Telegram Group Search
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን አስጀመሩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታው የተጀመረው በአዳማ እና ሞጆ ከተሞች መካከል በምትገኘው ሉሜ ወረዳ ነው። የኢኮኖሚ ዞኑ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርምን፣ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምን እና የአነስተኛ ቢዝነስ እንቅስቃሴዎችን ለማጎልበት እንዲሁም የማይበገር የኢኮኖሚ ስትራቴጂ ለመገንባት ታስቦ በጨፌ ኦሮሚያ ውሳኔ መሠረት ወደ ሥራ የገባ ነው ተብሏል።

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ፕሮጀክት ዋና ዓላማም በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የንግድ ማዕከል መገንባት እንዲሁም የአፍሪካ የፋይናንስ ማዕከል በመሆን የቀጣናውን ኢኮኖሚ ፈጣን እና ጠንካራ ማድረግ ነው። የፕሮጀክቱ ግንባታ ከ24 ሺህ ሔክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የሚከናወን እንደሆነም የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ETHIO-MEREJA®
Photo
ለማህበረሰቡ ወግና ባህል ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
             ***
ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን  በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከመጠቀም ይልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ  ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን  የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት  የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣  ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣  እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡  ከላይ ከተጠቀሱት ስምንት የዩቲዩብ ገፆች በተጨማሪ ክህሎት እና ሲንግል የተባሉ ሌሎች ሁለት የዩቲዩብ ገፆችም በዚያው ህንፃ ላይ የፈጠራ ወሬ ሲፈበርኩ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ተከራይተው በሚሰሩበት ህንፃ 8ኛ እና 13ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአቸው ላይ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ የፈጠራ ወሬ ለመቅረፅ እና ለማሰራጨት የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክ እቃዎች  ተይዘዋል፡፡

ግለሰቦቹ መረጃውን ለማሰራጨት የሚያስችል ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የህጋዊነት ማረጋገጫም ሆነ ፈቃድ እንደሌላቸው በምርመራው ሂደት መረጋገጡንም ከየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሃሰተኛ እና የፈጠራ ወሬዎቹን የሚሰራጩት ታሪኩን ለሚተውኑላቸው ግለሰቦች ገንዘብ በመክፈል ሲሆን በወቅቱ ጉዳዩን በጥልቀት ሳይረዱ እና መረጃው ሳይኖራቸው የማያውቁትን የፈጠራ ታሪክ ሊሰሩ ለቀረፃ ስራ የተጠሩ ሌሎች ሶስት ሰዎችን  ፖሊስ አግኝቷል፡፡   
 
መሰል የውሽት ታሪኮችን ቀልብ በሚስብ መልኩ እያቀናበሩ በማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ መደናገርን የሚፈጥሩ ሌሎች ግለሰቦችም ተለይተው የታወቁ  እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትል ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት ከባህልም ከስነ ምግባርም ያፈነገጡ የፈጠራ ወሬዎችን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ በሚመለከትበት ወቅት ገፆቹን ከመከተል እንዲቆጠብ እና የሌሎች መረጃዎችንም ትክክለኛነት በማረጋገጥ ራሱን ከአላስፈላጊ መደናገር እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
🌺Adjustable Laptop & Tablet Stand
💯High Quality(ብረት የሆነ)

የቀሩት ጥቂት ናቸው!

✔️ላፕቶፕ ጭን ላይ አስቀምጠው መጠቀም ለከፋ ጉዳት እንደሚያጋልጥ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ ፤ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ተጣጣፊ የላፕቶፕ ፣ ታብሌት Holder በተመጣጣኝ ዋጋ ገዝተዉ ጤንነቶን ይጠብቁ።

💦 ዋጋ፦  1200 ብር! Free delivery

ሱቅ ሲመጡ ና ብዛት ለምፈልጉም ቅናሽ አለን።
 ☎️ 0901882392   ☎️ 0931448106
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌺Waterproof Kitchen Sticker

ለኪችንዎ ግርማሞገስ የሚያላብስ
ኪችንዎትን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ ተመራጭ
ሙቀትንእና እርጥበትን የሚቋቋም
ለማፅዳት ምቹ የሆነ
ለመሳቢያ ፣ ለካቢኔ ፣ ለኩሽና

Size: 60cm×5m(ትልቁ) ዋጋ፦  800ብር
        :60cm*3m(ትንሹ) ዋጋ:- 550ብር

 ☎️ 0901882392  ☎️ 0931448106

   🌞 https://www.tg-me.com/AddisEka1

የዴሊቨሪ ጨምረው ያሉበት እናደርሳለን።
5በላይ እቃ ካዘዙ ነፃ ዴሊቨሪ እንሰጣለን።
     
አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት "የቅስቀሳ ወንጀል" ጥፋተኛ ተባሉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምስራቅ አዉስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት የገዳማት መምሪያ የበላይ ሃላፊ ሊቀጳጳስ አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት "የቅስቀሳ ወንጀል" የጥፋተኝነት ፍርድ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ችሎት ተላለፈባቸው።

ከ3 ወራት በፊት የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ስር እና የወንጀል ህግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች አቅርቦባቸዋል።

በቀረበባቸው ክስ ላይ፤ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በጵጵስና በማገልገል ላይ እያሉ ስለ ሰላም እና አንድነት የመስበክ ሃይማኖታዊ ግዴታቸዉን ወደ ጎን በመተዉ በታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገረ አሜሪካ ቴክሳስ እና አካባቢዉ በሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተክርስቲያን ታቦት ወጥቶ በቆመበት አዉደምህረት ላይ በመገኘት "የአመፅ ቅስቀሳ" ማድረጋቸውን ዐቃቤ ሕግ በዝርዝር ጠቅሷል።

በዚህ በቀረበባቸው ክስ ላይ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሌሉበት የተከሰሱባቸው ክሶች በአንቀጽ 247 (ሐ) ስር ተጠቃሎ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ፋና ዘግቧል።

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር በመሆን የአባይ ድልድይን መረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር በመሆን ከአራት አመት ተኩል በፊት ግንባታው የተጀመረውን የአባይ ድልድይን መርቀዋል።

ይህ ዘመናዊ ድልድይ የ380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት ያለው በሁለቱም የመንገድ ክፍል ባለሶስት መስመር የተሽከርካሪ መንገድን ብሎም በጎን የብስክሌት መጋለቢያ መስመር የተሰናዳለት ግዙፍ ድልድይ ነው።

የባህርዳር ከተማ ታላቅ መለያ ምልክት እንዲሆን የተገነባው የአባይ ወንዝ ድልድይ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እድገት ብሎም የመገናኛ አውታር የሚያነቃቃ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ጠ/ሚኒስትሩ እና ርዕሰ መስተዳደሩ በመሳሪያ የተደገፈ ትግል ለሚያካሂዱ #የአማራ ክልል ታጣቂዎች "መገዳደል ይብቃን" ሲሉ ጥሪ አቀረቡ!!

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ በአማራ ክልል መሳሪያ አንግበው ትግል ላይ የሚገኙ ሃይሎች “ትጥቃቸውን ፈትተው በሳላማዊ መንገድ ኑ እና ታገሉ፣ መገዳደል ይብቃን” የሚል ጥሪ አቀረቡ።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ “ጫካ ለሚገኙ ወንድሞቻችን” ሲሉ መሳሪያ አንግበር በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ባቀረቡት ጥሪ “ዛሬ አማራ መሪ አግኝቷል አረጋ ከበደን የመሰለ ታማኝ፣ ትጉህ መሪ አግኝቷል” ሲሉ በማወደስ “ለአማራ መብት የሚታገል ግለሰብም ይሁን ቡድን ከአረጋ አመራር ስር ሁኖ ክልሉን እና ህዝቡን መጥቀም ስለሚችል መገዳደል ይብቃን” ሲሉ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምሥጋና ባቀረቡበት መልዕክታቸው “በጫካ ለምትገኙ ወንድሞቻችን” ሲሉ በመጥራት “በእውነት ከክልላችን ሕዝብ ጥቅም እና ክብር ውጭ ሌላ ስውር አጀንዳ ከሌላችሁ በስተቀር ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) ባቀረቡላችሁ ጥሪ መሠረት ችግሮቻችንን በውይይት እና በድርድር እንድንፈታና ሕዝባችንም እፎይታ እንዲያገኝ በድጋሜ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ” ብለዋል።

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ከሐዋሳ ወደ አዲስ_አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ያጋጠመው ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ ከሐዋሳ ወደ አዲስ_አበባ በመጓዝ ላይ በነበረዉ በአዉሮፕላል ላይ የተከሰተው ጭስ ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ ሲል ገልጿል።ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል።

የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት፤ "በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መጋጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ፤ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ" ብለዋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን እና መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን ማስቃወቁ ይታወሳል። (ካፒታል ጋዜጣ)


     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
ማይክ ሀመር ከኦሮሞ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ዳውድ ኢብሳ ጋር መምከራቸው መከሩ

የአሜሪካን መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር #ከኦሮምያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ።

ሀመር የመከሩት ከኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ከኦነጉ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ጋር መሆኑም ታውቋል። የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከማይክ ሀመር ጋር በሀገራዊ እንዲሁም በኦሮምያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች መምከራቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል።

በሀገራዊ እና በኦሮምያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለማይክ ሀመር ሙሉ ገለጻ እንዳደረጉላቸው ፕሮፌሰር መራራ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል። ከማይክ ሀመር ጋር በነበረን ቆይታ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው ሀገራዊ ምክክሩ ነበር ሲሉ የገለጹልን ፕሮፌሰር መረራ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ "ኢትዮጵያን የትም አያደርሳትም፣ ምክንያቱም ደግሞ ሁሉን ያሳተፈ አይደለም፣ በሁሉም ዘንድ ደግሞ እምነት የሚጣልበት አይደለም" ሲሉ እንደገለጹላቸው ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

ሌላኛው ከማይክ ሀመር ጋር በነበረን ውይይት የተነሳው ነጥብ የበቴ ኡርጌሳ ግድያ ነበር ያሉት መረራ ጉዲና የፈጠረባቸውን ድንጋጤ እና የቤተሰቦቹ እስር እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ስሜቴን ለልዩ ልዑኩ አጋርቻለሁ ብለውናል።

በተያያዘ ዜና የአሜሪካ መንግስት ልዩ ልዑኩ ማይክ ሀመር በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ከኦነጉ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ ጋር መምከራቸውም ከፓርቲያቸው ቃል አቀባይ ለሚ ገመቹ የኤክስ ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ዳውድ ኢብሳ እና ማይክ ሀመር በምን ጉዳዮች ላይ እንደመከሩ ቃል አቀባዩ ያሉት ነገር የለም።

     T.me/ETHIO MEREJA®/com.ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ
2024/05/15 01:24:58
Back to Top
HTML Embed Code: