tg-me.com/ortodox_27/20131
Last Update:
⛪️✍ #ጻድቅስ_ከመ_በቀልት ይፈሪ ወይበዝኀ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ ትኩላን #እሙንቱ_ውሰተ_ቤተ_እግዚአብሔር
(መዝ/ዳዊት ፺፪ ፥፲፪)❤🙏❤
#እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች
( ፰🕯) ለጻዲቁ አባ ኪሮስ🦋
✍አባ ኪሮስ አባቱ #ንጉስ_ዮናስ_እናቱ_አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡ አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ #ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡
በ17 ዓመቱ #ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ #ከዚህ_በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ #መላእክት_መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት #ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።
⛪️ #አባ_ኪሮስ_አባቴ 🕯
በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ #ገዳም_ገብተህ
በሀዘን ስሜት ውስጥ እንባህን አፍሰስህ
እመቤቴ ጠራህ አትለይኝ ብለህ
ሰባት መቶ ስግደትን ለእመ አምላክ ሰግደህ
ምህረትን አገኘህ እንደ እንግዳ ሆነህ
ወደ እግዚአብሔር ፀለይክ በሽተኛ ልታድን
#መላእክትም_መጡ ካንተ ጋር ለመሆን
እልፍ አዕላፋት እንዲሁም ጌታችን
ለችግረኞች ተስፋ የሆነው አምላካችን
ልክ እንደ አብርሀም እንደ #ፃድቁ_ሰው
ሰው ስትቀበል በሰላም በፍቅር ነው
የራስ ፀጉር እንደ በረዶ የነጣ
የፂምህ ውበት ነጭ ሆኖ የወጣ
አሟሟትህ ይገርማል ለሰማው የደንቃል
#እግዚአብሔር ተቀበሎ ለሚካኤል ሰጣት
በመቃብርህ ላይ መስቀሉን ተከሉት
ነፍስህን ከአምላክ ጋር እንዲ አሳረጓት
እርሷም በተሰጣት #ክብር_ደስ እያላት
❤️ወስብሐት #ለእግዚአብሔር 🦋
"ወር በገባ በ8 ፃድቁ አባታችን ቅዱስ አቡነ ኪሮስ ናቸው ።
ካልታሰበ አደጋ ወቶ ከመቅረት ይሰውሩን በቃል ኪዳናቸው ያስምሩን🙏
መልካም ቀን ❤🙏ቤተሰብ በስላም ያውለን
🤲 🤲 🤲
#አሜን......... 🧡 ......... #አሜን
⊹ #አሜን🙏³⊹
BY የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹
Share with your friend now:
tg-me.com/ortodox_27/20131