Telegram Group Search
Forwarded from Jordin
ዘመናዊ የሴቶች አለባበስና የወንዶች ፍርሃት!

በኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በየጊዜው የመነጋገሪያ ርዕስ ከሚሆኑት ነገሮች ውስጥ አንዱ ዘመናዊ (ወሲብ ቀስቃሽ) የሴቶች አለባበስ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ አጀንዳ ወደ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲመጣ አፋጣኝ ምክንያት የሚሆነው ደግሞ በየጊዜው ታዋቂ ሴት አርቲስቶቻችን በሰርግና በሌሎች የግል ፕሮግራሞቻቸው ላይ ለብሰው የሚነሱት ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እንዲለቀቅ መደረጉ ቢሆንም፤ ዘመናችን የብሄሮች ዘመን መሆኑ ደግሞ ረጅም የጀርባ ድጋፍ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡

እንደሚታወቀው በብሄሮችና ብሄረሰቦች ዘመን ላይ ዋነኛ ማጠንጠኛው ማንነትና ባህል ነው፡፡ አለባበስ በባህል ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ እናም እያንዳንዱ ብሄር የራሱን ማንነትና ባህል በሚያቀነቅንበት ዘመን ላይ ከብሄሩ ባህል ወጣ ያሉ አለባበሶች ሲታዩ መንጫጫት የዘመኑ ፋሽን ሆኗል፡፡

ዘመናዊ የሴቶችን አለባበስ ክፉኛ በመቃወም ረገድ ትልቁን ስፍራ የሚይዙት ደግሞ ወንዶች ናቸው፡፡ እኔም በዚህ ፅሁፌ ውስጥ የምዳስሰው ወንዶች ዘመናዊ የሴቶች አለባበስ ጉዳይ ይሄንን ያህል የሚከነክናቸው እውን ለባህላቸውና ለሃይማኖታቸው ጠበቃ ሆነው ነው? ወይስ ከውስጥ ሌላ ገፊ ምክንያት አላቸው? የሚለውን ሐሳብ ይሆናል፡፡

በሀገራችን ዘመናዊ የሴቶች አለባበስ አጨቃጫቂ ሆኖ ወደ ህዝባዊ አደባባይ መውጣት የጀመረው በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው። ክስተቱም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተዘጋጀው የሴቶች የፋሽን ውድድር ጋር የተገናኘ ነው፡፡ በአሜሪካ ኤምባሲ ደጋፊነት የተዘጋጀው ይህ የሴቶች የፋሽን ውድድር በሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለምና በአሜሪካ ጥላቻ ነደው ለነበሩት የዩኒቨርሲቲው ወንድ ተማሪዎች የተቃውሞ መነሻ ሆኖ ነበር፡፡ በመሆኑም በወቅቱ የተቃውሞው መነሻ ርዕዮተ ዓለማዊ እንጂ የስነምግባር አሊያም የባህል ጉዳይ አልነበረም፡፡ ለምስራቁ ርዕዮተ ዓለም ተጋላጭ የነበሩት ተማሪዎች፣ የምዕራቡን የባህል ተጋላጭነትን በመቃወም ነገሩን ሙሉ በሙሉ አስቆሙት፡፡

ይሄ ከሆነ ከ20 ዓመታት በኋላ፣ ያንጊዜ በዩኒቨርሲቲው ተቃዋሚ የነበሩት ተማሪዎች ወደ ስልጣን የመጡበት የመንግስት ለውጥ ተካሄደ፡፡ ይሄንን የ1983ቱን የመንግስት ለውጥ ተከትሎም ኢኮኖሚያችንም ከሶሻሊዝም ወደ ካፒታሊዝም ሥርዓት ተሸጋገረ ያን ጊዜ ነበር ለረጅም ዘመናት በረጃጅም ተራሮቻችን ከልለን ያቆየነው ባህላችንም እንደ በፊቱ መከልከል በማይቻል ደረጃ ለካፒታሊስታዊው ባህል መጋለጥ የጀመረው። ይህ ካፒታሊስታዊ ባህል ከገለባበጠብን ነገሮች አንደኛው የሴቶቻችን አለባበስ ነው።

በድሮው ባህል የሴት ውበት የሚያተኩረው ከአንገት በላይ ነበር - መልክ ላይ ብቻ። ይሄ የውበት አመለካከት ግን በመልክ ቆንጆ ለሆኑ ሴቶች ብቻ ያደላ በመሆኑ፣ የሰውነት ቅርፃቸው ለሚያምርና ለፉንጋ ሴቶች ተመራጭ የውበት መስፈርት አልነበረም፡፡ ካፒታሊስታዊው ባህል ግን መላውን የሴትን ልጅ አካል የውበት ምንጭ አድርጎ አመጣው፡፡

እንደ አብዛኛዎቹ አባታዊ ባህሎች (Patriarchal Culture) ሁሉ፣ የእኛ ባህልም የሴት ፍርሃት አለበት፡፡ ባህላችን የሴትን ልጅ አካልና ውበት መቋቋም አይችልም፡፡ ይሄንን አቅመ ቢስነቱን ለመሸፈን ደግሞ ሴቷን ‹‹አሳሳች» እያለ ጣቱን ወደ እሷ ይቀስራል፡፡ ሊበራሊዝም ሴትን ልጅ ከነ ተፈጥሮዋ ወደ አደባባይ ሲያወጣት ግን፣ ያን ጊዜ እኛም ከፍርሃታችን ጋር መጋፈጥ ግድ ሆነብን፡፡

ለካፒታሊስታዊው ባህል ተጋላጭ መሆናችንን ተከትሎ ከፍተኛ የባህል ግጭትና ቀውስ ውስጥ እንድንገባ ያደረገን ደግሞ ካፒታሊስታዊው የውሰት መገለጫ ‹‹የሴቶች የመራቢያ የአካል ክፍሎች» አካባቢ ላይ ማተኮሩ ነው፡፡ ይሄም የሴቶችን አካል በመሸፈን ላይ ለተመሰረተው የድሮው ባህላችን ይህ አዲሱ የውበት መስፈርት በጣም የሚረብሽ ነበር፡፡

የባህል ቀውሱ ሲሰክንና ሽግግሩም ሲጠናቀቅ፣ እንዲሁም አዲሱ የሴቶች አለባበስም መለመድ ሲጀምር ግን እኔም የሴቶችን አለባበስ የምመለከትበትን መነፅር ቀየርኩ ከባህላዊ/ሃይማኖታዊ መነፅር ወደ ‹<የኃይል ግንኙነት (Power Relation)» መነፅር፡፡ አሁንም ቢሆን ወንዶች ዘመናዊ የሴቶች አለባበስ ላይ የሚያነሱትን ጥያቄ «የሥነ ምግባር፣ አሊያም የባህልና የሃይማኖት ጥያቄ›› አድርጌ አላየውም፡፡ ጥያቄው ከዚያ የተሻገረና በወንዶችና በሴቶች መካከል ያለ የኃይል ግንኙነት ጥያቄ አድርጌ ነው የምመለከተው፡፡

የወንዶች ተቃውሞ ከላይ ከላይ እንደሚታየው የአለባበስ ሥነምግባር ላይ ያነጣጠረ አይደለም። ከላይ ከላይ ስናየው እንደዚያ ሊመስለን ይችላል:: በእርግጥ መፅሐፍ ቅዱስም ሆነ ቁርአን ሴቶች እንዲከናነቡ ያዛሉ፡፡ ሆኖም ግን ጥያቄው - እውን ወንዶች የሴቶችን ዘመናዊ አለባበስ የሚቃወሙት ከሴቶች ይበልጥ እነሱ ለሃይማኖታቸው ተቆርቋሪ ሆነው ነው ወይ? የሚለው ነው፡፡ አይደለም!! ወንዶችን እንዲህ የበለጠ ተቆርቋሪ አስመስሎ ያወጣቸው ገፊ ኃይል ሌላ ነው፡፡ ጉዳዩ በኃይል ግንኙነት ውስጥ ወንዶች በሴቶች እየተበለጡ መምጣታቸው ነው፡፡

በመሆኑም የኔ ክርክር፣ ዘመናዊ የሴቶችን አለባበስ ከባህልና ከሃይማኖታዊ ክበብ አውጥተን ‹‹ለምንድነው ወንዶች የማህበረሰቡ፣ የባህሉ፣ የሃይማኖቱ፣ የኢኮኖሚውና የፖለቲካው መሪ በሆኑበት ዘመን ውስጥ ሁሉ ሴቶች እንዲከናነቡ ህግ ሲያወጡ የኖሩት?› የሚለው ጥያቄ ላይ የሚያጠነጥን ነው።

ይሄንን ጥያቄ ጠለቅ ብለን ስንመረምረው ጉዳዩ የሥነምግባር ወይም የባህል አሊያም የሃይማኖት ሳይሆን «የሃይል ግንኙነት/ power Relation)” ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አዎ!! የሴቶች አለባበስ የባህልም ሆነ የሃይማኖት ጉዳይ ሳይሆን በወንዶችና በሴቶች መካከል ያለ የኃይል ሚዛን ፉክክር ነው፡፡

ወንዶችና ሴቶች የኃይል ምንጫቸው የተለያየ ነው:: ለዘመናት የወንዱ የኃይል ምንጭ ‹‹ጉልበቱ>› ሲሆን፣ የሴቷ የኃይል ምንጭ ደግሞ ‹‹አካሏ>> ነው፡፡ የወንዱ የሃይል ምንጭ ላይ የሴቷ ሃይል ደካማ ሲሆን፣ የሴቷ የሃይል ምንጭ የሚገኝበት ቦታ ላይ ደግሞ የወንዱ ሃይል ደካማ ነው፡፡ ስለዚህ የሱ የሃይል ሚዛን ደካማ የሚሆንበት ቦታ ላይ ሴቷ ሃይሏን እንዳትጠቀምና ሁልጊዜ በእሱ የሃይል ሚዛን ስር ተንበርክካ እንድትኖር የሴቷን የሃይል ምንጭ በባህልና በሃይማኖት ስም ያደርቅባታል። ወንዱ እንደለመደው በጉልበቱ እንዳይኖር ጉድ አድርጎት የሄደው የኢንዱስትሪ አብዮት ነው፡፡

ከኢንዱስትሪ አብዮት በኋላ ‹‹ጉልበትን የሃይል ምንጭ የመሆኑ ነገር እየቀረ መሄዱ ወንዱን ይበልጥ አቅመ ቢስ እያደረገው ሄዷል፡፡ ድሮ አካል ብቸኛው ‹‹የስራ መሳሪያ» (power of production) ነበር፡፡ ‹<የስራ መሳሪያ» ደግሞ የሃይል ምንጭ ነው። ከኢንዱስትሪ አብዮት በኋላ ግን ማሽኖች አካልን እየተኩ የስራ መሳሪያ መሆን ጀመሩ፡፡ ወንዱ አቅመ ቢስ መሆን የጀመረው ያኔ ነው - የኃይል ምንጩ በማሽኖች መተካት ሲጀምር፡፡ .

ከዚህ በተጨማሪ፣ ማሽኖች ሲመጡ የአካል ሚና ከስራ መሳሪያነት ወደ ሌላ ሚና መሸጋገር ነበረበት:: ይሄኔ ነበረ ሴቶች አካላቸውን «የውበትና የደስታ ምንጭ>> ማድረግ የጀመሩት፡፡ ሴቷ ኃያል ሆና የወጣችው ያኔ ነው:: ይሄም በወንዱ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሮበታል። ወንዱ ሴቷን «የድሮ የአለባበስ ስነምግባርን» እያነሳ የሚቃወማት አካሏን የውበትና የደስታ ምንጭ አድርጋ እንዳትጠቀምና ወደ ቀድሞው ደካማነቷ እንድትመለስ ነው።
Forwarded from Jordin
ሴቷ አካሏን የውበትና የደስታ ምንጫ አድርጋ ስትጠቀምበት፣ ወንዱ ግን ከስራ ያሳረፈውን አካሉን ምን ያድርገው? ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በከፍተኛ የድብርት ስሜት የሚሰቃዩት ለዚህ ነው። ከዚህ ድብርት ለመውጣት እሱም እንደ ሴቶች አካሉን የውበትና የደስታ ምንጭ አድርጎ እንዳይጠቀምበት ተፈጥሮ ፀጋዋን ነፍጋዋለች:: እናም በማሽኖች ግፊት፣ አካል ከስራ ጡረታ መውጣቱ የወንዱን የሃይል ምንጭ እያደረቀው ሄዷል። ወንዱ ይሄ ደካማነቱ እንዳይገለጥበት ሴቷን የድሮውን የአለባበስ ሥነ ምግባር እያነሳ እሷም አቅመ ቢስ እንድትሆን ይጥራል። በዚህ ረገድ ወንዱ ሴቷን ማስገደድ ስለማይችል ያለው አማራጭ የሃይል ምንጩን ‹‹ከጉልበት›› ወደ ‹‹ዕውቀት» ማሸጋገር ነው:: እሱ የሃይል ምንጩን እያሸጋገረ፣ እሷን ግን አሁንም የሃይል ርሃብተኛ እንድትሆን ይፈልጋል፡፡

ችግሩ ግን፣ 21ኛው ክ/ዘ ላይ «የግለሰብ ነፃነትና እኩልነት›› የሚባሉ አዳዲስ እሴቶች መምጣታቸው ነው፡፡ እናም በዚህ ዘመን ላይ «ዕውቀት›› ለሁለቱም - ለወንዱም ለሴቷም - እኩል የሃይል ምንጭ እንዲሆን ለሁለቱም እኩል ዕድል ተሰጥቷቸዋል። ይሄን ዕድል ተጠቅመው ወንዱና ሴቷ የዕውቀት ባለቤት ቢሆኑ እንኳ፣ ሴቷ ግን ሌላ ተጨማሪ የሃይል ምንጭ አላት - አካሏ/ውበቷ። በመሆኑም በ21ኛው ክ/ዘ ላይ የወንዱ የሃይል ምንጭ ‹‹ዕውቀቱን ብቻ ሲሆን፣ የሴቷ የሃይል ምንጭ ግን ሁለት ናቸው «ዕውቀትና ውበት»፡፡ በመሆኑም ወንዱ በሃይል ሚዛን እየተበለጠ ሄዷል። ይሄንን ደካማነቱን ለማካካስና የሃይል ሚዛኑን ከሴቷ ጋር ለማስተካከል ጥረት እያደረገ ይገኛል።

ምንጭ ፦ ፍልስፍና ፫
ፀሀፊ ፦ ብሩህ አለምነህ
#ፍልስፍና_ከፈላስፎች
Forwarded from Jordin
A MUST READ GUYS!!!
Finally a pink heart emoji🩷🩷🩷
if you eat less and move more, you'll lose weight.

if you eat less, move more and eat plenty of protein, you'll drop body fat.

if you eat less, move more, eat plenty of protein, and strength train, you'll lose body fat and build muscle.
If you have these books please send them to me
Perky tips🩰
https://www.tg-me.com/+rUoApIRXLntkMWJk
This is where i collect books i find online, feel free to join
[email protected]
1.4 GB
Spider-Man : Across the Spider verse 2023
FULL HD
1080p
[email protected]
601.4 MB
Spider-Man : Across the Spider verse 2023
FULL HD
720p
If you're not watching "the summer I turned pretty", what are you doing with your life?

#teamjeremiah🩵
Mermaid mesh skirt
Color brown
Size small
Price 1400
Available on hand
Contact @bertade1
Forwarded from Addis Powerhouse
በታዳጊ ፋጡማ ኡጋስ የተፈጸመውን በቡድን አስገድዶ መድፈር እና ግድያ በጥብቅ በመቃወም የሚከተሉትን በጋራ እየጠየቅን እንገንኛለን!

1. መንግስት ወንጀለኞችን በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ፤
2. በህብረተሰባችን ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስወገድ መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሰራ፤
3. የፍትህ አካላት፣ አቃብያነ ህጎች እና ህግ አስከባሪዎች በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የስርዓተ-ፆታ ስሜትን እና ግንዛቤን በመያዝ እንዲሰሩ፤
4. የመገናኛ ብዙሃን በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሱን ጥቃቶች እና ወንጀሎች ለመከላከል ህብረተሰቡን የማስገንዘብ ስራ በተከታታይ እንዲሰሩ

በነዚህ ጥያቄዎች የሚስማሙ ከሆነ ፊርማዎትን በመግለጫው ላይ በማዋል ድምፅ ይሁኑ!

https://chng.it/4vTTXJ8JC6
Perky tips🩰
https://vm.tiktok.com/ZM61FexbW/
Share this to all your girl-friends‼️
2024/04/16 06:41:35
Back to Top
HTML Embed Code: