ፣
በፍቅር በመዋል በሰላም ያድራሉ ፣
ዋ! ወፎች ልዩ ናቸው ከእኛ ይለያሉ ።
እኛ ግን ለስሙ #አስተዋይ ተብለናል ፣
በራሱ በአምሣሉ በእርሱ #ተፈጥረናል ፣
~ ... ግን ... ግን ... ~
እንደ ሰው ቀርቶብን
እንደ ወፍ ለመሆን ብዙ #ይቀረናል ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 11/2014 ዓ•ም
"#ተረኛው ታፋኝ"
•••
👌 ማን ነበር ይኼ
መንጋ ነው መንግሥት ?
ብልጥግና የሚሉት ፣
ውርደቱን ተመለከትኩት ፣
ድድብናውን አጤንኩት ፣
እናም አዘንኩበት ፣
ደግሞም አዘንኩለት ፣
በኋላም ሳቅኩበት ፣
ተንከረከርኩበት ፣
አሽካካሁበት ፣
ይኼ እበት ፣
ገተት ፣
አልኩ እና ሰደብኩት ፣
እናንተም ስደቡት ።
•••
ሕጻን ልጅ በማገት ፤
አባትክን ውለድ ባይ ፣
መነኩሴ በመድፈር ፤
ወጣትን ሚጨቁን ፤
የመንደር አውደልዳይ ፣
ታዲያ መንጋ መንግሥት ፤
የታል ተዚህ በላይ ?
ሐሰቴን ከሆነ አሁን የገጠምኩት ፣
ነገ ጧት ያስገቡኝ ያው እንደለመዱት ፣
ሁሌ በቀን በቀን ፤
ልክ እንደ ተፈራ ስሜን ከሚፈሩት ፣
እንደ ኮስትር በላይ ነፍጠኛ እንደሚሉት ፣
እንደ ሸዋው ንጉሥ ጡት ቆራጭ እንዳሉት ፣
እየተሳቀቁ ስሜን ከሚፈሩት ፣
ነገ ጧት ያስገቡኝ እነርሱም ይረፉት ።
እኔም አልተው መግጠም እውነቱን መናገር ፣
ማንንም አልፈራ ከፈጣሪ በቀር ።
ዝም ብለህ ተኝተህ በፌስቡክ አውድማ ፣
ብልግና እየሠራህ በሚዲያ ከተማ ፣
ሰው ከምትተች ዘመድ ከምታማ ፣
ይልቅስ እውነት ጻፍ ወይ ሲነግሩህ ስማ ።
እኔ ግን ምን ነካኝ ግጥሜ ግጣም አጣ ፣
ዓምኻራ ዓይኑ ጠፋ በማንም ገሽላጣ ፣
ወገኔ ዓይኑን አጣ በመለስ መላጣ ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 17/2014 ዓ•ም
•••
👌 ማን ነበር ይኼ
መንጋ ነው መንግሥት ?
ብልጥግና የሚሉት ፣
ውርደቱን ተመለከትኩት ፣
ድድብናውን አጤንኩት ፣
እናም አዘንኩበት ፣
ደግሞም አዘንኩለት ፣
በኋላም ሳቅኩበት ፣
ተንከረከርኩበት ፣
አሽካካሁበት ፣
ይኼ እበት ፣
ገተት ፣
አልኩ እና ሰደብኩት ፣
እናንተም ስደቡት ።
•••
ሕጻን ልጅ በማገት ፤
አባትክን ውለድ ባይ ፣
መነኩሴ በመድፈር ፤
ወጣትን ሚጨቁን ፤
የመንደር አውደልዳይ ፣
ታዲያ መንጋ መንግሥት ፤
የታል ተዚህ በላይ ?
ሐሰቴን ከሆነ አሁን የገጠምኩት ፣
ነገ ጧት ያስገቡኝ ያው እንደለመዱት ፣
ሁሌ በቀን በቀን ፤
ልክ እንደ ተፈራ ስሜን ከሚፈሩት ፣
እንደ ኮስትር በላይ ነፍጠኛ እንደሚሉት ፣
እንደ ሸዋው ንጉሥ ጡት ቆራጭ እንዳሉት ፣
እየተሳቀቁ ስሜን ከሚፈሩት ፣
ነገ ጧት ያስገቡኝ እነርሱም ይረፉት ።
እኔም አልተው መግጠም እውነቱን መናገር ፣
ማንንም አልፈራ ከፈጣሪ በቀር ።
ዝም ብለህ ተኝተህ በፌስቡክ አውድማ ፣
ብልግና እየሠራህ በሚዲያ ከተማ ፣
ሰው ከምትተች ዘመድ ከምታማ ፣
ይልቅስ እውነት ጻፍ ወይ ሲነግሩህ ስማ ።
እኔ ግን ምን ነካኝ ግጥሜ ግጣም አጣ ፣
ዓምኻራ ዓይኑ ጠፋ በማንም ገሽላጣ ፣
ወገኔ ዓይኑን አጣ በመለስ መላጣ ።
•••
✍ #እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 17/2014 ዓ•ም
ዮሐንስ እና ካንጋሮ
•••
ወንድም ከወንድሙ በማይስማማበት ፣
አባቱ ከልጁ ጋር በማይግባባበት ፣
እናት ከሴት ልጇ በማታወራበት ፣
ዘመድ ከዘመዱ በተራራቀበት ፣
ወዳጅ ከወዳጁ በተኳረፈበት ፣
እጅግ ያስገርማል የእንስሳት ደግነት ።
~ ዳሩ ግን እውነት ነው ፤
እንስሳት ተሽለው ከሰው ብዙ ርቀው ፣
ከራሳቸው አልፎ ለሰው ልጆች አዝነው ፣
ከእኛ ያላዩትን ለእኛው አሳይተው ፣
ነቢይ ይወልዳሉ ከአምላክ ተቀብለው ።
ሰዎች ሲያሳድዷት ኤልሳቤጥ እናቱን ፣
ሄሮድስ ሲቀላው ዘካርያስ አባቱን ፣
ያለ ወላጅ ሲቀር ያለ እናት ብቻውን ፣
ካንጋሮ እናት ሆና አጥብታው ጡቶቿን ፣
ብርድ እንዳያገኘው በኪሷ ሸጉጣው ፣
ረሃብ እንዳይርበው አምላኳን ተማጽናው ፣
አሳድጋዋለች ዮሐንስን አዝላው ።
መቼም የእኔ ትውልድ በዚህ ባይማርም ፣
ሃቁ ውስጡ ገብቶ ደግነት ባይሠራም ፣
እውነታው ገዝፎበት ጭራሹን ባይራራም ፣
እኔ ግን ጽፌያለሁ ብትሰማም ባትሰማም ።
ሰው ሆይ! ተማር እንጂ ከሰው ከእንስሳቱ ፣
ከድንጋይ ከወንዙ ከሳሩ ከእንጨቱ ፣
ከገደል ከዱሩ ከምንጩ ከአለቱ ።
እንስሳት በልጠውህ ከሰው ጋ ሲሞቱ ፣
አንተ ስለት ይዘህ ቀጥል በመውጋቱ ፣
ወንድምህን ቅላ በሰይፍ በቀስቱ ።
አዲስ ዓመት መጣ አንተ ግን እዛው ነህ ፣
አዲስ ዘመን ጠባ ቤትህ ተቀምጠህ ፣
እስኪ ለዘንድሮ አንተም አዲስ ሆነህ ፣
ዘመኑን ምሠለው ዘመንህን ሆነህ ።
✍️ በዐምደ ብርሃን
•••
ወንድም ከወንድሙ በማይስማማበት ፣
አባቱ ከልጁ ጋር በማይግባባበት ፣
እናት ከሴት ልጇ በማታወራበት ፣
ዘመድ ከዘመዱ በተራራቀበት ፣
ወዳጅ ከወዳጁ በተኳረፈበት ፣
እጅግ ያስገርማል የእንስሳት ደግነት ።
~ ዳሩ ግን እውነት ነው ፤
እንስሳት ተሽለው ከሰው ብዙ ርቀው ፣
ከራሳቸው አልፎ ለሰው ልጆች አዝነው ፣
ከእኛ ያላዩትን ለእኛው አሳይተው ፣
ነቢይ ይወልዳሉ ከአምላክ ተቀብለው ።
ሰዎች ሲያሳድዷት ኤልሳቤጥ እናቱን ፣
ሄሮድስ ሲቀላው ዘካርያስ አባቱን ፣
ያለ ወላጅ ሲቀር ያለ እናት ብቻውን ፣
ካንጋሮ እናት ሆና አጥብታው ጡቶቿን ፣
ብርድ እንዳያገኘው በኪሷ ሸጉጣው ፣
ረሃብ እንዳይርበው አምላኳን ተማጽናው ፣
አሳድጋዋለች ዮሐንስን አዝላው ።
መቼም የእኔ ትውልድ በዚህ ባይማርም ፣
ሃቁ ውስጡ ገብቶ ደግነት ባይሠራም ፣
እውነታው ገዝፎበት ጭራሹን ባይራራም ፣
እኔ ግን ጽፌያለሁ ብትሰማም ባትሰማም ።
ሰው ሆይ! ተማር እንጂ ከሰው ከእንስሳቱ ፣
ከድንጋይ ከወንዙ ከሳሩ ከእንጨቱ ፣
ከገደል ከዱሩ ከምንጩ ከአለቱ ።
እንስሳት በልጠውህ ከሰው ጋ ሲሞቱ ፣
አንተ ስለት ይዘህ ቀጥል በመውጋቱ ፣
ወንድምህን ቅላ በሰይፍ በቀስቱ ።
አዲስ ዓመት መጣ አንተ ግን እዛው ነህ ፣
አዲስ ዘመን ጠባ ቤትህ ተቀምጠህ ፣
እስኪ ለዘንድሮ አንተም አዲስ ሆነህ ፣
ዘመኑን ምሠለው ዘመንህን ሆነህ ።
✍️ በዐምደ ብርሃን
~ ~ ~ ኤ ደ ን ~ ~ ~
አዳም አባቴ ከገነት ሲወጣ ፣
ለመኖር ወደ አንች መጣ ፣
የእኔዋ ኤደን ልቤ በፍቅር ሲራቆት ፣
በልብሽ መንደር አረፈበት ፣
እንደ ትልቅ ዛፍ ተጠለለበት ፣
እንደ ደብር አድባር መሸገበት ፣
ኤዱዋ የልቤ ትርታ የነፍሴ ገነት ።
• • •
ኤደን ቅድስቷ ግዮንን ያፈለቅሽ ፣
ኤፍራጥስን ያንፏፏሽ ፣
ጤግረስን ያንፎለፎልሽ ፣
ኤፌሶንን ያፈሰስሽ ፣
የእኔዋ ኤደን ከልብሽ ባለው ንጹሕ ፍቅርሽ ፣
ከውስጥሽ ባለው ሕያው ሰውነትሽ ፣
አዲሱ ምኒሊክ ተወለደብሽ ፣
ተስፈኛው ወጣት መነጨብሽ ፣
ስደተኛው አረፈብሽ ፣
ባይተዋሩ ተጽናናብሽ ።
• • •
~ ❤️ ኤ ዱ ❤️~
አምላክ አንችን ሲፈጥርሽ ፣
ከቀኝ ጎኔ ሲቀንስልሽ ፣
ከአጥንቴ ለአጥንትሽ ፣
ከሥጋዬ ለሥጋሽ ፣
ከነፍሴ ለነፍስሽ ፣
ከእስትንፋሴ ለእስትንፋስሽ ፣
ከእኔ ወስዶ ሲያበጃጅሽ ፣
ለአንች አስቦ እንዳይመስልሽ ፣
ለእኔ መሆኑ በደንብ ይግባሽ ።
~ አንችማ ኤዱ ~
የፍቅር ሃብታም ምን ጎሎብሽ ፣
የሰው የዋህ እንከን የለሽ ፣
የተስፋ እናት ምን ጠፍቶብሽ ፣
የህልም ዓለም ምን ቸግሮሽ ፣
የጥያቄ መልስ ሁኚ ያለሽ ፣
ሁሉ ያለሽ የተረፈሽ ፣
ለሰው ኗሪ አልፈሽ ተርፈሽ ፣
ደግ ሩኅሩኅ ስስት የሆንሽ ፣
አድርጎ ነው ያዘጋጀሽ ።
~ እናም ውዴ ~
ለምን ስሜን ኤደን አልከኝ ፣
ብለሽ ዛሬ ለጠየቅሽኝ ፣
በግጥም መልክ መልሴን ስሚኝ ።
• • •
ኤደን ስልሽ በምክንያት ነው ፦
ኤደን ሚሏት በሰማይ ቤት ፣
ግዮን ጤግረስ የሚያጠጧት ፣
ቅዱሳኑ ሚረኩባት ፣
ደናግሉ ሚኖሩባት ፣
የደስታ ምንጭ እስትንፋስ ናት ።
ኤደን ወንዝን እንዳፈለቀ ፣
ቅዱሳንን እንዳጸደቀ ፣
አዳምን እንዳደመቀ ፣
ደስታዎችን እንደሰነቀ ፣
~ እኔም በአንች ~
በፍቅርሽ ጸዳል ቀኔ ደምቋል ፣
በልብሽ ማይ ጥሜ ጠፍቷል ፣
በተስፋ ስንቅ ውስጤ ጎልቷል ፣
ማንነቴ ተመልሷል ፣
እስትንፋሴ ህያው ሆኗል ፣
~ እና ታዲያ ~
ኤዱ ብልሽ ያንስብሻል ?
ውዱ ልቤ ደክሞልሻል ፣
በፍቅርሽ ባሕር ሰጥሞልሻል ፣
ከውቅያኖስ ገብቶልሻል ፣
ኤዱ የእኔ ተፈቅረሻል ።
••••
አፍቃሪሽ
ሚ ኒ
አዳም አባቴ ከገነት ሲወጣ ፣
ለመኖር ወደ አንች መጣ ፣
የእኔዋ ኤደን ልቤ በፍቅር ሲራቆት ፣
በልብሽ መንደር አረፈበት ፣
እንደ ትልቅ ዛፍ ተጠለለበት ፣
እንደ ደብር አድባር መሸገበት ፣
ኤዱዋ የልቤ ትርታ የነፍሴ ገነት ።
• • •
ኤደን ቅድስቷ ግዮንን ያፈለቅሽ ፣
ኤፍራጥስን ያንፏፏሽ ፣
ጤግረስን ያንፎለፎልሽ ፣
ኤፌሶንን ያፈሰስሽ ፣
የእኔዋ ኤደን ከልብሽ ባለው ንጹሕ ፍቅርሽ ፣
ከውስጥሽ ባለው ሕያው ሰውነትሽ ፣
አዲሱ ምኒሊክ ተወለደብሽ ፣
ተስፈኛው ወጣት መነጨብሽ ፣
ስደተኛው አረፈብሽ ፣
ባይተዋሩ ተጽናናብሽ ።
• • •
