tg-me.com/simetube/2992
Last Update:
🖥 ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ለመግዛት አስባችኀል?
📍እንግዲያውስ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ከመግዛቶ በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡ 10 ነገሮች!
1. ካገለገለ ኮምፒውተር ይልቅ አዲስ ኮምፒውተር ይምረጡ....
2. PCI Express x16 slot ያለው ማዘረቦርድ መሆን አለበት ይህም ሌሎች ካርዶችን ለመጨመር ይረዳዎታል::
- ለምሳሌ ቲቪ ካርድ፣ ግራፊክስ ካርድና ሌሎች....
3. ሚሞሪው ቢያንስ 4GB RAM መሆን አለበት ይህም ኮምፒውተሮ እንዳይጨናነቅና ፈጣን እንዲሆን
ያደርገዋል.....
4. ፕሮሰሰሩ Quad-core processor ያለውን ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ፈጣንና ብዙ ፕሮግራሞችን ባንዴ
የማስተናገድ አቅም እንዲኖረው ያረጋል...
5. ኮምፒውተሮን ለቤት ከሆነ የፈለጉት ፉኑ የማይጮህና የማይረብሽ ይምረጡ::
6. An All-in-one PC ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ ኮምፒውተር ይምረጡ (ሞኒተሩ ፍላት ስክሪን፣እና
ሌሎችንም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች ያሟላ)
7. A Single, High Powered Graphics card ያለው
ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ ይጠቅሞታል
8. የሃርድ ዲስኩ ሳይዝ 500GB እና ከዛ በላይ ቢሆን ይመረጣል ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ብዙ ፋይሎችን እንዲያስቀምጡ ይረዳዎታል...
9. ሃይል ቆጣቢና አነስተኛ ወጪ የሚያወጣ ይምረጡ...
10. ኮምፒውተሮን ሲገዙ አብረው External Hard Drive ይግዙ ይህም ዳታዎችዎን ባክ አፕ (መጠባበቂያ)
ለማረግ ይረዳዎታል
@simetube @simetube
@simetube @simetube
BY Sime Tech
Share with your friend now:
tg-me.com/simetube/2992