tg-me.com/ortodoxtewahedo/22083
Last Update:
#የሊባኖሷ_ሙሽራ
✝በመጀመርያ በክንፍ ላይ ስሎ ለመላእክት ሲገልጣት የጠባቂነት መዓረግን መስጠቱ ነበርና ከማኅፀን ጀምሮ እንዲጠብቃት አደራ በተሰጠው መልአክ በኩል እንደተናገረው በዘመድ በኩል ቢሆንም ቅሉ ለምትወለደዋ ሕፃን ዘመዶቿ የሰማይ መላእክት ነበሩና በእነርሱ ተከባ ወደ ምትወልድበት ስፍራ እንዲሄዱ ተነገራቸው ።
✝እራሷ ከዓለም አይደለችምና በመወለዷ በቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ዓለማዊ ተድላ ደስታን እንዳያደርጉ በመንፈሳዊያን ዘመዶቾ በመላእክት ታጅባ ከቤት ወጣች ። ከቤቱ ወጥቶ ሕገ እግዚአብሔርን ስቶ የነበረ አዳምን የሚፈልግ ጌታ እናቱ ናትና ከቤት ወጥታ ቀድሞ አባቶቿ ነብያት እርሷን በራዕይ ወደ ተመለከቱበት ታላቅ ስፍ ወደ ሊባኖስ ተራራ ተጓዘች ። በሊባኖስ ተራራ ጉያ ስር በእንበሶች ጉድጓድ እንደምትወለድ ትንቢት የተነገረላት የሊባኖስ ሙሽራ እርሷ ናትና ።
✝ከጉሩማኑ አናብስት ከነዳዊት ከነሰሎሞን ፤ ከተላላቁ ተራሮች ከነ አብርሃም ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ አብራክ የተገኘችው እመቤታችን ሰው በማይኖርበት ስፍራ ልትወለድ ተወሰነ። በዚያም ሳሉ ክብሯ ከአድባራት ሁሉ በላይ የሆነ ከቀደሙትም ከኋለኞቹም በላይ ስሟ የገነነ ፣ ከፀሐይ ይልቅ የምትደምቅ እመቤታችን በግንቦት አንድ ቀን ተወለደች ።
✝እሷ የሁሉ ፍጥረት ናት እንጅ የሐናና የኢያቄብ ብቻ ባለመሆኗ በአንድ ሰው ቤት ውስጥ እንዳትወለድ መንፈስ ቅዱስ ከለከለ ።
( ሕይወተ ማርያም ገጽ 85-87 ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ )
አማላጅነቷ የእናትነት ፍቅሯ ይጠብቀን ።
http://www.tg-me.com/us/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/ortodoxtewahedo/22083