~ ❤️ ኤ ዱ ❤️~
አምላክ አንችን ሲፈጥርሽ ፣
ከቀኝ ጎኔ ሲቀንስልሽ ፣
ከአጥንቴ ለአጥንትሽ ፣
ከሥጋዬ ለሥጋሽ ፣
ከነፍሴ ለነፍስሽ ፣
ከእስትንፋሴ ለእስትንፋስሽ ፣
ከእኔ ወስዶ ሲያበጃጅሽ ፣
ለአንች አስቦ እንዳይመስልሽ ፣
ለእኔ መሆኑ በደንብ ይግባሽ ።
~ አንችማ ኤዱ ~
የፍቅር ሃብታም ምን ጎሎብሽ ፣
የሰው የዋህ እንከን የለሽ ፣
የተስፋ እናት ምን ጠፍቶብሽ ፣
የህልም ዓለም ምን ቸግሮሽ ፣
የጥያቄ መልስ ሁኚ ያለሽ ፣
ሁሉ ያለሽ የተረፈሽ ፣
ለሰው ኗሪ አልፈሽ ተርፈሽ ፣
ደግ ሩኅሩኅ ስስት የሆንሽ ፣
አድርጎ ነው ያዘጋጀሽ ።
~ እናም ውዴ ~
ለምን ስሜን ኤደን አልከኝ ፣
ብለሽ ዛሬ ለጠየቅሽኝ ፣
በግጥም መልክ መልሴን ስሚኝ ።
• • •
ኤደን ስልሽ በምክንያት ነው ፦
ኤደን ሚሏት በሰማይ ቤት ፣
ግዮን ጤግረስ የሚያጠጧት ፣
ቅዱሳኑ ሚረኩባት ፣
ደናግሉ ሚኖሩባት ፣
የደስታ ምንጭ እስትንፋስ ናት ።
ኤደን ወንዝን እንዳፈለቀ ፣
ቅዱሳንን እንዳጸደቀ ፣
አዳምን እንዳደመቀ ፣
ደስታዎችን እንደሰነቀ ፣
~ እኔም በአንች ~
በፍቅርሽ ጸዳል ቀኔ ደምቋል ፣
በልብሽ ማይ ጥሜ ጠፍቷል ፣
በተስፋ ስንቅ ውስጤ ጎልቷል ፣
ማንነቴ ተመልሷል ፣
እስትንፋሴ ህያው ሆኗል ፣
~ እና ታዲያ ~
ኤዱ ብልሽ ያንስብሻል ?
ውዱ ልቤ ደክሞልሻል ፣
በፍቅርሽ ባሕር ሰጥሞልሻል ፣
ከውቅያኖስ ገብቶልሻል ፣
ኤዱ የእኔ ተፈቅረሻል ።
••••
አፍቃሪሽ
ሚ ኒ
😭😢😰 ~ እኔን ወንድማለም ~ 😢😰😥
•••
አለማወቅ ደጉ ምንኛ ድንቅ ነው ፣
ሰውን አለመቅረብ እንዴት መታደል ነው ፣
አንተን ባውቅህ አይደል እንዲህ የማለቅሰው ።
እናትህ በደስታ ለሰርግህ ስትደግስ ፣
አባትህ በሀሴት ለጫጉላህ ሲያሳርስ ፣
ወንድምህ ለአዱኛህ መሠረትክን ሲምስ ፣
እህትህ ለፌሽታህ እንጀራ ስታስስ ፣
~ አንተ ግን ~
ሰርጉን ከቁብ ሳትቆጥር ትተህ አናንቀህ ፣
እንዲያ እየጠበቁህ እናትህ አባትህ ፣
እንዲያ እየናፈቁህ እህት ወንድሞችህ ፣
እንዲያ እየሳሱልህ ዘመድ አዝማዶችህ ፣
ትትኻቸው ሮጥክ ለላይ ቤቱ ሰርግህ ።
😥
•••
አወይ የሰው ነገር የእኛ መጨረሻ ፣
ፈራሽ እንደ ሸክላ ተናጂ እንደ ዋሻ ።
ትላንት ታይተን ዛሬ እንዲህ ለምንጠፋው ፣
በሰዓት በቅጽበት ለምንሰበረው ፣
በጠዋት በማታ ወድቀን ለምንቀረው ፣
በገደል በዋሻ ለምንቀበረው ፣
በሰይፍ በክላሽ ለምንጋደመው ፣
መጨካከናችን ከቶ ለምንድን ነው ።
~ ልጥገብ ~
እናትህ አባትህ ሁኔታቸው ታየኝ ፣
የእህት ወንድሞችህ እንባቸው አጠበኝ ፣
የዘመድ አዝማዱ ሲቃው አስለቀሰኝ ፣
ሰፈር ጎረቤቱ እሮሮው አባባኝ ፣
የትልቅ ትንሹ ኃዘኑ ገረፈኝ ፣
በድንህን ስልከው እኔን ግን አስቻለኝ ።
😰
•••
ምናለ ባላውቅህ ባልሰማ ምክርህን ፣
አብሬህ ባልበላ ባልጠጣ ፍቅርህን ።
አሁን ነው የገባኝ የምክርህ ውጤቱ ፣
ዛሬ ነው የታየኝ የፍቅርህ ጉልበቱ ፣
እኔ ብንገላታም ታድሏል መሬቱ ፣
አንተን ተንተርሷል ሰምሮለት ጸሎቱ ፣
ምንኛ ደስ ይለው አንተን በማግኘቱ ።
የልጅ አዋቂ ነህ ሃሳብህ ተራራ ፣
ውሸት የምትጠላ ጌታን የምትፈራ ።
ምናለ ሲፈጥረኝ አፈር ባደረገኝ ፣
አንተን ከሰው መርጦ ለራሴ እንዲሰጠኝ ።
ምናለ ከእንግዲህ ምስጥ ባደረገኝ ፣
ልጥገበው ገላህን መዓዛህ ያውደኝ ።
እንዴት ቢጸልይ ነው አፈሩ መሬቱ ፣
ልጥገብ የአንተን ገላ በነጻ ማግኘቱ ።
~ ለነገሩ ~
እሱም አምላክ አለው ሚሰማው ጸሎቱን ፣
ይኸው ዛሬም ሰጠው አንተን መኳንንቱን ።
ምናሉ ሰዎቹ ለቅሶህን ሲሰሙ ፣
ምናሉ ጎረቤት ሞትህን ሲሰሙ ፣
ለሰርግህ ደግሰው በአንተ ሲታመሙ ።
እያለህ መካሪ ስትሞት አስተማሪ ፣
መዋቲ መሆኔን በሞትህ አብሳሪ ።
ዛሬ ነው የገባኝ ሞት እንደሚወስደኝ ፣
አንተን መሳይ ወንድም ከክንዴ ሲነጥቀኝ ፣
አለኝታ ጋሻዬን አታሎ ሲሰርቀኝ ፣
እኔም ሰው መሆኔ ዛሬ ነው የገባኝ ።
ላደረግከው ነገር እኔን ለመቀየር ፣
ለለፋኸው ልፋት ለጣርካው መጣጣር ፣
ሰው ከፍሎ አይችለውም ከፈጣሪ በቀር ።
እንዲያ እንደናፈቀከው በጠዋት በማታ ፣
እንዳገለገልከው በሀሴት በደስታ ፣
እንደዘመርክለት በክራር በእምቢልታ ፣
ዛሬ ጠቅልለህ ሄድክ ከሰማዩ ጌታ ።
😥
•••
ስትወጣ ስትገባ መዝሙር እየዘመርክ ፣
ስትሄድ ስትቀመጥ ምስጋና እያቀረብክ ፣
ታዲያ እንዴት ልተውህ እንዴት ብዬስ ልርሳክ ።
እኛ የምናውቀው ዶክተር ሲያስመርቅ ነው ፣
ሲባል የሰማነው ምሑር ሲያፈልቅ ነው ፣
ሲሆንም ያየነው ልሒቅ ሲያፈራ ነው ፣
ዛሬ ለአንተ ሲያለቅስ ማርቆስ ምን ተሰማው ።
እናትህ እድሏ አባትህ መከራው ፣
እህትህ ስቃይዋ ወንድምህ ፈተናው ፣
ጓደኛህ ኃዘኑ ወዳጅህ ሮሮው ፣
እንዴት ሊችሉት ነው መች ጨረሱህ ጠግበው ።
😥
~ ስንብት ~
መሄድህ ካልቀረ ንሳ ሰላም በለን ፣
መጓዝህ ካልቀረ ቻው ብለህ ተለየን ፣
መንገድህን ካልተውክ ተመለሱ በለን ፣
እኛም እኮ ደከምን አንተን ተከትለን ።
~ እኔ ምለው ልጥገብ ~
ምነው ሆድህ ቻለው እናትህን ተውካት ፣
የአባትህን ሲቃ እንባ ሳትጠርግለት ፣
የእህትህን ተስፋ ዋይታ ጭነህበት ፣
ወንድምህን ገድለህ አረም ጥለህበት ፣
ልጥገብ እንዴት ቻልከው የዘመዱን ጩኸት ።
~ እኛማ ~
እኛ ወደ አንተ እንጂ አንተስ አትመጣም ፣
ብንከተል እንጂ አትከተለንም ፣
ብትመራን እንጂ በእኛስ አትመራም ፣
ከእንግዲህ ወደ እኛ አትጠረጠርም ።
አደራ መሬቱ ለአፈሩም ንገረው ፣
የልጥገብን ገላ ምስጥ እንዳያፈርሰው ፣
የወንድሜን ውበት አፈር እንዳይበላው ፣
እንደራሴ አድርገህ ወንድሜን ጠብቀው ፣
እኔም ቀኔ ደርሶ መጥቼ እስከማየው ።
• • •
✍ ዐምደ ብርሃን
😭😭😭😭😭😭😭😭😭
•••
አለማወቅ ደጉ ምንኛ ድንቅ ነው ፣
ሰውን አለመቅረብ እንዴት መታደል ነው ፣
አንተን ባውቅህ አይደል እንዲህ የማለቅሰው ።
እናትህ በደስታ ለሰርግህ ስትደግስ ፣
አባትህ በሀሴት ለጫጉላህ ሲያሳርስ ፣
ወንድምህ ለአዱኛህ መሠረትክን ሲምስ ፣
እህትህ ለፌሽታህ እንጀራ ስታስስ ፣
~ አንተ ግን ~
ሰርጉን ከቁብ ሳትቆጥር ትተህ አናንቀህ ፣
እንዲያ እየጠበቁህ እናትህ አባትህ ፣
እንዲያ እየናፈቁህ እህት ወንድሞችህ ፣
እንዲያ እየሳሱልህ ዘመድ አዝማዶችህ ፣
ትትኻቸው ሮጥክ ለላይ ቤቱ ሰርግህ ።
😥
•••
አወይ የሰው ነገር የእኛ መጨረሻ ፣
ፈራሽ እንደ ሸክላ ተናጂ እንደ ዋሻ ።
ትላንት ታይተን ዛሬ እንዲህ ለምንጠፋው ፣
በሰዓት በቅጽበት ለምንሰበረው ፣
በጠዋት በማታ ወድቀን ለምንቀረው ፣
በገደል በዋሻ ለምንቀበረው ፣
በሰይፍ በክላሽ ለምንጋደመው ፣
መጨካከናችን ከቶ ለምንድን ነው ።
~ ልጥገብ ~
እናትህ አባትህ ሁኔታቸው ታየኝ ፣
የእህት ወንድሞችህ እንባቸው አጠበኝ ፣
የዘመድ አዝማዱ ሲቃው አስለቀሰኝ ፣
ሰፈር ጎረቤቱ እሮሮው አባባኝ ፣
የትልቅ ትንሹ ኃዘኑ ገረፈኝ ፣
በድንህን ስልከው እኔን ግን አስቻለኝ ።
😰
•••
ምናለ ባላውቅህ ባልሰማ ምክርህን ፣
አብሬህ ባልበላ ባልጠጣ ፍቅርህን ።
አሁን ነው የገባኝ የምክርህ ውጤቱ ፣
ዛሬ ነው የታየኝ የፍቅርህ ጉልበቱ ፣
እኔ ብንገላታም ታድሏል መሬቱ ፣
አንተን ተንተርሷል ሰምሮለት ጸሎቱ ፣
ምንኛ ደስ ይለው አንተን በማግኘቱ ።
የልጅ አዋቂ ነህ ሃሳብህ ተራራ ፣
ውሸት የምትጠላ ጌታን የምትፈራ ።
ምናለ ሲፈጥረኝ አፈር ባደረገኝ ፣
አንተን ከሰው መርጦ ለራሴ እንዲሰጠኝ ።
ምናለ ከእንግዲህ ምስጥ ባደረገኝ ፣
ልጥገበው ገላህን መዓዛህ ያውደኝ ።
እንዴት ቢጸልይ ነው አፈሩ መሬቱ ፣
ልጥገብ የአንተን ገላ በነጻ ማግኘቱ ።
~ ለነገሩ ~
እሱም አምላክ አለው ሚሰማው ጸሎቱን ፣
ይኸው ዛሬም ሰጠው አንተን መኳንንቱን ።
ምናሉ ሰዎቹ ለቅሶህን ሲሰሙ ፣
ምናሉ ጎረቤት ሞትህን ሲሰሙ ፣
ለሰርግህ ደግሰው በአንተ ሲታመሙ ።
እያለህ መካሪ ስትሞት አስተማሪ ፣
መዋቲ መሆኔን በሞትህ አብሳሪ ።
ዛሬ ነው የገባኝ ሞት እንደሚወስደኝ ፣
አንተን መሳይ ወንድም ከክንዴ ሲነጥቀኝ ፣
አለኝታ ጋሻዬን አታሎ ሲሰርቀኝ ፣
እኔም ሰው መሆኔ ዛሬ ነው የገባኝ ።
ላደረግከው ነገር እኔን ለመቀየር ፣
ለለፋኸው ልፋት ለጣርካው መጣጣር ፣
ሰው ከፍሎ አይችለውም ከፈጣሪ በቀር ።
እንዲያ እንደናፈቀከው በጠዋት በማታ ፣
እንዳገለገልከው በሀሴት በደስታ ፣
እንደዘመርክለት በክራር በእምቢልታ ፣
ዛሬ ጠቅልለህ ሄድክ ከሰማዩ ጌታ ።
😥
•••
ስትወጣ ስትገባ መዝሙር እየዘመርክ ፣
ስትሄድ ስትቀመጥ ምስጋና እያቀረብክ ፣
ታዲያ እንዴት ልተውህ እንዴት ብዬስ ልርሳክ ።
እኛ የምናውቀው ዶክተር ሲያስመርቅ ነው ፣
ሲባል የሰማነው ምሑር ሲያፈልቅ ነው ፣
ሲሆንም ያየነው ልሒቅ ሲያፈራ ነው ፣
ዛሬ ለአንተ ሲያለቅስ ማርቆስ ምን ተሰማው ።
እናትህ እድሏ አባትህ መከራው ፣
እህትህ ስቃይዋ ወንድምህ ፈተናው ፣
ጓደኛህ ኃዘኑ ወዳጅህ ሮሮው ፣
እንዴት ሊችሉት ነው መች ጨረሱህ ጠግበው ።
😥
~ ስንብት ~
መሄድህ ካልቀረ ንሳ ሰላም በለን ፣
መጓዝህ ካልቀረ ቻው ብለህ ተለየን ፣
መንገድህን ካልተውክ ተመለሱ በለን ፣
እኛም እኮ ደከምን አንተን ተከትለን ።
~ እኔ ምለው ልጥገብ ~
ምነው ሆድህ ቻለው እናትህን ተውካት ፣
የአባትህን ሲቃ እንባ ሳትጠርግለት ፣
የእህትህን ተስፋ ዋይታ ጭነህበት ፣
ወንድምህን ገድለህ አረም ጥለህበት ፣
ልጥገብ እንዴት ቻልከው የዘመዱን ጩኸት ።
~ እኛማ ~
እኛ ወደ አንተ እንጂ አንተስ አትመጣም ፣
ብንከተል እንጂ አትከተለንም ፣
ብትመራን እንጂ በእኛስ አትመራም ፣
ከእንግዲህ ወደ እኛ አትጠረጠርም ።
አደራ መሬቱ ለአፈሩም ንገረው ፣
የልጥገብን ገላ ምስጥ እንዳያፈርሰው ፣
የወንድሜን ውበት አፈር እንዳይበላው ፣
እንደራሴ አድርገህ ወንድሜን ጠብቀው ፣
እኔም ቀኔ ደርሶ መጥቼ እስከማየው ።
• • •
✍ ዐምደ ብርሃን
😭😭😭😭😭😭😭😭😭
መወድስ ... መቀንጥስ
...///....
እባክህን አምላክ እባክህን ጌታ ፣
የፍጥረታት ንጉሥ የሰው ልጅ አለኝታ ።
አንዴ ... ልለምንህ 🙏
ሙሴን መሆን ሚችል መሪ ባናገኝም ፣
ባህር ሚከት እንጅ ሚያወጣን ባይኖርም ፣
አንደበት ሚሆነን አሮንን ባንወልድም ፣
አንድ አልያስ ስጠን ሰማይ የሚለጉም ።
..//..
ሰማይ ብትከፍት አይደል እንዲህ የሚደፍሩህ ፣
ዝናብ ብትሰጥ አይደል እንዲህ የሚሰድቡህ ፣
አየር ብትሰጥ አይደል እንዲህ የሚሰቅሉህ ፣
መልክህን የሚያርዱት አንተን ሚያሳዝኑህ ፣
ኤልያስ ባይኖር ነው ከብሮ ሚያስከብርህ ።
..// እናም ..//
ኤልያስን ስጠን ሙሴ ጥንቅር ይበል ፣
መሪ አንተ ከሆንከን ባህር ይፈራናል ፣
ሰማይ ሚቆልፍ ብቻ ኤልያስ ይበቃል ።
© ዐምደ ብርሃን
...///....
እባክህን አምላክ እባክህን ጌታ ፣
የፍጥረታት ንጉሥ የሰው ልጅ አለኝታ ።
አንዴ ... ልለምንህ 🙏
ሙሴን መሆን ሚችል መሪ ባናገኝም ፣
ባህር ሚከት እንጅ ሚያወጣን ባይኖርም ፣
አንደበት ሚሆነን አሮንን ባንወልድም ፣
አንድ አልያስ ስጠን ሰማይ የሚለጉም ።
..//..
ሰማይ ብትከፍት አይደል እንዲህ የሚደፍሩህ ፣
ዝናብ ብትሰጥ አይደል እንዲህ የሚሰድቡህ ፣
አየር ብትሰጥ አይደል እንዲህ የሚሰቅሉህ ፣
መልክህን የሚያርዱት አንተን ሚያሳዝኑህ ፣
ኤልያስ ባይኖር ነው ከብሮ ሚያስከብርህ ።
..// እናም ..//
ኤልያስን ስጠን ሙሴ ጥንቅር ይበል ፣
መሪ አንተ ከሆንከን ባህር ይፈራናል ፣
ሰማይ ሚቆልፍ ብቻ ኤልያስ ይበቃል ።
© ዐምደ ብርሃን
ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ ንጉሥ ምኒሊክ ጀግንነቱ ወእምነቱ በዘመናችን ይደር!
••//••
ማርያም ብሎ ጠርቶ የማይደራደር ፣
በስሟ በክብሯ የማይጠራጠር ፣
ሸዋን ግዛ ሚሉት ደግ ንጉሥ ነበር ።
ሣህለ ማርያም የጊዮርጊስ ወዳጅ ፣
የጠላት ማርከሻ የወንበዴ አሳዳጅ ።
እናትህ ከመቅደስ ታጅባ ገብታለች ፣
ምኒሊክ እያለች ትፈልግሃለች ።
እሷ መቅደስ ገብታ አንተን ስትፈልግህ ፣
ከላይ ቤቱ ቤትህ ማን ነው የወሰደህ ?
እምዬ እርሶን ወስዶ አማኝ ንጉሣችን ፣
ምኒሊክ እግዚአብሔር አምባ መጠጊያችን ።
••//••
••//••
ማርያም ብሎ ጠርቶ የማይደራደር ፣
በስሟ በክብሯ የማይጠራጠር ፣
ሸዋን ግዛ ሚሉት ደግ ንጉሥ ነበር ።
ሣህለ ማርያም የጊዮርጊስ ወዳጅ ፣
የጠላት ማርከሻ የወንበዴ አሳዳጅ ።
እናትህ ከመቅደስ ታጅባ ገብታለች ፣
ምኒሊክ እያለች ትፈልግሃለች ።
እሷ መቅደስ ገብታ አንተን ስትፈልግህ ፣
ከላይ ቤቱ ቤትህ ማን ነው የወሰደህ ?
እምዬ እርሶን ወስዶ አማኝ ንጉሣችን ፣
ምኒሊክ እግዚአብሔር አምባ መጠጊያችን ።
••//••
☆ ሀ_ሴቴ ☆
•••
ፍቅር ጠምቶኝ ፍቅር ናፍቆኝ ፣
ብቸኝነት ሲያሳቅቀኝ ፣
ባይተዋርነት ሲያስለቅሰኝ ፣
ሰማይ ምድሩ ሲርቅብኝ ፣
ዘመድ ወዳጅ ሲስቅብኝ ፣
•
•
•
•
የሁሉ አምላክ የላከልኝ ፣
ሀ_ሴት ብሎ የሾመልኝ ።
•••
እሱ ቢሰጥ አያልቅበት ፣
እሱ ቢሾም አይጎድልበት ፣
ጠዋት ማታ አይነጥፍበት ፣
አንችን ሰጠኝ ለበረከት ።
ሀ_ሴቴ ደስታዬ ፤
ሀ_ሴቴ ስኬቴ ፣
ሀ_ሴቴ ውበቴ ፤
ሀ_ሴቴ ድምቀቴ ፣
ሀ_ሴቴ ግርማዬ ፤
ሀ_ሴቴ እኔነቴ ፣
ሀ_ሴቴ ረሃቤ ፤
ሀ_ሴቴ ናፍቆቴ ፣
ሀ_ሴቴ መሪዬ ፤
ሀ_ሴቴ ጉልበቴ ፣
ሀ_ሴቴ ልደቴ ፣
ሀ_ሴቴ ሕይወቴ ፣
•••
ዘመኔን ከአንች ጋር ማርጀትን እሻለሁ ፣
እንደ አባት ወንድምሽ እሆንልሻለሁ ፣
አይቼ አልጠግብሽም እሳሳልሻለሁ ፣
የቤትሽ ምሦሦ ራስ እሆናለሁ ፣
ዘወትር እንደ አዲስ ሳፈቅርሽ ኖራለሁ ፣
እንደ እናት እንደ እህት እመካብሻለሁ ፣
ፈጣሪ እንደሰጠኝ ተቀብዬሻለሁ ፣
ለፍቅርሽ አምኃ ልቤን ሰጥቻለሁ ።
ሀ_ሴቴ አፈቅርሻለሁ ፣
ሀ_ሴቴ እወዳሻለሁ ፣
ሀ_ሴቴ ራሴን እሰጥሻለሁ ።
☆ ☆ ☆
ሀ_ሴትዬ የእኔ ውድ ....... ከዚህ በላይ ብልሽ ደስ ይለኛል። ግን አልችልም።
© ᵞᴱ'ᴬᴮᵀˢᴱᴳᴬ ᵞᴱ ᴴᴬˢˢᴱᵀ 💥
•••
ፍቅር ጠምቶኝ ፍቅር ናፍቆኝ ፣
ብቸኝነት ሲያሳቅቀኝ ፣
ባይተዋርነት ሲያስለቅሰኝ ፣
ሰማይ ምድሩ ሲርቅብኝ ፣
ዘመድ ወዳጅ ሲስቅብኝ ፣
•
•
•
•
የሁሉ አምላክ የላከልኝ ፣
ሀ_ሴት ብሎ የሾመልኝ ።
•••
እሱ ቢሰጥ አያልቅበት ፣
እሱ ቢሾም አይጎድልበት ፣
ጠዋት ማታ አይነጥፍበት ፣
አንችን ሰጠኝ ለበረከት ።
ሀ_ሴቴ ደስታዬ ፤
ሀ_ሴቴ ስኬቴ ፣
ሀ_ሴቴ ውበቴ ፤
ሀ_ሴቴ ድምቀቴ ፣
ሀ_ሴቴ ግርማዬ ፤
ሀ_ሴቴ እኔነቴ ፣
ሀ_ሴቴ ረሃቤ ፤
ሀ_ሴቴ ናፍቆቴ ፣
ሀ_ሴቴ መሪዬ ፤
ሀ_ሴቴ ጉልበቴ ፣
ሀ_ሴቴ ልደቴ ፣
ሀ_ሴቴ ሕይወቴ ፣
•••
ዘመኔን ከአንች ጋር ማርጀትን እሻለሁ ፣
እንደ አባት ወንድምሽ እሆንልሻለሁ ፣
አይቼ አልጠግብሽም እሳሳልሻለሁ ፣
የቤትሽ ምሦሦ ራስ እሆናለሁ ፣
ዘወትር እንደ አዲስ ሳፈቅርሽ ኖራለሁ ፣
እንደ እናት እንደ እህት እመካብሻለሁ ፣
ፈጣሪ እንደሰጠኝ ተቀብዬሻለሁ ፣
ለፍቅርሽ አምኃ ልቤን ሰጥቻለሁ ።
ሀ_ሴቴ አፈቅርሻለሁ ፣
ሀ_ሴቴ እወዳሻለሁ ፣
ሀ_ሴቴ ራሴን እሰጥሻለሁ ።
☆ ☆ ☆
ሀ_ሴትዬ የእኔ ውድ ....... ከዚህ በላይ ብልሽ ደስ ይለኛል። ግን አልችልም።
© ᵞᴱ'ᴬᴮᵀˢᴱᴳᴬ ᵞᴱ ᴴᴬˢˢᴱᵀ 💥