ሰላም እንዴት ቆያችሁ? በ ነገሮች መደራረብ ምክኒያት ለትንሽ ጊዜያት ምንም አይነት post አይኖርም በትዕግስት እንድትጠብቁን አደራ እላለሁ😔
ጠየቅኳት.......
ሰወች ሁል ጊዜ ይጨነቃሉ ስለነገም ያስባሉ ያዝናሉ፣አንቺ ግን ለምን ..........
በእርጋታ የተሞላ አጭር መልስ
"ለራሴ ስለምኖር".......
✍bee

የእኔ ጥያቄ....
መልስ እፈልጋለሁ.....
ፍቅር መንገድን አስትቶ በጭፍን የሚነዳ መሰናክል
ወይስ
መፅሐፍ እንደሚለው "የህይወት መዓዛ" ?
wait is love really exists🤔
መልስ እፈልጋለሁ.....
ፍቅር መንገድን አስትቶ በጭፍን የሚነዳ መሰናክል
ወይስ
መፅሐፍ እንደሚለው "የህይወት መዓዛ" ?
wait is love really exists🤔
“ሁለት እናት ወፎች ነበሩ እና አንደኛዋ ወፍ በጠዋት ተነስታ አስፓልቱ ላይ ያለውን ጥሬ በሙሉ ለቅማ ለራሷም በላች ለልጆቻም አበላች። አርፍዳ የተነሳችዋ ሌላኛዋ እናት ወፍ ግን ለሰዓታት በጽናት ብትፈልግ አንዳች ጥሬ አላገችም። ከዚህ ታሪክ ምን ትረዳላችሁ።”
ኒቼ፦ ''የመጀመርያዋ እናት ወፍ ስግብግብ መሆኗን''
ማርክስ፦ ''የሰው ልጅ በኑሮ ውድነት ምክንያት ቅንጣት ያህል ምግብ መጣል ማቆሙን።''
ሾፐንአወር፦ ''ወፍ ሆኜ አላውቅም፤ ለምን እራሷን አንጠይቃትም!''
ሲዮራን፦ ''ምትመገበው ያጣችው ወፍ በልጆቿና በጎጆዋ ውስጥ ዝማሬ የለሽ ድብርት እንደምታስተናግድ።''
አርስቶትል ፦ ''በጠዋት መነሳት የስኬት ቁልፍ እንደሆነ''
ዲዮጋን፦ ''ምግብ በቀላሉ በጎዳና ላይ እንደሚገኝ''
ሶቅራጠስ፦ ''ወፎች ጥሬ እንደሚበሉ''
እኔ:- ወፉአ ያረፈደችው አምሽታ ስለተኛች ነው::ለምን አመሸች? ሰለልጆችዋ ስታስብ::😇
እናተስ ምን ትላላችሁ🤔
✍Aiden
@nibab_lehiwot

የእኔ ታሪክ (በ አዲስ ምዕራፍ)
ቪቪያን እንደፃፈችው........
የሰው ልጅ ታሪክ መጨረሻ የለውም። ሞት መጨረሻ ነው ብዬ እንዳልደመደም ከሚያደርጉኝ ነገሮች አንዱ ልጅ ነው። የአባቴ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃ ቢመስልም በእኔ እና በአሌፍ ግን ነፍስ ዘርቶ ቀጥሏል። እንዲህ ሆነ.........ወደኋላ ተመልሳ ከአባቷ ጋ ያሳለፈችውን የመጨረሻ ቀን አስታወሰች።
ያቀፏት የሕዝቅኤል እጆች ድንገት ተንሸራተው ሲወድቁ የእርሷም ልብ ላይ የሆነ ነገር ቁርጥ ብሎ ሲወድቅ ታወቃት። ለመናገር ቃላቶች አልነበሯትም አይኗ ብቻ በሚያፈሰው ውሃ ያወራል። ያ ሕይወቱን ሙሉ በመከራ ያሳለፈው ሕዝቅኤል ለዘለዓለም አልተነሳም። ከቁስሉ ሊያገግም ፣ ለብዙ አመት የተከደነው ጥርሱ ሊስቅ ፣ በእንባ ብዛት የሟሙ አይኖቹ እንደገና የተስፋ ጭላንጭል ሊያበሩ በነበረበት ቅፅበት ሕዝቅኤል ድንገት አመለጠ። ከእነሱ ከእናት እና አባቱ፣ ከእህቱ እና ከወንድሙ ጋ ተቀላቀለ....... ህይወት ፍትሃዊ አይደለችም። ያንን ሁሉ የስቃይ እና የመከራ አመታት ሲያሳልፍ ዞር ብሎ ያላየው ሞት...... ለደስታው በተቃረበ ሰዓት ግን ሊወስደው አሰፈሰፈ።
ማቲያስ የተደወለለትን ስልክ አናግሮ ከጨረሰ በኋላ አንድ ጋዜጣ እያነበበ የነበረ ሰው አጠገብ ሄዶ ተቀመጠ። የሰውዬውን ሁኔታ ከላይ እስከታች አጤነው....የሚያውቀው መስሎ ተሰማው ግን የት እንደሆነ ማስታወስ አልቻለም ለዛም ሊያናግረው ፈልጎ ጉሮሮውን ጠራረገ። እንዴት ዋሉ አባ.....? ሰውየው ጋዜጣቸውን ዝቅ አድርገው ወደጠራቸው ሰው ዞር አሉና ፈገግ አሉ። ምኔን አይተህ ነው አባ ያልከኝ ልጄ .......ፂምወትን አለ ቀለል ያሉ ሰው እንደሆኑ ከንግግራቸው ተረድቶ......ቀጠል አድርጎም እርሶስ ምኔን አይተው ነው ልጄ ያሉኝ አለ ጨዋታ ለመፍጠር ያክል.......እሳቸውም ወጣትነትን ብለው ፈገግ አሉ። ማቲያስ እባላለሁ አለ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋላቸው፤ ሰውየው ድንግጥ ብለው ማቲያስ አሉ የተዘረጋላቸውን እጅ እየጨበጡ። አወ የእርሶስ አለ ማቲያስ የፊታቸውን መቀየር እያጤነ። የእኔን ስም ነበር ማቲያስ ያልኩህ ማቲያስ እባላለሁ ..........የስማችን መመሳሰል ገርሞኝ ነውኮ መደንገጤ።
ወጣቱ ማቲያስ ወዲያው የሜሮን የቀድሞ ፍቅረኛ አእምሮው ላይ ብልጭ አለ። ጋሽ ሕዝቅኤል ጓደኛወት ነው? አብርሃምም?.....ሽማግሌው ደነገጠ ማነህ አንተ?..............መጀመሪያ ጥያቄዬን ይመልሱልኛ.... አወ ማን ነህ?......የሜሮን ልጅ.........በእድሜ ብዛት የማያረጀወሰ የሽማግሌው ማትያስ ፍቅር ስሟን ሲሰማ እንደገና አገረሸ። ወጣቱን አስተዋለው እውነትም እሷን ይመስላል ..........እኔኮ አመጣጤ ሕዝቅኤል መታመሙን ሰምቼ ነበር......አለ አሁንም ድንጋጤው እንደወረረው። ና ወደውስጥ ጋሽ ሕዝቅኤልንም እየው እማዬም አለች.........ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ።.......ሲገቡ ግን የሕዝቅኤል አይኖች ከሚወደው ጓደኛው ከማትያስም በቅፅበታት ቀድመው ተከድነዋል።
ሆስፒታሉ ሌላ ድባብ ሞልቶታል ቃል የሞላው ቃል አልባ እንባ ከየ አቅጣጫው ይፈሳል ማቲያስ በቁሙ ራደ። ሀዘን ሀዘን ብቻ ተነበበ። ሁሉም የምሬት እንባውን ያነባል......የአሌፍ ግን ቃልም አለው። ለዚህ ነው እንዳውቅህ ያደረግከው? ትተኸኝ ለመሄድ...አባ ለምን? እስከዛሬ ትናፍቀኝ አልነበረ? ስታገኘኝ ጥለኸኝ ለመሔድ ነበር?
ግን ሆነ ሕዝቅኤል ላይመለስ አይኖቹ ተከደኑ። የሚወዱትም ነፍሶች ላይጠገኑ ተሰበሩ። ስርዓተ ቀብሩም ራቢያም ራሷ በተገኘችበት ተፈፀመ።ራቢያ ለዚህ ሁሉ አመታት አፍና የያዘችውን የስቃይ እንባ በመቃብሩ ላይ ዘረገፈችው አልቅሳ አልቅሳ አልጠገበችም አትጠግብምም። አለመኖሩን ሳታይ አምና የነበረችው ራቢያ አይታ ስታረጋግጥ ግን ለመቀበል አልቻለችም አቃታት።
ኤልሳ ልትናገር ይቅርና መቆም አቅቷት ለቀብሩም በሰወች ተደግፋ ነበር የመጣችው። የመጨረሻ ቃሏ " ላልድን ሰበርከኝ አይደል?" የሚል ነበር ከዛ ቃል በኋላ ከ አፏ የወጣ አንድም ቃል የለም። የእሷም አንደበት ከ ህዝቅኤል ጋር ተቀበረ።
ቪቪያን ውስጧ ነው የሚያወራው አይኗ ደግሞ በእንባ ቃላቶቹን ያወጣል። ብቻ ግን ስትታይ ከማዘን አልፎ ሕመሟ ይጋባል ።
ጓደኛው ማቲያስ ቪቪያንን አይቷት ውስጧን አነበበው። እንደ ሕዝቅኤልም ሊጠብቃት ለራሱ ቃል ገባ።
ሁሉንም ሰው በአንድ ላይ የሰበረ ቀን.....
ይቀጥላል ........

ሕይወትን - በገፅ pinned «የእኔ ታሪክ (በ አዲስ ምዕራፍ) ቪቪያን እንደፃፈችው........ የሰው ልጅ ታሪክ መጨረሻ የለውም። ሞት መጨረሻ ነው ብዬ እንዳልደመደም ከሚያደርጉኝ ነገሮች አንዱ ልጅ ነው። የአባቴ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃ ቢመስልም በእኔ እና በአሌፍ ግን ነፍስ ዘርቶ ቀጥሏል። እንዲህ ሆነ.........ወደኋላ ተመልሳ ከአባቷ ጋ ያሳለፈችውን የመጨረሻ ቀን አስታወሰች። ያቀፏት የሕዝቅኤል እጆች ድንገት ተንሸራተው…»
የማይነጋ ሕልም ሳልም፣
የማያድግ ችግኝ ሳርም፣
የማይድን በሽታ ሳክም፣
የሰው ሕይወት ስከረክም፣
እኔ ለ እኔ ኖሬ አላውቅም።
✍ፀጋዬ ገ/መድህን
የማያድግ ችግኝ ሳርም፣
የማይድን በሽታ ሳክም፣
የሰው ሕይወት ስከረክም፣
እኔ ለ እኔ ኖሬ አላውቅም።
✍ፀጋዬ ገ/መድህን
አንዳንድ ትምህርቶች ከመጽሐፍ ወይም ከምክር አይመጡም።
እነሱ የሚመጡት ከክህደት፣ ከተስፋ መቁረጥ እና የተሳሳተ ሰው ለመርዳት በመሞከር ነው።
✍️ I amme♾️