Telegram Group Search
ኢትዮጵያን በዚህ ዘመን እንደገጠማት አስመሳይ፣ አሽቃባጭ፣ አታላይ መሪ ተብየ ደደብ ገጥሟት አያውቅም።

እርሱ ስለ ሰላጣ፣ ጎመን፤ ጓሮ ለጓሮ እየሄደ ይትኮረኮራል፤
በዚያ የስንት ንጽሐን ደም ይፈሳል።
አይሉት የግብርና ምንስቲር፣ ምን እሚሉት ነው እንድ ኩኖ መደዴብ።

ምን ያክል ጭካኔ ቢሞላብህ ነው፣ ምን አይነት ጥብዑ ልብ ቢኖርህ ነው፣
ምን አይነት ስጋ ለበስ አጋንንት ብትሆን ነው እንዲህ በሰው ደም ስልጣንህን የእምታረዝም።

ትንሽ ስቅቅ አይልህም። እንዴት የ 300 ንጽሐን ደም የአንድ ሰላጣ ያህል አላሳስብህ አለ?
እንዴት የአንድ የጎመን ቅጠል ያህል ቦታ አልሰጠው አልህ።

እግዚአብሔር የፍርዱን ይስጥህ፣ የንጽሐን የግፉዓን ደምና እንባ ይፋረድህ።

😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭


ሼር

ለበለጠ join 👇👇👇
🇨🇬🇨🇬 @ETHIOPIA_Hagerie

@Afe_Werk
ንጹሐን አቤላውያን ሞተው እኩያን ቃኤላውያን የሚፈነጩባት ኢትዮጵያ ፣ የዋሃን ናቡቴያውን ተገድለው አማጽያን ኤልዛቤላውያን እና አክአባውያን የሚንደላቀቁባት ኢትዮጵያ ፣ ክርስቶሳውያን ተሰቅለው በርባናውያን የተፈቱባት ኢትዮጵያ ድንኳኖቿ በዐራቱም ማዕዘን ተጨንቀዋል ።

በእግዚአብሔር አርዓያ እና አምሳል የተፈጠረ ክቡር የሰው ልጅ እንዲህ እንደ ቅጠል በከንቱ እየረገፈ እያዩ ከመኖር አለመኖር ይሻላል !!!!

የሰው ልጅ ከእንስሳ እና ከቁስ አካል በእጅጉ አንሶ የታየበት ጊዜ ጌታ ሆይ ቀን አምጣ !!!

ለበለጠ join and share 👇👇👇
🇨🇬🇨🇬🇨🇬 @ETHIOPIA_Hagerie 💧

💦💦💦 @Afe_Werk
🛑ክርክር ለማን በጀ ?🛑

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እኛ #ልጆቿ በሁሉ ጎዳና ዝግጁ እንድንሆን ትፈልጋለች::
በሃይማኖት በምግባር
በጾም በጸሎት
በፍቅር በደግነት
በትህትና በትእግስት . . . ሁሉ ምሉዓን እንድንሆን ፈቃዷ ነው::

+በተረፈውም በቃለ እግዚአብሔር እንድንበረታና ለሚጠይቁን ተገቢውን ምላሽ የምንሰጥ እንድንሆንም ትመክረናለች:: (1ዼጥ3:15) ዛሬ ዛሬ ግን ብዙዎቻችን በጐ ምግባራትን ዘንግተን በመሰለን ጎዳና እንሔዳለን::

+በተለይ በዚህ የፌስ-ቡክ ገጽ ላይ ብዙ ነገሮችን (ያልተገቡትን ማለቴ ነው) ከክርስቲያኖች መመልከቱ ከመለመድ አልፎ አሰልቺ እየሆነ የመጣ ይመስላል::

እስኪ እነዚህን ጥያቄዎች ልብ በሏቸውና መልሱን ለራሳችሁ ስጡ:-

1.የፌስ ቡክ Account ለመክፈት ለምን አስፈለገን?

2.አሁን በየገጻችን ምን እየሰራን ነው?

3.በየጊዜው የምንጽፋቸውና የምንለጥፋቸው ነገሮች አላማቸው ምንድን ነው?

4.ፌስ ቡክ ውስጥ በመኖራችን ምን አተረፍን? ምንስ አጎደልን?

5.ፌስ ቡክ ይዘጋ (ይቅር) ቢባል ምን ይሰማናል?

6.በዚህ ገጽ ላይ እስከ መቼ ልንቀጥል አስበናል?

7.መጨረሻችን ምንድን ነው?

እስኪ እርሶ! እነዚህን ጥያቄዎች ለራስዎ ይመልሱና ራስዎን ይመርምሩ:: እኔ ግን በዚህ የማኅበረ-ሰብእ መገናኛ ገጽ ላይ ከተመለከትኩአቸውና መታረም ካለባቸው ነገሮች አንዱን ላንሳ::

(ከዓመታት በፊት የነበረው ችግር እጅጉን ገኖ፡ ከፍቶም በማየቴ ነው ጉዳዩን ዳግም ያነሳሁት)

☞ ብዙዎቻችን: በተለይ ሃይማኖትንና ሀገርን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ክርክር ውስጥ ገብተናል::

+በተለይ ደግሞ በተለያየ ጊዜ ማን እንደከፈታቸው እንኩዋ ባልተረዳናቸው ቡድኖች (Groups) ከኢ-አማንያን ጋር ከመከራከር አልፎ መዘላለፍ ዘወትራዊ ሥራ ሆኗል:: አስቸጋሪው ነገር ደግሞ ወደ ቡድኖቹ ማን እንደ ጨመረን አናውቅም::

+የከፋው ግን #የፈጣሪያችን: #የእመቤታችንና #የቅዱሳኑ ስም በክፉና በከንቱ ይነሳል:: ሀገርም ትሰደባለች፡፡ ትናንታችን ይንቋሸሻል፡፡ አበውም ይዘለፋሉ፡፡ ምናልባት "በእነዚህ የቡድን ገጾች የሚለጠፈው ነገር አስተማሪ ነው:: ቡድኖችም የተመሠረቱት ለበጎ ውይይት ነው" ትሉኝ ይሆናል::

☞እንደምትሉት ቢሆንማ ሸጋ ነበር:: ግን አልሆነም::

+ቀላል ቁጥር የሌላቸው ባልንጀሮቻችን ከክርክር አልፈው ጸብ የሚመስል ነገር ውስጥ በመግባታቸው ከክርስቲያን በማይጠበቅ መንገድ ሌሎች እምነቶችን፡ አንዳንዴም ጎሳን ጨምረው ሲዘልፉ እያየን ነው::

☞ ወንጌልን በዚህ መንገድ (በክርክር: ሲከፋም በብሽሽቅ) የምናስፋፋ የመሰለን ሰዎች ካለን ተሳስተናል:: እንዲያውም በነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እየቀለልን ይመስላል::

+ሲጀመር #ክርስትና የክርክር ሃይማኖት አይደለም:: ሲቀጥል ጥራዝ ነጠቅ የሆነ እውቀት ይዞ እንዲህ ዓይነት ነገር ውስጥ መግባቱ እጅጉን አደገኛ ነው:: ምክንያቱም ብዙዎቻችን የክርስትናን ስሙን ይዘናል እንጂ ጣዕሙ የገባን፡ ምስጢሩንም ያጣጣምን አይደለንም::

+እንዲያውም ፌስቡክ፡ ቴሌግራምና፡ ዋትሳፕ ላይ ባነበባትና ባደመጣት ትምህርት ራሱን እንደ አዋቂ ቆጥሮ የተማሩ ሰዎችን እንኳ የሚዘረጥጥ ሰው መመልከቱ አሁን አሁን ብርቅ አይደለም፡፡

+በዚያ ላይ አስፈላጊ ለሆኑ ጥያቄዎች በጊዜው መልስ ከመስጠት በቀር (ይሔውም በመምህራን ነው) እንድንከራከርም ሆነ መሰል ድርጊቶች ላይ እንድንሳተፍ እናት ቤተ ክርስቲያን ፈቃዷ አይደለም::

ምንተ ንግበር (ምን እናድርግ?) (ሐዋ. 2:37)

1.በልኩ እንማር!

=>እንኩዋን ለሌላ ለማስረዳት: ለራስ ለመዳንም በልኩ መማር ያስፈልጋል:: ጥቂት ነገርን ብቻ ይዞ የፌስ-ቡክ አርበኛ ለመሆን መሞከሩ አይረባንምና እንማር::

+ለዚህ ደግሞ ተመራጩ መንገድ . . . ከአበው: ከመምሕራን: ከጉባኤያት ተገኝቶ ከምንጩ መጠጣት ይገባል:: እድሉ የሌለን: በሰው ሃገር ያለን ደግሞ ከመልካም ድረ ገጾች አስፈላጊውን ትምህርት በጥሞና እንውሰድ::

+ያልገባን ነገር ካለም ማኅበረ ቅዱሳንን ለመሰሉ አገልጋዮች ልከን ማብራሪያዎችን ማግኘት እንችላለን::

2. ዓላማ ይኑረን!

=>የምናደርገው እያንዳንዱ ነገር ሁሉ እኛን ጠቅሞ ለሌሎቹ እንደሚተርፍ ካላመንበት ይቅር:: መጻፋችንም: መለጠፋችንም ለዓላማ ይሁን::

3.የከንፈር ምስክርነት ይብቃን!

=>ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ያጣችው በከንፈሩ የሚደልላት አይደለም:: ክርስትና የገባው: ሕይወተ አበውን የሚኖር ምዕመን ያስፈልጋል:: ስለ ተናገርን: ወይ ስለጻፍን መሰከርን ማለት አይደለም::

መመስከር ማለት እንዲህ ነው:-
ሀ..በሕይወት (አብነት በመሆን)
ለ..በአንደበት (ፊት ለፊት ሔዶ ዋጋ በመክፈል)
ሐ..በጽሑፍ (ይህ ግን ጾምና ጸሎት ትሩፋትም ካልተጨመረበት ፍሬ አይኖረውም)

4.በፍቅር ማስረዳት!

=>አንድን ኢ-አማኒ እምነቱን ስለ ሰደብክ አትመልሰውም:: የሚፈለገው በፍቅር: በማስተዋልና በጥልቀት ማስረዳቱ ነው:: ስብከት በፍቅር እንጂ በእልክ አይሆንምና:: (አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ለመገሰጽና የተሳሳተ መንገዳቸውን ለመግለጥ ጊዜ ምረጥ)

+ስለ ሃይማኖታችን የማይገባ ነገር ሲባልም ከቻልን በማስተዋል መመለስ: ካልሆነልን ነገሩን ከመምህራን ማድረስ ይገባል:: ዓላማችን የእኛና የሰው ሁሉ መዳን ከሆነ የእኛን መሻት ትተን የጌታን ፈቃድ ልንከተል ግድ ይለናል::

+ክርስትና ጠላትንም የመውደድ ጥልቅ ምስጢር አለውና ኢ-አማንያንን "ንስጥሮስ ሆይ! አንተን እወድሃለሁ:: ትምህርትህን ግን እጠላዋለሁ" ብለን እንደ ታላቁ ሊቅ #ቅዱስ_ቄርሎስ ልንናገር ይገባል::

ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍም እንዲህ ይላል:-

"" ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ: ብትበላሉ: እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ::
ነገር ግን እላለሁ:: በመንፈስ ተመላለሱ:: የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ . . .

የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው:: እርሱም ዝሙት: ርኩሰት: መዳራት: ጣዖትን ማምለክ: ሟርት: ጥል: #ክርክር: ቅንዓት: ቁጣ: አድመኝነት: መለያየት: መናፍቅነት: ምቀኝነት: መግደል: ስካር: ዘፋኝነት: ይህንም የሚመስል ነው::
አስቀድሜ እንዳልሁ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም:: "" (ገላ. 5:15-21)

"" አንዳንንድ ተከራካሪዎችንም ውቀሱ:: "" (ይሁዳ. 1:22)

=>ለዚህ ደግሞ #የሥላሴ ቸርነት: የድንግል #እመ_ብርሃን አማላጅነት: #የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን::

ስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል!
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር፡ ዕጸ ሣሕል!
አሜን!

https://www.tg-me.com/zikirekdusn
በሀገረ እግዚአብሔር / በቅድስት ምድር /
በእመቤታችን ርስተ ምድር በሆነችው በኢትዮጵያ የሰው ልጅ ደም እየፈሰሰ ነው ፡፡
ኢትዮጵያ ሹሙ እንደ ጠፋበት ንብ ህዝቡ ከተበታተነ ሰነበተ። የሰው ሕይወት የውሻ ሕይወት ያክል ተቆጥሮባታል ፡፡
አምላክ ከ 22ቱ ፍጥረታት ለይቶ አምላካዊ ክብሩን
የሰጠው የሰው ፍጡር እየሞተም እየገደለም ነው ፡፡ ሰው ሠውን እያደነ ነው ፡፡
ከሰው ሕይወት ይልቅ ስንዝር መሬት ትልቅ ከበሬታ አግንታለች። ሁሉም ነገ ጥሎት ለሚሄድ መሬት እየተስገበገበ ነው። በዚች ሀገር የጥይት
ባሩድ እየሸተተ ነው ፡፡ ህዝቡ ደስታውን ሳያጣጥም ጥቁር ደመና እየመጣበት ነው ፡፡ በዚች ሀገር ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው አስታራቂ ሽማግሌ ይፈለጋል፡፡
ቅዱሳን የመነኑበት ምድር በእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እስራኤላውያን ቤተ መቅደስ እንዳትሆን እንፈራለን፣የሙሴ ጽላት ያለባት ምድር የሶረያን እጣ እንዳታገኝ እንፈራለን። ምንግዜም ሰው ሲያጠፋ ሀገር ባድማ ትሆናለች፡፡
በፈረሱ የተማመነ ይጠፋል ይላል ነብዩ ዳዊት።
የፈርዖን ታሪክ እንዳይደገም እንፈራለን ፡፡ የሰው ደም ከባድ ነው። ትልቅ መከራ ያስከፍላል ፡፡ ሳጥናኤል ክፉ
ነው። ከላይ ከትዕቢት ተራራ ላይ ሰቅሎ ወደ ውርደት ሸለቆ ይፈጠፍጣል፡፡
ምን ይሁን ኢትዮጲያውያን እርስ
በርስ አዳኝና ታዳኝ ሆነው በደማቸው ይራጫሉ ፡፡
አንደበቱ ቅባ ቅዱስ የተቀባ መሪ እቺ ሃገር ትፈልጋለች።


ለበለጠ join and join 👇👇👇

🇨🇬🇨🇬🇨🇬 @ETIOPIA_Hagerie


@Afe_Werk
"ይስማዕከ እግዚአብሔር በዕለተ ምንዳቤከ!"

"እግዚአብሔር በመከራህ ቀን (ልመናህን) ይስማህ!" (መዝ. ፲፱:፩)

በአንደበቱ እየመረቀ በልቡ ከሚራገም፤
•በወሬ ብዛት ለጠላት አሳልፎ ከሚሰጥ፥
•የሚመክሩትን ከማይሰማ፥
•የወደደ መስሎት በግብረ ጸራዊ ከሚገኝ
•በአጠቃላይ ከቢጽ ሐሳዊ ሁሉ ይሰውርዎ!

@ Dn Yordanos Abebe

https://www.tg-me.com/zikirekdusn
ያልገባቸው፣ ድውይ አዕምሮ ያላቸው፣
መናፍቃን ለአንች ክብር መስጠት ቢያቅታቸው፣
እኛ ግን እንድህ ከፍ አድርገን፣
እንዴ አበው አባቶቻችን፣
"ታኦሎጎስ" እንልሻለን።

"የአምላክ እናት በረድኤት ትጎብኘን!

@Afe_Werk
እናት ኢትዮጵያ!

በአላዋቂዎች አዋቂ፣ በጨዋዎች ጥርቅም፣
እናት ኢትዮጵያ ምስቅልቅል ብትይም፤
ትንሳኤሽ ይመጣል አምላክ አይተውሽም።

Join Join Join 👇👇👇
🇨🇬🇨🇬🇨🇬 @Ethio_Betecrstian
ምነው ዳር ዳሩን እየቀደዱ ማሳየት ጀመሩሳ______

ኦርቶዶክሳዊ አለባበሳችን የት ሄደ? ይህንን ልብስ በመልበስስ ለራሳቸው ምን ሊጠቀሙ ይሆን? ከብርድ እንዳያስጥል ቀዳዳ ነው። ክርስቲያናዊ እንዳትለው የዘማውያን ልብስ ነው?!።

ራቁትን መሄድም ስልጣኔ ሆነ እንዴ??? ይህ ስልጣኔ ከሆነ የመጀመሪያዋ ሥልጡን ፍየል ናት። እናንተ ደግሞ የፍየል እህት። ዘረፍረፍ ያለ ግርማ ሞገስ ያለው ቀሚሳችሁ የት ሄደ?

እረ እናስተውል ጎበዝ!
ይሄ ሳይዋጋ የተማረከ ከንቱ ትውልድ!

Join 👇👇👇
🇨🇬🇨🇬🇨🇬 @Ethio_Betecrstian
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ ውድ የክርስቶስ ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ።

#የፍቅር #ትርጓሜ
ፍቅር የአንዱን ድካም አንዱ ሲሸከም ነው። ሰማዕትነት የሌለበት ፍቅር ፍቅር አይባልም። በአፍ ብቻ እወድሃለሁ እወድሻለሁ ማለት ውሸት ነው። ይህንንስ ባላገሩ "የአፍ ዘመድ ከገበያም አይገድ" ብሎ ተርቶበታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ. ፲፭፣፲፫ "ነፍሱን ስለወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ብሎ የፍቅርን ትርጓሜ አስተማረን። ፍቅር በአፍ የሚናገሩት ብቻ አይደለም በሕይወት የሚኖሩትም ነው እንጂ። ለዚያም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በቃል ከተናገረ በኋላ በተግባር ደግሞ አዳምን ለማዳን በመስቀል የተሰቀለ። መስቀል ፍቅር በተግባር የተገለጠበት አደባባይ ነው። ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት ብሎ ሊቁ የገለጠው ይህንን ነው። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ፩ኛ ዮሐ.፬፣፰-፳ "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና----ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው" ይላል። ይህ የሚነግረን በፍቅር ጥላቻ እንደሌለ ነው። ፍቅር ሌላውን እንደ ራስ መውደድ ነው። ማቴ. ፯፣፲፪ "ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው" ተብሎ እንደተጻፈ ሰውን መውደድ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል።ዮሐ. ፲፬፣፳፩ "ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው" እንዲል።
√√√
√√√
ማቴ. ፯፣፳፩-፳፫ "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ" እንዲል የጌታን ስም ብዙ ጊዜ ብትጠራ፣ በስሙ ተአምራትን ብታደርግ፣ በስሙ ትንቢትን ብትናገር፣ በስሙ አጋንንትን ብታወጣ ይህ የፍቅር ምልክት ተደርጎ አይያዝም። እግዚአብሔርን የመውደድ ዋናው ምልክቱ ፈቃዱን መፈጸም ነው። ፈቃዱ ምንድን ነው ከተባለ ዘጸ. ፳፣፩ ጀምሮ ያሉ አስሩን ሕግጋት መፈጸም ነው። ማቴ. ፲፱፣፲፯ "ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ" እንዳለ። ዮሐ. ፲፪፣፶ "ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ"እንዲል።
√√√
√√√
ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅርን ጠቅለል አድርጎ ሲያቀርበው እንዲህ ብሎታል። ፩ኛ ቆሮ. ፲፫፣፪-፰ " ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድኾችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሣል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" ብሎ ገልጾታል።


@Ethio_Betecrstian
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ ውድ የክርስቶስ ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ።

#የፍቅር #ትርጓሜ
ፍቅር የአንዱን ድካም አንዱ ሲሸከም ነው። ሰማዕትነት የሌለበት ፍቅር ፍቅር አይባልም። በአፍ ብቻ እወድሃለሁ እወድሻለሁ ማለት ውሸት ነው። ይህንንስ ባላገሩ "የአፍ ዘመድ ከገበያም አይገድ" ብሎ ተርቶበታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ. ፲፭፣፲፫ "ነፍሱን ስለወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ብሎ የፍቅርን ትርጓሜ አስተማረን። ፍቅር በአፍ የሚናገሩት ብቻ አይደለም በሕይወት የሚኖሩትም ነው እንጂ። ለዚያም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በቃል ከተናገረ በኋላ በተግባር ደግሞ አዳምን ለማዳን በመስቀል የተሰቀለ። መስቀል ፍቅር በተግባር የተገለጠበት አደባባይ ነው። ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት ብሎ ሊቁ የገለጠው ይህንን ነው። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ፩ኛ ዮሐ.፬፣፰-፳ "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና----ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው" ይላል። ይህ የሚነግረን በፍቅር ጥላቻ እንደሌለ ነው። ፍቅር ሌላውን እንደ ራስ መውደድ ነው። ማቴ. ፯፣፲፪ "ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው" ተብሎ እንደተጻፈ ሰውን መውደድ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል።ዮሐ. ፲፬፣፳፩ "ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው" እንዲል።
                     √√√
                      √√√
ማቴ. ፯፣፳፩-፳፫ "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ" እንዲል የጌታን ስም ብዙ ጊዜ ብትጠራ፣ በስሙ ተአምራትን ብታደርግ፣ በስሙ ትንቢትን ብትናገር፣ በስሙ አጋንንትን ብታወጣ ይህ የፍቅር ምልክት ተደርጎ አይያዝም። እግዚአብሔርን የመውደድ ዋናው ምልክቱ ፈቃዱን መፈጸም ነው። ፈቃዱ ምንድን ነው ከተባለ ዘጸ. ፳፣፩ ጀምሮ ያሉ አስሩን ሕግጋት መፈጸም ነው። ማቴ. ፲፱፣፲፯ "ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ" እንዳለ። ዮሐ. ፲፪፣፶ "ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ"እንዲል።
                     √√√
                      √√√
ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅርን ጠቅለል አድርጎ ሲያቀርበው እንዲህ ብሎታል። ፩ኛ ቆሮ. ፲፫፣፪-፰ " ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድኾችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሣል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" ብሎ ገልጾታል።


@Ethio_Betecrstian
ሆድ ሊጠግብ ይወዳል፣
አንደበት ሊናገር ይሻል፣
ወንበደም ሊቀማ ይወዳል፣
ሳይጣንም ሊያጠፋ ይወዳል፣

#ጠቢብ ግን ከዚህ ሁሉ ይድናል።

The stomach likes to be full.
A tongue would rather speak.
A storm likes to steal,
evil loves to destroy,

But the wise will be saved from all this.
🇨🇬 #ነገረ_ተዋሕዶ 🇨🇬

ሥጋ በቃል ሰማይንና ምድርን ፈጠረ አይባልም።ምክንያቱም ፈጢረ ዓለም ቅድመ ተዋህዶ የተፈጸመ ግብር ነው። በ ወይም ርስት እንዲሁም ዚአሁ ወይም ገንዘብነት የሚነገር ድኅረ ተዋህዶ ለተፈጸመ ነገር ነውና።በነገራችን ላይ ካቶሊኮችም ፕሮቴስታንቶችም ሌሎች አሕዛብም ትልቁ ልዩነት የተፈጠረው ነገረ ክርስቶስ ላይ ባለው የአረዳድ ልዩነት ነው።

ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ እንዲሉ። ነገሩን ከጥንት ጀምረን ብንመረምረው ይህች ዓለም ሳትፈጠር ቅድመ ዓለም እግዚአብሔር በአንድነት በሦስትነት ይኖር ነበር።ከዚያም ዓለምንና በዓለም ያሉትን ፍጥረታት ፈጠረ። ሰውን በዕለተ አርብ ፈጥሮ ከዕፀ በለስ እንዳይበላ ቢበላ የሞት ሞትን እንደሚሞት ነገረው። አዳም ግን ትእዛዙን ቸል ብሎ ዕፀ በለስን በላ ጸጋውም ተገፈፈ።

አዳም በበደለው በደል አለቀሰ ተጸጸተ ንስሓ ገባ።ያን ጊዜ ፈታሒነትን ከመሐሪነት አስማምቶ የያዘ እግዚአብሔር 5500 ዓመት ፈረደበትና።ከዚያ በኋላ ግን ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ገባለት። ሐዋርያው ዘመኑ በደረሰ ጊዜ ከሴት ተወለደ ብሎ እንደተናገረው ጌታ ቃሉን ለመፈጸም ከድንግል ማርያም ተወለደ። ኢነስኦ ለዘነስኦ እመላእክት አላ እምዘርዓ አብርሃም የነሳው የመላእክትን ባሕርይ ሳይሆን የአብርሃምን እንደሆነ ይናገራል። የተወለደው ወልደ ዳዊት ነው።

ትልቁ ጥያቄ ???
የተወለደው ሰው የሆነው ቅድመ ዓለም የነበረው ቃል በተለየ አካሉ ነው።ሌላው ደግሞ ዓለም ከተፈጠረ በኋላ የተገኘ ሥጋ አምላክ ሆነ።ይህ እንዴት ነው? የሚለውን እንመልከት።ይህን ለማየት ሦስት ነገሮችን ማየት ይገባል።እኒህም ቅድመ ተዋሕዶ ጊዜ ተዋሕዶ እና ድኅረ ተዋሕዶ ናቸው።ድኅረ ተዋሕዶ የሚነገረውን ለቅድመ ተዋሕዶ ብንናገር ቅድመ ተዋሕዶ የተደረገውን ለጊዜ ተዋሕዶ ወይም ለድኅረ ተዋሕዶ ብንናገር ታላቅ ተፋልሶ ስለሚመጣ እነዚህን ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል።

ቅድመ ተዋሕዶ
የቃል አኗኗር ከተዋሕዶ በፊት በምልአት በርቀት በከሀሌ ኩሉነት ከአብ (ልብ) ከመንፈስቅዱስ (እስትንፋስ) ከህልውና ሳይለይ ይኖራል።ሊቁ ሱኑትዩ በሃይማኖተ አበው ሥላሴ በተዋሕዶ ወተዋሕዶ በሥላሴ ይላል።በአካል ልዩ የሆኑ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በህልውና አንድ ናቸው።በከዊን ደግሞ ቃል ልብ እስትንፋስ ይባላሉ። በከዊን ተገናዝቦ እንጂ ተሌልዮ አይነገርም። በተገናዝቦ አንድ ሕያወ ባሕርይ ይባላሉ። በዚህ አንድ ሕያወ ባሕርይም አምላክ አምላክ አምላክ ሕይወት ሕይወት ሕይወት እየተባሉ ይጠራሉ። ይህም ሥልጣናዊ ወይም ባሕርያዊ ግብር ይባላል።ሥላሴ በባሕርያዊ ግብር አንድ ናቸው።ይህም በመፍጠር በማዋሐድ በማጽናት በማንጻት እና በመሳሰሉት አንድ ናቸው ማለት ነው። በከዊን ግን ሕይወትነት ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ የሚሰጥ የሚነገር ሆኖ አብ ወልድ ሕያዋን ሆነው ይኖሩበታል ይባላል። ቃልነት ለወልድ ብቻ ይሰጣል አብ ወመንፈስ ቅዱስ ይናገሩበታል። ልብነት ለአብ ይሰጣል ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስቡበታል። ይህ የቃል ሕልውና ቅድመ ተዋሕዶ ነው። የሥጋ ህልውና ቅድመ ተዋሕዶ ሲነገር ባሕርየ አዳምን መናገር ነው ይኽውም በአካል ውስንነቱን የሚራብ የሚጠማ መሆኑን ሞት የሚስማማው መሆኑን ወዘተ መናገር ነው። ስለዚህ ቅድመ ተዋሕዶ ቃል ኃያል ረቂቅ ምሉእ ስፉሕ ፈጣሪ ወዘተ ነው። ሥጋ ደግሞ ድኩም ግዙፍ ውስን ፍጡር ነው።

ጊዜ ተዋሕዶ
ሃይ.አበ.102፥7 ንሕነሰ ነአምሮ ለክርስቶስ ድሙር እም ክልኤቱ ህላዌያት።ወእምድኅረ ተዋህዶሰ ኢነአምሮ ዘእንበለ አሐዱ ሕላዌ ወአሐዱ አካል ቃል ሥግው።ይላል ይህም ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ ሥግው ቃል ነው ማለት ነው። በጊዜ ተዋሕዶ ረቂቁ ምሉኡ ኃያሉ ቃል ረቂቅነቱን ምሉእነቱን ኃያልነቱን ሳይለቅ ደካማ ውስን እና ግዙፍ ሥጋን ተዋሐደ። የሥጋ ገንዘብ ለቃል የቃል ገንዘብ ለሥጋ ሆነ ሊቁ እንደተናገረው እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል። ሃይ.አበ.82፥3 አንደየ ርእሶ በፈቃዱ። መታመምን መራብን ገንዘብ ማድረግ ንዴት ነውና።የሚራብ የሚጠማ ሥጋን እንደተዋሐደ ለማጠየቅ አንደየ ርእሶ አለ።በሌላ ገጸ ንባብ ወአጥፍአ ንዴተ ህላዌ ዘትካት ወገብአ ውስተ ስብሐቲሁ ወክብሩ ይላል።ይህም ከትንሳኤ በኋላ መራብ መጠማት የለምና አጥፍአ ንዴተ ህላዌ ተባለ።ሲዋሐድም ሲከፈልም አንድ ጊዜ ነው።ተከፍሎ ቆይቶ በኋላ ቃል ያደረበት አይደለም። ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ የምንለውም።ሥጋን ከፍሎ ክቡር ቃል ሲዋሐደው ሥጋ ክቡር ሆነ። ይህም ሲከፈልም ሲዋሐድም ሲከብርም አንድ ጊዜ ነው። ይህንን ወደጎን ብሎ ቃልን ከክብር አውጥቶ ክብርን ለመንፈስ ቅዱስ ሰጥቶ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ብሎ ማስተማር ስህተት ነው። ነገረ ሥላሴን ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ ነው። ማክበር ማዋሐድ የሥላሴ ሥልጣናዊ ግብር ስለሆነ አብ አከበረው መንፈስ ቅዱስ አከበረው ማለት እንችላለን።ለሥጋ ክብር መሆን ግን በተለየ አካሉ የተዋሐደው ቃል ስለሆነ ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ እንላለን። ክብር በተዋሕዶ የሚገኝ ነው። በተለየ አካሉ የተዋሐደ ደግሞ ቃል ነው።

ድኅረ ተዋሕዶ
ሃይ.አበ.74 መጻሕፍትሰ ቦ ዘይቤላ በእንተ ትስብእቱ ወቦ ዘይቤላ በእንተ መለኮቱ ወቦ ዘይቤላ በእንተ መለኮቱ ወበእንተ ትስብእቱ።ከተዋሕዶ በኋላ እንደ ሰውነቱ ብቻ ሲነገር ብትሰማ አምላክነቱን ትቶ እንዳልሆነ እንደ አምላክነቱ ሲናገር ብትሰማ ሰውነቱን ትቶ እንዳልሆነ መረዳት አለብን። ከተዋሕዶ በኋላ ተራበ ተጠማ ሲባል ብትሰማ ለሥጋ ብቻ አይነገርም።ለሥግው ቃል ይነገራል እንጂ። የተሰቀለውም የሞተውም ከሙታን የተነሳውም ሥግው ቃል ነው። ሊቁ በመሰለበት በእሳትና በብረት ተዋሕዶ መስለን ብናየው ከተዋሐዱ በኋላ ቢፈጀን ለይተን እሳቱ ብቻ ፈጀን አንልም የጋለው ብረት ፈጀን እንላለን እንጂ።ከተዋሕዶ በኋላ መራቡ መጠማቱ እንኳ የፈቃድ ነው እንጂ እንደ እኛ በግድ ተራበ በግድ ተጠማ አንልም። ሥጋ በቃል ረቀቀ ማለት በምሳሌ ዘየሐጽጽ ብረት በእሳት ሞቀ እንደማለት ያለ ነው። ቃል በሥጋ ከበረ ማለት አይገባም እሳት በብረት ሞቀ እንደማለት ያለ ነውና።

#መምህር_በትረማርያም_አበባው
(የትርጓሜ መጻሕፍት መምህር)
ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮጵያ

join 👇👇👇
🇨🇬 @Ethio_Betecrstian
#ምሥጢረ #ተዋሕዶ


ሞቱ ለክርስቶስ መድኃኒት ለዓለም። የክርስቶስ ሞት ለዓለም መድኃኒት ነው።ብርሃን በመስታዎት ተከፍሎ እንዲገባ ክርስቶስ ተከፍሎ አልተዋሐደም።ኩሉ መለኮቱ ኀደረ በሥጋ ሰብእ እንዲል።ቄርሎስ 18 ኩለንታ መለኮት ከኩለንታ ሰውነት እንደተዋሐደ እናምናለን እንዲል። ኩለንታሁኬ ለቃል ወኩለንታሁ ለትስብእት ከመተደመረ ነአምን።ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር እያለ ያደረጋቸው ድርጊቶች በዋናነት በ4 ይከፈላሉ እነዚህም፦
>>#ለቤዛነት
>>#ለአርአያነት
>>#ለአጽድቆተ ትስብእት
>>#ለአቅርቦተ ሰይጣን
ናቸው።አርአያነት ማለት ተመሀሩ እምኔየ ከእኔ ተማሩ ብሎ የሚያስተምር ነውና።ለእርሱ ላይጠቅመው ለሌላው ምሳሌ ለመሆን የሚያደርገው ነው። ለምሳሌ በቁርባን ጊዜ የራሱን ሥጋ ቀምሶ ለሐዋርያት አቀመሳቸው።የራሱ ሥጋ ለራሱ ምንም አይጠቅመውም።ነገር ግን ለካህናት አርአያ ለመሆን ይህን አደረገ።ካህናት እነርሱ ሥጋውን ደሙን አቀብለው ለሕዝቡ ያቀብላሉና።ለአጽድቆተ ትስብእት ማለት ሰው መሆኑን ለማስረዳት ነው።ይህም ማለት ታላላቅ ተአምራትን ሲያደርግ ሰውነቱ ተለውጦ አምላክ ሆኗል እንዳይሉት የሰውነትን ሥራ ሠራ። አምላክነቱ ጠፍቶ ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) የሚሉት መ*na*ፍ-ቃን አሉና የእነርሱን ነገር ለማፍረስ የአምላክነትን ሥራ ሠራ።የሰውነትንም የአምላክነትንም ሥራ የሚሰራው አንዱ ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ቦ ዘይቤላ መጻሕፍት በእንተ ትስብእቱ ወቦ ዘይቤላ መጻሕፍት በእንተ መለኮቱ ወቦ ዘይቤላ መጻሕፍት በእንተ ትስብእቱ ወበእንተ መለኮቱ እንዲል።ለአቅርቦተ ሰይጣን ያልነው ሰይጣንን በራሱ በሰይጣን ፈቃድ አቅርቦ አስወድዶ አዳም እና ሔዋንን ባሸነፈበት ለማሸነፍ ያደረገው ነው።ይኽውም አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ የመሳሰሉ ቃላት ናቸው።ቤዛነት ማለት ህየንተ አዳም (በአዳም ምትክ) ሆኖ አዳም ባጠፋው ጥፋት ምክንያት ሊያደርገው ይገባ የነበረውን ማድረግ ነው።በዚያውም አዳምን መካስ ነው።ክርስቶስ ወደ ግብጽ ፈርቶ የሸሸ አይምሰልህ የእርሱ ስደት አጋንንትን የሚያሰድድ ነውና ሸሸ እንጂ።አንድም ሰውነቱን ለማስረዳት ሸሸ እንጂ። ተይዞ ባይገደል ኑሮ ምትሐት ያሰኛልና። ይህ እንዳይሆን ሸሸ።

ሃይማኖታችን ነገር በማሳመር አይደለም።በሰውም ልባምነት የተመሠረተ አይደለም።መንፈስ ቅዱስ በገለጠው ትምህርት ነው እንጂ። እስመ ምሥጢርነሰ ኢኮነ በቅድው ነገር ወበጥበበ ሰብእ።አላ በአርእዮ መንፈስ ቅዱስ።ቄር.31 ክርስቶስ የሴትና የወንድ ሩካቤን ሳይሻ ተወለደ።ይኽውም ርኩሰት ሆኖ አይደለም። ቀዳማዊ ልደቱን በደኃራዊው ልደቱ እናውቅ ዘንድ ነው።ያለ አባት ከእናት ብቻ ተወለደ እንጂ።ተወልደ ክርስቶስ ኢጸኒሖ ሩካቤ ብእሲ ወብእሲት።አኮ እስመ ኅሡር ውእቱ።እስመ ክቡር ውእቱ ሰብሳብ።ቄርሎስ 62 ወኢየሱስ ይተረጎም መድኃኒተ።ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው።ክርስቶስ በልዑል ልደቱ ወልድ በትሑት ልደቱ ሕጻን ይባላልና ሕጻን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ ለነ ይለዋል።ክርስቶስ በሕማሙ በሞቱ በጥምቀቱ እኛን አከበረበት እንጂ ለእርሱ ምንም ዓይነት ጥቅም አላገኘበትም።እርሱ እከብር አይል ክቡር ነውና።

ቄርሎስ 21፣11 መለኮቱ በሁሉ ቦታ ያለ ነው።በሥላሴ ዘንድ ፍጡር እና አንዱ ተላኪ አንዱ ላኪ የሆነ የለም። አልቦ ውስተ ሥላሴ ፍጡር ወተለአኪ።ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

በመ/ር በትረ ማርያም

በቅንነት #ሼር ታደርጉት ዘንድ ጠየቅናችሁ። ምክንያቱም ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ!


ቻናሉን ይቀላቀላሉ 👇👇👇
🇨🇬🇨🇬🇨🇬 @Ethio_Betecrstisn
🇨🇬 #ሞትን ስታስብ ምን ይሰማሀል? 🙏


ልክ ስትሞት በዚህ ምድር አለኝ የምትለው ነገር ሁሉ የአንተ ወዳለመሆን ይሸጋገራል።የለፋህበት የተጣላህበት ነገር ሁሉ ከንቱ ይቀራል። በዚህ ምድር ያሉት ሀብት ሥልጣን ክብር ጉልበት ዕውቀት እና የመሳሰሉት በዚህ ምድር እስካለህ ድረስ ብቻ የሚያገለግሉህ ናቸው።ስትሞት እነዚህ ሁሉ ምንም ናቸው።በእርግጥ እኒህን ነገሮች ከሞት በኋላ ለሚመጣው ሕይወት ካዋልካቸው ለነፍስህ ጥቅምን ይሰጣሉ።

ብዙ ቅዱሳን የዚችን ዓለም አጭርነት ተረድተው ንቀዋት በምናኔ በየጫካው በየፍርክታው በጾም በጸሎት ተወስነው ያሳልፏታል።ሞት አንዱ የሕይወታችን አካል ነው።ቀድሞ የነበሩ ሰዎች አሁን በሥጋ የሉም።ዓለምን አንቀጥቅጠው የገዙ ዝናቸው በዓለም የታወቀ ሰዎች አሁን የሉም ሞተዋል።

መጀመሪያውንም ካለመኖር ያመጣን እግዚአብሔር በሥጋ ወደ አለመኖር ይወስደናል።ሞት ሲታሰብ ይጨንቃል ምክንያቱም ሞተን ስላላየነው አናውቀውም።ሞት በዚህች ምድር ሳሉ ሥልጣናቸውን ጉልበታቸውን እውቀታቸውን ሀብታቸውን በአግባቡ ለመልካምነት ለተጠቀሙት ሰዎች ዕረፍት ነው። በተቃራኒው ሀብታቸውን ሥልጣናቸውን እውቀታቸውን ሌላውን ለመጉዳት ለተጠቀሙት ሰዎች ሁለት ሞት ነው።

ስለዚህ ሞትን ላለመፍራት ከፈለግህ በዚህች ምድር እስካለህ ድረስ ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቅ።3 ነገሮች ያስፈሩኛል ብሏል አንድ ሊቅ።እኒህም አለ፦
1ኛ ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ
2ኛ ለፍርድ በእግዚአብሔር ፊት ስትቆም
3ኛ ሲፈረድባት
ሁላችንም ካለመኖር እንድንኖር ያደረገን እግዚአብሔር ፊት እንቆማለን።ስለዚህ የእርሱን ረድኤት ጋሻ አድርገን በእርሱ ፊት ለመቆም የሚያበቃንን ስራ እንስራ።

እግዚአብሔር በቸርነቱ ይቅር ይበለን።

© M/r B.M

ሼር ታደርጉት ዘንድ በትህትና ጠየቅን ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ!

linkun 👇👇👇 በመንካት join አድርጉ!
🇨🇬🇨🇬 @Ethio_Betecrstian
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ ባለፈው እሁድ በምድር ላይ ታላቅ እሳተ ገሞራ መከሰቱን ዐል ዓይን ነግሮናል።

ለምን ልትለጥፈው አሰብክ ትሉኝ ይሆናል። ግን ቪድዮን ሳየው ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃላችሁ ሲኦል።

የምድር እሳተ ገሞራ እንድህ ካስፈራ የሲኦልማ እንዴታ?

እናም እስኪ ነፍሳችሁን ለራሳችሁ ጠይቋት? መድረሻሽ የት ነው በሏት?
መንግስተ ሰማያት ወይስ ከዚህ ከምንመለከተው እሳተ ገሞራ የእጥፍ እጥፍ ወደ ሆነው ገሃነም?

ለዚህ ነው ሁል ጊዜ #ንስሐ_ግቡ እምትል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን!

አሁንም ንስሐ ግቡ! ደግሜ እላለሁ ንስሐ ግቡ! ንስሐ ግቡ አዎ ንስሐ ግቡ!

አስቡት የምትመለከቱት እሳተ ገሞራ አያስፈራም? አይሰቀጥጥም? በዚሁ ደግሞ ገሀነምን አስቧት ምን አይነት እሳት ይነድባት ይሆን!?

ላስጨንቃጭሁ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜም ገሃነምን ብናስባት ጥሩ ነው ብየ ነው።

ይህንን ደግሞ መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "የገሃነምና የመንግስተ ሰማያት ጥቅም ለእኛ ለሰዎች አንድ ነው፣ መንግስተ ሰማያት ንብኝ ኑብኝ እያለች ትማርከናለች እሷን ለማግኘት እያልን መልካም ምግባር ለመስራት ታፋጥነናለች።
ገሃነምም በማስፈራራት ክፉ ብትሰሩ ትሰቃያላችሁ እያለች ክፉ እንዳንሰራ ትመክረናለች ትገስጸናለች" ይለናል።

እኛም ፦ መንግስተ ሰማያትን እና ገሃነመ እሳትን በአእምሯችን እናስባቸው፣ ሁለየ እንዘክራቸው፣ ከዚያ ንስሐ እንግባ።

አምላካችን በቸርነቱ መንግስቱን ለመውረስ ያብቃን። ይማረን።

በቅንነት ሼር አድርጉትና ሰዎችን ለንስሐ እናነሳቸው የበኩላችንን እንወጣ እናሳውቃቸው።

ይቀላቀሉን JOIN👇👇👇
🇨🇬🇨🇬🇨🇬 @Ethio_Betecrstian
2024/04/19 06:33:39
Back to Top
HTML Embed Code: