tg-me.com/realitysensation/7885
Last Update:
መልካም ጓደኛ
አንዱ ለጓደኛው ስልክ ይደውልና "እባክህ እናቴ በጣም ታማ ሆስፒታል ገብታለች እናም አሁን 3ሺ ብር ስለተባልኩኝ ከየትም ፈልገህ በፍጥነት ይዘህልኝ ና" ይለዋል። ጓደኛውም "እሺ 30 ደቂቃ ያህል ታገሰኝ" አለው እሺ ብሎ ሲጠብቀው 30 ደቂቃ አለፈ፡፡ ከዚያም ስልክ ሲደውልለት ስልኩ ጥሪ አይቀበልም ይላል ደጋግሞ ቢሞክርም ዝግ ነው በዚህ በጣም ይናደድና "እንዲያውም በቃ ተወው ያንተን ገንዘብ አልፈልግም ድሮም ጓደኛ አይወጣልኝም" ብሎ ሜሴጅ ላከለት። ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ጓደኛው ሆስፒታል መጣ ገና እንዳየውም "ስማ ባታገኝ እንኳን ለምን ስልክህን ትዘጋለህ?" ብሎ ጮኸበት ጓደኛውም እንዲህ ሲል መለሰለት "ጓደኛዬ ስልኬን ዘግቼው አይደለም የማውቃቸውን ሰዎች ሁሉ ብድር ስጠይቅ የለንም አሉኝ ከዚያም አማራጭ ሳጣ ስልኬን ሽጬ ይኸው 3000 ብር ይዤልህ መጣሁ አለው" ከዚያም ጓደኛው አቅፎ ሳመው።
አንዳንዴ ሰዎች ለእኛ ብለው ደፋ ቀና እያሉ እና ዋጋ እየከፈሉ ነገር ግን ያሉበትን ሁኔታ ሳንረዳ እንዲሁ ነገሮች በምንፈልገው ፍጥነት ስላልሆኑ ብቻ ለንግግር አንቸኩል።
እግዚአብሔርም በችግር ቀን ደርሶ እንዲህ ከጎን የሚሆን፣ ሲኖር አብሮ በልቶ ሳይኖር የማይርቅ በመልካም ቀን ኖሮ በክፉ ቀን ጀርባ የማይሰጥ ሞላ ቀርቦ ሲጎድል የማይሸሽ ችግርን አብሮ የሚካፈል ቅን ወዳጅ ያድለን። አሜን
#hiyaw_qal
#hiyaw_qal
@books_centerr
@books_centerr
BY 👥Ĥĩďďęñ Ř€ăłĩŧÿ
Share with your friend now:
tg-me.com/realitysensation/7885