Telegram Group Search
ሙስሊም ብሎ ማለት እጅና እግሩን ለአሏህ የሰጠ ማለት ነው ሌላው ደግሞ
መገለጫው ሰላም ነው አጉል ህውከት ማንሳት ረብሻ ሰዎችን አዛ ሚያደርግ አሳቃቂ ከሆኑ ነገሮች ሁሉ የተቆጠበ ነው
ታዲያ እኔ እና አንተ አንቺ እኛ ከላይ የተጠቀሱትን እንወክላለን ወዳጆቼ??
መልካምና የተባረከ የአሏህ
ባሪያ መሆንን ይወፍቀን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇https://www.tg-me.com/muhammed ye allha bariya/com.muneshidmuhammed
https://www.tg-me.com/muhammed ye allha bariya/com.muneshidmuhammed
Audio
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጁመዓ ሙባረክ❤️❤️❤️😍😍😍ሀያያያያትትት
ለእናቶቻችን በደስታ በኢማን በዓማን ያኑርልን
ውዶችዬ አሚን በሉሉ!!!
ወደ ሐበሻ ተሰደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ በሀገራችን ከኖሩና እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ካለፉ የረሱላችንﷺ ባልደረቦች[ሱሐቦች] መካከል እኚህ ታላቅ ሱሐባ ዑደይ ኢብኑ ነድላ አንዱ ናቸው[رضي الله عنهم]

"ወደ ሐበሻ ከመጡ ሱሐቦች ውስጥ ቀድመው ወደ አኺራ የተሻገሩ የመጀመሪያው ሰው" በሚልም የታሪክ ድርሳናት የጻፉ ሲሆን በተጨማሪም በኢስላም የውርስ ህግ የመጀመሪያው ተወራሽ ሰው ናቸው ይባላል።ምክንያቱም እርሳቸው ሲያልፉ አብሯቸው የመጣው ልጃቸው ኑዕማን ወራሻቸው ሆኗልና ይላሉ።


የታላቁ ሱሐባ የዑደይ ቀብር ንጉስ ነጃሺን ዘይራችሁ ስትወጡ በስተቀኝ በኩል የሚገኝ ሲሆን ገና ለመዘየር ስትገቡ ደግሞ በስተግራ አቅጣጫ ይገኛል።

በገናናውና በቀደምቱ የኢትዮያዊያን ሙስሊሞች ታሪክ ውስጥ እንደዚህ ስፍራ ልዩና ሰላም ያለው ቦታ ያለ አይመስለኝም።ልክ እዚህ ስትደርሱ 7ኛው ክፍለ ዘመን በአይነ ህሊናችሁ ይመጣል።የንጉሱ ሁኔታ፣የሱሐቦች እንግድነት፤ ያ ወርቃማ ታሪክ ድቅን ይልባችኋል።

ይህ ድንቅ ታሪክ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ልብ ብቻ ሳይሆን በመላው ሙስሊሞች ልብ የማይጠፋ የኢስላም ደማቁ ታሪክ ነው።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ፕሮግራሙን አመቻችቶ ሊዘይረው የሚገባ፤የትኛውም ኢትዮያጵያዊም ታሪኬ ነው ብሎ ሊጎበኘው የሚመርጠው ድንቅ ስፍራ ነው።እንደውም እኔ ባስተዋልኩት ከሆነ ከዓሹራ ውጭ ቀላል ቁጥር የማይባሉ ሙስሊም ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ይጎበኙታል።የውጭ ቱሪስቶችም እንዲሁ!

ከመዲናችን አዲስ አበባ 790 ኪ.ሜ፣ከመቐለ 60 ኪ.ሜ ከውቅሮ ከተማ አቅራቢያ ልዩ ስሙ ነጃሺ በተባለ ስፍራ ይገኛል። አል‐ነጃሺ

ስለ ረሱላችን ሱሐቦች አንዱ የሀገራችን ታላቅ ሸይኽና ማዲሕ እንዲህ በሚል ከትበው አንጎራጉረዋል።

እኔስ ምን ፈቀዱኝ ያሉት እሱ ጋር ፣
ሲያበራ ውስጣቸው የዓለም አድባር፣
በጀማሉ ጨርሬ አልብሷቸው ኑር፣
አቀማማጮቹ ግራ ቀኝ ወንበር፣
አንድኛው አቡበክር አንድኛው ዑመር፣
አንዱ ሰይድ ዑስማን አንዱ ዓሊ ሐይደር፣
የገለጠባቸው የዑሉም ሚስጥር፣
የገለጠባቸው የአስራሩን ጨረር፣
ግርማ አውርዶባቸው የተቅዋን አስራር፣
አሱሐባው ሁላ ሁሉም ነው አብራር፣
ሙላውም ጥሩ ነው ሙላውም አኽያር፣
ሐዲሰል ሙስጦፋን ሁሉም ነው ሐራር፣
ከላመል ጀሊልን ሁሉም ነው ከራር፣
ሙላውም ራኪዕ ነው ሳጂድ ነው ዛኪር፣
ስራቸው ጥሩ ነው የለውም ከደር፣
የጌታዬ አስሐቦች ሙላውም አኽያር፣
ሴትም ወንድም ቢሆን ሙላውም ዘል ኸይር፣
ወዲህም ብዙ ነው ተጥራቱ ጋር፣
እኩሉም ዘማች ነው እኩሉም ዛኪር፣
እኩሉም ጦመኛ እኩሉም ነው ቸር፣
ልብሳቸው ጌጣቸው ነህይና አምር፣
ጦም ሶላት አጥባቂ በሺዳም ሷቢር፣
አልቃሻ አዛኝተኞች ለአኺራ ነገር፣
ቧልተኞች አይደሉም ስራቸው የምር፣
በግልባጩ ሆነ ዛሬ የኛ ዓስር።
[ረዲዬሏሁ ዓንሁም ጀሚዓን]
ኢስነይን!
2024/06/01 08:23:41
Back to Top
HTML Embed Code: