Telegram Group Search
Ethiopian_Instrumental(256k)
<unknown>
"#ተረኛው ታፋኝ"
•••

👌 ማን ነበር ይኼ
መንጋ ነው መንግሥት ?
ብልጥግና የሚሉት ፣
ውርደቱን ተመለከትኩት ፣
ድድብናውን አጤንኩት ፣
እናም አዘንኩበት ፣
ደግሞም አዘንኩለት ፣
በኋላም ሳቅኩበት ፣
ተንከረከርኩበት ፣
አሽካካሁበት ፣
ይኼ እበት ፣
ገተት ፣
አልኩ እና ሰደብኩት ፣
እናንተም ስደቡት ።
•••
ሕጻን ልጅ በማገት ፤
አባትክን ውለድ ባይ ፣
መነኩሴ በመድፈር ፤
ወጣትን ሚጨቁን ፤
የመንደር አውደልዳይ ፣
ታዲያ መንጋ መንግሥት ፤
የታል ተዚህ በላይ ?
ሐሰቴን ከሆነ አሁን የገጠምኩት ፣
ነገ ጧት ያስገቡኝ ያው እንደለመዱት ፣
ሁሌ በቀን በቀን ፤
ልክ እንደ ተፈራ ስሜን ከሚፈሩት ፣
እንደ ኮስትር በላይ ነፍጠኛ እንደሚሉት ፣
እንደ ሸዋው ንጉሥ ጡት ቆራጭ እንዳሉት ፣
እየተሳቀቁ ስሜን ከሚፈሩት ፣
ነገ ጧት ያስገቡኝ እነርሱም ይረፉት ።

እኔም አልተው መግጠም እውነቱን መናገር ፣
ማንንም አልፈራ ከፈጣሪ በቀር ።
ዝም ብለህ ተኝተህ በፌስቡክ አውድማ ፣
ብልግና እየሠራህ በሚዲያ ከተማ ፣
ሰው ከምትተች ዘመድ ከምታማ ፣
ይልቅስ እውነት ጻፍ ወይ ሲነግሩህ ስማ ።
እኔ ግን ምን ነካኝ ግጥሜ ግጣም አጣ ፣
ዓምኻራ ዓይኑ ጠፋ በማንም ገሽላጣ ፣
ወገኔ ዓይኑን አጣ በመለስ መላጣ ።
•••

#እብነ_ሜሌክ (#ከራድዮን)
✏️ ግንቦት 17/2014 ዓ•ም
#ጊ_ጊንጥ እና ዘንዶውን ከአጠገቤ አርቀህ ፣
#ዮ_ዮርዳኖስ ፍቅርህን በውስጤ አፍስሰህ ፣
#ር_ርኅራኄኅን በልቤ ላይ ዘርተህ ፣
#ጊ_ጊዜያዊ ያልሆነ ምልጃህን ለግሰህ ፣
#ስ_ስንፍናዬን ደምስስ አባቴ ስጠራህ ።
ዮሐንስ እና ካንጋሮ
•••
ወንድም ከወንድሙ በማይስማማበት ፣
አባቱ ከልጁ ጋር በማይግባባበት ፣
እናት ከሴት ልጇ በማታወራበት ፣
ዘመድ ከዘመዱ በተራራቀበት ፣
ወዳጅ ከወዳጁ በተኳረፈበት ፣
እጅግ ያስገርማል የእንስሳት ደግነት ።

~ ዳሩ ግን እውነት ነው ፤
እንስሳት ተሽለው ከሰው ብዙ ርቀው ፣
ከራሳቸው አልፎ ለሰው ልጆች አዝነው ፣
ከእኛ ያላዩትን ለእኛው አሳይተው ፣
ነቢይ ይወልዳሉ ከአምላክ ተቀብለው ።

ሰዎች ሲያሳድዷት ኤልሳቤጥ እናቱን ፣
ሄሮድስ ሲቀላው ዘካርያስ አባቱን ፣
ያለ ወላጅ ሲቀር ያለ እናት ብቻውን ፣
ካንጋሮ እናት ሆና አጥብታው ጡቶቿን ፣
ብርድ እንዳያገኘው በኪሷ ሸጉጣው ፣
ረሃብ እንዳይርበው አምላኳን ተማጽናው ፣
አሳድጋዋለች ዮሐንስን አዝላው ።
መቼም የእኔ ትውልድ በዚህ ባይማርም ፣
ሃቁ ውስጡ ገብቶ ደግነት ባይሠራም ፣
እውነታው ገዝፎበት ጭራሹን ባይራራም ፣
እኔ ግን ጽፌያለሁ ብትሰማም ባትሰማም ።

ሰው ሆይ! ተማር እንጂ ከሰው ከእንስሳቱ ፣
ከድንጋይ ከወንዙ ከሳሩ ከእንጨቱ ፣
ከገደል ከዱሩ ከምንጩ ከአለቱ ።
እንስሳት በልጠውህ ከሰው ጋ ሲሞቱ ፣
አንተ ስለት ይዘህ ቀጥል በመውጋቱ ፣
ወንድምህን ቅላ በሰይፍ በቀስቱ ።
አዲስ ዓመት መጣ አንተ ግን እዛው ነህ ፣
አዲስ ዘመን ጠባ ቤትህ ተቀምጠህ ፣
እስኪ ለዘንድሮ አንተም አዲስ ሆነህ ፣
ዘመኑን ምሠለው ዘመንህን ሆነህ ።

✍️ በዐምደ ብርሃን
~ ~ ~ ኤ ደ ን ~ ~ ~


አዳም አባቴ ከገነት ሲወጣ ፣
ለመኖር ወደ አንች መጣ ፣
የእኔዋ ኤደን ልቤ በፍቅር ሲራቆት ፣
በልብሽ መንደር አረፈበት ፣
እንደ ትልቅ ዛፍ ተጠለለበት ፣
እንደ ደብር አድባር መሸገበት ፣
ኤዱዋ የልቤ ትርታ የነፍሴ ገነት ።

• • •

ኤደን ቅድስቷ ግዮንን ያፈለቅሽ ፣
ኤፍራጥስን ያንፏፏሽ ፣
ጤግረስን ያንፎለፎልሽ ፣
ኤፌሶንን ያፈሰስሽ ፣
የእኔዋ ኤደን ከልብሽ ባለው ንጹሕ ፍቅርሽ ፣
ከውስጥሽ ባለው ሕያው ሰውነትሽ ፣
አዲሱ ምኒሊክ ተወለደብሽ ፣
ተስፈኛው ወጣት መነጨብሽ ፣
ስደተኛው አረፈብሽ ፣
ባይተዋሩ ተጽናናብሽ ።

• • •

~ ❤️ ኤ ዱ ❤️~

አምላክ አንችን ሲፈጥርሽ ፣
ከቀኝ ጎኔ ሲቀንስልሽ ፣
ከአጥንቴ ለአጥንትሽ ፣
ከሥጋዬ ለሥጋሽ ፣
ከነፍሴ ለነፍስሽ ፣
ከእስትንፋሴ ለእስትንፋስሽ ፣
ከእኔ ወስዶ ሲያበጃጅሽ ፣
ለአንች አስቦ እንዳይመስልሽ ፣
ለእኔ መሆኑ በደንብ ይግባሽ ።

~ አንችማ ኤዱ ~

የፍቅር ሃብታም ምን ጎሎብሽ ፣
የሰው የዋህ እንከን የለሽ ፣
የተስፋ እናት ምን ጠፍቶብሽ ፣
የህልም ዓለም ምን ቸግሮሽ ፣
የጥያቄ መልስ ሁኚ ያለሽ ፣
ሁሉ ያለሽ የተረፈሽ ፣
ለሰው ኗሪ አልፈሽ ተርፈሽ ፣
ደግ ሩኅሩኅ ስስት የሆንሽ ፣
አድርጎ ነው ያዘጋጀሽ ።

~ እናም ውዴ ~

ለምን ስሜን ኤደን አልከኝ ፣
ብለሽ ዛሬ ለጠየቅሽኝ ፣
በግጥም መልክ መልሴን ስሚኝ ።

• • •

ኤደን ስልሽ በምክንያት ነው ፦
ኤደን ሚሏት በሰማይ ቤት ፣
ግዮን ጤግረስ የሚያጠጧት ፣
ቅዱሳኑ ሚረኩባት ፣
ደናግሉ ሚኖሩባት ፣
የደስታ ምንጭ እስትንፋስ ናት ።
ኤደን ወንዝን እንዳፈለቀ ፣
ቅዱሳንን እንዳጸደቀ ፣
አዳምን እንዳደመቀ ፣
ደስታዎችን እንደሰነቀ ፣

~ እኔም በአንች ~

በፍቅርሽ ጸዳል ቀኔ ደምቋል ፣
በልብሽ ማይ ጥሜ ጠፍቷል ፣
በተስፋ ስንቅ ውስጤ ጎልቷል ፣
ማንነቴ ተመልሷል ፣
እስትንፋሴ ህያው ሆኗል ፣

~ እና ታዲያ ~
ኤዱ ብልሽ ያንስብሻል ?
ውዱ ልቤ ደክሞልሻል ፣
በፍቅርሽ ባሕር ሰጥሞልሻል ፣
ከውቅያኖስ ገብቶልሻል ፣
ኤዱ የእኔ ተፈቅረሻል ።

••••

አፍቃሪሽ
ሚ ኒ
😭😢😰 ~ እኔን ወንድማለም ~ 😢😰😥

•••

አለማወቅ ደጉ ምንኛ ድንቅ ነው ፣
ሰውን አለመቅረብ እንዴት መታደል ነው ፣
አንተን ባውቅህ አይደል እንዲህ የማለቅሰው ።
እናትህ በደስታ ለሰርግህ ስትደግስ ፣
አባትህ በሀሴት ለጫጉላህ ሲያሳርስ ፣
ወንድምህ ለአዱኛህ መሠረትክን ሲምስ ፣
እህትህ ለፌሽታህ እንጀራ ስታስስ ፣
~ አንተ ግን ~
ሰርጉን ከቁብ ሳትቆጥር ትተህ አናንቀህ ፣
እንዲያ እየጠበቁህ እናትህ አባትህ ፣
እንዲያ እየናፈቁህ እህት ወንድሞችህ ፣
እንዲያ እየሳሱልህ ዘመድ አዝማዶችህ ፣
ትትኻቸው ሮጥክ ለላይ ቤቱ ሰርግህ ።

😥
•••
አወይ የሰው ነገር የእኛ መጨረሻ ፣
ፈራሽ እንደ ሸክላ ተናጂ እንደ ዋሻ ።
ትላንት ታይተን ዛሬ እንዲህ ለምንጠፋው ፣
በሰዓት በቅጽበት ለምንሰበረው ፣
በጠዋት በማታ ወድቀን ለምንቀረው ፣
በገደል በዋሻ ለምንቀበረው ፣
በሰይፍ በክላሽ ለምንጋደመው ፣
መጨካከናችን ከቶ ለምንድን ነው ።
~ ልጥገብ ~
እናትህ አባትህ ሁኔታቸው ታየኝ ፣
የእህት ወንድሞችህ እንባቸው አጠበኝ ፣
የዘመድ አዝማዱ ሲቃው አስለቀሰኝ ፣
ሰፈር ጎረቤቱ እሮሮው አባባኝ ፣
የትልቅ ትንሹ ኃዘኑ ገረፈኝ ፣
በድንህን ስልከው እኔን ግን አስቻለኝ ።

😰
•••
ምናለ ባላውቅህ ባልሰማ ምክርህን ፣
አብሬህ ባልበላ ባልጠጣ ፍቅርህን ።
አሁን ነው የገባኝ የምክርህ ውጤቱ ፣
ዛሬ ነው የታየኝ የፍቅርህ ጉልበቱ ፣
እኔ ብንገላታም ታድሏል መሬቱ ፣
አንተን ተንተርሷል ሰምሮለት ጸሎቱ ፣
ምንኛ ደስ ይለው አንተን በማግኘቱ ።
የልጅ አዋቂ ነህ ሃሳብህ ተራራ ፣
ውሸት የምትጠላ ጌታን የምትፈራ ።
ምናለ ሲፈጥረኝ አፈር ባደረገኝ ፣
አንተን ከሰው መርጦ ለራሴ እንዲሰጠኝ ።
ምናለ ከእንግዲህ ምስጥ ባደረገኝ ፣
ልጥገበው ገላህን መዓዛህ ያውደኝ ።
እንዴት ቢጸልይ ነው አፈሩ መሬቱ ፣
ልጥገብ የአንተን ገላ በነጻ ማግኘቱ ።
~ ለነገሩ ~
እሱም አምላክ አለው ሚሰማው ጸሎቱን ፣
ይኸው ዛሬም ሰጠው አንተን መኳንንቱን ።
ምናሉ ሰዎቹ ለቅሶህን ሲሰሙ ፣
ምናሉ ጎረቤት ሞትህን ሲሰሙ ፣
ለሰርግህ ደግሰው በአንተ ሲታመሙ ።
እያለህ መካሪ ስትሞት አስተማሪ ፣
መዋቲ መሆኔን በሞትህ አብሳሪ ።
ዛሬ ነው የገባኝ ሞት እንደሚወስደኝ ፣
አንተን መሳይ ወንድም ከክንዴ ሲነጥቀኝ ፣
አለኝታ ጋሻዬን አታሎ ሲሰርቀኝ ፣
እኔም ሰው መሆኔ ዛሬ ነው የገባኝ ።
ላደረግከው ነገር እኔን ለመቀየር ፣
ለለፋኸው ልፋት ለጣርካው መጣጣር ፣
ሰው ከፍሎ አይችለውም ከፈጣሪ በቀር ።
እንዲያ እንደናፈቀከው በጠዋት በማታ ፣
እንዳገለገልከው በሀሴት በደስታ ፣
እንደዘመርክለት በክራር በእምቢልታ ፣
ዛሬ ጠቅልለህ ሄድክ ከሰማዩ ጌታ ።

😥
•••
ስትወጣ ስትገባ መዝሙር እየዘመርክ ፣
ስትሄድ ስትቀመጥ ምስጋና እያቀረብክ ፣
ታዲያ እንዴት ልተውህ እንዴት ብዬስ ልርሳክ ።
እኛ የምናውቀው ዶክተር ሲያስመርቅ ነው ፣
ሲባል የሰማነው ምሑር ሲያፈልቅ ነው ፣
ሲሆንም ያየነው ልሒቅ ሲያፈራ ነው ፣
ዛሬ ለአንተ ሲያለቅስ ማርቆስ ምን ተሰማው ።
እናትህ እድሏ አባትህ መከራው ፣
እህትህ ስቃይዋ ወንድምህ ፈተናው ፣
ጓደኛህ ኃዘኑ ወዳጅህ ሮሮው ፣
እንዴት ሊችሉት ነው መች ጨረሱህ ጠግበው ።

😥
~ ስንብት ~

መሄድህ ካልቀረ ንሳ ሰላም በለን ፣
መጓዝህ ካልቀረ ቻው ብለህ ተለየን ፣
መንገድህን ካልተውክ ተመለሱ በለን ፣
እኛም እኮ ደከምን አንተን ተከትለን ።
~ እኔ ምለው ልጥገብ ~
ምነው ሆድህ ቻለው እናትህን ተውካት ፣
የአባትህን ሲቃ እንባ ሳትጠርግለት ፣
የእህትህን ተስፋ ዋይታ ጭነህበት ፣
ወንድምህን ገድለህ አረም ጥለህበት ፣
ልጥገብ እንዴት ቻልከው የዘመዱን ጩኸት ።
~ እኛማ ~
እኛ ወደ አንተ እንጂ አንተስ አትመጣም ፣
ብንከተል እንጂ አትከተለንም ፣
ብትመራን እንጂ በእኛስ አትመራም ፣
ከእንግዲህ ወደ እኛ አትጠረጠርም ።
አደራ መሬቱ ለአፈሩም ንገረው ፣
የልጥገብን ገላ ምስጥ እንዳያፈርሰው ፣
የወንድሜን ውበት አፈር እንዳይበላው ፣
እንደራሴ አድርገህ ወንድሜን ጠብቀው ፣
እኔም ቀኔ ደርሶ መጥቼ እስከማየው ።
• • •
ዐምደ ብርሃን

😭😭😭😭😭😭😭😭😭
መወድስ ... መቀንጥስ

...///....
እባክህን አምላክ እባክህን ጌታ ፣
የፍጥረታት ንጉሥ የሰው ልጅ አለኝታ ።

አንዴ ... ልለምንህ 🙏

ሙሴን መሆን ሚችል መሪ ባናገኝም ፣
ባህር ሚከት እንጅ ሚያወጣን ባይኖርም ፣
አንደበት ሚሆነን አሮንን ባንወልድም ፣
አንድ አልያስ ስጠን ሰማይ የሚለጉም ።

..//..
ሰማይ ብትከፍት አይደል እንዲህ የሚደፍሩህ ፣
ዝናብ ብትሰጥ አይደል እንዲህ የሚሰድቡህ ፣
አየር ብትሰጥ አይደል እንዲህ የሚሰቅሉህ ፣
መልክህን የሚያርዱት አንተን ሚያሳዝኑህ ፣
ኤልያስ ባይኖር ነው ከብሮ ሚያስከብርህ ።

..// እናም ..//

ኤልያስን ስጠን ሙሴ ጥንቅር ይበል ፣
መሪ አንተ ከሆንከን ባህር ይፈራናል ፣
ሰማይ ሚቆልፍ ብቻ ኤልያስ ይበቃል ።

© ዐምደ ብርሃን
ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ ንጉሥ ምኒሊክ ጀግንነቱ ወእምነቱ በዘመናችን ይደር!

••//••
ማርያም ብሎ ጠርቶ የማይደራደር ፣
በስሟ በክብሯ የማይጠራጠር ፣
ሸዋን ግዛ ሚሉት ደግ ንጉሥ ነበር ።
ሣህለ ማርያም የጊዮርጊስ ወዳጅ ፣
የጠላት ማርከሻ የወንበዴ አሳዳጅ ።
እናትህ ከመቅደስ ታጅባ ገብታለች ፣
ምኒሊክ እያለች ትፈልግሃለች ።
እሷ መቅደስ ገብታ አንተን ስትፈልግህ ፣
ከላይ ቤቱ ቤትህ ማን ነው የወሰደህ ?
እምዬ እርሶን ወስዶ አማኝ ንጉሣችን ፣
ምኒሊክ እግዚአብሔር አምባ መጠጊያችን ።

••//••
☆ ሀ_ሴቴ ☆

•••
ፍቅር ጠምቶኝ ፍቅር ናፍቆኝ ፣
ብቸኝነት ሲያሳቅቀኝ ፣
ባይተዋርነት ሲያስለቅሰኝ ፣
ሰማይ ምድሩ ሲርቅብኝ ፣
ዘመድ ወዳጅ ሲስቅብኝ ፣




የሁሉ አምላክ የላከልኝ ፣
ሀ_ሴት ብሎ የሾመልኝ ።
•••

እሱ ቢሰጥ አያልቅበት ፣
እሱ ቢሾም አይጎድልበት ፣
ጠዋት ማታ አይነጥፍበት ፣
አንችን ሰጠኝ ለበረከት ።

ሀ_ሴቴ ደስታዬ ፤
ሀ_ሴቴ ስኬቴ ፣
ሀ_ሴቴ ውበቴ ፤
ሀ_ሴቴ ድምቀቴ ፣
ሀ_ሴቴ ግርማዬ ፤
ሀ_ሴቴ እኔነቴ ፣
ሀ_ሴቴ ረሃቤ ፤
ሀ_ሴቴ ናፍቆቴ ፣
ሀ_ሴቴ መሪዬ ፤
ሀ_ሴቴ ጉልበቴ ፣
ሀ_ሴቴ ልደቴ ፣
ሀ_ሴቴ ሕይወቴ ፣
•••

ዘመኔን ከአንች ጋር ማርጀትን እሻለሁ ፣
እንደ አባት ወንድምሽ እሆንልሻለሁ ፣
አይቼ አልጠግብሽም እሳሳልሻለሁ ፣
የቤትሽ ምሦሦ ራስ እሆናለሁ ፣
ዘወትር እንደ አዲስ ሳፈቅርሽ ኖራለሁ ፣
እንደ እናት እንደ እህት እመካብሻለሁ ፣
ፈጣሪ እንደሰጠኝ ተቀብዬሻለሁ ፣
ለፍቅርሽ አምኃ ልቤን ሰጥቻለሁ ።
ሀ_ሴቴ አፈቅርሻለሁ ፣
ሀ_ሴቴ እወዳሻለሁ ፣
ሀ_ሴቴ ራሴን እሰጥሻለሁ ።
            ☆       ☆      ☆

ሀ_ሴትዬ የእኔ ውድ ....... ከዚህ በላይ ብልሽ ደስ ይለኛል። ግን አልችልም።


© ᵞᴱ'ᴬᴮᵀˢᴱᴳᴬ ᵞᴱ ᴴᴬˢˢᴱᵀ 💥
2025/05/31 15:36:49
Back to Top
HTML Embed Code: