tg-me.com/poimFitsae/2569
Last Update:
የጨለመ ጊዜ
""""""""""""""""
ለምን?
ጊዜ ዘመን ሰዓት እያዋጀን፤
ለብርሃን ስንሮጥ
እንደ እሳት እራት ብርሃኑ ፈጀን?
ለምን?
እያደር ሰቆቃ እያደር ጭካኔ፤
ለአዘቅዝቆ ኗሪው
መትረየስ ነበረ የሚገባው ለኔ?
ለምን?
በሚስቴ አስክሬን ሀዘን 'ምቆራመድ
በልጆቼ እሬሳ በቁጭት የምነድ
ከሀገሬ ቆሜ በሀገሬ የምሰደድ
ለምን?
ብለን ስንጠይቅ
እሳት ሲለቁብህ
አንተ ምጣድ ሆነህ ዝምብለህ ተጋገር፤
በነገር ቢጠብሱህ
አንተ ምድር ሆነህ በሆድ ችለህ እደር፤
እንረድህ ሲሉህ
ትንፋሽህን ውጠህ ከአንገትህ በል ሰበር፤
በጨለመ ጊዜ
ጠይም ፀሀይ አስብ ደም ያለበት ጀንበር፤
እውትና ንጋት ይፈካል እያደር!
የሚል መልስ አለ እንዴ?
ልክ ያጣ ቀን ሲኖር
ለካም ቤተ መቅደስ ይኖራል ወንበዴ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
BY የፍፄ ግጥሞች
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/poimFitsae/2569