Notice: file_put_contents(): Write of 10891 bytes failed with errno=28 No space left on device in /var/www/tg-me/post.php on line 50
TIKVAH-MAGAZINE | Telegram Webview: tikvahethmagazine/19352 -
Telegram Group & Telegram Channel
ወ/ሮ ማርታ ገብረ ጻዲቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ በ91ኛ ዓመት የልደት ቀናቸው እውቅና ተሰጣቸው

የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ወዳጆች ማኅበር ለወ/ሮ ማርታ ገብረ ጻዲቅ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ሥራና አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሴት በሚል እውቅና ሰጥቷቸዋል።

ወ/ሮ ማርታ ገ/ጻዲቅ በ ቀ.ኃ.ሥ ዘመነ መንግስት የመጀመሪያዋ ሴት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል እና የፕሮጀክት ሜርሲ መስራች ናቸው።

ማኅበሩ ያሰናዳው መድረክም የእውቅና የማስታወሻ መድረክም በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ግቢ ራስ መኮንን አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን የወ/ሮ ማርታ ገብረ ጻድቅ የ 91ኛ ዓመት የልደት ቀናቸውም በዕለቱ ተከብሯል።

ወ/ሮ ማርታ፥ ከባለቤታቸው ጋር በመሠረቱት ፕሮጀክት "ሜርሲ" ከመነሻው ጀምሮ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላደረጉት የበጎ አድራጎት ሥራ በአሜሪካን ሀገር "#የዓመቱ_እናት" የተባሉ ሲሆን ከTaylor University ሁለቱም የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።

የህይወት ታሪካቸው ሲነገርም፥ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የውጭ ሀገር ሴት የበረራ አስተናጋጆችን ሲያዩ ይቆጩ እንደነበርና በሄዱበት ሁሉ የሚያያዋቸውን ሎጋና መልከ መልካም ሴቶች እያግባቡና እያስተማሩ / እያስረዱ ወደ አውሮፕላን የበረራ አስተናጋጃነት ሥራ እንመጡ አድርገዋል።

በ1967 ዓ.ም የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት፣ ለእስር ሊዳርጋቸው እንደሆነ በመስማታቸው ያላቸውን ንብረት ጥለው ከአዲስ አበባ ተነስተው የሰባት ቀን አድካሚ ጉዞ በማድረግ ወደ ኬንያ ተሰደዱ፡፡

ከኬንያ የስደት ቆይታ ወደ ግሪክ ሌላ የስደት ሕይወት አመሩ፡፡ በግሪክ ቆይታቸው ላይ ዘላቂ የሆኑና እስከአሁንም ድረስ የተተገበሩ እና በመተግበር ላይ የሚገኙትን ልዩ ልዩ ሰብዓዊ ተግባራትና ስራዎችን ለመጀመር ቻሉ፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ በተከሰተው ድርቅ ኢትዮጵያም በእጅጉ ተጎድታ ስለነበረ (1977) ሕፃናትን ለመታደግ ወ/ሮ ማርታ "#አጥሚት" የሚባለውን አልሚ ምግብ አስተዋወቁ፡፡

ይህ አልሚ ምግብም በአሜሪካን አገር የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ድርጅት ታይቶ ዕውቅና እንዲሰጠው ለማድረግ በመቻሉ በድርቁ ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን በመላክ የብዙ ሰው ህይወትን ማዳን ተችሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ወደተለያዩ 30 አገራት ይህንን አጥሚት የተሰኘ አልሚ ምግብ በመላክ የህፃናትን ሕይወት በመታደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተደርጓል፡፡

@tikvahethmagazine

tg-me.com/tikvahethmagazine/19352
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-MAGAZINE

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethmagazine/19352

View MORE
Open in Telegram

TIKVAH MAGAZINE Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Telegram Auto-Delete Messages in Any Chat

Some messages aren’t supposed to last forever. There are some Telegram groups and conversations where it’s best if messages are automatically deleted in a day or a week. Here’s how to auto-delete messages in any Telegram chat. You can enable the auto-delete feature on a per-chat basis. It works for both one-on-one conversations and group chats. Previously, you needed to use the Secret Chat feature to automatically delete messages after a set time. At the time of writing, you can choose to automatically delete messages after a day or a week. Telegram starts the timer once they are sent, not after they are read. This won’t affect the messages that were sent before enabling the feature.

TIKVAH MAGAZINE from ms

Telegram TIKVAH-MAGAZINE
FROM USA