Telegram Group & Telegram Channel
ሸረሪት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

ከሦስቱ ሡራዎች ከሡረቱል ፋቲሓህ፣ ከሡረቱል አንቢያእ እና ከሡረቱል ኢኽላስ በስተቀር እያንዳንዱ ሡራህ የተሰየመው በውስጡ በያዘው ይዘት እና ጭብጥ ነው፥ የሡራዎችን ቅድመ-ተከተል እና ስም ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በተናገሩት መሠረት የተቀመጠ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3366
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ ”ለዑስማን ኢብኑ ዐፋን፦ “ሡረቱል አንፋልን ከመቶ በታች የሆነችበት፣ ሡረቱል በራኣህ(ተውባህ) ከመቶ በላይ የሆነችበት፣ በመካከላቸውም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ያልተጻፈበት(ሱረቱል በራኣህ) እና ባለ ሰባት አናቅጽ(ሡረቱል ፋቲሓህ) የሆችበት ምክንያታችሁ ምንድን ነው? አልኩኝ። ዑስማን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አንዳች የቁርኣን ክፍል በሚወርድላቸው ጊዜ ከጸሐፊዎቹ አንዱን በመጥራት፦ “ይህንን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት” ይሉ ነበር። አሁንም በድጋሚ የተወሰኑ የቁርኣን አንቀጾች ሲወርድላቸው፦ “እነዚህን አንቀጾች እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት” ይሉ ነበር”። حَدَّثَنَا ابْنُ عَبَّاسٍ، قَالَ قُلْتُ لِعُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ مَا حَمَلَكُمْ أَنْ عَمَدْتُمْ، إِلَى الأَنْفَالِ وَهِيَ مِنَ الْمَثَانِي وَإِلَى بَرَاءَةَ وَهِيَ مِنَ الْمِئِينَ فَقَرَنْتُمْ بَيْنَهُمَا وَلَمْ تَكْتُبُوا بَيْنَهُمَا سَطْرَ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ وَوَضَعْتُمُوهُمَا فِي السَّبْعِ الطُّوَلِ مَا حَمَلَكُمْ عَلَى ذَلِكَ فَقَالَ عُثْمَانُ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِمَّا يَأْتِي عَلَيْهِ الزَّمَانُ وَهُوَ تَنْزِلُ عَلَيْهِ السُّوَرُ ذَوَاتُ الْعَدَدِ فَكَانَ إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ الشَّىْءُ دَعَا بَعْضَ مَنْ كَانَ يَكْتُبُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَؤُلاَءِ الآيَاتِ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا وَكَذَا وَإِذَا نَزَلَتْ عَلَيْهِ الآيَةُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَذِهِ الآيَةَ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا

ስማቸው በውስጣቸው ከያዙ ሡራዎች አንዱ ሡረቱል አንከቡት ነው፥ ስለ አንከቡት ትንሽ እንበል። ጋጥመ-ብዙ"Arthropoda" የእንስሳ ክፍለ-ስፍን"phylum" ሲሆን ሸረሪት ክፍለ ምድቡ ከጋጥመ-ብዙ ነው። "አንከብ" عَنْكَب‎ ማለት "ወንድ ሸረሪት" ማለት ሲሆን "አንከባህ" عَنْكَبَة‎ ደግሞ "ሴት ሸረሪት" ማለት ነው፥ "ዐንከቡት" عَنكَبُوت የሚለው ቃል ደግሞ ለሁለቱም ፆታ ያገለግላል። ድርን በማድራት ቤት የምትሠራው ግን ሴቷ ሸረሪት ናት፦
29፥41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا

እዚህ አንቀጽ ላይ በድሯ ቤት የምትሠራዋ ሴት ሸረሪት እንደሆነች ለማመልከት የገባው ቃል በሙዘከር "ኢተኸዘ" اتَّخَذَ ሳይሆን በሙአነስ "ኢተኸዘት" اتَّخَذَتْ ነው፥ አምላካችን አሏህ ግን ሁሉም ዐዋቂ ስለሆነ በቁርኣኑ ነግሮናል። የሥነ-ሕይወት ጥናት እንደሚያትተው የሸረሪት ሐር"silk" ተፈጥሯዊ ፕሮቲን ሲሆን የምትፈትለው ሴቷ ሸረሪት መሆኗ የታወቀው በ1984 ድኅረ-ልደት ነው፥ የሸረሪት ሐር እየተጠላለፈ "ድር"web" ይሆንና እራሷን መከላከያ፣ መሸሸጊያ፣ መጠለያ ይሆናል። "ቤተ-ሰብእ" ማለት "የሰዎች ቤት" ማለት ነው፥ "ቤት" የሚለው ጣሪያ እና ግድግዳውን ብቻ ሳይሆን ስብስቡን ያመለክታል። እሩቅ ሳንሄድ፦ "እዚህ ቤት" ስንል ከውስጥ "አቤት" ወይም "እመት" የሚሉን "ቤት" የተባለው ፍካሬአዊ እንጂ እማሬአዊ እንዳልሆነ እሙን እና ቅቡል ነው፥ በቁርኣን "ቤተ-ሰብእ" የሚለው ቃል "አህለል በይት" أَهْلَ الْبَيْت ነው፦
33፥33 *"የነቢዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከእናንተ ላይ እርክሰትን ሊያስወግድ እና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ اللَّهُ لِيُذْهِبَ عَنكُمُ الرِّجْسَ أَهْلَ الْبَيْتِ وَيُطَهِّرَكُمْ تَطْهِيرًا

"እመ-ቤት" ማለት "የቤት እናት" ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ "ቤት" የሚለው ጣራ እና ግድግዳ ማለት አይደለም፥ አንድ ሰው ትዳሩ ሲበተን "ቤቱ ፈረሰ" ይባል የለ እንዴ? እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አሏህ ሸረሪት ለመከላከል፣ ለመሸሸግ እና ለመጠለል የምታደራውን ድሯን "በይት" بَيْت ማለቱ የሚደንቅ ነው። ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው ሸረሪት በድሯ ያደራችው ቤት ነው፦
29፥41 ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ

የሸረሪት ድር ዝናብ ሆነ ሙቀት መቋቋም የማይችል ደካማ ቤት ነው፥ እነዚያ ከአሏህ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶችን አድርገው የያዙ ሰዎች ልክ እንደሸረሪት ቤት እጅግ በጣም ደካማ ናቸው። ይህንን ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር፦

አምላካችን አሏህ ይህንን ቡሩክ መጽሐፍ ያወረደው የአእምሮዎች ባለቤቶች አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ ነው፦
38፥29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ቡሩክ መጽሐፍ ነው፥ የአእምሮዎች ባለቤቶች አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

አሏህ የቁርኣንን አንቀጽ አስተንትነው ከሚገሰጹት ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

tg-me.com/slmatawahi/8893
Create:
Last Update:

BY የሰለምቴዎች ቻናል

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280

Share with your friend now:
tg-me.com/slmatawahi/8893

View MORE
Open in Telegram

የሰለምቴወች ቻናል🥀 Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

How to Buy Bitcoin?

Most people buy Bitcoin via exchanges, such as Coinbase. Exchanges allow you to buy, sell and hold cryptocurrency, and setting up an account is similar to opening a brokerage account—you’ll need to verify your identity and provide some kind of funding source, such as a bank account or debit card. Major exchanges include Coinbase, Kraken, and Gemini. You can also buy Bitcoin at a broker like Robinhood. Regardless of where you buy your Bitcoin, you’ll need a digital wallet in which to store it. This might be what’s called a hot wallet or a cold wallet. A hot wallet (also called an online wallet) is stored by an exchange or a provider in the cloud. Providers of online wallets include Exodus, Electrum and Mycelium. A cold wallet (or mobile wallet) is an offline device used to store Bitcoin and is not connected to the Internet. Some mobile wallet options include Trezor and Ledger.

Tata Power whose core business is to generate, transmit and distribute electricity has made no money to investors in the last one decade. That is a big blunder considering it is one of the largest power generation companies in the country. One of the reasons is the company's huge debt levels which stood at ₹43,559 crore at the end of March 2021 compared to the company’s market capitalisation of ₹44,447 crore.

የሰለምቴወች ቻናል🥀 from us

Telegram የሰለምቴዎች ቻናል
FROM USA