Telegram Group Search
ሀላል በጎ አድራጎት
#በቡሌ ለሚገኙ ወንድሞቻችን

አካባቢው ለሚገኙ ሙስሊም  ማህበረሰቦች በበቂ ሁኔታ የኡዱህያ ስጋ የማከፋፈል መርሀ ግብሩን በተሳካ መልኩ አጠናቋል።ከኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር እናመሰግናለን

👋 ስለሆነም ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
     ስልክ፦ 09-12-33-00-91
               09-10-88-30-37
               09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla
ሀላል በጎ አድራጎት ማህበር ዲላ እና አከባቢው እየሰራ በሚገኘው ዘርፈ ብዙ ስራወች ከጎን ሆኖ ዘርፈ ብዙ ስራወችን እያገዘ ለሚገኘው ለኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክቷል።በዕለቱም ከኢማን የማኔጅመንት አባላት ጋር  የልምድ ልውውጥ ተደርጓል።
🥀 ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
     ስልክ፦
09-12-33-00-91
              
09-10-88-30-37
              
09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla
#የዓሹራ_ፆም ያለው ትሩፋት
فضل صوم يوم عاشوراء
ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ አንሁ) በዘገቡት ሀዲስ ነቢዩ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በመጡ ግዜ የሁዶች ዓሹራን ሲፆሙ አይተዋቸው ለምን እንደሚፆሙት ሲጠይቋቸው "ይህ ቀን መልካም ቀን ነው፣ አላህ በኒ ኢስራኢልን ከጠላታቸው ነፃ ያወጣበት ቀን ነው፣ በዚሁ ምክንያት ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ፆሙት" በማለት መለሱላቸው። ነቢዩም (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) "እኔ ለሙሳ ከናንተ ይበልጥ የተገባው ነኝ" በማለት ፆሙት ሌሎችም እንዲፆሙት አዘዙ። (ቡኻሪ) በሌላ
በሙስሊም ዘገባ "ይህ ታላቅ ቀን ነው። ሙሳንና ህዝቦቹን ነፃ ያወጣበትና ፈርኦንንና ህዝቦቹን ያሰመጠበት" በማለት ተዘግቧል።
عن ابن عباس رضي الله عنهما قال: قَدِمَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ المَدِينَةَ فَرَأَى اليَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ، فَقَالَ: «مَا هَذَا؟» قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ، فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ: «فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ»، فَصَامَهُ، وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ. أخرجه البخاري في صحيحه.
وفي رواية مسلم- ((هذا يوم عظيم أنجى الله فيه موسى وقومه وغرّق فرعون وقومه))

فعَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ : مَا رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَحَرَّى صِيَامَ يَوْمٍ فَضَّلَهُ عَلَى غَيْرِهِ إِلا هَذَا الْيَوْمَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ وَهَذَا الشَّهْرَ يَعْنِي شَهْرَ رَمَضَانَ . " رواه البخاري

ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ አንሁ) "ነቢዩ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከዓሹራእ እና ከረመዳን ሌላ አንድንም ፆም ከሌላው አስበልጠው ትኩረት የሰጡበት አላየሁም" ብሏል። (ቡኻሪ)

فعن عَبْدِ اللهِ بْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا قال: حِينَ صَامَ رَسُولُ اللهِ صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّهُ يَوْمٌ تُعَظِّمُهُ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ: «فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ إِنْ شَاءَ اللهُ صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ» قَالَ: فَلَمْ يَأْتِ الْعَامُ الْمُقْبِلُ حَتَّى تُوُفِّيَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ. أخرجه مسلم في "صحيحه"

አብደላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም የአሹራን ቀን ፁመው ሰሀባዎቻቸውንም እንዲፃሙ ባዘዙ ጊዜ፦ ይህ ቀን እኮ አይሁዶችና ነሳራዎች የሚያልቁት ቀን ነው አሉዋቸው። እሳቸውም፦ "የአላህ ፍቃድ ሆኖ ቀጣይ አመት ከደረስን ዘጠነኛውንም ቀን እንፃማለን" አሉ። ነገር ግን የቀጣዩ አመት አሹራ ሳይደርሱ ሞቱ።" (ሙስሊም)

ዘጠነኛውን ቀን መጨመር የተፈለገበት ምክንያት ከአይሁዶችና ከነሳራዎች ለመለየት ነው።

وقال رسول الله صلى الله عليه وسلم : " صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ " رواه مسلم

የአላህ መልክተኛ ( ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) "የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን አመትና የቀጣዩን አመት ወንጀል እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ። የዓሹራ ፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ" ብለዋል። (ሙስሊም)

በነዚህ ፆሞች የሚታበሱት ወንጀሎች ትናንሽ (ሰጋኢር) ወንጀሎች ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለየ ተውባ ይፈልጋሉ።

በዘንድሮ አመት 1446 አመተ ሂጅራ ዘጠነኛው ቀን ሰኞ ሲሆን አስረኛው ማክሰኞ ስለሆነ ሁላችንም እንዳያመልጠን በጉጉት እንጠባበቅ ።
★ በእነዚህ ቀናት ጾም ከመጾም ውጭ ከወትሮው ለየት ያለ የሚደረግ ኢባዳም ሆነ የሚኬድበት ቦታ የለም ።

አላህ ደርሰው ከሚፆሙት ያድርገን ይወ ።
በኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን አማክኝነት በሀላል በጎ አድራጎት ማህበር አስተባሪነት የተገነባው  መስጂድ በነገው እለት ማለትም 8/11/16 ሰኞ በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙርያ ወረዳ አይጠሌ ሱኬ ቀበል ይመረቃል። ሁላችሁም ተጋብዛችሁል።ምርቃቱ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ጠዋት ቢላል መስጂድ መኪና ተዘጋጅቷል።
https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኡስታዝ ሸህ ሙሀመድ አሚን አዛን የተመረቀው መስጂዳችን


ስለሆነም ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
     ስልክ፦ 09-12-33-00-91
               09-10-88-30-37
               09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla
[. . . በፍቅር ነው አላህን ያወቅኩት። በፍቅር ነው ከአላህ ባሮች ጋር የተኗኗርኩት።. . .
የአላህን ፍቅር ዋና ሀብታችን እንደምናደርግ ተስፋ አደርጋለሁ። ትዕዛዛቱ ላይ መፅናት ቢሳነንም . . .ከክልከላው መታቀብ ቢከብደንም። . . .]
:
ሸይኽ ረመዷን አል-ቡጢ (ረሂ)
ለአንዳንድ ሰዎች ከልባችሁ ወደ አላህ ዱዓ ልታደርጉላቸው ካልሆነ በቀር በቃላቶቻችሁ ምንም ልትፈይዱላቸው አትችሉም። የታመመ ሁሉም አይፅናናም። የተገኘ ሁሉም አይመከርም። አንዳንድ የሰዎችን ጉዳይ በዱዓ ብቻ ለመፍታት ሞክሩ። በቃ ተግታችሁ ዱዓ ብቻ አድርጉ! ብቻ አብሽሩ! አላህ ለልባችሁ ሰላም ይስጣችሁ!
ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ ፦
" ከኢማን ቀጥሎ ልትደክምለት የሚገባው ትልቁ ነገር መልካም ጓደኛ ይሁን። መልካም ጓደኛ ምኗም እንደማይጣል መልካም ዛፍ ነው። በጥላው ትጠለላለህ። ከግንዱ ቤት ትሠራለህ። ከፍሬው ትመገባለህ።"
የተማሪዎች የደብተር እደላ ፕሮግራም እለተ ማክሰኞ ቀን 14/1/2017ዓ/ል በ3:00 ከጠዋቱ ጀምሮ በቢላል መስጂድ አዳራሽ ውስጥ ይታደላል የዛሬ አመት በተሰጠው መሰረት ዘንድሮም የሚታደል ይሆናል በዚህ ከይር ስራ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ወንድምና እህቶች ቀድማቹ በመገኘት የመልካም ስራን ምንዳ መቋደስ ትችላላቹ

https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla
ሰላም ለነሱ •••••••••
ዝምታችን እንደ ንግግራችን
ለሚገባቸው ሁሉ !!
2024/09/26 07:04:53
Back to Top
HTML Embed Code: