Telegram Group Search
† በኬንያ ምድር ኦርቶዶክስ እንደ ፀሐይ እየደመቀች ነው።†

በአፍሪካ ውስጥ በቅኝ ገዚዎች የተስፋፋው ፕሮቴስታንቲዝም በአሁን ሰዓት ልክ በአውሮፓ የገጠመው ክስረት በአፍሪካም እየገጠመው ነው።በአውሮፓ አብዛኛው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ለዘመናት በውሸት አስተምህሮ የኖርንበት ዘመን ይበቃል ብለው ፓስተሮቹ፣ዘማሪዎቹና ሕዝቡ ሁሉ እምነቱን እየለቀቁ ቤተ እምነታቸውን እየዘጉ ይገኛሉ።አውሮፓ ውስጥ የፕሮቴስታንት ማምለኪያ ስፍራዎች የሚመጣባቸው ሰው ስለጠፋ እየተሸጡ ለቢራ መጠጫ ግሮሰሪ፣ለልብስና ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቅነት፣ለግለሰቦች መኖሪያ ፣ቤትነትና ለመስኪድነት አገልግሎት እንዲውሉ እየተደረገ ነው።

ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ኦርቶዶክሳውያንም በርካሽ ዋጋ እየገዙ ወደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ መቅደስነት እየቀየሩ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

አፍሪካ ውስጥም የቀኝ ገዢዎቻቸውን እምነት ሲከተሉ የነበሩ ጥቁር ሕዝቦችም አውሮፓውያኑ የፕሮቴስታንት እምነት በስህተት የተሞላ መሆኑን አውቀው እምነቱን ሲተው እነርሱም ለመተው እየተገደዱ ነው።እግዚአብሔር የረዳቸው ደግሞ የቅድስት ኦርቶዶክስን እምነትና ሥርዓተ አምልኮ በመቀበል ክርስቶስ ኢየሱስን በመቅደስ በእውነትና በመንፈስ እያመለኩ ነው።በኬንያ በቋንቋቸው የሚሰብኩ ኦርቶዶሳዊ ካህናት፣ዲያቆናትና ሰባክያነ ወንጌልን እያፈሩ ሕዝባቸውን ወደ እውነተኛይቱ ሃይማኖት እየመለሱ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ያላችሁ ፕሮቴስታንትም እስከዛሬ የኖራችሁበት የስህተት መንገድ ይበቃልና ወደ ቅድስት ኦርቶዴክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንድትመለሱ በፍቅር እንመክራለን።

መ/ር ታሪኩ አበራ

👉 @ortodoxtewahedo
ከ780 ሚሊዬን ብር በላይ የሚዘውሩት የቤተክህነት ሰው
***

ያ እኛ የምናውቀው ክህነት አባቶች መንጋውን ከቅስጥ እና ከመከራ የሚሸሽጉበት ጋሻ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የገለጠው ክህነት ዓለምን ንቆ በተጋድሎ ማለፍ የታተመበት የእግዚአብሔር አይኖች የመሆን ጸጋን የመቀበል መንገድ ነው።

ለ1 ቢሊዬን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በጥምጣም ውስጥ መዘወር ከተቻለ ዓለም መነነች እንጅ እኛ መቼ ከዓለም ተነጠልን !!!

አሁን ላይ ቤተክርስቲያን ለሚድኑ ምስኪኖች የድኅነት ማዕከል ስትሆን ለነጋዴ አገልጋዮች ደግሞ ታልባ የማታልቅ አክሲዮን ሆናለች።

ወደ እዚህች ታልባ ወደማታልቀው አክሲዮን ወደ ሆነችው ቤተክህነት ለመግባት ደግሞ የሚመዙ ካርዶች ዘር እና የፓለቲካ ውግንና ነው።

በነገራችን ላይ 780 ሚሊዬን ብር (6.5 ሚሊዬን ዶላር) ማለት ጋሞ ጎፋ ሀገረስብከት በአገልግሎት ላይ ያሉ ሁሉም አብያተክርስቲያናት (ወደ 672 አድባራት እና ገዳማት ) ህንጻ መቅደሳቸው ቢተመን አያወጣም ።

ይቅር ይበለን !! ምሕረቱን ይላክልን !!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

@ortodoxtewahedo
#11 የቅዱስ ያሬድ በዓል]

#በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ (ይሥሐቅ) እናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻፭ ዓ.ም. ነው፡፡ ሰባት ዓመት ሲመላው አባቱ ስላረፈ፤ እናቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲያስተምረው ለአባ ጌዴዎን ሰጠችው፡፡ ነገር ግን ማጥናት ስላልቻለ አባ ጌዴዎን ይቈጣው ነበርና ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ፤ ከዐዘኑም ብዛት የተነሣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንዲት ታናሽ ትል ከዛፍ እኩሌታ ደርሶ ሲወድቅ ሲነሣ በመጨረሻም በጭንቅ ከዛፉ ላይ ሲወጣ በማየቱ እግዚአብሔር በዚኽች ታናሽ ፍጥረት እንዳስተማረው በመረዳት ይቅርታ ጠይቆ ወደ መምህሩ ተመልሷል፡፡

“ወእምዝ ሶበ ሰአለ ኀበ እግዚአብሔር በብካይ ብዙኅ ተርኅወ ልቡናሁ ወተምህረ በሐጺር ዕለት መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ” ይላል ከዚኽ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ኾኖለት በዐጭር ጊዜ ውስጥ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተምሮ በመጨረስ ዲቁናን ተሾመ፤ እስከ ርሱ ዘመን በማነብነብ እንጂ በከፍተኛ ድምፅ የመዝሙር ማሕሌት አልነበረም፤ እግዚአብሔርም ለዚኽ አባት የመላእክትን ዝማሬ ሊያሳየው ስለወደደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ እንደተነጠቀ ኹሉ ሊቁም ተነጥቆ የኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይን የምስጋና ዝማሬ ሰምቶ ተመለሰ፡፡

ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር እንደ ደረሰ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ፡- “ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ” (ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ለሙሴ የድንኳኑን ሥራ እንዴት እንደሚሠራ አሳየው) ሲል ዘምሮ ይቺኑ መዝሙር ከሰማይ መላእክት አገኘኹት፣ በማለት አርያም በሚል ሥያሜ ጠርቷታል፡፡

ይኽነኑ ድርሳነ ዜማ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል በሰማ ጊዜ ጫማውን ሳይጫማ ንግሥቲቱም ደንገጡሮቿን አጃቢዎቿን ሳታስከትል መኳንንቱ፣ ካህናቱና መምህራኑ እነሱን ተከትለው እየተጣደፉ ወደ ዐደባባዩ በመኼድ በተመስጦ ሲሰሙት ውለዋል፡፡
ቅዱስ ያሬድ ዐምስት የዜማ መጻሕፍትን የደረሰ ሲኾን እነርሱም

፩ኛ) ድጓ ፪ኛ) ጾመ ድጓ
፫ኛ) ምዕራፍ ፬ኛ) ዝማሬ ፭ኛ)መዋሥዕት ናቸው፡፡

እነዚኽንም ታላላቅ ድርሰቶቹን በሦስት የዜማ ስልቶች ማለት በግእዝ፣ በዕዝል፣ በአራራይ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ “ወአሐተ ዕለተ እንዘ ይዜምር ያሬድ ቀዊሞ ታሕተ እገሪሁ ለንጉሥ ገብረ መስቀል ወእንዘ ያጸምዕ ንጉሥ ቃሎ ለያሬድ ተከለ በትረ ኀጺን ውስተ መከየደ እግሩ ለያሬድ” ይላል፤ ከዕለታት ባንዳቸው ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ ልዑል እግዚብሔርን በዝማሬ ሲያመሰግን ንጉሥ ገብረ መስቀል ሳያውቁት ልባቸው በጣዕመ ዜማው በመመሰጡ የብረት ዘንጉን በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተክለውታል፤ ከእግሩም ብዙ ደም ቢፈስስም ቅዱስ ያሬድ ግን ማሕሌቱን እስከሚፈጽም ድረስ ምንም አልሰማውም ነበር፡፡

ንጉሡም የደሙን መፍሰስ አይቶ ደንግጦ ቅዱስ ያሬድን “የደምኽ ዋጋ የፈለግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ቅዱስ ያሬድም ተምኔቱ ወደ ገዳም መኼድ እንደኾነ ነገረው፤ ያን ጊዜ ንጉሡ እያዘነ አሰናብቶታል፡፡

“ወእምዝ ቦአ ያሬድ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወቆመ ቅድመ ታቦተ ጽዮን” ይላል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት በመቆም የአንቀጸ ብርሃንን ምስጋና ከመዠመሪያው እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ በእግዚአብሔር ኀይል ክንድ ያኽል ከምድር ከፍ ከፍ አለ፤ ከዚኽ በኋላ ወደ ሰሜን ተራራዎች ወደ ገዳም ሲኼድ የአኲስም ጽዮን ካህናት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት ርሱም እጅግ ባማረ ጣዕመ ዜማ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ሰላም እግዚአብሔር ኲሉ ባቲ ተሃሉ ወትረ ምስለ ኲልክሙ” (በኹሉ ላይ ጸንታ የምትኖር የእግዚአብሔር ሰላም ዘወትር ከኹላችኊ ጋር ትኑር) ብሎ የስንብት መዝሙርን ዘመረ፤ ካህናቱም ይኽነን ቃል ሰምተው መሪር እንባን አለቀሱና ተሰነባበቱ፡፡

በትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም መቅድም ላይ እንደምናነብበው ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ በተባለው ቦታ ተሰውሮ ጸዋትወ ዜማን ሲያስተምር እመቤታችን ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምን የብህንሳውን አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ እንዲመጡ አድርጋ ኤፍሬም ውዳሴዬን፤ ሕርያቆስ ቅዳሴዬን ነግራችኹት ቅዱስ ያሬድ በዜማ ይድረስልኝ ብላ ነግረውት በዜማ ደርሶታል፤ ይኽም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡

ርሱም ጸዋትወ ዜማን ለደቀ መዛሙርቱ እያስተማረ መላእክት ዘወትር እየጐበኙት በጾም በጸሎት ተወስኖ በተጋድሎ ለኻያ ኹለት ዓመት ጸንቶ ኖረ፤ በመጨረሻም ጌታችንም ለቅዱስ ያሬድ ተገልጾለት “ኦ ፍቁርየ ቀዳሚኒ በከመ ሰመርኩ ትርአይ ሥርዐተ ስብሐተ መላእክት ዘበሰማያት ወአስተኀለፍከ ዘንተ ማሕሌተ ዲበ ምድር... ” (ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዐተ ማሕሌት እንድታይና ወደ ምድርም አስተላልፈኽ ይኽነኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኊ ኹሉ እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሰው ሕፃናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊልና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልኻል” ብሎት ቃል ኪዳንን ሰጥቶት በክብር ዐረገ፡፡ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያውም ግንቦት ዐሥራ አንድ ነው፡፡

ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ያሬድን ነገር በአርኬው ላይ፦

“ሰላም ለያሬድ ስብሐተ መላእክት ለሕዋጼ እንተ አዕረገ በልቡ ኅሊና መንፈስ ረዋጼ ለትምህርተ መጽሐፍ ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ በብዙኅ ጻማ ዘአልቦ ሑጻጼ*መልዕልተ ጒንደ ዖም ነጺሮ እንዘ የዐርግ ዕጼ”

(የመላእክትን ምስጋና ለመጐብኘት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ፈጣን ዐሳብን ወደ ልቡናው ያሳረገ ለኾነ፤ ጒድለት በሌለበት በብዙ ድካምም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ፤ ኰብልሎ ከኼደበት መጻሕፍትን ለመማር የተመለሰ ለኾነ ለያሬድ ሰላምታ ይገባል) በማለት ሊቁ ማሕሌታይን አመስግኖታል፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሲያወድስ፡-
“ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤
ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት
ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት
ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ
ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ
ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ”፡፡

(የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

[የጽሑፉ ምንጭ፡- አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የደረሰው ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የተጻፈ፤ ከገጽ 232-235]፡፡
የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን፤ እናንተም ይኽነን ሊቅ አወድሱት።

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Audio
እግዚአብሔር ለምን አይሰማንም
                         
Size 17MB
Length 48:43

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

👉 @ortodoxtewahedo
በዓለ ቅዱስ ሚካኤል

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል በዓል አደረሳችሁ!

ሚካኤል ማለት ‹‹መኑ ከመ አምላክ (እግዚአብሔር)፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው›› ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እርሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ፣ ርኀሩኅ፣ ኃያልና ረቂቅ ማንም እንደሌለ የሚያመለክት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል ሌሎች መጠሪያዎች አሉት፤ እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣…›› ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸና ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡

መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡ መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታልና በእርሱ አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ፣ በጸሎቱ ተማጽኖና በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከሠራዊተ አጋንንት ተንኰል የሚያድን መልአክ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ ሙሴንና እስራኤልን በሲና በረሃ (ዘፀ.፳፫÷፳-፳፪)፤ (ዘፀ.፲፬÷፲፭-፳) ኢያሱን በኢያሪኮ (ኢያ.፭÷፲፫-፲፭)፤ ከአሞራውያንም እጅ ሕዝቅያስን እንደረዳቸው ተጽፏል፡፡ (ኢሳ.፴፯÷፴፮) በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፫ ላይ ‹‹የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› በማለት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ተገልጿል፡፡ በዚሁ የመጽሐፍ ክፍል ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፩ ላይ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ታላቅነቱን፣ ለሰው ልጆች ሁሉ በአማላጅነቱና በተራዳኢነት የሚቆም እንደሆነ በማያሻማ ቃል ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በኦሪት የእግዚአብሔር መልአክ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ፤ በድርሳነ ሚካኤልም ተጽፎ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያልረዳው ቅዱስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በዘመነ ሰመዕታትም ሰማዕታትን በተጋድሎ ያጸናቸው ይህ ሩኅሩኅ መላክ እንደሆነ በእነ ቅዱስ ፋሲለደስ እንዲሁም በእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገድላት ላይ በሰፊው ተገልጿል፡፡
የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየወሩ በ፲፪ ቀን መታሰቢያውን እንድናደርግ አዘውናል፡፡ ይህንንም ያልቻለ በዓመት አራት ዓበይት በዓላትን ከቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ጀምሮ እንደተቻለ ማዝከር ይገባል፡፡ እነዚህም ኅዳር ፲፪ ቀን ቀጥሎ ሰኔ ፲፪ ቀን ከዚያም ነሐሴ ፲፪ ቀንና ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ናቸው፡፡

ሰኔ ፲፪፡- በቅዳሴያችን ‹‹ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ለሚካኤል ምሕረት (ይቅርታ ርኀራኄ) ተሰጠው እንላለን፤ ነቢዩ ሄኖክም ምሕረት ለሚካኤል መሰጠቱን ገልጿል፤ ትሕትናውን ታዛዥነቱን አስረድቷል፡፡ (ሄኖ.፮÷፭፣፲÷፲፪)

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ፣ ለሰው ሁሉ የሚራራና ስለ ሰው ልጆች ሳያቋርጥ ወደ ፈጣሪው የሚለምን፣ ርኀሩኀና ትሑት የሆነው ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን ከሞት ያዳነበት፣ የሞቱን ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት የመታሰቢያው ዕለት ነው፡፡

@ortodoxtewahedo
ከሦስት ወራት በፊት ጥር 2/2016 ዓ.ም. ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ጀምሮ “አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ” የሚሉ ልጥፎች በበርካታ የኢትዮጵያውያን የፌስቡክ አካውንቶች እና ገጾች መሠራጨት ጀመሩ።
በፎቶ እና ጽሁፍ ከተቀናበረ ምስል ጋር የተሠራጩት እነዚህ ልጥፎች ፌስቡክ ላይ የወጡት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አቡነ ጴጥሮስ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ መጓዛቸውን ተከትሎ ነበር።
የኒው ዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር የወጡት፤ “ይፋዊ የሆነውን መደበኛ የአሠራር ሥርዓት ተከትለው” እንደሆነ ቢቢሲ ከቤተ ክርስቲያኗ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዕለቱ የተሠራጩት ሦስት ዋነኛ ጽሁፎች “ሰበር መረጃ፤ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ”፣ “አሜሪካዊው አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮብልለዋል!” እና “ከአሜሪካዊ አቡነ ጴጥሮስ ኩብለላ ጀርባ ያሉ እውነታዎች!” የሚል መግቢያ ያላቸው ናቸው።
ጽሁፎቹ አቡነ ጴጥሮስን፤ “በቤተ ክህነት ውስጥ ህቡዕ የፖለቲካ አደረጃጀት በመምራት” እና “የቤተክህነት ሃብት የሆነ በርካታ ገንዘብ እና ንብረት ይዞ በመጥፋት” ይከስሳሉ።
ከሦስቱ ጽሁፎች ውስጥ በብዛት የተሠራጨው “ሰበር መረጃ፤ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ” የሚለው ሲሆን፣ ይህ ጽሁፍ በጥር 2 እና 3/2016 ዓ.ም. ብቻ ቢያንስ 1,004 ጊዜ በተለያዩ የፌስቡክ አካውንት እና ገጾች እንደተለጠፈ ቢቢሲ አረጋግጧል። ከግራፊክስ ምስሎች ጋር የተለጠፈው ይህ ጽሁፍ፤ ጥር ሁለት ቀን ብቻ ይህ ቢያንስ 898 ጊዜ ፌስቡክ ላይ ተጋርቷል።
https://bbc.in/3Q4Mfjh

https://www.facebook.com/100068240109154/posts/736159432002054/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
ኒቆዲሞስ ፯ ሣምንት ዐብይ ጾም

ኒቆዲሞስ የትህትና፣ የትጋትና የጽናት አብነት ነው።

ኒቆዲሞስ ማለት:- በግሪክ ቋንቋ “አሸናፊ/ነት” ማለት ነው፡፡

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን የፈሪሳውያን አለቃ፣ የኦሪት መምህር ብቻ ሳይሆን የኦሪት ምሁርም ነበር፡፡

በእርሱ ደረጃ የነበሩ ታላላቅ የአይሁድ ምሁራን መንፈሳዊ ስልጣናቸውና ሹመታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ረስተው በህዝቡ ላይ የሚመፃደቁ ነበሩ፡፡

በዘመናቸው እውቀትን የሚገልጥ እውነተኛ አምላክ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ ለመሆን ወደዚህ ዓለም ሲመጣ አልወደዱም ነበር። እርሱ ግን የትህትና ባለቤት በመሆኑ ሁሉን ችሎ ያስተምር ነበር።

ዮሐ ፫÷፩-፲፪ ፣ ማቴ ፭÷፳
ማቴ ፲፮÷ ፮ ኢየሱስም፦ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ አላቸው።

እግዚአብሔር አምላክ ትዕግስቱን ሰጥቶ ክፉውን በመጠየፍ ደግ ደጉን ብቻ በመስራት የመንግሥቱ ወራሾች፣ የስሙ ቀዳሾች ያድርገን፣ ወዶና ፈቅዶ ለዚህ ዕለት እንደ አደረሰን ሁሉ እንድ በደላችን ሳይመለከት ቀሪውን ጊዜ ያስፈጽመን አሜን!

" ኢትዮጵያ ሠላምሽ ይብዛ"

@ortodoxtewahedo
2024/04/20 10:51:29
Back to Top
HTML Embed Code: